"የሞት በቃ ፍርድ"ን በመቃወሙ ረገድ እጅግ አድርገን እንደግፍዎታለን::አንደኛ "አትግደል::"የሚለው የፈጣሪያችን ት'ዕዛዝ በመሆኑ::ሁለተኛ እኒህ የአፍሪካ ጀብደኞች በየምክንያቱ እየተነሱ ክቡሩንና መተኪያ የሌለውን የሰውን ህይወት እንዳይቀጥፉ ልጕም ይሆንባቸዋል ብለን ስለምናምን::
እዚህ የተጠቀሱትን ግለሰብ አስመልክቶ ምንም አለማወቅዎ ትንሽ ለማመን ቢያዳግተንም በአይናችን ባናይም በይሁኔ ከተገለጸው በከፋ አረመኔያዊ ተግባራቸው እጅግ የታወቁ ናቸው:: ከገደሏቸው ይልቅ በሕይወት ያሉና የርሳቸውን ስም ሲሰሙ የሚያንቀጠቅጣቸውን ማየቱ ይሰቀጥጣል::ያ ሳያበቃ የመለስ መቀጠሉ....!!!!
የዘር ማጥፋት የሚለው ጠባብ ትርጉም ያለው ይመስለናል::"ጄኖሳይድ" የሚለውን የውጭውን ቃል የሚተካ አይመስለንም::ይህንኑ ሁኔታ መለሳውያን እየተጠቀሙበት ናቸው::በጊዜው ነበርን::የአንድ ቤተ-ሰብ አባላት በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ በመግባት ተራኩተዋል!!!!
አንዲት ገጠመኝ ብቻ በማንሳት ይህንኑ ለማስረዳት እንሞክር::
ጎረቤታችን አንድ ቤተ-ሰብ ነበር::በዚህ ቤተሰብ ውስጥ አባት:ሁለት ወንድ ልጆችና አንዲት ሴት ልጅ ነበሩ::አባት "ተስፋለ-ዘውድ" ተብሎ የሚጠራው ኢዲዩ አባል: አንዱ ልጅ የመኢሶን አባል:ሌላው ልጅ የኢሕአፓ አባል ሆኑ::መኢሶኑ አባቱንና ወንድሙን "በጸረ-አብዮተኝነት" አሳሰረ::መኢሶን ሲፈረጥጥ እርሱም አባቱንና ወንድሙን ከርቸሌ ተቀላቀለ::እነርሱ ሲፈቱ እርሱ እዚያው...ከዚያ በኆላ ያለውን አናውቅም::ደም በጁ የለም::እንዲህ እንዲህ እያለ በቤተሰብ መካከል እንኩዋን ደም የፈሰሰበት ስለመኖሩ እርግጠኞች ነን::ዜር ማጥፋት የሚለው ሊነሳ ይችላልን?
መለሳውያን የጀኖሳይድን ትርጉም ለአላማቸው እያዋሉት ነው::የትግራይን ሕዝብ ከጎናቸው ለማሰለፍና ማለቂያ ወደ ሌለው የርስበርስ ጦርነት ለመግባት የሚያደርጉት ይመስለናል::ያ ጦርነት ደግሞ የትግራይ ትግሪንን መንግስት ለመመስረት ከነበራቸው የጠኆቱ አላማቸው የመነጨ ይመስለናል::መለሳውያንን ለማስወገድ ከተፈለገ እያንዳንዱ ቤቱን ማጽዳት ያሻዋል::በሰላማዊው ትግል::ክሎኒንግን መለሳውያን እየተጠቀሙበት ነውና ክሎኖቹን ለይቶ በማውጣት ወደ ሕዝቡ እንዲመለሱ ማድረግ ነው::ሆድ አደሮች ናቸው ትናንትም ሆነ ዛሬ ይበልጥ ያጠቁን::
"የቅንጅትን አባላትም በሞት ይቀጣል::" የሚል ፍራቻ ያሳደረብዎ የመላኩ መቀጣት መሆኑ ሳይገርመን አልቀረም::እንዲያውም ግብዝነቱን ነው ቁልጭ አድርጎ ያሳየው::ሕዝቡ የተደረግውንና የሚደረገውን ሁሉ በአርሞሞ ያየዋል እኮ!!!!"በማንም ላይ ለመፍረድ የሞራል ብቃቱ እንኮአን የለህም!እንኮአን የሕግ ድጋፍና መሰረት ይቅርና! አንተ የምት'ሰራው እርሱ ከፈጸመው በምን ይለያል?" እያለ እየጠየቀ ነው::መላኩን 'በሞት ቅጣት" መቅጣቱ ልዩ ምልክት ሊሆነን አይችልም::ምልክቱ የታየው ከዚያ በፊት ነው:_ሀገር ሲገድል::እነመላኩንም ያሳበደውና ለዚህ ያበቃውስ ማን ሆነና ነው? ካድሬዎቻቸው በመሀል ሀገር አልነበሩምን? ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል....
Monica**** wrote:ይሁኔ
ስላም ያገር ልጅ
በመጀመሪያ ስለጨዋ አስተያየትሽ/ህ ሳላመስግን አላልፍም!!
በትክክል ሻለቃ ተፈራን አላውቃችውም ስማችውን ለመጀመሪያ ጊዜ ስስማው ነው!!!!
ይሄን ያህል ካጠፉና ስው ከገደሉ በርግጥ ፍርድ ይገባችዋል ግን ሞት?
በዚህ አይነት እኮ በእስር ላይ ያሉትም የቅንጅትን መሪዎች ይሄ ስውዬ ሊጨፈጭፍ ነው! ካለፈው መማር ሲገባን እንዴት ወደህዋላ እንሄዳለን?
በርግጥ ስውየው በዘር ከፋፍሎ ነው ስው የገደለው ወይስ በፖለቲካ አመለካከት?
እንደዛ ማለት ጥፋቱን ቀላል ወይም ከባድ ያደርገዋል ለማለት ሳይሆን የዘር ነገር በወያኔ ጊዜ ነው በሀይል የከፋው እንጂ ከዛ በፊት ብዙ መጥፎ ነው ብዬ አላስብም! ወይም ህዝቡ ደርግን ፈርቶ ዝም ብሎ እንደሆን አላውቅም!
ወያኔ ግን ይሄንን ስውዬ በዘር በመከፋፈል ብሎ ሲወነጅል በጣም ገርሞኝ ነው!
በዛ ላይ an eye for an eye የሚሉት ሁዋላ ቀር አስተሳስብ የት ሊያደርስን ነው??? ያጠፋን በቁም ስቅል ማሳየቱ ሳይሻል ይቀራል ከመግደል? እሱን ለአምላካችን መተው ይሻላል ብዬ ነው!!!
አክባሪሽ/ህ
ሞኒካ
1. "Ignorance is the night of the mind, but a night without moon and star." -
-- Confucius
2. "Reading maketh a full man, conference a ready man, and writing an exact man." -
-- Sir Francis Bacon