"" ዋርካ ዲቤት "" ቅንጅት የፓርላማው አካል ይሁን ወይስ ፓርላሜንታሪነቱን ይሰርዝ?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የሚታወቁ'ና የማይታወቁ አደጋዎች በሀገሪቱ ዙሪያ አሉ

Postby ሳምቻው » Wed Oct 19, 2005 12:05 pm


እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በኢኮኖሚ የደቀቁ'ና በጎሳ የተከፋፈሉ ሀገሮች ውስጥ ...... በምርጫ ተሽንፎ ስልጣን አለቅም የሚለውን ቡድን ከቢሮ አሽቀንጥሮ ለመጣል ሌሎች ነባራዊ የሆኑ የሀገሪቱን ሁኔታዎች "" ህዝባዊ መንግስትን "" የመሻት ያህል አብሮ ማየት ያስፈልጋል ::

ሀገሪቱ "" ኦሮምያ ሀገራችን !! "" ብለው ከሚናገሩት ጀምሮ እስከ "" ኦጋድያ ሀገራችን !! "" ወደሚሉት ጠባብ ናሽናሊስቶች ስለተላለፈች አደጋ አለ :: አደጋው በዚያ አይቆምም :: ከድንበር ጥያቄ በላይ የማያባራ የኢኮኖሚ ኢንተረስት ባላቸው ኤርትራ እና ግብጽም ሀገሪቱ ተውጥራለች :: እንዲህ ሆና ስለተከፋፈለች ድሀ ሀገር ምን አይነት አደጋዎችን" መዘርዘር ይቻላል ??

አሁን ባለው የሀገሪቱ ሁኔታ የህዝብ ነውጥ ቢነሳ በትክክል ሊፈጠሩ የሚችሉ አደጋዎች እንዳሉ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል ::

ዛሬ በአውሮፓ አደባብዮች ራሱ ያቋቋመውን "ብሄራዊ" ባንዲራ እያውለበለበ የሱማሊኛ ኢንቶኔሽን በተሞላው የእንግሊዘኛ ቃና ደሙ እየፈላ "" መለስ ኢዝ ዘ ወያኔ !! መለስ ኢዝ ዘ ---- !! "" እያለ ለያዥ ለገልጋይ እስኪታክት የሚፎክረውን ቡድን አስተውለናል ::

ለ'አሳይለም ኬዝ ማሳመርያ ይሁን ለነጻነት በማይገባ ሁኔታ 30 ሚሊዮን ህዝብ ነጻ አወጣለሁ እስከሚለው የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር የተዘራውም; ዛሬ ከኃገሪቱ ብርቱ ተኩሳቶች ውስጥ የማይረሳው ነው ::

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚነሳ ብሄራዊ ቀውስ ሌላ አካባቢ ከሰማይ እንደወረደ ህብስት እንደሚሆን ሳንገምት እንዴት እናድራለን ??

የግብጽን ኣለም አቀፍ ጸረ-ኢትዮጵያ ጫና ሳንረሳ ትንሽዋ ኤርትራ የኢትዮጵያን የውስጥ መዳከም አጋጣሚ ካገኘች በደህና ጊዜ በአቶ መለስ የተውሰነላትን ድንበር ከመቆጣጠር አልፋ ኢትዮጵያ ላይ ያላትን የማያባራ የኢኮኖሚ ኢንተረስት የሚያስጠብቅላት ሀይል አዲስ'ባ ላይ በመሳርያ ኅይል እንዲደራጅ ሌት ተቀን ደፋ ማለቷን እንደማታቆም ግልጽ'ና ግልብ የሆነ ጉዳይ ሆኖ እናያዋለን !!

ይቀጥላል
Last edited by ሳምቻው on Thu Oct 20, 2005 11:16 am, edited 2 times in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

የቀጠለ..

Postby ሳምቻው » Wed Oct 19, 2005 1:23 pm


ዛሬ የምንጮህለት ህዝባዊ ፓርላማ'ና የተመካንበት ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ድንገት ሊረፍድበት እንደሚችል ስንቶቻችን እናስስተውል ይሆን ?

የብዙሀን ፓርላማ 'ና ጨዋ ባህል ከመጤፍ የሚሆን ጉልበት አጥቶ ዐባባሉን የምንረሳው ገና ድንገተኛውን ማእበል መዋኘት ስንጀምር ይሆናል ::

የህዝብ ማእበል ሲነሳ ነውጡ ማሰብ ከሚቻለው በላይ ዘግናኝ ነው :: ያኔ ፓርላማ የለ ባህል የለ ! "ጨዋነት "ቃሉን መናገር ቀርቶ ማሰቡ ራሱ ሊያስጠላን እንደሚችል እንገምት ::

የዚህ አይነት ማእበል ራሳችን ላይ ፈትነን ልናረጋግጥ የተዘጀን ሰዎች ሁለት መቶ ጊዜ ልናስብበበት የሚገባ ይመስለኛል :: ሀገር የሌለው ፓርልማ'ና መንገስት ለማቆም እያሰብን ነው ::

በራሳችን በሚጀመር አጉል ስህተት ፓርማና የሰፈር ጨዋነት ወዲያው ተረስቶ "" ሀገሬን " ኃገሬን !"" ብሎ የሚያስለፈልፍ ረጅም ቀን እና ረጅም ለሊት በድንገት ሊጀመር እንደሚችል እናስተውል ::

ለጊዜው ክፉም ቢሆን መንግስት ያስፈልገናል :: ዛሬ የዚህችን ሀገር ጸጥታ'ና ብሄራዊ ደህንንነት ለመጠበቅ ሀላፊነቱን በጠላነው መንግስት ትከሻ ላይ ጥለነው መንግስቱን አውቀንም ይሁን ሳንውቅ ክ ፉኛ እያእዋከብነው እንገኛለን ::

" እዚህ መጥቶ ቃለ-መሀላ ያልፈጸመ ተመራጭ የፓርላማው አባል አይደለም :: "" እያሉ የሚናገሩት አቶ መለስ ; ጥሪው ሲጋባን የማንቆጣ ስዎች ተታለን አይደለም :: ጥሪው "" እባክህ ፓርላማ ግባና ያ'ንበሳ ጥርስህን ተነቅለህ ተቀመጥ :: እንቢ ካልክ ደግሞ እስር ቤት ገብተህ ከፈለክ ተነቀሰው "" መሆኑ ቢገባንም የጠ/ሚንስትሩ ስቴትመንት "" ተቃዋሚው ፊቴ መጥቶ ካልማለ he would not enjoy the lexuries of parliament ማለት ሳይሆን ባጭሩ ፓርላማ ካልገባ -ያለ'መታሰር መብቱ ይነሳና የመታሰር እድሉን ከዚህ በኋላ አንድ የአመጽ ጥሪ ለህዝብ ከማስተላለፍ ጋር በቀጥታ ይያያዛል ::

ይህን ለማለት የፈለኩት : ይህን አይነት የመንግስት ክፋትም ለማየት እኮ መንግስት ሲኖር ነው :: መንግስትን ስናማ በየቤታቸን ውስጥ ከምሳ በኋላ ትራስ ተደግፈን ; በየመስሪያ-ቤቱ የታሽገ የፒዛ ካሮቶን የፒሲ-ኪቦርድ ላይ አስደግፈን ወይም በ ት/ቤቶች ፓርክ ውስጥ ሻይ ቡና እያልን ነው ::

ስለ ወንበዴ መንግስት ለማውራትም , በአሪፎቹ አነጋገር ( ለመቅደድ) ለካ መንግስት ሲኖረን ነው :: ማለቴ ኅገር----ኃገር ሲኖረን ...ነው ለካ !!
!
Last edited by ሳምቻው on Thu Oct 20, 2005 4:41 pm, edited 3 times in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

view of the fragile face ......

Postby ሳምቻው » Wed Oct 19, 2005 2:05 pm

questions of the fragile face......
Image


እኔስ ሀገሪቱን አደጋ ላይ ከመንጥል ይህንኑ ቢሮክራሲያዊ ኮንፈደንሱ የተናጋውን መንግስት በተጀመረው ሰላሚዊ ትግል እያዳከምን ብንጥለው እመርጣለሁ ::

የተቃዋሚው ኃይል ወደ ፓርላማ ገብቶ ባለው ሪሶርስ እንዲታገል እጄን አውጥቼለታለሁ ::

MAY GOD BLESS ETHIOPIA !

ሳም[b]
Last edited by ሳምቻው on Thu Oct 20, 2005 2:59 pm, edited 1 time in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Postby ዞብልየ » Wed Oct 19, 2005 3:00 pm

ሳምቻው:

ባሁኑ ወቅት ህዝባዊ አመጽ ቢነሳ የህገሪትዋ ህልውና አደጋ ላይ ይወድቃል;; ኢትዮጵያ ውስጥ የርስ በርስ ዕልቂት ይኖራል በማለት ያቀረብካቸውን እይታዎችን ለማየት ሞከርኩ;; ያቀረብካቸው ባብዛኝአው ምክንያቶች ሳይሆኑ ማስፈራራቶች ሆኑብኝ;; በመረጃ የተደገፈ አንድም ምክንያት አላገኝእሁም;; ግብጽ, ኢርትራ ወይም ሶማልያ ብለህ የጥቃቀስካቸው በሙሉ ለኢትዮጵያ አንድነት ጸሮች መሆናቸውን ብታስረግጥም, ባሁኑ ወቅት አደጋው እንዲት ሊከስት እንደሚችል ግን መረጃ አጥአቅሰህ አላቀረብክም;; ለነ የማስፈራራት ጉዳይ እንጂ የማሳመን ሁኒታ ላላየሁበትም;;
የምርጫው ውጥእት ቁልጭ አርጎ የሚያሳየው ህዝቡ ዲሞክራሲ , ህቀኝአ መሪ መፈለግን እንጂ የርስ በርስ ጥኦርነትን አላመላከተም;; እንዲያውም የዘረኝአን ፖሊሲን አሽቀንጥሮ ለመጥአል ቁርጥእኝአ ውሳኒ ላይ መድረሱን ነው የምረዳው;;
ስጋትህንና ፍርህእትን በመጥእኑ ብጋራም የተጋነነ ነው ለማለት እደፍራለሁ;;
አሁንም ቢሆን ከማስፈራራት ና ከፍርህእት ውጭ የምታቀርበው ትንተናና ና ጭብጥ ከነመረጃው ህእሳብ ካለ እንወያይበት;;

በቸር ያቆየን
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ዞብልየ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 52
Joined: Thu Feb 24, 2005 7:22 pm

Postby አለታ » Wed Oct 19, 2005 6:49 pm

ይህንን አርዕስት በተወሰነ መልኩ ብዙዎች እንደተከታተሉት ሁሉ ተከታትየዋለሁ:: ጽሁፎቹን ባየኋቸው ቁጥር ስለተሰሙኝ ስሜቶች ማውራቱ ለዋናው ነጥብ የሚጨምረው ምንም ፋይዳ የለምና እዘለዋለሁ ::
አልፎ አልፎ ግን የተንጸባረቁት አላስፈላጊ ንትርኮች ብዙዎቹን እንደኔ እንዳሸሸ እገምታለሁ::

ይሁን እንጂ እየተደጋገሙ የሚቀርቡት አስተያየቶች ፍጹም የሚፈታተኑ ናቸውና መሆን አለባቸው ብዬ የማምንበትን ሀሳብ እንዳቀርብ አስገድደውኛል

ፓርላማ የመግባቱና ያለመግባቱ ሀሳብ ሁላችንንም የሚያነጋግርና ቀላል ያልሆነ ፈተና ነው , ለዚህም ፈተና ተቃዋሚዎችም ሆኑ ደጋፊዎቻቸው የምናቀርባቸው መልሶች ተመሳሳይነት ሊኖራቸው እንደማይችል ሁሉ በቀላሉም ሊቀመጡ የሚችሉ አይደሉም ::

ከላይ ፓርላማ ባለመግባት ምክንያት ስለሚመጡት ጦሶች በአንደኝነት የተጠቀሰው "በህግ የተደራጀ የፓርቲ አመራር ማጣት እንደሆነ ነው"
ለምን ይህ እንደተባለ ቢገባኝም ይህንን ህገወጥ የወያኔ "ሊሆን ይችላል ውሳኔ" ተቀብሎ እንደመከራከርያ ነጥብ አቅርቦ 'ለማስፈራራትና' ለማሳመን መሞከሩ በራሱ ትልቅ ድክመት ነው::

ትግላችን ወያኔ በሚፈቅደውና በማያስቀይመው መልኩ መደራጀት አለበት ብለን የምናምን ከሆነ መቼም የትም አንደርስም :: ወያኔ ኢትዮጵያዊ አይደለምና ለኢትዮጵያ ብለው የተነሱ የትኛውም ድርጅቶች የሚያቀርቡለትን ሀሳብ መቼም ወዶ አይቀበልም::
ተመራጮች ፓርላማ ባለመግባታቸው ምክንያት አባል የሆኑበት ድርጅት ህጋዊነት አይኖረውም የሚለው ጽንሰሀሳብ ወይም ውሳኔ ፍጹም ኢዲሞክራሲያዊ የሆነ ራቁቱን የወጣ አቀራረብ ነውና በቁርጠኝነት የምንታገለው እንጂ በአቋራጭ የምንሸውደው ቀላል ስህተት አይደለም::
ለምንም ይህን አደገኛና መሆን የሌለበት ወንጀል በቀላሉ እንደምናየው ሊገባኝ አልቻለም :;

የወያኔ አንዱ መሳርያ የሆነው የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ በቅንጅት (ፓርቲ) ህጋዊነት ላይ አሁኑኑ አደገኛ ጨዋታ ሊጫወት እየሞከረና የኅዝቡንም ትግስት እየተፈታተነ ያለ መሆኑን ሁላችንም ሳናጤነው አልቀረንም::
ይህ ማለት ፓርላማ ገቡ አልገቡ, ያ ማስፈራሪያ "ህጋዊነት" የሚለው በራሱ ሊቆም አይችልምና የወያኔን በቀል አያስቀረውም::

እንደሚሰማኝ ይቺን አደገኛ ጨዋታ አጥብቆ በየትኛውም መልኩ መታገሉን ማሰብ እንጂ ለወያኔ ማስፈራሪያ ማጎንበሱና በጓሮ በር መሹለኩ አንዱ የትግል ስልታችን ተደርጎ መወሰድ የለበትም ::
ስለዚህም ትኩረታችን, ጥንካሬያችን ወያኔ ለሚወስዳቸው እያንዳንዱ የበቀል እርምጃዎች (ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማዳከምና መሰረዝ, አባላቶቻቸውን ማሰር ማንገላታትና መግደል ) ምንድነው የተቃውሞ መልሱ የሚለው ላይ እንጂ እጅግ ዘግናኝ በሆኑ ወደፊት ኢትዮጵያ ላይ የሚመጡ "መዐቶችን" አጉልቶ በማሳየት የትግሉን ጥንካሬና የኅዝቡን ወኔ መስለብና ማኮላሸት ላይ መሆን አልነበረበትም, አይኖርበትምም::

ሌላው....
አለታ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 306
Joined: Tue Sep 16, 2003 4:42 pm
Location: vatican city

Postby አለታ » Wed Oct 19, 2005 7:18 pm

ሌላው ፓርላማ ባለመግባት የሚመጣው ጦስ ,
"ዋን ፓርቲ ሲስተም ወደሆነ ሸንጎ ለመግባት መመቻቸት"? የሚል ነው::

የዚህ ችግሩ ምን እንደሆነ አልታየኝም:: የተቃዋሚ ፓርቲዎች መግባት መድበለ ፓርቲ ሲስተምን ነው ይህ መንግስት የሚያራምደው የሚለውን ቅጥፈት ለመሸፈን እና ያለው የወያኔ መንግስት "ዋን ፓርቲ ሲስተም" እንዳይባል ነው?
ይህ ታድያ ለተቃዋሚዎችም ሆነ ለኢትዮጵያ ኅዝብ ምኑ ላይ ነው ጥቅሙ?
'ይህም ጸረ ኢትዮጵያ ፖሊሲዎችን ብሎክ ለማድረግ ጠንካራ ስፒች እና ቮት ማድረጉ ቀርቶ የመንግስትን ከህግ ውጭ የተሰሩ አፈጻጸሞች ለማጋለጥ እንኳን እድሉ የለም" የሚለው አቀራረብ ደሞ ፍጹም ካለው እውነታ ጋር ያልተገናዘበ ነው::

ከ170 በማይበልጥ መቀመጫ እንዴት ነው ፖሊሲዎች ብሎክ የሚደረጉት?
በ170 መቀመጫዎች የሚደረጉት "ቮቶች" ያን ያህል ቀሩብን ተብለው ተቃዋሚዎች ጸጥ ለጥ ብለው ወደፓርላማ እንዲገቡ የሚያስገድዳቸው ነጥብ ሆኖ አላገኘሁትም::
የወያኔን ፓርላማ(የተበተነውን) የመጨረሻ ውሳኔ የምናስታውስ ከሆነ ተቃዋሚዎች አሁን ባላቸው መቀመጫ ቁጥር አንጻር አጀንዳ እንኳን እንዳያቀርቡ የታገዱበት ውሳኔ የተመቻቸበት ነው::
ወያኔ የማይፈልገው ወይም የሚያስቀይመው "ስፒች" ከቀረበ ፖሊስ ያንን ተቃዋሚ ማጅራቱን አንጠልጥሎ ይዞ እንዲያስረው የፈቀደለት ፓርላማ ነው::
ታድያ ይህ ፓርላማ ነው ከላይ የቀረቡትን ሀሳቦች በመመርኮዝ የሚገባበት?

(ከሁሉ በላይ ግን ፓርላማ የሚገባው ህይወትን ለማዳን ከሆነ,,, ለምን ሞትን ፈራህ? ለምን እስርን ፈራህ? ብዬ የትኛውንም ሰው አልኮንነውም)

ለእንደዚህ አይነቱ ተቃዋሚ ለራሱም ሆነ ለቤተሰቡ ደህንነት ሲል ወደፓርላማ ሲገባ መልካሙን እየተመኘሁለት ከመሸኘት በስተቀር ሌላ አንዳችም ጉዳይ አይኖረኝም:: ከትግሉ አኳያ, ከድጋፉ አንጻር, አብሮ ከመታገሉ እይታ አንጻር ግን ይህ ሰውና እኔ ተለያይተናል ::
የኔ ድጋፍ ለአጼ ቴዎድሮሶች ነው; የኔ ድጋፍ ለአጼ ዮሀንሶች ነው:: ድጋፌ ለእምዬ የቁርጥ ቀን ልጆች እንደሻማ ቀልጠው ብርሀንን ለሌሎች ለሚሰጡት ነው::

የፖለቲካ ትግል ንኪኪ የሌለበት የመረብ ኳስ ጨዋታ አይደለም :: በተቻለ አቅም አላስፈላጊ የሆኑ መስዋዕትነቶችን ለማስቀረት ከፍተኛ ጥንቃቄና ስልትን የምንመኘውን ያህል በየምክንያቱ ሊወድቅ ለተቃረበ ድልብ ወንበዴ ጊዜ የምንሰጥበትና እሹሩሩ የምንልበት ምንም ምክንያት አይኖርም::
ወያኔ ከቅንጅት የቀረቡለት ቅድመ ሁኔታዎች አሉና ተገቢውንና የሚጠበቀውን መልስ ይስጥበት:: አርኪና የተጠበቀው መልስ ካልተሰጠ ግን ትግሉን እነዚህ ድርጅቶች በጀመሩት መልክ መቀጠል አለባቸው::

አሁንም ድርድር በሚሉና ተመሳሳይ ምክንያቶች የተቀጣጠለውን የህዝብ የትግል እሳት ውሀ እንዳይከልሱበት እያስታወስናቸው , በየትኛውም መልኩ ከጎናቸው መቆማችንን ማስመስከር ይኖርብናል::
ተቃዋሚ ፓርቲ ተነካ ማለት እኔ ተነካሁ ማለት ነው የሚለውን ጽንሰሀሳብ በሁላችንም ዘንድ ማጎልበት ይኖርብናል:;
.......[/u]
አለታ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 306
Joined: Tue Sep 16, 2003 4:42 pm
Location: vatican city

Postby አለታ » Wed Oct 19, 2005 7:32 pm

ግብጽ ከዚህ ኤርትራ ከዛ የመጡባትን ምስኪን ኢትዮጵያ ታዳጊው (አዳኝ) ወያኔ መሆኑ ደግሞ በጣም የሚያነጋግረን ነውና እሱንም በተከታታይ ማየት ይኖርብናል ::
በመሰረቱ ግብጽ ልትወረን በግልጽ እየተዘጋጀች አይደለም ::
ኤርትራም ቢሆን የምትፈልገው ወያኔ አምኖ የፈረመበትን "የትግራይን ባድሜ" እንጂ "ኢትዮጵያን" አይደለም ::
ይህም ቢሆን ለኢሳያስ መለስ አያንሰውምና የኢትዮጵያን ህልውና እንደሚያሰጋ አድርጎ ማቅረቡ ሀላፊነት የጎደለው አቀራረብ ነው::

ባድሜ ብቻ ሳይሆን የኤርትራንም መሄድ የኢትዮጵያ ህዝብ ገና ያልተነጋገረበት, ያልመከረበትና ያልፈቀደበት ስለሆነ ለጊዜው በባድሜ ወገኖቻችን የሞራልም ሆነ ማንኛውም ችግር ማዘናችን ባይቀርም , "እናቱ የሞተችበትና ገበያ የሄደችበት ልጅ እኩል ሊያለቅስ" አይገባም::

ለማንኛውም በዚህም ላይ እስቲ ሌላ ጊዜ በሰፊው እንመለስበት::
አለታ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 306
Joined: Tue Sep 16, 2003 4:42 pm
Location: vatican city

Postby ዞብልየ » Wed Oct 19, 2005 8:51 pm

አለታ,,,

ምንም የምጨምረው የለም ;; በጥሩ ሁኒታ ገልጸህዋል

ዋናው ጉዳይ ባሁኑ ወቅት መደረግ ያለበት ይህን ይመስላል;
1. ፓርላማ መግባት አለመግባት ጥያቂ ለጊዚው ትተን ቅንጅት በቅድመ ሁኒታ ያቀረባቸውን መሰረታዊ የዲሞክራሲ ጥያቂዎች እንዲመለሱ መታገል;;
ቅንጅት በቅደመ ሁኒታ ያቅርባቸው እንጂ እነዚህ ጥያቂዎች ምርጫ ተደረገ አልተደረገ ባንድ አገር ውስጥ ዲሞክራሲን ለማጎልበት መመለስ ያለባቸው አስፈላጊና መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸው;;
2. የተቀዋሚ ፓርቲዎች የትግል አጋርነታቸውን ከመቸውም ጊዚ ይበልጥ አጥእናክረው ህዝቡን ባንድ እንድምታ እንዲጉዋዝ ማድረግ
3.ፓርቲዎቻችን እስከአሁን ካሉበት የመከላከል ና የዝግምታ አካሂድ ፖሊሲ ወደ ማጥቃት ጎራ እንዲያዘነብሉ አስፈላጊውን ምክር, ሞራል መለገስ;;

ሊሎቻ ሁም ጨምሩበት

በቸር ያቆየን
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ዞብልየ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 52
Joined: Thu Feb 24, 2005 7:22 pm

ማጥቃት ሲባል?

Postby ልጁነኝ1 » Wed Oct 19, 2005 9:37 pm

በሩን ለህወኃት ወያአኔ ኢሕ አዴግ መክፈት አይገባም::

ማጥቃት ማለት ትርጉሙ "በወታደራዊ ቃል ነው:: እሱም ጠላትህን ማጥቃት ማግለልና የበላይነትን ይዞ መቆጣጠር ነው" ይህን ለማድረግ ቅንጅቱ በዚህ ወቅት የማይቺልበት ደረጃ ያለ ይመስለኛል::

አዎ ሲቪላዊ ውይይትና ተቃውሞው መቀጠል ይኖርበታል:: ከዚያም በዲፕሎማሲው ስራ ቀድሞ መገኘትና ጫና እንዲደርስበት ለወያኔው ማድረግ::

ቀጥሎም ህዝቡ ግብር መክፈሉን:: መታዘዙን:: ንግዱን በቅጡ ያለማካሄድ ከዚያም ህዝቡ የሚፈልገውን በሚያጣበት ጊዜ በመንግሥት ላይ እንዲቆጣ::

ያም ሲሆን ደግሞ ታጣቂው መንግሥት የነጋዴዎቹን ሱቆች ሊዘጋ ይቺላል:: በዚያም ላይ ጥንቃቄ ማድረግ:: ይህ ያለ መንግሥት መላዋን ኢትዮጵያን እንዲያምን እንጂ የሱን ታጋይና ታጣቂ ብቻ አምኖ መጓዝ እንደሌለበት መንገርና በሥራም መተርጎም::

ቅንጅቱ በሚቻለው ሁሉ ዕለት ተዕለት ከአገሪቱ መሪዎች ጋራ መነጋገር በተለይብ የአዲስ አበባ ጉዳይን በቶሎ ማስፈጸም መፈጸም ነው:: ከዚያ ነገሮችን በኢትዮጵያዊነት መመልከት::

ዛሬ ወያኔ ብቻ ሳይሆን ከወያኔውም ጉያ ያሉት ብዙ ወያኔዎች አሉ:: ታዲያ ያንን ሁሉ በዘዴ ይዞ ከጃቸው ፈልቅቆ ማውጣት ናቸው::

ስለ ኤርትራ የምናልባት ወረራ!!! እሺ በኡሙ ኃጀር በኩልና በመተማ በአብደራፊ በኦሜድላና በተለያዩ ስፍራዎች ሁሉ ፀው በመግባት የኢትዮጵያን ድንበሮች መያዝ ነው:: ከጃንጥላው ወታደራዊ እቅዳቸው ውስጥ ብለው አባይ ድረስ ሄደው አባይን ከተቆጣጠሩትንና ከግብጽም ድጋፍ አግኝተው ያን ቦታ ለብዙ ጊዜ ለመቆጣጠር ቢቺሉስ?

አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ባሰብሽ ኑሮ ዛሬ እንዲህ ግራ አይገባሽም ነበር አለቻት ይባላል ጎበዟ ሴትዮ ለገልትዋ::

ጉዳዩን ማዬት ያለብን ከስልጣን ብቻ ሳይሆን ስለ አገሪቱም ልናስብላት ይገባል በሚል አስባለሁ የናንተስ? ወያኔው ኢህ አዴጉ ህወኃቱ ይውደቅ ብቻ ሣይሆን ኮንስኮንሶቹንም አብረን ልናገናዝባቸው ይገባል:: ድንበሬ አዋሽ ነው የሚለውንም ማስታወስ አለብን::

ከምሥጋና ጋር

አክባሪያች ሁ

ልጁነኝ1
ከ(ሰሐሊን)


ዞብልየ wrote:አለታ,,,

ምንም የምጨምረው የለም ;; በጥሩ ሁኒታ ገልጸህዋል

ዋናው ጉዳይ ባሁኑ ወቅት መደረግ ያለበት ይህን ይመስላል;
1. ፓርላማ መግባት አለመግባት ጥያቂ ለጊዚው ትተን ቅንጅት በቅድመ ሁኒታ ያቀረባቸውን መሰረታዊ የዲሞክራሲ ጥያቂዎች እንዲመለሱ መታገል;;
ቅንጅት በቅደመ ሁኒታ ያቅርባቸው እንጂ እነዚህ ጥያቂዎች ምርጫ ተደረገ አልተደረገ ባንድ አገር ውስጥ ዲሞክራሲን ለማጎልበት መመለስ ያለባቸው አስፈላጊና መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸው;;
2. የተቀዋሚ ፓርቲዎች የትግል አጋርነታቸውን ከመቸውም ጊዚ ይበልጥ አጥእናክረው ህዝቡን ባንድ እንድምታ እንዲጉዋዝ ማድረግ
3.ፓርቲዎቻችን እስከአሁን ካሉበት የመከላከል ና የዝግምታ አካሂድ ፖሊሲ ወደ ማጥቃት ጎራ እንዲያዘነብሉ አስፈላጊውን ምክር, ሞራል መለገስ;;

ሊሎቻ ሁም ጨምሩበት

በቸር ያቆየን
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ልጁነኝ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 641
Joined: Tue Dec 30, 2003 2:17 pm
Location: united states

ዞብል 'ና አለታ

Postby ሳምቻው » Thu Oct 20, 2005 12:09 pm

ሰላም !

ከማክበር ጋር ሀሳብ አሰጣጣችሁን ለዩልኝ ፕሊስ !

"" እውነተኛውን እና ተጨባጩን የወቅቱን ሁኔታ በመተንተን መጪውን መተንበይ "" በሚለው አቀራረብ እና ..

"" በኢትዮጵዊነታችን ለሀገሪቱ የሚንሰማን ጥሩ ነገር "" በሚለው መሀከል ያለውን ልዩነት ባንደባልቀው መልካም ነው .......

የሀሳብ መቃረኖች የሚኖሩት በሁለቱ አመለካከቶች መሀከል ያለውን ልዩነት ሳናጤን ሀሳቡን ሚክስ ማድረግ ስንጀምር ነው ::

ለማለት የምችለው ብዙ ነገር ቢኖረኝም ለማሳጠር ግን እሞክራለሁ ::

በቅድምያ በዚህ ርእስ ስር ስንጽፍ "" ውሳኔ"" መሰጠታችን እኮ አይደለም :: ስለራሴ ብናገር ለምሳሌ ጽሁፎቼ የራሴን ""አቋም ወይም ምኞት"" እየገለጹ ሳይሆን ያለውን የፖለቲካ ኢንቫይሮመንት ምን እንደሚመስል መተቸት እና ቀጥሎ ምን ሊሆን እንደሚችል ከመተንበይ ጋር የተያያዘ አናሊስስ ነው :: አዲስ ነገር አይደለም !

ጉዳዩ በእኔ እጅ ቢሆን ኖሮ ደግሞ ይህንን ቀውስ እንዴት እይዘው እንደነበር ለማወቅ ቢያስፈልግ ........ ይህም ሌላ ራሱን የቻለ ጉዳይ ይሆናል ::

ይህንን ለጊዜው ወደ ጎን ትቼ በሰጣችሁት ሀሳብ ላይ ግን ትንሽ የምለውን እላለሁ .........
Last edited by ሳምቻው on Thu Oct 20, 2005 4:42 pm, edited 1 time in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

ዞብል

Postby ሳምቻው » Thu Oct 20, 2005 12:26 pm

ዞብል ማይነ ክላይነ ብሩደር

የካናዳውን ዊንተር የሚያስጥል ቆንጆ ሙቀት እንዲሰጥህ ከመመኘት ጋር በዚህ ርእስ የመጨረሻውን አርቲክሌን ለቅቄብሕ "" ሳበቃ "" እኔም ወደ ጨለመው በረዶዬ ልግባ ......[b]
Last edited by ሳምቻው on Sat Oct 22, 2005 2:32 pm, edited 3 times in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

"ሓ !" ኃገርህን አድን !! "መ" እይተኖረ ይታሰብበታል

Postby ሳምቻው » Thu Oct 20, 2005 2:11 pm

እንደው የተቀጣጠለውን የሀገር ፍቅር ስሜት ማደፈን ተብሎ አይተርጎምብኝ እንጂ የሀይል ሚዛኑ እኮ አሁንም ለጊዜው እንኳ ያለው ኢሀዲግ እጅ ነው :: ኢሀዲግ ሲሞት ደግሞ ለቅርጫ የተሰለፉት ተቀራማቾች ይለጥቃሉ :: ተቃዋሚው ቅንጅት እና ህብረቱ አንድ ሰባራ መድፍ እንኳ እንደሌላቸው ኣጢናሀልን !!?

ኃገር አቀፍ ቀውስ ሲነግስ , ያኔ ኢኒጂነር ሀይሉ ሻውል እና ዶክተር መረራ ጉዲና ድምጻቸው ከኣጥር አልፎ አይሰማም :: ይልቁኑ በየመንደሩ መግቢያ ላይ ቆመው"" ማይት ኢዝ ራይት "" ብለው የሚያምኑ ታጣቂዎች ብቻ ናቸው "" ተው ! "" ብለው ለመናገር ወኔው እና ሀሞቱ ያላቸው :: በየመንደሩ ቆመው ታያለህ :: ያለጥርጥር !!

የሚከፈለው መስዋትነት ለመንደር'ና ለጎሳ ሽፍቶች አሳልፎ ሊሰጠን ይችላል :: ላይሰጠንም ይችል ይሆናል :: ሆኖም ማንም እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይችልም :: እየተጠራጠርን ደግሞ መጀመር የለብንም:: ለዚህ ትግል ኃገሪቱ መያዥያ ሆና መቅረብ የለባትም ነው የኔ እምነት :: የተረጋጋ ሀገር ይዘን ነው ስለ አዲስ መንግስት ማሰብ ያለብን ::

ህልም ሌላ ፍቺው ሌላ ነው ዲር ብራዘርስ :: እንደ ህልማችሁ'ማ ቢሆንልን እኔ የመጀመርያ ሰው በመሆን እጋራው ነበር ...

ምን አለፋህ ሓገር አቀፍ ረብሻ ሲነሳ : ኢሀዲግ እንደ መንግስትነቱ ሀገሪቱን የመጠበቅ ሀላፊነት ላይ ይሰማራል let us say :: ግን ህዝባዊ ነውጡ ከአቅሙ በላይ እየሆነ ሲመጣ ና <<"" ከዚህ በኋላ >> የራሱ ጥፋት አለመሆኑን የሚያሳየው ደረጃ ላይ ሲደርስ'ና መንግስቱን ማዳን ሲሳነው እሱም በተጨማሪ የቻለውን ያህል ኃገሪቱን ይዟት እንደሚጠፋ አትጠራጠሩ !! :

ለምን'ድነው ኢሀዲጉ እንዲህ የሚያደርገው ? አንዱ ምክንያት : ......... ነውጡ የመረረው ህዝብ "" ለካ የመንግስት አቋም ትክክል ነበር "" ብሎ በሀዘን ከንፈሩን እየመጠጠ እንዲያስታውሰው ሲሆን :: ሁለተኛው እና ትልቁ ደግሞ ተቃዋሚውን ሀይል በሀላፊነት ለመያዝ 'ና ብሎሞ ተቃውሚው የሚሻውን እንዳያገኝ በማድረግ እና በዚህም በህዝብ ዘንድ የነበረውን ጥላቻ በተቻለው መጠን ወደ ተቃዋሚው ትከሻ ላይ ለማራገፍ እንዲቻል ኅገሪቱን እንደምንም ከማትወጣው እሳት ውስጥ ጥሏት ያልፋል :: የኢሀዲግን ታሪካዊ አመጣጦች እና የፖሊቲካ ተሞክሮዎች አሳምሮ ሊሚያውቅ ሰው ይሄ ብዙ ግር አይለውም ::

በማህበራዊ ቀውሳችን ውሥጥ ኤርትራ እና ኦነግ በሁሉም በታዎች ውስጥ ፈጥነው እንደሚገኙ የሚያሳይ ትንታኔ ለኢትዮጵያውያን አንባቢያን አሁን መዘርዘሩ አስፈላጊ አይመስለኝም :: ባጭሩ እንደኛው ህልም ሁሉ ለ'ነሱም ጉዳዩ "" ህልውና "" እና "" ጥሩ አጋጣሚ"" ነው :: "ትክክል አይደሉም" ብሎ ማመን ሌላ ነገር ነው :: ተጽእኗቸው ሲከሰት እና ከጉዳዩ ጋር ዲል ለማድረግ መገደድ ደግሞ ሌላ ራሱን የቻለ ጉዳይ ነው ::

የደሀ አገሮች ማህበራዊ ነውጥ በቀላሉ የሚበርድ አይደለም :: መራራ'ና ረጅም ነው :: እኛ ሥንታመስ የም'ራቡም ምላሽ የዘገየ ሲሆን ( too little too late ) ይተሰኘ የዱቄት እርዳታውን በCNN እየታየ በአውሮፕላን ከማራገፍ የዘለለ አይሆንም ::ምንአልባት UN ጥቂት ሰላም አስከባሪዎችን ነገሩ ሲሰክን ጠብቆ ያሰማራል :: አለቀ::

የህዝብ ማእበል ሲነሳ ቀጣዩ መንግስት ማንም ይሁን ማ , መንግስቱ እሲከረጋ ድረስ ,ምን አልባትም ለበርካታ አመታት ትልቅ ቀውስ ይነግሳል ::

ሀገር አቀፍ ቀውስ ሲነሳ ዘራፊውን ; ቀማኛውን ; ነበሰ-ገዳዩን ሁሉ የሚፍጥረው እራሱ አዲሱ ሲስተም ይሆናል :: ስራ የለም :: ገቢ የለም :: የጸጥታ ዋሳትና የለም :: በህግ ተጠያቂነትም የለም :: ኃገሪቱን የሚመራ የህግ ሰንሰልት ተበጥሷል :: ማን ምን እንደሆነ አይለይም ::

ሀገር በአመጽ ስትርድ : ከተራ -አስገድዶ መድፈር እና የቂም-በቀል ግድያዎች አንስቶ እስከ የጦፈ- የጎሳዎች ጦርነት ይናኛል ::ልብ አድርጉ ይህንን ነገር ""ጨዋዎቹ"" እኛ ና እናንተ አንፈልገውም ነበር :: ግን ተከስቷል :: ለህዝባችን የሚገባው ነገር እንዳልሆነም እናምናለን ::

ምንም አይነት የህግ አስራር በሌለበት ምድር ውስጥ ስረአተ- አልበኝነት (lawlessness) ባያሌው ይከሰታል :: በየቤቱ ኪመደነግጠው ደካማ ክፍል በተጨማሪ በእንዲህ አይነት ነውጥ መንግስት ሲለወጥ በአጋጣሚው ለመጠቀም አሰፍስፎ የሚጠብውን የዘራፊ ቡድን ማሰብ ያስፈልጋል :: ወይ ያልፍልኛል ወይ ያልቅልኛል ብሎ የሚነሱት ቡድኖች ከተራ የግለሰብ-ቤቶች ዝርፊይ እስከ ኅጋር አቀፍ የመሳርያ ንግድ እና ዝውውር ይሰማራሉ ::ማንን ያፍራሉ ምንን ይፈራሉ ?

ዞብል : ማስረጃ ስትጠይቀኝ :: ትንሽ ቆምጠጥ ያለች ሳቅ ስቄ ነበር :: የፖለቲካ አናሊስስ እንደ ሂሳብ እና ፊዚክስ ፕሩፍ የምታደርገው አሳይመንት ሳይሆን አካባቢህን በተቻለህ መጠን ተገንዝበህ ያንን መናገር መቻል ነው :: ሀገርን ያህል ግዙፍ ቅርስ እና ህዝብን ያህል ክቡር ፍጡር እንደ ቤተ-ሙከራ አይጦች እያነሳሁ በሚግም እሳት ላይ በመጣል ሕመሙን መቋቋምና አለመቋቋም መቻለቻውን ላሳይህ ባለመቻሌ አዝናለሁ ::

በጎሳ ፖለቲካ በተከፋፈለ ሀገር ውስጥ የህዝብ ነውጥ የሚያነሳው ማእበል ምን ሊሆን እንደሚችል እንዴት ማስረጃ ትጠይቃለህ ?

ጥሩ ማስረጃው ሱማሊያ'ና ሩዋንዳ ሲሆኑ :: ማእበሉን ከለኮስን እኛም የ'እነሱ እጣ ላይደርሰን የማይችልበትን (ማስረጃውን ትተህ) ሎጂካል አናሊስስ እንኳ ልታስቀምጥልን ብትሞክር መልካም ነበር :: ጨዋነታችን ይጠብቀናል ብለሀል ::ለኔ ግን አይታየኝም :: በሽፍቶች የተከበበን የድሆች መንደር ጨዋነት የሚታድገው አይመስለኝም ::

ልብ በል እስካሁን መንግስት የሌላት ሶማሊያ እንኳ እንደኛ ሀገር ብዙ ልዩነት አልነበራትም :: አንድ ሀይማኖት : አንድ ቋንቋ :: አንድ ባህል ነው ያላቸው :: ሲጀምሩ ጥያቄያቸውም የመገንጠልና የጎሳ የበላይነት ሳይሆን የፖለቲካ ስልጣን ባለቤትነት ነበር .....! ሱማሌ የት ናት ዛሬ ??

ሲ-ዩ ኢን ሰመር ! በረዶው ሲቀልጥ
Last edited by ሳምቻው on Fri Oct 21, 2005 10:47 am, edited 2 times in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Re: ዞብል 'ና ሀለታ

Postby ዞብልየ » Thu Oct 20, 2005 3:06 pm

[quote="ሳምቻው"][b]ሰላም !

ከማክበር ጋር ሀሳብ አሰጣጣችሁን ለዩልኝ ፕሊስ !

"" እውነተኛውን እና ተጨባጩን የወቅቱን ሁኔታ በመተንተን መጪውን መተንበይ "" በሚለው አቀራረብ እና ..

"" በኢትዮጵዊነታችን ለሀገሪቱ የሚንሰማን ጥሩ ነገር "" በሚለው መሀከል ያለውን ልዩነት ባንደባልቀው መልካም ነው ....... ""
end of quote


ወንድም ሳምቻው የካናዳ በረዶ እስካሁን አልጀመረም በተለይ እነ ያለሁበት አካባቢ;; እንዲያው መልመድ ያቃተኝ ቢኖር ይህን በረዶ ነው;; ለነ ሁሊም በየአመቱ አዲስ ነው
see u summer ላልከው አይዞህ የካናዳ net በረዶውን ጥሶ አንተ ጋ ስለሚደርስ አትጥፋ

ከላይ እንዳልከው የስሚት ጉዳይ ሆኖብኝ አይደለም;; ስሚታዊነት ከነባራዊ ሁኒታ እንደሚያርቅ ና ጎደሎ እይታን እንደሚያስከትል አውቃለሁ''
ሁለታችንም የወያነን አምባገነንት ጨካኝነት መወገድ እንዳለበት እናምናለን;; ጥያቂው መቸ ይሁን ነው;; አንተ ጊዚው አሁን አይደለም;; ህልውናቸን አደጋ ላይ ይወድቃል, በህገሪቱ ህልውና ላይ ቁማር አንጫወት ባይ ነህ;;
በሊላ በኩል እኒ ደግሞ ቅንጅት ያቀረበው መሰረታዊ የዲሞክራሲ ጥያቂእዎች አሁን ይመለሱ ነው;;
ይህንን ለማስፈጸም የምናደርገው ትግልና የትግል ዘዲዎች ነው ልዩነት በነና ባንተ መህከል የፈጥእረው;;
አንድ ነገር ለማስረገጥ የምፈልገው ቢኖር ቅንጅት ከስምንቱ የመደራረሪያ ወይም የቅድመ ሁኒታዎች ውስጥ ቀሪውን አምስቱን አላካተተም;; በተለይም ብህእራዊ የርቅ መንግስትን አልጨመረም;; ይህ በሚገባ እንዲሰመርበት እፈልጋለሁ;; ንግግራችን ሁሉ በዚህ ዙሪያ መሆን ይኖርበታል ብዪ አምናለሁ;;

ይቀጥላል.......
ዞብልየ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 52
Joined: Thu Feb 24, 2005 7:22 pm

Postby ዞብልየ » Thu Oct 20, 2005 3:33 pm

ወንድም ሳምቻው

ብህራዊ የርቅ መንግስትን ያላካተተ ቅድመ ሁኒታ በቅንጅት መቅረቡ ምን ማለት ነው;;

1. ስለምርጫው ና አልፎም ወያነ አቸንፍኩ ብሎ የመሰረተው መንግስትን አያካትትም ድርድር ውስጥ አያስገባም
2. 299 የምርጫ ጥአብያዎች ጉዳይ በድርድሩ ውስጥ አይነሳም
3. ያለው status quo አይነካም

እስቲ በጽሞና እነዚህን መጥይቆች እያቸው;; እንዚህ ጥያቂዎች ምርጫ ተደረገም አልተደረገ በማንኝአውም ጊዚ ለነሱ የሚችሉ መስረታዊ የዲሞክራሲ ጥያቆዎች ናቸው;; ይህንን ለመመለስ ወያነ ለምን አዳገተው? ልብ በል ቅንጅት ሰላምን ብቻ አይደለም ዲሞክራሲንም ለማጎልበት ብዙ ተጉዙዋል;; ከብዙ ጥያቂዎቹ አፈግፍዋል ;;
የነ ጥያቂ ታድያ
1. ይህንን ለመመለስ ያልፈለገ መንግስት ለወደፊቱ ዲሞክራሲ ብቻ ሳይሆን የህእገሪቱን አንድነት ና ህልውና ለማስጥእበቁ ምን ዋስትና አለ? ወያነ በየጊዚው ህእገሪቱን ከየማእዘኑ እየቆረሰ ሲሰጥ እንጅ ድንበር ሲያሰፋ አላየንም;;
2. አሁን የህእገሪቱ ህልውና ይብሳል በሚል ወደ ጎን የምናደርገው መሰረታዊ የዲሞክራሲ ጥያቂ መቸ መልስ ያገኝናል? ካምስት አመት በህዋላ ወያነ ተመሳሳይ ድርጊት ላላመፈጸሙ ምን አሰማማኝ ነገር አለ'' ልብ በል መለስ በ CNN ስልጥአን መቸ ትለቃለህ ተብሎ ሲጥየቅ ምናልባት ካምስት አመት ብህዋላ ነበር ያለው.\;; ይህንንም ያለው ጋዚጥእኝአው አጥብቆ ስለተየቀው ነው;;
3. በሚቀጥለው አምስት አመት ውስጥ የተቀዋሚ ፓርቲዎች መሪዋቻቸውን አንድ ባንድ ስበብ እየፈለገ ዘብጥያ አለመዶሉ ወይም አለመግደሉ ምን ዋስትና አለ;; ካሁኑ ከስር ያሉትን መጥረግ ጀምሮታል;;

ይቀጥላል
ዞብልየ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 52
Joined: Thu Feb 24, 2005 7:22 pm

Postby ዞብልየ » Thu Oct 20, 2005 8:01 pm

ካንተው ጥቅስ ልነሳና:
'"ዞብል : ማስረጃ ስትጠይቀኝ :: ትንሽ ቆምጠጥ ያለች ሳቅ ስቄ ነበር :: የፖለቲካ አናሊስስ እንደ ሂሳብ እና ፊዚክስ ፕሩፍ የምታደርገው አሳይመንት ሳይሆን አካባቢህን በቻለህ መጠን ተገንዝበህ ያንን መናገር መቻል ነው :: ሀገርን ያህል ግዙፍ ቅርስ እና ህዝብን ያህል ክቡር ፍጡር እንደ ቤተ -ሙከራ አይጦች እያነሳሁ በሚግም እሳት ላይ በመጣል ሕመሙን መቋቋምና አለመቋቋም መቻለቻውን ላሳይህ ባለመቻሌ አዝናለሁ :: "" የጥቅሱ መጨረሽ

ወንድም ሳምቻ;

የፖለቲካ አናሊሲስ በመረጃ ና በህእዝም እንደሚደገፍ መሳት የለብህም;; ለምሳለ ህዝቡ በቃኝ ወያነን አልፈልግም ለማለቱ ምርጫውና የምርጫው ወጥእት በቀመር የሚታይ አህእዝ አሳይቶናል;; ልጨምርልህና በግንቦቱ ህዝባዊ ማእበል ህዝቡ ጎጥ ና ጎሳ ሳይለይ በነቂስ ወጥቶ ስሚቱን ና የሚፈልገውን መግለጹ ራሱ ጭብጥ መረጃ ነው;; ይህንና ለሎችንም መረጃዎች አሰባስበህ ነው የፖለቲካ አናሊሲስ ውስጥ በመግባት የፖለቲካ ወሳነ ላይ የምትደርሰው ወይም ፖሊሲ የምትቀርጸው;; ወይም ቀጥአይ የፖለቲካ የትግል ስልትህን የምታወጥአው;;
አሁንም ደጋግሚ የማምነው ከጥቂት ሆዳም በስተቀር የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋና የሚያደርገውን በትክክል የሚያውቅ ህዝብ ነው;; ምንም እንክዋን የኢኮኖሚ ድህነት ቢያደቀውም የአስተሳሰብ ና የእውቀት ደህ አይደለም;; የሚያደርገውን ጥእንቅቆ ያውቃል;; ከሩዋንዳ ጋር ማመስሳስለህ በታሪክና በባህል የዳበረውን ህዝባችንን በሚገባ ካለማወቅ ነው ብየ አልፈዋለሁ;; ወያነ አዲስ አበባን ከመያዙ በፊት ላምስት ቀናት መንግስት አልነበረም ማለት ይቻላል;; አንድም ባንክ አልተዘረፈም አንድም ህንጻ አልፈረሰም;; አሁን ያለው ሁኒታው ለላ ነው ብትለኝ,,, ያ የነበረው ትውልድ አሁንም አለ ነው የምልህ;; አምስት ቀናት ራሱን ያስተዳድር የነበረው ትውልድ አሁንም አለ;; ያንኑ ይደግመዋል

quote ያንተኑ ጥቅስ ልድገመው
""በማህበራዊ ቀውሳችን ውሥጥ ኤርትራ እና ኦነግ በሁሉም በታዎች ውስጥ ፈጥነው እንደሚገኙ የሚያሳይ ትንታኔ ለኢትዮጵያውያን አንባቢያን አሁን መዘርዘሩ አስፈላጊ አይመስለኝም :: ባጭሩ እንደኛው ህልም ሁሉ ለ 'ነሱም ጉዳዩ "" ህልውና "" እና "" ጥሩ አጋጣሚ "" ነው :: "ትክክል አይደሉም " ብሎ ማመን ሌላ ነገር ነው :: ተጽእኗቸው ሲከሰት እና ከጉዳዩ ጋር ዲል ለማድረግ መገደድ ደግሞ ሌላ ራሱን የቻለ ጉዳይ ነው""
end of quote

ይህ ሁኒታ የሚከሰተው የኢትዮጵያ ህዝብ ጎራ ለይቶ ሲዋጋ ብቻ ነው;; ህዝቡ በጎሳ ወግኖ ርስ በርስ ሲጨፋጨፍ ብቻ ነው;; ቀደም ብየ ማ ማንን ይወጋል በማለት ጥያቂ አንስቸልህ ነበር;; ቆይተህ የመለሰክልኝ ግን ኢርትራንና ኦነግን ነው የጥእቀስከው;;
ኢርትራ ኢትዮጵያን ወርራ በመያዝ አሽንጉሊት መንግስት አዲስ አበባ ላይ ትመሰርታለች ነው ከሆነ ፍርህእትህ,, ይህ መቸም አይሆንም;;
ኦነግ ኢትዮጵያን ከፋፍሎ ለመያዝ ሳይሆን እነደወያነ በለስ ከቀናው መላው ህገሪቱን ይዞ ተራው አሁን ደግሞ የነ ነው በሚል ብህእራዊ መንግስት በመመስረት የዲሞክራሲ አስተማሪ ሆኖ በመቅረብ ደፋ ቀና ይል ይሆናል''

ሳምቻው;
ከመረት ተነስቶ ብጥብጥ አይነሳም;; የሚሆነውን ጭብጥ ማስረጃ እያቀረቡ መተንበይ ይቻላል;; ተቀዋሚ ፓርቲዎች ከበት መዋል ከሚል አድማ ተነስተው ቀስበቀስ ወደ ብህራዊ ስራ ማቆም አድማ የሚሽጋገር አንድ ወጥ የፖለቲካ አመራር በመስጥእት ነው የሚጀመረው;; ይህ ደግሞ ከቁጥጥር ውጭ አይወጥአም;;

ይቀጥላል
ዞብልየ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 52
Joined: Thu Feb 24, 2005 7:22 pm

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests