አዲስ አድማስ - 17-12-2005
የቅንጅት መሪዎችንና ጋዜጠኞችን ጨምሮ 23 ታሳሪዎችን የሚወክሉ ጠበቆች ላቀረቡት የዋስትና ጥያቄ አቃቤ ህግ በሰጠው ምላሽ ታሳሪዎቹ በከባድ ወንጀል የተጠረጠሩና ሌላ ወንጀል ሊፈጽሙ የሚችሉ በመሆናቸው በዋስ ሊለቀቁ አይገባም ሲል ትናንት ለፍ/ቤት መቃወሚያ አቀረበ። ሀይሉ ሻውል ታመው ፖሊስ ሆስፒታል የገቡ ሲሆን አቶ ደበበ እሸቱ አስቸኳይ ህክምና እንዲያገኙ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ሰጠ።