ውድ:ቅንጅት:አባላት:የአእምሮ:ሳይሆን:የህሊና:ጥበብን:አስቀድማችሁ:ለዚህ:ያበቃችሁን:ሕዝብ:ስሙት

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ውድ:ቅንጅት:አባላት:የአእምሮ:ሳይሆን:የህሊና:ጥበብን:አስቀድማችሁ:ለዚህ:ያበቃችሁን:ሕዝብ:ስሙት

Postby SAY-NO-TO-HATRED » Sun Oct 09, 2005 6:53 am

KINIJIT ETHIOPIA

Fax: +251-1-136371

e-mail: kinjitethiopia@yahoo.comየእግዚአብሔር:ሰላምታ:ይድረስልኝ!!እየከፋላችሁ:ላላችሁት:
ከፍተኛ:መስዋእት:የጥሩ:ነገሮች:ሁሉ:ምንጭ:የሆነው:አምላካችን:
ይክፈላችሁ!!


የሀገር:ጉዳይ:የሕዝብ:ፍቅር:ከሚያንገበግባቸው:ዜጋዎች:አንዷ:ነኝ::ከዚያ:
ውጭ:ምንም:የፖለቲካ:background ም: የለኝ:: ድሀው:ወገኔ:ሌላው:ሌላው:እንኩዋ:ቢቀር:የዲሞክራሲ:መብቱ:
ተጠብቆለት:እንደልቡ:ብሶቱን:ሳይፈራ:የሚናገርበትን:ዘመን:
ለማምጣት:የሚደረገው:የአሁኑ:ትግል:እጅጉን:በጣም:ካስደሰታቸው:
ኢትዮጲያውያን:አንዷ:ነኝ::የሚቻለኝንም:በፊናኜ:እያረግሁ:ነው::

ኢትዮጲያውነቴ:ግልጽና:ተቆርቁዋሪ:እንድሆን:ያስገድደኛል::ሰለዚህም:ዛሬ:
ለእናንተ:ልል:የተገደድሁት:ይህች:የመጨረሻ:ቀን:አካሄዳችሁ:ፈጽሞ:
አልወደድኩላችሁም::አላማረኝም::ልሳሳት:እችላለሁ:ሆኖም:የእኔ:መሳሳት:ጉዳት:
እንኩዋ:ቢያስከትል:እኔው:ላይ:ብቻ:ነው::ስህተትም:መስራት:እንደማያሳፍር:ከቅን:የተነሳ:ስው:ይገነዘበዋል::
የፖለቲካ:እውቀቱ:ሊያንሰኝ:እችላለሁ:ያሁኑ:ጉዳይ:የማወራው:
ግን:የፖለቲካ:ጥያቄ:እንዳልሆነ:በመገንዘቤ:ነው::ቸኮልሽ:ልባል:
ግን:አልችልም:ምክንያቱም:በኢትዮጲያ:ታሪክ:ትልቅ:ውሳኔ:የሚደረጉበት:
ቀናቶች:ሊመጡ:ሰአቶች:ብቻ:ነው:የቀሩት:

ይህ: ነው:መልእክቴ:

1.የወያኔን:የዘረኛ:መንግስት:ለማሰናበት: (የሕዝቡ:ጥያቄ:ይህ:ነውና) ከሕዝቡ:ጋር:ብቻ:ስትሆኑ:ሕዝቡ:ያላችሁን:ብቻ:ስታደርጉ:
የሕዝቡን:ድምጽ:ስታከብሩ:እንጅ:ከሕዝቡ:ተገንጥላችሁ:
ሕዝቡ:ያላችሁን:አቃላችሁ:ትታችሁና:የሕዝቡን:ድምጽ:ሳይሆን:
የእናንተን:የግል:የትግል:ስልት:ተጠቅሞ:ከወያኔ:ጋር:ለመታገል:
ፓርላመንት:እገባለሁ:ብሎ:ማሰብ:ሌላ:ትልቅ:አደገኛ:መልእክት:
እዚህ:ላላችሁበት:ቦታ:ላደረሳችሁ:ድሀ:ሕዝብ:መላክ:ነው!!

2.ፈልቶ:የቀዘቀዘን:ውሀ:እንደገና:ትኩስ:ለማድረግ:"ሀ" ብሎ:እንደገና:ዉሀውን:መጣድ:ያስፈልጋል::ውሀው:ለሁለተኛ:
ጊዜ:ሲፈላ:እስከሚፈላ:ድረስ:ምን:ያህል:energy:እንደሚወስድ:
አናውቅም::እድለኞች:ከሆንን:ያንኑ:የመጀመሪያውን:ያህል:
ብቻ:energy በቂ:ሊሆን:ይችላል::ሆኖም:ግን:አናውቀውም::ወይም:ደግሞ:ከበፊቱ:
የበለጠ: energy ሊያስፈልገን:ይችላል(ወይ:ምድጃው:ጉልበቱ:ቀንሶ:ሊሆን:ይችላል)
አናውቀውም::ለዚህም:ነው:እንግዲህ:ሁለተኛ:ከማፍላትና:አላስፈላጊ:
energy ከማውጣት:ሌላ:መፍትሄ:ፈልጎ:ከመጀመሪያውኑ:ውሀው:እንዳይቀዘቅዝ:
ማድረጉ:ብልህ:መፍትሄ:ሊሆን:የሚችለው::

ለማለት:የፈለግሁት:ወያኔ:አሁን:የያዘው:የሕዝቡን:ትግልና:
የእናንተን:የትግል:momentum እያቀዘቀዘው:ነው::አንዳንዴ:ከውስጥ:ሲሆኑ:አይታይ:ይሆን?
ሊፈላ:ትንሽ:የቀረው:ውሀ: እሳቱ:ቢቀነስበት:ለመፍላት:የጀመረውን:process እዛው:ላይ:ያቆመዋል::
የኢትዮጲያ:ሕዝብ:ትግል:ደግሞ:እዚህ:ደረጃ:ላይ:ለመድረስ:
የድሀ:ሕይወት:ተከፍሎበታል::ከዚህ:በኍላ:ትግሉን:ለማቀዝቀዝና:
እንደገና:ወደፊት:አሁን:የደረሰበት:የትግል:ደረጃ:ላይ:ለመድረስ:
እንደገና:የሌላ:ተጨማሪ:ድሀ:ህዝብ:ሕይወት:መከፈል:ሊኖርበት ነው:ማለት:ነው::ቁጥሩም:የከፋ:ሊሆን;ይችላል::አናውቅም::
ትክክለኛው:አማራጭ:ድሀ:ሕዝባችን:ህይወቱን:ከፍሎ:እዚህ:ደረጃ:ላይ:ያደረሰውን:
ትግል:አታቀዝቅዙበት::እዚህ:ደረጃ:ትግሉ:ለመድረሱ:ምክንያት:ሕዝቡ:
ነውና:ፓርላማ:መግባት:አለመግባት:የሚለው:ውሳኔም:መወሰን:ያለበት:
በሕዝቡ:ነው:: ሕዝቡም:ደግሞ:ድምጹን:አለአሻሚ:ሁኔታ:በመግለጥ:አትግቡ:
ብሎ:አንዳንድ:ለሀቅ:ሕዝቡን:ለማገልገል:የተነሱ:የተቃዋሚ:አባላትም:
ድሀውን:በማክበርና:ዞር:ብለው:ለዚህ:ያበቃቸውን:በማሰብ:ወደ:ፓርላማ:
አንገባም:ብለው:ይገኛሉ::የኢትዮጲያ:ሕዝቡ:ያያል:ይታዘባል::እውነተኛን:ይወዳል::
እውነትንም:ለማየት:በሚገርም:ሁኔታ:ከእናቱ:ማህጸን:እንድወረሰ:
ለማወቅ:አያዳግትም::

የወያኔን:የዘረኛ:መንግስት:እንዲከትም:የሚያደርገው:
የሕዝብ:ትግል:ብቻ:ነው!!!በግል:ፓርላመንት:ተገብቶ:ወንበር:መያዝ:
ሕዝብን:መናቅ:ሕዝብን:ግራ:ማጋባት:ሕዝብን:ልክ:እንደወያኔ:መጉዳትና:
በሕዝብ:አይን:ጥላቻን:ማትረፍ:ብቻ:ነው:ብዬ:አምናለሁ!!

በመጨረሻም: ከአእምሮ:እውቀት:ይልቅ:የህሊናን:ጥበብ (የተሳሳተ:ሊሆን:ስለማይችል) አስቀድማችሁ:በነገው:እለት:ወደ:ፓርላመንት:እንግባ:የሚለውን:
option ውድቅ:በማድረግ: የኢትዮጲያን:ሕዝብ:መንፈስ:አረጋጉት::ብዙ:የተጎሳቆለ:ሕዝብ:
ነውና:ከእናንተ:አመንኩዋችሁ:ካላችሁ:ድንጋጤ:አታሰሙት:
እያልኩ:እማጸናችኍለሁ::ይህ:የአእምሮ:ሳይሆን:የሕሊና:ጉዳይ:ይሁን:
እያልኩ:በመለመን:ደብዳቤየን:አበቃለሁ!!


ታማኙ:ዋናውና:የመጨረሻው:ዳኛ:ስራችሁን:ያያል!!!
ውሳኔም:ስታደርጉ:እሱው:ይከተላችሁ!!
ድሀውን:ሕዝባችንን:እናንተንም:ሀገራችንንም:ያስብልን!!

አክባሪያችሁ:

እምቢ:ለጥላቻ:

ነኝ
WE ARE NOW AMBASSADORS FOR OUR BELOVED COUNTRY AND ONE DAY WE WILL BE CITIZENS IN ETHIOPIA, ONCE AGAIN!!
SAY-NO-TO-HATRED
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1354
Joined: Sat Mar 12, 2005 8:29 pm
Location: united states

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests

cron