ወደ አነሷቸው ነጥቦች ስንመለስ የርስዎ ሻለቃውን አለማወቅ የርስዎን ማንነት የሚገልጽ ስለመሆኑ ያነሳነው ነገር የለም::ቢያንስ ቢያንስ በዚህ የውይይት መድረክ የሚካፈል ሊያውቃቸው ይችላል ከሚል ግምት ብቻ ነው ያንን ያልነውና በዚሁ ቢያልፉት ደስ ይለናል::የርስዎንም ኢትዮጵያዊነት ለማሳነስ ያደረግነው ሙከራ የለም::ኢትዮጵያዊነትን ማንም ለማን የሚሰጠው ወይንም የሚነሳው አለመሆኑን ጠንቅቀን እናውቃለን::...
ስለዘር ማጥፋት የሰጠነው ትርጉም አልነበረም::የተፈለገው ጄኖሳይድን የዘር ማጥፋት በሚል የአማሪኛ ሐረግ ልንተካው የምንችል አልመስላች'ሁ እንዳለን ለመግለጽ ነበር::ስለዘር ማጥፋት እርስዎ "እኔ ዘር ማጥፋት ሲባል የመስለኝ አማራ ወይም ጉራጌ, ትግሬ ብሎ አንዱን የጠላውን ዘር መደምስስ..." ካሉት የተለየ ትርጉም የሰጠን መስሎት ከሆነ ላለመግባባታችን ምክንያቱ እንደምሳሌ የተጠቀምንበት የአንድ ቤተሰብ ታሪክ መሰለኝ::የዚያን ቤተሰብ ታሪክ ያቀረብነው እነሻለቃ ያጨፋጨፉት ቤተሰብን በቤተሰብ ጭምር እስከሆነ ድረስ ያ የዘር ማጥፋት ሊባል ይችላል ወይ? የሚል ጥያቄያዊ አስተያየት ነበር ያቀረብነው::የፖለቲካቸው ተቀናቃኝ የሆኑትን ሁሉ ይደመስሱ ነበር እንጂ ያንድን ዘር ተወላጅ/ ተወላጆች አነጣጥረው ያጠቁበት ጊዜ ያለ አልመስላች'ሁ እንዳለን ነው የገለጽነው::
"..የአንድን ቤተስብ ዘር ማንዘር ማጥፋት አልመስለኝም!" ያሉት ሌላ ጥያቄ ቀስቅሶብናል::በመጀመሪያ የአንድ ቤተሰብ ዘር ማንዘሩ እንዲጠፋ ለምን ተፈለገ?ማነውስ ፈላጊው?መልሱን ለባለ ሙያ እንተወዋለን::
ስለግብዝነት ያነሳነውም ቢሆን እርስዎን የሚመለከት አይደለም::ለማለት የተፈለገው መለሳውያንን ብንሆን የትናንት ወንጀለኞችን ለፍርድ በማቅረቡ ላይ ትንሽ የዳተኝነት እርምጃ እናሳይ ነበር:: በጃችን ደም አለና!!! አንድ የመድረኩ ተሳታፊ "አረመኔ በአረመኔ ላይ ሲፈርድ::" ሲሉ የኛን አባባል እጥር ምጥን ባለ አገላለጽ ረድተውናል::አሁን የተግባባን ይመስለናል::
Monica**** wrote:አለም 1
በቅድሚያ ለአስተያየትህ/ሽ አመስግናለሁ!!!
እኔ ሻለቃ ተፈራን አላውቃችውም የአገሬን ባለስልጣኖች ከመንግስቱ ህ/ማርያምና አንዳንድ ሌሎች በጣም ይታወቁ ከነበሩ አምባገነኖች በስተቀር.......የአገሬን ጸሀይ ሳልጠግብ ቶሎ ስለተስደድኩኝ እድሉን አላገኝሁም!! ያ ግን ኢትዮጵያዊነቴንና ለአገሬ ያለኝን ፍቅር በፍጹም ዝቅ አያደርገውም!!!
ስለዘር ማጥፋት ያደረግክልኝ ገለጻም በጣም ግሩም ነው! እኔ ዘር ማጥፋት ሲባል የመስለኝ አማራ ወይም ጉራጌ, ትግሬ ብሎ አንዱን የጠላውን ዘር መደምስስ እንጂ የአንድን ቤተስብ ዘር ማንዘር ማጥፋት አልመስለኝም!
ጥያቄ ያለኝ ግብዝነቱን ያሳያል ያልከው እኔን ነው ወይስ የመለስን ግብዝነት? እስኪ ያገር ልጅ አብራራልኝ
ከአክብሮት ጋር
ሞኒካ