የተመረጡት በሙሉ እስር ቤት ተቀምጠው ማን ነው እወያኔው እድር የሚገባ ??

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የተመረጡት በሙሉ እስር ቤት ተቀምጠው ማን ነው እወያኔው እድር የሚገባ ??

Postby ይገርማል » Fri Oct 07, 2005 12:31 pm

ውድ ኢትዮጵያውያን በዚች በመጨረሻዋ ጊዜ ህዝባችን ምን አይነት ስቃይ ላይ እንዳለ ሁላችንም የምናውቀው ነው ::
ይሁን እንጂ ባሁኑ ወቅት ወደ ወያኔው እድር እንግባ አንግባ የሚለው ሁሉም ያየውና የወሰነው ይምስለኝ ነበር :

በጎንደር ክፍለ ሀገር ጠቅላላ የተመረጡትና መረጡ የተባሉት በሙል በእስር ቤት ውስጥ ናቸው :
በጎጃም ክፍለሀገር በሙሉ የተመረጡትና መረጡ የተባሉት እስር ቤት ናቸው :
በወሎ ክፍለ ሀገር በመላ ወጣቶች የተወሰኑት እስር ቤት ናቸው የተወሰኑት የት እንዳሉ አይታወቅም :
በሽዋ ክፍለ ሀገር እንደዚሁ :
በደቡብ በኩሉም በረዳት ፕሮፌሰር መራራ ላይ እንዲዘምቱ በተገዙ ሆዳሞች እየተጠቆሙ በሙሉ እስር ላይ ናቸው:

ታዲያ ማነን ተይዞ ነው እድሩ ውስጥ የሚገባው :
አንድ ሰው ካለፈ ታሪክ መማር የሚገባው ይመስለኝ ነበር :

ሻቢያ - ወያኔ ጫካ በነበሩበት ወቅት ከወታደሮች ጋር እንደራደር በማለት ወታደሮቹ እውነት መስሏቸው ወደ ድርድሩ ጠረጴዛ ሲሄዱ በዚያን ወቅት እነሱ ያችን የማዘናጊያ ስአት ተጠቅመው ከፍተኛውን ጦርነታቸውን ያወርዱባቸው ነበር:
አሁንም ያ ቆሻሻ ልማዳቸውን በመጠቀም የዛሬ የህዝብ ተመረጫ መሪወችን እንደራደር በማለት በገጠሩ ያገሪቱ ክፍል ከፍተኛ ጭፍጨፋ እያደረጉ ይገኛሉ :ብሎም የገጠሩን መስተዳደር አቌቈምን እያሉ ይጨፍራሉ እዚህ ላይ በቁጥር ከምናነበው በእጥፍ የሚበልጥ ህዝባችን በእስር ላይ ይገኛል : ጎጃም ውስጥ በተልይም በቢቸና አውራጃ እጅግ ታላላቅ ሰወች እራቁታቸውን በጨለማ እገድል አፋፍ ላይ እየታሰሩ ሲሰቃዩ ያድረሉ : ታዲያ ምን ለማድረግ ነው እዚህ እድር ውስጥ ይገባል ብለን የምናስብ ????

<I><B> እኔ በበኩሌ ማንም ይሁን ማን ባሁኑ ወቅት ከወያኔ እድር ለመጨመር የሚፈልግ ካለ እራሱን ከወያኔ የበለጠ የህዝብ ጠላት ለማድረግ ካልሆነ ሌላ አማራጭ የለውም : </I></B>

እነዚህ ሰወች እዚህ ውስጥ ከገቡ ደግሞ ህዝባችንን የቀረውን ላለማስጨረስ በግሌ የግድ ወያኔን አለመተናኮል የሚገባ ይሆናል እዚህ ላይ ለማለት የምፈልገው እነዚህ ሰወች እዚህ እድር ውስጥ እንግባ ካሉና ከገቡ በነሱ ስም ወያኔ ህዝባችንን ከዛሬው የበለጠ ስለሚጨፈጭፈው ነው :
ያህያ ባል ከጅብ አያስጥልም የሚለውን እንዳናመጣው ከቻልን ከህዝባችን ጋር ጎን ለጎን እስከመጨረሻዋ እስትንፋሳችን መታገል አለዚያም ዝም ብሎ መቀመጥ እንጂ በእኔ አስተሳሰብ እዚህ እድር ውስጥ ማንም ሊካፈል አይገባውም ባይ ነኝ !!


ሰላሙን ላገራችንና ለድሀ ህዝባችን እመኛለሁ !!
ይገርማል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 43
Joined: Thu Nov 13, 2003 12:10 pm

Postby አባዊርቱ » Fri Oct 07, 2005 4:15 pm

ትክክል ብለሀል ወንድሜ!
እንደጀመሩት, ፓርላማ እንዲገቡ ፈልጌ በግሌ, እያደር ግን የህዝቡን ፍላጎት ከተረዳሁ በሁዋላ (ምንም እንኩዋ በነገሩ ባላምንበትም) ያለመግባታቸውን በጣምም አክብረ ነበር....አሁንም በዚሁ የጸናሁ ነኝ!
ባጭሩ, ባሁኑ ጊዜ ይህ ሁሉ እልቁትና እስራት እየተካሄደ (ያውም ስብሰባ ላይ ቁጭ ብለው) ፓርላማ መግባት ለወያኔ ከበስተ ሁዋላ እንደማጎንበስ ነው.....ያለው አማራጭ አንድ ነገር ብቻ ነው:


ይህውም መቼውንስ ፓርላማ ለመግባቱ በጣም የታያቸው (against all odds) ምንም እንኩዋ በጣም የማደንቃቸው ኢትዮጵያውያን ቢሆኑም ሁለቱ ዶሮች ብርሀኑና በየነ ስለሆኑ እንዳማረባቸው ካገር ወጥተው ወደኛው ቢቀላቀሉና በሰላማዊው ትግሉ እዚሁ ቢተባበሩን እመርጣለሁ.....ትግሉን ለቆራጥ ታጋዮች ቢተውት በበኩሌ እመርጣለሁ......የናንተን አላውቅም እንጂ የሆነ መጥፎ ነገር ይሸተኛል ጎበዝ....እግዚአብሄር ቶሎ ብሎ መቁዋጪያውን ይላክልን!

አሜን!
አባዊርቱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 800
Joined: Mon Feb 23, 2004 4:11 am

Postby መሳይ101 » Fri Oct 07, 2005 4:22 pm

አር አዑንማ ነገር ሆናል ስራቻው
መሳይ101
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Thu Sep 22, 2005 5:25 pm
Location: ethiopia

Postby ይገርማል » Sat Oct 08, 2005 1:37 pm

ማንም ይሁን ማን ማወቅ የሚገባን አንድ ነገር አለ እሱም ብዙ ጊዜ ቀደም ብየ ለመናገር ሞክሪያለሁ ::
ባሁኑ ወቅት ሻቢያ - ወያኔ በህዝባችን ላይ የሚያደርሰው ግፍና በደል የማያውቅ ያለ አይመስለኝም :
ህዝባችን ይህ ዱላ በዛብኝ ብሎ ከነገረን ቆይቷል :
ህዝባችን ከላይ እንደጠቀስኩት በየሜዳው እየታነቀ ባለበት ወቅት ከነዚህ በሽታወች ጋር ድርድር መቀመጡም አያስፈልግም ነበር ለዚህም ነበር :
መጀመሪያ ወደ እድር ቀርቶ ወደ ድርድር ለመሄድ ህዝባችንን ከዘጉበት በረት ሊለቁት ይገባል ከዚያ ውጪ የሚደረገው ሁሉ ስህትት ነው በኔ እምነት ይህን ማለት ደግሞ..

የተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው የሚያሰኝ ሳይሆን
ከድጡ ወደማጡ መሄድ የለብንም የሚል ነው በእኔ እመነት ::
ሰላሙን ላገራችንና ለድሀ ህዝባችን እመኛለሁ !!
ይገርማል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 43
Joined: Thu Nov 13, 2003 12:10 pm

Postby ይገርማል » Sat Oct 08, 2005 9:22 pm

መላ ህዝባችንን ሻቢያ - ወያኔ ሲጨፈጭፈው ማንም የሚናገርው የለውም ከልብ እላችኌለው ከእኛ ውስጥ አንዱ ቢሞት ግን ቢአንስ ለምን የሚል ጥያቄ ያስነሳ ነበር ::
ለምን ይህን እንዳልኩት እራሴም አላውቅም...
ልመለስና :..
<I>
የወያኔው ቁንጮ ተቃዋሚወቹን የጠሩትን የስራ ማቆም አድማ ያቁሙና ልደራደር ሲል ተቃዋሚወችም ቢአንስ አንተ እንዲህ እንድናደርግ ከፈልክ አንተ ደግሞ በምትጨፍርበት የቴልቪዥንና የራዲዮ ጣቢያ በመላ ሀገሪቱ በተመረጡት ላይና በህዝባችን ላይ የሚደረገውን ጭፍጨፋ አቁሙ በል መባል ነበረበት : ይህን ማለት ማንም የሚያቅተው አይመስለኝም : እዚህ ላይ ባያድርገውም ቢአንስ ህዝባችን ምን ያህል አብረነው እንዳለን ይገነዘብ ነበር ::

አሁንም መሆን ያለበት ይህ ብቻ ነው ምንም ይሁን ማን ወደ ወያኔው እድር የሚገባ ሁሉ ወያም ለመግባት የሚያስብ ሁሉ የሚገባው የህዝብን ድምጽ ይዞ ሳይሆን ወያኔ የቸረውን ድምጽ ይዞ መሆኑን ማንም ማወቅ አለበት :</I>
ሰላሙን ላገራችንና ለድሀ ህዝባችን እመኛለሁ !!
ይገርማል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 43
Joined: Thu Nov 13, 2003 12:10 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 4 guests