<< << << ታ ገ ስ >> >> >>

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

<< << << ታ ገ ስ >> >> >>

Postby > » Mon Oct 24, 2005 6:46 pm

ፈሠሠ ወረደ ጉንጬም እረጠበ
ከ "B" መለየትን ከቶ እያሰበ
እንባዬ አልቆመም መፍሰሱን ቀጥሏል
"እዛ አገር" ከሄደች ማትመጣ መስሎታል
እባክሽ ተው በይው
አንጀቴ ይቻለው
ነገም ቀን መሆኑን ጠንቅቆ ይወቀው
የለመደሽ ልቤ ቅስሙ የተሰበረው
እስቲ ታገስ በይው
መዳኛ ጊዜ አለው
ይመስለዋል እንጂ እምባ ስንቅ አይሆነው
መመለሻዋን አምላክ አፍጥነው
ብላችሁ ፀልዩ ነበር አይደል ያልሽው?
ፈጣሪ ያሳካው ይሁን እንደተመኘሽው
ባለሽበት ደስታን እመኝልሻለሁ
አምላክ ካንቺ ይሁን ብዬ እሰናበታለሁ
ለ "B"
>
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Mon Oct 24, 2005 6:11 pm
Location: ethiopia

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 0 guests