የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና ፓርቲዎች ውይይት እንዲጀምሩ ጳጳሳት ጠየቁ

The news in Amharic from Ethiopia are stopped as a result of the total repression of the Free Press by the TPLF/EPRDF regime. Image

ክርስቶስን መስለን ግብዝ ፈሪሳዊ ጳጳሳትን እናጋልጣለን!

Postby ዲጎኔ » Wed Dec 14, 2005 7:19 pm

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር በተመላለሰባቸው ቀናት እጅግ አድርጎ የገሰጻቸው ግብዝ የሀይማኖት መሪዎችን ሲሆን ዛሬም መንፈሱ የሚያነጣጥረው እነርሱን በመሰሉ ግብዝ ጳጳሳትና ሆድ አምላኩ ተከታዮቻቸው ላይ ነው::

በእርግጥ በሀገር ቤት በጥቂቱ በስደት ደግሞ በመጠኑ ከፈሪሳዊነት የራቁ መኖራቸው ባይካድም አብዛኛዎቹ ስልጣን የያዘውን ሁሉ ሺ አመት ያኑር እያሉ ሲመርቁ እንደነበርና ዛሬም አረመኔው ኢሀዲግን "ያሰንብትልን" ያሉትን የሲኖዶስ ተብዬው መሪዎችን ስም እየተጠቀሰ ከለፈፉበት ስፍራ ጭምር ማቅረብ ይቻላል::

ርእሱ "ጳጳሳት" ስለሚል ህዝባችን ጳጳስቱ እነዚያ ግብዝ የጭቆናና የአፈና ተባባሪዎች ሳይሆኑ አንድ ሚሊዮን የማይሞሉትና በጳጳስ ብርሀነኢየሱስ የምትመራው የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን መሆናቸው ተለይቶ መታወቅ ስላለበት"ኮተለኩ" "ተኩላ" እየተባሉ የተነቀፉትን ካቶሊኮችን እንድንቀበል ያቀረብኩት መጣጥፍ ነው::

ይህ ሰናይ ግብር የሚያቃጥለው የደብተራዎቹ አፈቃላጤ እኔን ለእናት ኢትዮጵያ በጎ ምግባርን ከየትም ቢከሰት የምዘግበውን አንዴ የካቶሊኮች ወገንተኛ አድርጎ ሲከሰኝ ሌላ ጊዜ ደግሞ "ተዋህዶን"መሰልክ እያለ ያንጉዋጥጠኛል እኔ ግን በዋርካ ላይ ያለአንዳች ልዩነት ለኢትዮጵያ በጎ መንፈሳዊም ሆነ ስጋዊ ተሀድሶን ለመዘገቤ ይህው ግለሰብ ያወጣው ፋይሌ ያረጋግጣል::

እጅግ አሳፋሪው ታሪካቸው ቄስ አበበ ፈንቴ የተባሉ የቆሬ አርሲ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ካህን በጀርመን ድምጽ ያቀረቡትን ተማጽኖ ሰምተው ለወገኖችና ለአለም ሰብአዊ ድርጅቶች ከማሳወቅ ይልቅ የሌላውን እምነት ለመሳደብና ለማውገዝ ሲተጉ ይገኛሉ:እኔ ግን በዋርካም ሆነ በግሌ የእነዚህ የአርሲ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ወገኖቼን የብሶስት ጥሪ ለአለም አስተጋብቻለሁ:: ይህ ቅን ተግባሬ ወይም በሀገሬም ሆነ በባህር ማዶ በኢ/ኦ/ቤ/ክ ፕሮግራሞች መካፈሌ "ተዋህዶን ለመምሰል" የሚል ጮርቃ ግንዛቤ በዚሁ ግለሰብ አሰጥቷል::

ለማጠቃለል ኢትዮጵያዊ አጀንዳችንን በእምነት መለያየታችን እንደማይገድበው ከብዙ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ወገኖች ጋር በሚኖረኝ ስብሰባና እንቅስቃሴ ሁሉን የሚያውቅ ጌታና ወገኖቼ ስለሚረዱ አሁን ይህ የክርስቶስ ቤተሰቦችን ካቶሊክ ኦርቶዶክስ ፕሮቴስታንት በማለት የሚከፋፍል ግለሰብ ሊነቅፈኝ አንዳች ብቃት ከቶ የለውም::

በተረፈ መከራዋ ለበዛው ሀገራችን የግፈኛ ጨቁዋኞች መሳሪያ በመሆን የህዝቡን ሰቆቃ ጆሮ ዳባ ልበስ ያሉትን "የቅዱስ ሲኖዶስ"ጳጳሳትህን እንድናስተናድ ላቀረብከው ጥያቄ ንስሀ ገብተው እስከተስተካከሉ ድረስ የጌታ ቤት በግዝት ሰው ለዘለአለም የሚታገድበት ያለመሆኑንና የምህረትና የፍቅር አምባ መሆኑን እገልጽልሀለሁ::

ዲጎኔ ሞረቴው ከፍቅር ምህረትና ሰላም ተሀድሶ አደባባይ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

ዳጎኔ

Postby ቃኘው » Wed Dec 14, 2005 10:48 pm

ሠላም ላንተ ይሁን የኃሣብህ ተካፋይ ነኝ:: ወገኔ!
"ሞረቴ" ማለት ምን እንደሆነ ሁኔታውን አስረዳኝ::

አክባሪህ
ቃኘው
ከ(ሰሐሊን)
tank you
ቃኘው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 500
Joined: Thu Oct 23, 2003 11:35 pm
Location: Man

Postby Acts 8:26-39 » Thu Dec 15, 2005 3:01 am

አንብቦ የመረዳት ችግርህን እንቶፈንቴህን በለቀለቅህ ቁጥር በተደጋጋሚ እያረጋገጥክ ነው:: ለራስህ በፈጠርከው የቅዥት ዓለም ውስጥ ላንተነትህ የሰጠኸውን ትልቅ ሥፍራ ጥያቄ ውስጥ የሚከት አስተያየት ክፉኛ ያበሳጭህና የማያቋርጥ አተካራ ውስጥ ያስገባሃል:: ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ መልስ ብለህ የምትለቀልቃቸው የበለጠ ስለሚያጋለጡህ ብስጭትህንና የደም ግፊትህን እያናሩት ይሄዳሉ::

ለምሳሌ እኛ ከላይ ያልነው የሚከተለውን ሲሆን

Acts 8:26-39 wrote:ዲጎኔ
አምዱ የዜና አምድ ነው:: ማንም ግለሰብ የጀመረው አይደለም:: ችግሩ የጀመረው አዲስ አድማስ - 26-11-2005 ያወጣውን ዜና በሚመለከት
አንተ

"እሰየው ነው ይሄ የካቶሊኮች ቅዱስ የእውነት ተሟጋችነት !

እንግዲህ ካቶሊኮችን ለማውገዝ ድሮ የተከተበው የአለቃ አያሌው ታምሩ "መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና " ተሻረ በለኛ !

አሁን እንግዲህ አለቃ አያሌው ወይም ደጋፊዎች የሚጽፉ ከሆነ ርእስ በትህትና ልጠቁም :
" መች ተለመደና ከልጅ ገዳይ ወያኔ ዝምድና ""


በማለት ዜናውን ጠልፈህ አርእስቱን ብቻ በምታውቀው ፈፅሞ ባላነበብከው የአለቃ አያሌው መጽሐፍ ነቀፌታ ስምና የካቶሊክ ቤተክርስትያንን የምታደንቅ መስለህ ያደረግከውን በፀረ -መለስ ፖለቲካ የተደበቀ ፀረ -ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፕሮፓጋንዳ ምክንያት ነው::

ዝርዝሩን ማንም ወድ ኹዋላ ሄዶ ሊያየው ይችላል::

በእምነትህ የማታፍር ከሆነ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለመምሰል እምታደርገውን ያልተሳካ ሙከራ ትተህ በግልጽ ፕሮቴስታንት ነኝ ብትል ችግር የለውም

የኛ አባቶች ጳጳሳት ንፁሃን ናቸው..."ሆዳምና ፈሪሳዊ" ወያኔ በቤትክርስትያን ላይ የጫናቸው ሲሆኑ እነሱን ተቀበሉ ከሆነ ከፈለግህ አንተ ሰፈር ውሰዳቸው እንጂ እኛ ጋ ቦታ የላቸውም....

አሁንም ቢገባህ በተደጋጋሚ እንነግርሃለን ፀረ -ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፕሮፓጋንዳህን በፀረ -መለስ ፖለቲካ ለመደበቅ አትሞክር :: ፕሮቴስታንት ሆነህ አፍቃሬ ካቶሊክ ለመምሰል አትሞክር:: ይኼ የተበላ ዕቁብ ነውና ሌላ ካለህ ሞክር !!


በዚህም ወያኔ "ጳጳሳት" "ፓትርያርክ" ብሎ የሾማቸው ቅድስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን አይወክሉም ...የኛ ጳጳሳት አይደሉም እያልንህ መልሰህና መላልሰህ እኛ ላይ ልትለጥፍ የምትሞክርበት ምክንያት አሁንም የፖለቲካ ትርፍ ስላለው ብቻ ነው::

TPLF የፖለቲካ ድርጅት ነው:: ካድሬዎቹ "ጳጳስ' "ሼኽ" ወይም "ፓስተር" ተብለው በሃይማኖት ድርጅት ውስጥ ቢመደቡ አለያም የመንግሥት ሚኒስቴር የግል ድርጅት ከበርቴ ወይም የመንገድ ላይ ለማኝ ተደርገው ድርጅታዊ ሥራ ቢሰጣቸው ያው የTPLF ካድሬዎች ናቸው የሚያገለግሉትም የፖለቲካ ድርጅታቸውን ነው::

TPLF ካድሬዎቹን በስመ "ጳጳስ" ና "ፓትርያርክ" የጫነባት ቤትክርስትያናችን ከማንም በላይ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ሆናለች:: "ፓትርያርክ" ተብዬውም ሆነ "ሲኖዶሱ" እንኳን በሕዝባችን ላይ ስለደረሰው ግፍና በደል ይቅርና "እንመራታለን" በሚሏት ቤተክርስትያን ላይ እጅግ ከፍተኛ ግፍ ሲፈጸም ትንፍሽ አይሉም:: ተልዕኵዋቸው ድርጅታቸው TPLF የስጣቸውን ግድጅ በታማኝነት መፈፀም ነውና::

ይሁን እንጂ ዛሬ ፀረ-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤትክርስትያን ኃይላት ሆነ ብለው እነዚህን "ጳጳሳት" እያሳዩ ቤትክርስትያኗን ለማጥፋት የወጠኑትን እቅድ ለማስፈፀም ይቅበዘበዛሉ:: እዩት TPLF የሚስራውን እንደማለት እዩዋት ቤትክርስትያናቸውን ይላሉ:: በሚፈጠረውም ውዥንብር ቅኖችና የዋሆችን ወደ ካምፓቸው ለመጥለፍ ይራውጣሉ::

በዚህም thread ላይ የታየው ይኸው ነው:: አምታቶ: ዋሽቶ:
ግራ አጋብቶ ቤተክርስትያንን ለመናድ የሚደረግ ጥረት::
አለያ በወያኔ ካድሬዎች ከፍተኛ ግፍ እየተፈጸምባቸው የሚገኙትን የቤትክርስትያናችን ሊቃውንት ጉባኤ ስብሳቢ አለቃ አያሌው ታምሩን ኢላማ ማድረግ: አፍ ሞልቶ ያላነበቡትን መጽሐፋቸውን ማውገዝ ምን ሊባል ይችላል??
ይህ አምዱ ከተከፈተለት የዜና ርዕስ ጋር ምን ዝምድና አለው??

የጎረቤት ሌባ ሲመቸው ይሰርቃል ከደረሱበት ይስቃል እንዲሉ ፀረ-ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅስቀሳ ሴራው እንደተነቃብህ ሲነገርህ ለማድበቅበቅ የባጥ የቆጡን ትዘባርቃለህ.....

እርምህን አውጣ.....የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤትክርስትያን እንኳን ባንተ በዋርካው የኪቦርድ ፋኖ ይቅርና በግራኝ ነፍጥ በጉዲት እሳት በሞሶሎኒ መርዝ ጋዝ አልጠፋችም...አትጠፋምም በጌታችን በመድሐኒታችን እንዲሁም በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ደም የማይናወጽ መሠረት ላይ ተገንብታለችና

በነገራችን ላይ እጅጉን ያበሳጨህ ማርቲን ሉተርን የሚመለከተው ጽሁፋችን ይቀጥላል ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችም በማግኘታችን እነዚህንም ለዋርካ ታዳሚ እንደምናቀርብ ከወዲሁ እንገልጽልሃለን...
Acts 8:26-39
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 216
Joined: Tue Apr 26, 2005 8:10 pm

መረቴው የተገረዘው በክፉው ትንኮሳ ክፉ አይወጣውም

Postby ዲጎኔ » Thu Dec 15, 2005 3:56 am

ሰላም ለሁላችን

1.ወዳጀ ልቤ ቃኘው

እንደማለፊያ ስምህ ቃኝተህ ስለሰጠህኝ ማበረታቻ እያመሰገንሁ: ሞረቴ ማለት በኦሮምኛ የተገረዘ ሲሆን ይህ ስም የተሰጣቸው ኦሮሞውቹ ባሉበት አካባቢ ፈልሰው የሰፈሩና ግዝረት የሚፈጽሙ ሴማዊያንና ይሁዲዎችን ለማጥላላት የተሰጠ ስም ነበር:: ሆኖም ግን እነዚህ ሰፋሪዎችን ጸረ ክርስቲያንና ጸረ ይሁዲ የሆኑትየቤተክህነት ደብተራዎች ላይጠቀሙበት በነገሰታቱ አዋጅ የያዙትን የሲሶ መንግስት መሬት እየከለከሉ ስያሜውንም አጠናከሩት:

ከእነዚህ ሞረቴ የሚባሉት ወገኖች በሰሜን ሸዋ የሰፈሩት ትውልድ የአጼ ቴዎድሮስ የልብ ወዳጅና አማካሪ የ19ኛው ክፍለዘመን የኢትዮጵያ ተሀድሶ በኩር አለቃ ዘነብ ሲገኙ ታሪኩንና ስያሜውን ከእኛ የበለጠ የሚያውቁት እንግሊዞችና በሎንደን ያሉት የብሪታኒያ የባህር ማዶ ሚሲዮን ጥራዞች ሲሆኑ በኢትዮጵያ የታተመው "የመጽሀፍ ቅዱስ ታሪክ ባማርኛ" የሚል በፍለድ የተዘጋጀ መግቢያው ላይአጼ ቴዎድሮስ ለአስተያየት ተሰጥቷቸው እጅግ ወደዉት እንዳስቀሩት የሚገልጸው ነው::

እኔም እንደዚህ ከሚብጠለጠሉት ሞረቴዎች ኦሮሞዎችና ከፊቾዎች የተወለድኩህ ድብልቅ ግን ፍጹም ኢትዮጵያዊ መሆኔን ለማሳየት እጠቀምበታለሁ:: ሞረቴዎች ሙሉ በሙሉ ሴማዊ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ከፊሎቹም ይሁዲነት ያለባቸውን ወደክርስትና ቢገቡም የእስራኤል መንግስት ፈላሻ ሙር ብሎ ተቀብሎ እየወሰዳቸው ነው:አንሄድም ያሉና እስራኤል ደርሰው የተመለሱትንም አለቃ አስረስ የተባሉ የተሀድሶ አባት ኮተቤ ሰፈር ሲያስተምሩዋቸው በአካል ለማየት ችያለሁ::በተጨማሪም በኦፕሬሽን ሙሴ አውሮፕላኑ ተጠቅጥቆ ሲጉዋዙ አዲስ ኪዳንና ትንቢተ ኢሳይያስን በአማርኛና በእብራይስጥ ያደልናቸው ወገኖቼ ሲሆኑ ባለፈው ፋሽስቱ መለስ እስራኤል በሄደበት ጊዜ በነቂስ እንዳይወጡ በከፍተኛ ማባበል የታቀቡ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ ወኔ ያላቸው ተሀድሶዎቹና ወንጌላዊያኑ "ቤት ሻሎም"በሚባል ማህበረም እመናን ያመልካሉ:ይሁን እንጂ የእስራኤል መንግስት ፖሊሲ ይሁዲ ስለሆነ ብዙ ድጋፍ አያገኙም ቤተክርስቲያንም ለማነጽም እንደመሲያኒኮቹ ችግር አለባቸው::ምናልባት ዝርዝሩን ወደዚያ ካቀኑት የልብ ወዳጄና የዘጋቢነት አጋሬ ሰምቶ እንዲጨምር አሳስባለሁ::

2. ለግብረ ሀዋርያ ተብዬው- እዚህ የቀጠለው ርእስ በወቅታዊው የሀገራችን ጉዳይ ላይ ትልቅ ጀብዱ ስለፈጸሙት የካቶሊክ ጳጳሳት በመሆኑና ህዝባችንም በአብዛኛው አንተም እንዳመንከው "ጳጳስ"ሲባል ትውስ የሚለው ተጋዳላይ ጳውሎስና ግበረአበሮቻቸው የነፈሰገዳዩ መለስ ዜናዊና የአሽከሮቹ የነፍስ አባቶችን በመሆኑ ተለይተው እንዲታወቁና በሀገራችን 'ኮተለከ" እየተባለ እንደጭራቅ ሲወገዝ የነበረው እምነት አባቶች አሁን የፈጸሙትን ታላቅ ወቅታዊ ጀብዱ ለማበረታታት በከንቱ የተጻፈባቸው "ተኩላ"ባይ መጽሀፍ ጊዜ እንዳለፈበት ለመግለጽና መቀባበል እንዲከሰትመሆኑን ቅን ህሊና ያለው የሚረዳው ስለሆነአንተ እንደምትከሰኝ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን ለመንቀፍ አይደለም::
( በነገራችን ላይ ቤ/ክርስቲያኒቱ በአድዋ ድል ያደረገችውን አስተዋጽኦና በአምስቱ አመት ትግል በዋሻ ሚካኤል ጀግኖች አርበኞች በተለይ ቀሳውስቱ የፈጸሙትን ጀብዱ እዚሁ ዋርካ ላይ የጠቀስኩትን በተለመደው የፋይል ብርበራህ ገብተህ እይልኝ)

በተረፈ የብዙሀኑ ኢትዮጵያዊ ህዝበ-ክርስቲያን "ጳጳስቶችን" በማጋለጥና በማስቀናትወደ ህዝቡ ጎራ እንዲቀላቀሉ ያቀረብኩት መጣትፍ ማጣመም አቁም:ይህ ደግሞወንጀል ነው ብለህ ብታወግዝ ቅ/ጳውሎስ አይሁዶችንሊያስቀናወደ አህዛብ እሄዳለሁ ያለውን አንብብ::

በሌላ አምድ ስለሉተር የዘበዘብከውንማ ታዛቢ አያሳጣንና ሴምና እንታደስ የአንተን የአሉባልታና ውንጀላ ሀተታ መናፍስት እጥር ምጥን ባለ ሁኔታ ድባቅ መተውልኛልና እዚህ ባትጠቅስው ደህና ነው ምናልባትዶ/ር ሉተርን የመሰለ ለእምነትና ለህዝብ የሚጋደል ጳጳስ ይስጠን ብለን ከርእሱ ጋር ካላያያዝነው በቀር!

ዲጎኔ ሞረቴው የእናት ኢትዮጵያ ሰቆቃ ዘጋቢ
ከዸክ ሀራራ(የእርቅ ሰፈር በኦሮምኛ) የአሁኑ ሸራተን አዲስ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby Acts 8:26-39 » Thu Dec 15, 2005 5:31 am

ዳጎን !
ስንት ጊዜ እንንገርህ?? ምን ብለን ብንነግርህ ይገባሃል??
አርእስቱን ብቻ በምታውቀው ከቶ ባላነብብከው የአለቃ አያሌው መጽሐፍ ላይ አስተያየት ከመስጠት የምትቆጠበው መቼ ነው?? ከመተችት ማንበብ ይቅደም!!!

አሁን ደግሞ የTPLF ካድሬ "ጳጳሳት"ን "አጋልጠህና አስቀንተህ" ወደ "ሕዝቡ ካምፕ ለማስገባት" ስለምታደርገው ጥረት ነግረኸናል:: ፋሽሽቱ አለቃቸው እንደሚለው መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ... ጳጳስ ተብለው እኛ ቤተክርስትያን ቦታ እንደማይኖራቸው ከወዲሁ ንገራቸው

በኛ እምነት ግን በቤትክርስትያናችን ላይ የተጫኑትን የTPLF ካድሬ "ጳጳሳት" ከስርዓቱ ጋር አብረው የሚወገዱ ናቸው::
የመለስ ዜናዊ መወገድ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስትያናችንንም ነፃ ያወጣታልና እጅግ የምንናፍቀውና የምንታገልለት ዓላማችን ነው! ይህም ቀን ሩቅ አይደለም!!
Acts 8:26-39
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 216
Joined: Tue Apr 26, 2005 8:10 pm

ምንም መደባበቅ አይቻልም "ተኩላ" የተባሉት ቅዱስ ሆነዋልና

Postby ዲጎኔ » Thu Dec 15, 2005 6:00 am

Axsis 8 of sss octagon not Acts 8 of the Holy book

"ተኩላ" ተብለው በምትወዷቸው የሊቃውንት ሰብሳቢ የተወገዙት የካቶሊክ ጳጳሳት ቅዱሳን ብጹአን ነን እያሉ ከሚያደሟት ከእናንተ ጳጳሳት ተለይተው(ተቀድሰው) ለኢትዮጵያ መድረሳቸው በይፋ የተረጋገጠውን ማስተባባል ፈጽሞ አይቻልም!(የስደተኞቹን ብሶት አትደጋግምልኝ)
መጽሀፍ ቅዱስ እራሱን ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል ይል የለ?

ደግሞ "ተኩላ" እያለ ክርስቶሳዊ ወገኑን የሚሰድብ መጽሀፍ


ለምን ብዬ ነው የማነበው? ዳቪንቼ ኮድንም አንብብ በለኛ?
ያነበብኩዋቸው
1."እረኛውአንድ" "ለምን አልሰለምኩም" በቀደሰ/ፕሮፌ አለማየሁ ሞገስ (ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አባል
2. "ቅዱስ ጋብቻ" ቀሲስ ከፍያለው መራሄ(ኢ/ኦ/ቤ/ክ አባል(ወገናዊና ኢተአማኒ)
3. "ገድል ወይስ ገደል"መምህር ጌታቸው(ኢ/ኦ/ተ.ቤ/ክ)'(ወቅታዊና ተአማኒ)

በቅርቡ ደግሞ የሚነበቡ

1.የስደት ዘመኔ-በቀሲስ መላኩ(ኢ/ኦ/ቤ/ክ አባል)
2. ነገረመለኮትበንቡረእድ ኤርሚያስ ከበደ(ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ)
3.ታምረ-ማርያም-ለንጽጽራዊ ሂስ ብቻ

በተጨማሪም በዋርካ ላይ ቃል እንደገባህው "ከተኩላ ጋር" ቅኝትህን በቅዱስ ቃሉ መሰረት እርቃኑን እንደማወጣልህ ቃል እገባለሁ:ግን ይህንኑ ሰግተህ እነሆ አዳፍነህዋል!

ዲጎኔ ሞረቴው ከኢትዮጵያ የተሀድሶ መንፈሳዊ ግንባር
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby Acts 8:26-39 » Thu Dec 15, 2005 8:54 pm

ታላቁ ዳጎን

እንደተሰበረ ሽክላ ማጫወቻ ያንኑ ቅኝትህን መልሰህ መላልሰህ ትደጋግመዋለህ:: ጎብልሳዊ "ውሽት ሲደጋገም እውነት ይሆናል" አቋምህን አንግበህ የተለመደውን የሐሰት ፕሮፓጋንዳህን ትነሰንሳለህ...schizophrenic ስበዕናህ እውነታን የመቀበል አቅም የለውምና አይፈረድብህም

ባለመታደል በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያችን ኢትዮጵያዊ መሪ እንደሌላት ሁሉ ቤተክርስትያናችንም ቢያንስ በሐገር ቤት አመራሯን ተነጥቃለች:: ይህንን የአደባባይ እውነት አትቀበልም:: ከመስሪ ዓላማህ ጋር ስለማይሄድ በስደት ላይ ከአሉት እውነተኞቹ አባቶች በቀር ጳጳስ እንደሌለን መስማት አትፈልግም::

ላንተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን የሚጎዳ እስከመሰለህ ድረስ ሁሉም ነገር ተቀባይነት አለው:: ላንተ ወያኔ ቤተክርስትያኗን ለመቆጣጠር የመደባቸው የTPLF ካድሬዎች የቤትክርስትያኗ "ጳጳሳት' ናቸው:: በእርግጥ የእነዚህ ካድሬዎች መኖር ለተልዕኮህ እጅግ ጠቃሚ ነው:: እነሱን በማሳየት ቤተክርስትያናችንን መኮነን ስለምትችል:: በእርግጥ የእነዚህ ካድሬዎች መኖር ለተልዕኮህ እጅግ ጠቃሚ ነው:: ያለመሪ ያለችን ቤትክርስትያን እንደልብ ቦርቡሮ ለመጣል ይበጀናል ብለህ ስለምታምን:: TPLF ካድሬዎቹን ቤተክርስትያን ላይ ስለመደባቸው ባለውለታህም ጭምር ነው::
ከእናንተ ጳጳሳት ተለይተው (ተቀድሰው ) ለኢትዮጵያ መድረሳቸው በይፋ የተረጋገጠውን ማስተባባል ፈጽሞ አይቻልም !(የስደተኞቹን ብሶት አትደጋግምልኝ )
ለማለት ይመችሃልና!

ሎጂክህ ግን ደካማ ነው:: ወያኔ ቤተክርስትያኗን ለመቆጣጠር የመደባቸው የTPLF ካድሬዎች የቤትክርስትያኗ "ጳጳሳት' ከሆኑ ፓርላማው ውስጥ በተሰረቀ የህዝብ ድምፅ የከተታቸው ካድሬዎቹም "የሕዝብ ተወካዮች" ሊባሉ ነው?? ፋሽሽታዊ አገዛዙስ "ሕዝብ የመረጠው" ሊባል ነው?? ቆም ብለህ አስብ.... የቋመጥክለትን የፖለቲካ ትርፍ ወደ ኪሳራ የሚቀይር አደገኛ መንገድ ነው::

ወዳጆችህ የወያኔ ካድሬዎች "ጳጳሳት' ደመወዝ ከልክለው በቤትክርስትያናቸው ሕዝባቸውን እንዳያስተምሩ አግደው በቁም እስርኝነት እያስቃዩዋቸው ያሉትን የቤትክርስትያኗን አባት ሊቃውንትን ታጥላላለህ :: ባንተ የመንደር ወሬኛ ደካማ ጭንቅላት የአለቃ አያሌውን ስራ "እርቃኑን" ለማውጣት ትፎክራለህ!! ታላቁ ዳጎን ምን ሊሳንህ!!

ሳታነበብው የምትቃወመውን የአለቃ አያሌው ታምሩ መጽሐፍ በሚመለከት በዚሁ thread ቀደም ሲል
ስለ መጽሐፉ ለማያውቁና ይህንን ሊያነብቡ ለሚችሉ የዋርካ ታዳሚዎች የሚከተለውን አቅርበናል
የመጽሐፉን ሽፋንና የመጀመርያ ገጽ ያየ ስው እንኳን እንደሚያነበው
1. መጽሐፉ አባ አየለ ተክለ ሃይማኖት የተባለ ካቶሊካዊ የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ስለ ክርስቶስ ባህርያት አካላዊ ተዋህዶ የምታምነው ትምህርት በሚል ስም ሐምሌ 9 ቀን 1951 ላወጣው መጽሐፍ ሙሉ መልስ ሆኖ የተዘጋጀ ነው ::
2. አባ አየለ በመጽሐፉ ሽፋን ላይ የኢትዮጵያን ካርታ ሰርቶ አንበሳው (በወቅቱ የኢትዮጵያ አርማ ) የቫቲካንን ሰንደቅ ዓላማ እንደያዘ ስላሳየ በወቅቱ ሊቀ ጠበብት አያሌው ታምሩ የመልስ መጽሐፉን "መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና " ብለውታል :: ተኩላ የሮማውያን አርማ እንደነበር ያጤኗል ::

3. ከሽፋኑና የመጀመርያው ገጽ አልፎ መጽሐፉን በጥሞና ያነበበ ደግሞ መጽሐፉ አንተ እንደምትለው "የግዘት " መጽሐፍ ሳይሆን በካቶሊክና ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነቶች መሀከል ያለውን ልዩነት አለቃ አያሌው ታምሩ መጽሐፍ ቅዱስን እና ታሪክን ተመርኩዘው በዝርዝርና በጥልቀት ያስተማሩበት ድንቅ ሥራ መሆኑን ሊመሰክር ይችላል !


ብለን ነበር::

..ያለበት ዝላይ አይችልም እንዲሉ የበግ ለምድ የለበስክ ተኩላ በመሆንህ በመጽሐፉ አርዕስት ላይ የለው ተኩላ የሚለው ቃል አንተን የሚያጋልጥ ስለአንተ የተነገረ እየመሰለህ ክፉኛ ያስደነግጥሃል::ደግሞ "ተኩላ " እያለ ክርስቶሳዊ ወገኑን የሚሰድብ መጽሀፍ ለምን ብዬ ነው የማነበው ? ትላለህ እናም የመጽሐፉ ይዘት ቀርቶ...ትንቅንቅህን ሁሉ በተኩላ ዙርያ አድርገኸዋል::..."በጎቹ ነቁብኝ...ተኩላ መሆኔን አወቁ..." እያልክ ትባንናለህና ቃሉ ያስፈራሃል:: አንፈርድብህም::

ይሁን እንጂ ማንም ጤናማና የሰከን አእምሮ ያለው መጽሐፉ በካቶሊክና ኦርቶዶክስ እምነቶች መሃል ያለውንና ከሺህ ዓመታት በላይ ዘመን ያስቆጠረውን የዶክትሪን ልዩነት የሚመለከት መሆኑን መገንዘብ አያቅተውም:: እነዚህ ሁለት እምነቶች ብዙ የሚያመሳስላቸው በጋራ ሆነውም ከፕሮቴስታንቱ እምነት የሚለያቸው ስፊ የዶክትሪን ልዩነቶች እንዳሉዋቸውም ለማንም የሚታወቅ ነው::

የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ሆነህ በካቶሊክና የኦርቶዶክስ የዶክትሪን ልዩነት ውስጥ ገብተህ ልፈትፍት ማለትህ ስሕተት መሆኑ ጠፍቶህ አይመስለንም ሳታነብ ለምን ትተቻለህ የተባለውን ለማድበቅበቅ እንጂ...ይኼንኑ ለመደበቅ ሌላ ውትወታ ውስጥ ገባህ:: እናም በቅዥቱ schizophrenic ዓለምህ ለራስህ የሰጠኸውን ታላቅ ቦታ ጥያቄ ውስጥ ከቷልና ከዚህ በምናብህ የተፈጠረ አስጊ ሁኔታ ለመውጣት ትዳክራለህ....አይዞህ በእውኑ ዓለም በዋርካ ስምህ የሚያውቅህ ብዙ ሰው የለምና አትስጋ::

ይሁን እንጂ በዋርካ ኪቦርድ ፋኖነት በቤትክርስትያን ላይ የጀመርከውን ዘመቻ በሚመለከት ከላይ ቀደም ሲል እንዳልንህእርምህን አውጣ .....የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤትክርስትያን እንኳን ባንተ በዋርካው የኪቦርድ ፋኖ ይቅርና በግራኝ ነፍጥ በጉዲት እሳት በሞሶሎኒ መርዝ ጋዝ አልጠፋችም ...አትጠፋምም በጌታችን በመድሐኒታችን እንዲሁም በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ደም የማይናወጽ መሠረት ላይ ተገንብታለችና


በመጨረሻም በቀላሉ የሚቆሰል ego ይዘህ እንዲህ የተለያዩ እምነቶች በሚንሽራሸሩበት መድረክ ላይ የሌሎችን እምነት የሚነካ ትችት ባትለቀልቅ ራስህን justify ለማድረግ የማያቋርጥ ንትርክና ውሸት ፈጠራ ከመግባት ያድንሃል:: ብስጭትና የደም ግፊትህን ከፍ ከማለት ትጠብቃቸዋለህ::
"ይህ አምድ የሃይማኖት አምድ ባለመሆኑ አዲስና የተለየ የምታቀርበው ጉዳይ ካለ ዋርካ ጄነራል ላይ እንገናኝ ::"
Acts 8:26-39
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 216
Joined: Tue Apr 26, 2005 8:10 pm

መምሬ ግብረውግዘት ከካቶሊክ ጳጳሳት ገድልተማሩ ዜና

Postby ዲጎኔ » Fri Dec 16, 2005 3:25 am

መምሬ ግብረ-ውግዘት

የተለመደውን ስድብህን በቀኝ ጆሮዬ ሰምቼው በግራ ጆሮዬ ማስወጣቴን እገልጽልሀለሁ::

ይህ ርእስ ትልቅ ወቅታዊ የእናት ኢትዮጵያ በጎ ዜና ስለሆነ "ለመንጋው ጳጳስ" የሚለውን ሀዋርያዊ ቃል የሚያሟሉትን የካቶሊኮች ገድል ሀገር ቤት ላሉት ወያኔያዊያን ጳጳሳት እንድታደርስልኝ እየጠየቅሁ በስደት ያሉ ጳጳሳቶችን ደግሞ በርቱ በዚሁ ይልመድባችሁ አንድ እርምጃ ወደፊት ሄዳችሁዋል በልልኝ::

እውነት እልሀለሁ እምዬ ዋርካ እንደልቤ መተንፈሻዬ እያለችልኝ ምንም ብስጭት የለብኝ ደግሞ ልክ ነህ በብእር ስም በመቅረቤ እንጂ በአካል ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ አራዳ ጊዮርጊስ ወረድ ብሎ በቆንጨራ ሊቆርጠኝ እንደፎከረብኝ ኢስቡላ መሰል ቀናተኛህ ትዘለዝለኝ ነበር ቂቂቂ ወደው ....

ዲጎኔ ሞረቴው ከእናት ኢትዮጵያ ሁለገብ ተሀድሶ አምባ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ዲጎኔ » Fri Dec 16, 2005 5:09 am

[quote=
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

ምነው ዘገዩ?

Postby አኒታ » Mon Jan 23, 2006 11:44 pm

እረ ጎበዝ . ምንው ዋርካ አዳዲስ ዜና ማቅረው ተወ እንዴ? ስንት ነገር ሆኖ አሁን ማይረባ ወሬ? ምነካቸው ይሄ እኮ ማታለያ የ መንግስት እቃቃ ነው... የ አውሮፓን መንግስትና የ ቡሽን አስተዳደር የ አንድ ጳጳስ የዘገየ ጩኽት አይመክትም.. እርዳታው ሰለቆመ ነው ወይስ የት ነበሩ? እኔ የማንን ጳጳስ ለመዝለፍ አይድለም,.... ግን ጅብ ከሄደ ውሻ እዳለው ተረቱ አልሆነምን? አይይይ ያሳዝናል ስንቱ በደጁ ተደፍቶ የሞተው እረ ስንት ስንት.. ምነው ለዛ አንድ ቀን እንኳን የህሊና ጸሎት ወይም..... እግዚዮ በሉ ብለው ህዝቡን አላነሳሱ? ይህስ ሆኖዋልን? ድሮ ቀረ! አምላካቸውን አስቀድመው ለህዝባቸው ሲሉ መንግስት የገደላቸው.. ለማስታረቅ.. ለመምከር ሲታገሉ እረ ስንት ነበሩ.. ያሁኑን ዝም ነው!
አምላክ ይመርምረው... ለማንኛውም ዋርኮች አዲስ ዜና አቆማችሁ እንዴ? ወይስ ጥይቱ ምንሰማው በየቀኑ እንደ 3 ብር እርችት ወደላይ ነው :lol: ቂቂቅቂቂቅ... ቸር ይግጠምን...
ለማንኛውም በፊት በትኩሱ እንጂ..በአፍላው ጊዜ.. በማክተሚያው አይሁን ጥረቱ.. ልቦና ለሁላችንም ይስጠን
እረ አምላክ ይቅር ይበለን.. ከምር መምህሮቻችን መንግስትን ፈርተው እግዚዮ በሉ ባይሉም ሁላችንም በየ እምነታችን ለፈጣሪ እንለምን.. መአቱን ያብርድልን ጥሩውን እንጂ ክፉው አያሰማን..
እግዚአብሄር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ያስባት!
አክባሪያችሁ
አኒታ
ቺርስ ....
አኒታ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 704
Joined: Sat May 29, 2004 10:03 am
Location: City of angels

Postby አክየ » Thu Feb 09, 2006 7:59 pm

አኒታ ደግሞ ሽማግሌ መሆን አማረሽ
"Say what you have to say in the fewest possible words"
አክየ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2615
Joined: Thu Jul 28, 2005 7:43 am

Postby አክየ » Thu Feb 09, 2006 8:01 pm

አኒታ wrote:ቂቂቂቂቂቂቂቂ


ምን ተብለሽ ነበር
"Say what you have to say in the fewest possible words"
አክየ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2615
Joined: Thu Jul 28, 2005 7:43 am

edemawen yestute

Postby ሙራጋ » Thu Feb 09, 2006 11:45 pm

አባ እድሚውን ይስት ከአባ አብነ poluse ላይ kensu [/b]
my name and e-male adriss
ሙራጋ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Thu Oct 30, 2003 7:41 pm
Location: ethiopia

EthioBusiness Center UK and US Cities

Postby sewd05 » Sat Feb 25, 2006 6:46 pm

የኢትዮጵያ ንግድ ማእከል በ ለእንግሊዝ እና ለአሜሪካ ነዋሪዎች አገልግሎት መስጠት ጀመረ
EthioBusiness Center Goes International
በቅድሚ ሰላምታችን ይድራሳችሁ፡፡
EthioBusiness Center is expanding its service in order to serve its customers efficiently and effectively. In our global service we are offering the following services to our customer’s more than ever.

የኢትዮንግድ ማእከል አገልግሎቱን በማስፋፋት በአሁኑ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ለማገልገል ከምንጊዜውም በበለጠ ታጥቆ ተነስቷል፡፡ በዚህም ልዩ የሆነ አለም አቀፍ አገልግሎት እርስዎም ተጠዋሚ እንዲሆኑ ከዚህ በታችች ያሉትን አገልግሎቶች እንደምንሰጥ ስናስታውቅ በታላቅ ደስታ ነው፡፡
1. Airlines Ticket: By partnering with the Ethiopian airlines and other major airlines we are offering airlines tickets sales for passenger who are departing to Ethiopia or from Ethiopia
1. የአውሮፕላን ትኬት፡ ሀገርን ወገንን ለመጎብኘት ወደ ሀገር ቤት ጎራ የሚሉ ከሆነና ወይም ከሀገር ቤት ወደ ተለያዩ የሀገር ክፍሎች የሚጓዙ ከሆነ ይደውሉልን ለማገልገል ዝግጁ ነን፡፡

Document Translation: For any kind of document translation from any Ethiopian language to English or vise-versa. Bring the document and we will offer the service
2. የዶክሜንት ትርጉም ስራ፡ ለማንኛው አገልግሎት የሚሆን በሙያው ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ከማኛውም የኢትዮጵያ ቋንቋ ወደ እንግሊዘኛም ሆነ ወደ ሌላ ቋንቋ እንተረጉማለን፡፡

የህም የሚያጠቃልለው፡ የልደት ወይም የጋብቻ ምስክር ወረቀት (Birth or Marriage certificate)_
የመንጃ ፍቃድ ማስረጃ )Driving license or ID translation)
የፍርድ ቤት ውሳኔ (court papers)
የውርስ ወይም የውክልና ማስረጃ (wills or power-of-attorneys)
የኢሚግሬሽን ማመልከቻ ወይም ማስረጃ እና ሌሎችንም (Immigration papers and applications))የሚያጠዋልል ሲሆነ፡ ወደ ህክምና ወይም ፍርድ ቤት ሲሄዱ አስተጓሚ. ካስፈለገዎት ደውለው ይጠይቁ ን ለማገልገል እግጁ ነን፡፡ (If you need court or medical interpretation please let us know )

3.የህትመት ስራ፡ ለሰርግ ለልደት ክርስትና እና ለመሳሰሉት የመጥሪያ ካርድ ካስፈለገዎ ይደውሉልን ለመርዳት ስግጁ ነን፡፡ (Printing service: For christening, wedding or other occupations invitation cards)

4.የቪዲዮ መገልበጥ ስራ፡ ያለዎን ወርቃማ የቪዲዮ ማስታዎሻ ከኢትዮጵያ ሲስተም ወደ አሜሪካ ሲስተም መለወጥ ከፈለጉ ያስታውቁን ለማገልገል ዝግጁ ነን፡፡ እንዲሁም ወደ ዲቪዲ እንለውጣለን፡፡ (video conversion. If you want to keep your golden memories in a digital media or if you want covert the PAL system to American NTSC system, we have the solution for you)

5. የወብሳይት ስራ፡ ድርጅትዎ በአለማ አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ከፈለጉ የብ ሳይት ስራ እንሰራለን፡፡ Web site development for your personal or business

6. ፎቶግራፍ የማደስ ስራ፡፡ አሮጌ ፎቶ ካለዎት እናድጋለን፣ እናድሳለን፣ እናትማለን፡፡ Image restoration
7. ማስታዎቂያ እንሰራን፣ መፅኃፍ ለመፃፍ ካሰቡ እናትማለን፡፡ Advertising and book printing

ሌሎችም ስራዎች ስለምንሰራ ባሉበት ሆነው የአገልግሎታችን ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በላሙሉ ተስፋ ነን፡፡ Use our service from the comfort of your house. Call us at:

London: 02 07 0960849
Los Angeles: (213) 291 8049
New York: (347) 293 0766
Washington, DC: (202)-536-4656
Coming soon
Frankfurter, Paris, Seattle, San Jose, Minnesota, Columbus, Ohio, Kansas City, Atlanta, Dallas and Houston
sewd05
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 79
Joined: Tue May 24, 2005 2:22 am
Location: ethiopia

Re: ወዳጄ ልቤ ግብረ -ሀዋርያ አስተያየቱን ተቀብያለሁ

Postby ውበት አድናቂ » Fri Mar 24, 2006 4:49 pm

ዲጎኔ wrote:ዲጎኔሞረቴው ከዸክ-ሀራራ(እርቅሰፈር) የአሁኑሸራተን አዲስ


ዲጎኔ:

ኢትዮጵያዊ መስለህ ግን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ከሚጥሩት ጋር አብረህ የምታጨበጭብ ርካሽ ሰው ስለሆንክ ላንተ ምንም አይነት አክብሮት የለኝም:: በየቦታው የምትለቀልቀውን ተመክቼ ምን ያህል ጸረ ኢትዮጵያ እና ጸረ ኦርቶዶክስ አቋም እንዳለህ ተረድቻለሁ:: ደግነቱ እንደነ "ግብረ ሀዋርያት" ያሉ እጅግ የበሰሉ አዋቂዎችና እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ከሚያንዘፈዝፍህ ክህደት ሊፈውሱህ ጥሩ አድርገው የማትወደውን መድሀኒት እያቀመሱህ ስለሆነ ተሽሎህ ሰው ትሆናለህ የሚል ግምት አለኝ:: ዳሩ ግን አንተ እነ ሉተር የጋቱህን ውሸት እያቀረሸህ መኖር የምትወድ አይነት ደካማ ነህና ክብር ያለው ኢትዮጵያዊ ለመሆን የምትፈልግ እንዳልሆንክ ግልጽ ነው:: ሉተርን እንተወውና ከላይ በፊርማህ ላይ እንዳስቀመጥከው ያዲሳባውን ሼራተን የገነባው የአረብ ቱጃር ገንዘብ ከፍሎህ "ሼህ" የሚል ሥልጣን ቢሰጥህ ጫማውን ልሰህ የምትቀበል ወራዳ መሆንክን እያሳየኸኝ ነው:: እስቲ እነግብረ ሀዋርያት ከሚጽፉት ቁምነገር ትምህርት ለመውሰድ ሞክር:: የራስህን ድንቁርና አውቀህ ለመማር መሞከር እኮ ትልቅነት ነው::

በኢትዮጵያዊ ስም ለመራቀቅ የሚሞክሩትን እንደ ዲጎኔ ያሉትን አላዋቂ ቅሌታሞች አጥብቃ የምታወግዘው
ውቢት
ውበት አድናቂ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Thu Sep 22, 2005 5:21 pm
Location: ethiopia

PreviousNext

Return to Warka News - ዋርካ ዜና

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest