ሰላም ለኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ሁሉ!
አረመኔው ወያኔ ከአፍሪካ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞችን በማሰር ግንባር ቀደም ሆኖ በመምራት ላይ ሲገኝ በአለም ደረጃም ከቀዳሚዎቹ ነጻ ፕሬስ ጨቁዋኝ መንግስታት የመጀመሪያ ረድፍ ላይ መሆኑን አለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት አስከባሪ ድርጅት ገልጿልhttp:
www.cpj.org
በዚህ ሳምንት ደግሞ የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማህበር መሪ ክፍሌ ሙላት በሰንሰለት ታስሮ በኖርዌይ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ደጋፊዎች ጋር መግለጫ ሰጥቷል::
የዋርካ የዜና አምድም አዲስ ዜና ያጣበት ዋና ምክንያት ይህ የወያኔ የፕሬስ አፈናና የኢንተርኔት እገዳ ነው::
ዲጎኔ ሞረቴው ከኢትዮጵያ አንድነት ነጻ ፕሬስና ሚድያ
[quote="ENH"]ጦማር - 21-12-2005
በኢትዮጵያ ውስጥ ከቀን ወደ ቀን ለእስር የሚዳረጉ ጋዜጠኞችና ምሁራን ቁጥር እየበረከተ መጥቶ በቅርቡ ተይዘው የታሰሩትን ጨምሮ በአሁኑ ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ቁጥር 18 መድረሱ እንዳሳሰበው ዓለም አቀፉ የፀሐፊና እስረኞች ኮሚቴ ፔን ገለፀ።