00

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Re: ለወንድም ተደማም::

Postby ተድባበ » Tue Oct 25, 2005 4:30 pm

ሰላም ወንድም ARERU.... አዎን ይህ የባረክልን ርእሰ ጉዳይ የጋራ ገጠመኛችን ማእከል በመሆኑ ስለሳበን ነው - መደረሳችን:: እናም እንዳልከው ሁሉ አንድ ደህና ኔበንተኔ/የራስ የሕይወት ታሪክ (AUTOBIOGRAPHY) አሳትመህ ለማውጣት ማሰብህ አስደስቶኛል:: በርታበት ግፋበት... ሕትመትንና የሕትመት ዝግጅትን በተመለከተ ሙያዊ እገዛና ምክር ካስፈለገ እንዳቅሜ ለመተባበር ፈቃደኛ ነኝ:: ብትፈልግ እዚሁ መድረክ ላይ ያለበለዚያም በprivate ጊዜ በፈቀደ እተባበራለሁ...... በተረፈ ገጠመኛችንን ለሌሎች ከማቋደስ እንዳንታቀብ አደራ እላለሁ...........

ተደራሲህ
ተድባበ

ARERU wrote:ሰላሙን ሁሉ እመኝልሀለሁ ከዛ በመቀጠል እምለው ነገር ግን ወደፊት ይሄን ታሪክ በስድ ንባብ መልክ እድሜውን ለሁለታችን ከሰጠን መስጸሀፍ ሆኖ ታነበዋለህ እኔም ታሪክን ግጥMም ይናገረዋል ብየ አስቤው አይደለም ነገር ግን ለጊዜው እንኩዋን በሚል ነው ስለዚህ የተዘጋጀ መጽሀፍ አለና ታትሞ ልታነበው ትችላለህ ብዙ ነገሮችን ያዘለ በዛም ላይ እህት ትትናን ሳላመሰግናት አላልፍም::
አመሰግናለሁ
አረሩ::
ተድባበ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 13
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:06 pm
Location: ireland

Postby ከርታታ » Tue Oct 25, 2005 5:37 pm

ሰላም ARERU ታሪኩ መቼም በጣም ልብ ይነካል እኔ በግሌ በስደት ብዙ የተንገላታሁ ይመስለኝ ነበር ግን ለካስ ከኔም የሚብስ የደርሰበት ስንት እንዳለ ቤት ይቁጠረው ለካስ ያልተነካ ግልግል ያውቃል ይሉኃል ይሄ ነው እስኪ የደረሰብህን ሁሉ አጫውተን ምናልባትም ከደረሰብህ ስቃይ የተነሳ ይሆናል ያገራችን ሴቶች ሌላ ዜጋ በማግባታቸው የተገረምከው??እስኪ ለሁሉም ታሪኩን ቀጥለው እባክህ ማኖ አስነክተህ ዞር እንዳትል::
አክባሪህ ከርታታ
ከርታታ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Thu Mar 03, 2005 1:00 am
Location: united states

ለወንድም ከርታታ

Postby ARERU » Tue Oct 25, 2005 7:35 pm

ሰላም ወንድም ከርታታ እንደምን ነህ እኔ ደህና ሳልሆን እምቀር አይመስለኝም ቢሆንም ወደ ነጥባችን እንመለስና ከመጀመሪያውም ይሄን ጽሁፍ እዚህ ቦታ ላይ ለማስፈር ያሳሰበኝ ነገር ቢኖር ያው አንተና እኔን መሰል ወንድሞቻችን በሀሳቡ ባንረካም ማስታወሻ ይሆነን ዘንድ ነውና መቀጠሉ አይቀርም ነገር ግን ድሮ ስጽፈው አንዳንድ ሀሳቦች በብሽቀት የጽፍኩዋቸው ስለነበር አሁን በዚህ ቦታ ማስፈሩ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘሁት አንዳንድ መስተካከሎች እያደረግኩበት ነውና ማኖ የለም ይቀጥላል በቃኝ እስክትል ድረስ::
አመሰግናለሁ
አረሩ::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

ስደተኛው:በአፍሪቃ::

Postby ARERU » Thu Oct 27, 2005 2:59 pm

ቁጥር 9 ከቁጥር 8 የቀጠለ:-

የመከራው መነደር ያሉት ወደህሊሎ
ጭራሽ የገባበት ሀገረ ተጠቃሎ
ሁልጊዜ እለቅሶ የበዛበት እሮሮ
ሰው እሚያልቅበት ወይ ታሞ ወይ ታስሮ
በረድፍ በረድፍ ሆኖ የተሰራው ድንኩዋን
የትየ ለሌ ነው ተቆጥሮ መች ያልቃል
ሀገሩ በርሀ ለሰው ያለተሰራ
የሙቀቱ ነገር ይቅር አይወራ
ቀን እስከሌት ጭራሽ ማያባራ
ስው እማያስተያይ በጉም ፈንታ አቡዋራ
የህመሙ ብዛት ወባውና ሌላው
ተኛ ከተባለ ሰው እማያተርፈው
ወይ የዝንቡ ብዛት ሰራዊቱ እንድ ላይ
ሁሉም በየተራ በሰልፍ በሰልፍ ሲታይ
ብርድ በመጣ ጊዜ በዝናቡ ወራት
ዋጥ ያደርግና ጭቃው እስከ ጉልበት
ዶፉ ከላይ ሲወርድ የለ መንቀሳቀስ
ጣራ እንኩዋን ለወጉ የለ የሚለበስ
የብዙው ቤት ወድቆ በንፋሱ ብዛት
መጠለያ አጥቶ ሲታይ ውሀ ውጦት
እሚያስጠጋው የለ ና ግባ እሚለው
በሩን ሚከፍትለት ከስቃይ ሚያድነው
በፓርቲ በፓርቲ ሁሉም ተከፋፍሎ
ያኛው ይሄኛውን ያለጥቅም አግሎ
ሁሉም በየፈርጁ ሞትን ይጠብቃል
ዛሬን ተሻገርኩ ሲል ከነገው መች ያልፋል
ምግቡ አይወራ መፈጠር ያስጠላል
እንዲያው ዝም ዝም ቢባል ይሻላል
ተብሎ የለም ወይ ሆድ ካገር ይሰፋል
የተቀበለውን መሸከም ይችላል
ሰው ይራብ ይጠማ ይቸገር ምን አለው
ከሁሉ እሚከፋው ሞራል ሲሰበር ነው
ሊጠብቀን ተብሎ የመጣው ሰራዊት
ሴት እየመረጠ ማሳደሩ አንሶት
ባልታወቀ ምክኒያት አመጣ ማስቀረት
የጠየቀው ደግሞ የት ሄዱ እያለ
ወይ ባል ወይም ወንድም ነኝ ብሎ ያለ
በሰበሰ እሬሳው መንገድ ላይ ተጣለ
ሁሉም ዝም ሆነ መላሽም ጠያቂም
እሽ ማለት ሆነ ብትወሰድ ሚስትም
የሁዋላ የሁዋል ነገሩ ሲመጣ
ለካስ ለህቶቻችን መጥፋትን ያመጣ
ስሜት እንዲያረኩ በታዘዙ ስአት
አረገዝን ብለው ላስረጋዥ ሲነግሩት
እየተገደሉ ነበር እሚቀሩት
ስንቷ ከንቱ ቀረች ሳትመለስ ወጥታ
ለሰው ሚከራከር አንድ ያገር ልጅ አጥታ
ነጻ አውጭ የተባሉ የወሬ አባቶች
አደረግን አደረግን ብቻ አሰልችወች
እገሌ እንዲህ ሆነች ብለን ካመልከትን
የማንስ አባል ናት ተብለን እንጠየቃለን
የማንም አይደለች ብለን ከተናገርን
እንደምሳቅ ብለው እያሾፍብን
በሉ ፈልጉላት አብል የሚያደርጋት
የትስ እንደገባች ሚከራከርላት
ነበረ መልሳቸው እግዜር ይይላቸው
በእህቶቻችን ደም ጊዜ እስኪጠይቃቸው::

አንድ ወር ሁለት ወር ተማርቶ አለፈ
ሶስተኛው ደረሰ እሱም እያረፈ
እኔም ሰው ተዋወቅኩ ካንድ ሁለት ሶስት አራት
ተመካከርንና ከዛ ቦታ መጥፋት
ጉዟችን ጀመርን ገዳሪፍ ለመግባት
እንዲህ እንዲህ እያልን እየተጠራመስን
ገዳሪፍ ለመግባት አንድ ሳምንት ፈጀን
ከኪሳችን የለ ቤሳ ይሁን ቢስቲን
የቱስ መጠለያ ምንስ ልንበላ ነው ከተማ ከገባን::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

የግል አስተያየቶች...

Postby ዋኖስ » Thu Oct 27, 2005 3:04 pm

:roll: የግል አስተያዬቶች በዉስጥ ቢፃፉ ምንኛ ደግ

ነበር!! ለምን አንተስ እንዳትሉኝ...ይችን መልዕክት

ሁሉም እንዲያያት ስለፈለግሁ::ማበረታቻችም ይሁን

ነቀፋ ( ክሪቲሳይዝ) ማድረግ የምትፈልጉ ሁሉ በግል

ብትፅፉለት ቆንጆ ይሆን ነበር!!ምክንያቱም የፅሁፉን

ዉበት እየተጋፋ ነዉ ይመስለኛል::

=====ዋኖስ====
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

ስደተኛው:በአፍሪቃ::

Postby ARERU » Thu Oct 27, 2005 6:48 pm

ቁጥር 10 ከቁጥር 9 የቀጠለ:-

ገዳሪፍ{ ያንድ ክ/ሀገር ዋና ከተማ ናት የሱዳን}

ሀበሻ እንደ እርኩስ ከሚቆጠርባት
የሰው መጨረሻ ሰልፍ ከሆነባት
እንደ አንድ ስድብ አህያ ወይ ውሻ
ከሚባልበቱ ሂድ አንተ ሀበሻ
ገባን እንደምንም ተጉዋተን ገዳሪፍ
ዘመድ ወዳጅ የለ ግን ወዴት እንረፍ
ቀኑን ባንድ ቦታ ተደብቀን ውለን
ማታ ወጣ አልን
በየመንገዱ ዳር የተረፈረፈው
የሀበሻው ብዛት ይሄስ ለብቻው ነው
አፈር አፈር መስሎ ካፈር ተደባልቆ
ሊያውቁት እንዲቸግር ወንድ ከሴት ተለይቶ
ሁሉም ኮርነር ኮርነር ይዞ ተጠግቶ
በካርቶና ምንጣፍ እራሱን አዝናንቶ
ያሸለበው አለ ሌላም ሚቁነጠነጥ
ደግሞ የጨነቀው አይኑ ያለ ፍጥጥ
እንዲሁ እያለፍን ብዙ እንደተጎዋዝን
የምናውቀው ቁዋንቁዋ ሹክሹክታ ቃል ሰማን
እኛም ቆም አልንና እንደ መረጋጋት
ጀሯችን ቀጥ ቀጥ አድረግን ለመስማት
ድምጹም እልም አለ
የተጠራጠረ ከነሱ ውስጥ አለ
የመጣው ይምጣ እንደተባባሉ
በደፈረ አባባል ጮክ ብሎ አንዱ
ብሎ ተናገረ ቆማችሁ ቀራችሁ ምን ነው ብትሄዱ
እኛም መለስንለት እንግዳ እንደሆን
እምናውቀው ዘመድ መጠጊያ እንደለለን
ደስታ እንደማለት አርጎት ሀበሻ ስንሆን
ኑና እዚህ ተኙ ብሎ አስተናገደን
እኛም ተደስተን ምስጋና ጨምረን
ወደነሱ ሄደን ቁጢጥ ቁጢጥ አልን
ተዛናኑ አለ አንዱ ሳቅ እየሞከረው
ስጋጃ አይደለም ምንጣፉ መሬት ነው
ከዛ ወሬ ጀመርን እኛም በሹክሹካታ
ሀሳብ ተለዋወጥን በተርታ በተርታ
አይዟቹህ በርቱ ምንም አትሆኑም
ቀንቀን ግን አትውጡ ፖሊሶች አይምሩም
ለመቀማት ሲሉ ወይም ሴት ፍለጋ
በዱላ በጥፊ እንዲሁም ባለንጋ
ያሰቃዩአቹሀል ሰው እንዳልሆናችሁ
ሞትም ቢሆን አለ ዱላው በዝቶባችሁ
እኛም ስለፈራን ስለተርበተበትን
ከውስጣችን ከምር ስላሶችን ጠርተን
ከዚህ ማአት አውጣን በለንም ተማጸን
እንዳሉን ወንድሞች እንድተመከርነው
ቀን ቀን እየጠፋን ማታ ማታ እንደጅብ
መኖሩን ጀመርነው
የሚረዳ የለ ወይም ገንዘብ ከኪስ
ወይም ፍርፋሪ ጭራሽ የሚቀመስ
ሆዳችን ድር ደራ አጥንት ገጠጠ
ህይወት ቅጡ ጠፋ ተስፋ ተሟጠጠ
እሮሯችን በዛ ወደ እግዚአብሄር ጯህን
ኡ ብለን አለቀስን አምላካችን ጠየቅን
ሌላውን እንዳዘዝክ እሚበላ ስጠን
የጠገበው በዝቶ ሲደፋው እያየን
እንዴት ባንተ ምድር እርቦን እንሞታለን
የነሱን አትቀማ የኛን ፈንታ ስጠን
ላንድ ስው ሁለት ሰው ተጭና እየመጣ
እንዴት ለኛ እሚሆን እንድ እፍኝ እንጣ
እሚበላው ሁሉ ሚለቅመው አጥቶ
እንዴት በራብ ይሙት ሰው ካገሩ ወጥቶ
ጤፉ ስንዴው ገብሱ እንዲሁም ምስሩ
ባቄላ ዳጉሳ ጉዋያውና አተሩ
በቆሎ ማሽላ እንዲሁም ሽምብራ
ሱፉ ኑጉ ሰሊጥ ሁሉም በየተራ
ብርጭቅና ሙዙ እንዲሁም ብርቱካን
ትርንጎና ኮኩ እንዲሁም መንደሪን
ዶቅማ እንኮዩ ዋንዛው
ኮሽም አጋም ቀጋው
በጉ በሬውና ሙክት የፍየሉን
ድኩላና ሰሳ ሚዳቁዋ አጋዘን
ቆቁና ዥግራ
ድምድም የደሮ አውራ
እንቁላሉ ማሩ ቅቤና ወተቱ
ድንቹ ቀይ ስሩ እያለ ካሮቱ
ሌላው ሌላው ሳለ በስም የረሳሁት
ባገራችን ሞልቶ ሚበቅል ሳይዘሩት
ሚደልብ ሳያደልቡት
እንዴት በግድ ወጥተን በርሀብ እንሙት
ወይ እሪ በከንቱ
አያሳዝንም ወይ ሰው ወጥቶ መቅረቱ::

ይቀጥላል::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

Postby ባይተዋር22 » Thu Oct 27, 2005 8:29 pm

:twisted ወይ ነዶ አለ ሰውየው
ባይተዋር22
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Wed Sep 21, 2005 8:10 pm
Location: iraq

ስደተኛው በአፍሪቃ::

Postby ARERU » Fri Oct 28, 2005 4:36 pm

ቁጥር 11 ከቁጥር 10 የቀጠለ:-

መቸስ ምን ይደረግ እርሀብ ሲጠና
ዱላው ከጠገብን ይሻላል አልንና
ስራ ለመፈለግ ቀን ቀን መውጣት ጀመርን
በየምግብ ቤቱ በየሱቁ ገብተን
ሽቁል አለ ስራ ብለን ብንናገር
ግማሹ ይስቃል በኛ ቁዋንቁዋ ማጠር
ግማሹ ሰው ያዛል እኛን ለማባረር
ግማሹ ያፌዛል በኛ መደናበር
ወዲህ ወዲያ እያልን ተንከልክልን ውለን
ማታ ሰብሰብ ስንል በየ ማደሪያችን
የቀኑን እሮሮ ያጋጠምን ነገር
አንድ ባንድ በተራ ስንዘረዝር
ወየው ዛሬ ደግሞ ያጋጠመኝ ፖሊስ
እንባ እንኩዋን እያየ ውስጡ ማይመለስ
ጭራሽ እንዳልሆነ ካዳም ልጆች አንዱ
ፍዳየን አሳየኝ በዛ ጠብደል ክንዱ
እምስጠው ባጣ ዱላ እንደፍርድ ቤት
ወንጀለኛ አድርጎ ቀጠቀጠኝ በውነት
እኔም ብየ ብየ ዱላው ሲጠናብኝ
ወደላይ ጎንቸ ምድር ተዘረርኩኝ
መሬቱ ታቅፌ ትንሽ እንደቆየሁ
እንደመንቃት ስለ ከጎኔ ሰው አጣሁ
ከዛም ተነስሸ እንደምንም ብየ አሁን ይሄው መጣሁ
ሌላው ደግሞ ይላል የደረሰበትን
ሲተፉብኝ ዋሉ ሲሰድቡ ሀበሻን
ሀይማኖቴንና ሀገሬንም ህዝቡን
ክብር እንደለለን ጭራሽ እንዳልነበርን
ያም ያም መሳለቂያ በየአፉ አድርጎኝ
ህጻኖች እንደእብድ ትልቁ እንደሞኝ
ሁሉም እየጠሩ ሲሰላለቁብኝ
ሲያሯሩጡኝ ዋሉ ሲያንከለክሉኝ
እንዲህ እንዲህ እያልን እሚሰራ ሲገኝ
እሚጠረግ ቤት እሚታጠብ እቃ ሚፈነቀል ቁዋጥኝ
አፈር ባፈር ሆነን ወይም ወጥ ወጥ ሸተን
እንመለሳለን የያዝነውን ይዘን
ያልሰራውም ሆነ ቀኑ ለሱ ያልሆነው
የሰራውም ይሁን ፍዳውን የበላው
ይጠራቀምና ሁሉም ከየፊናው
ቁርስ አይሉት ወይ ምሳ እራት ማይባለው
ብቻ ባንድ ጊዜ ሁሉን ሚያጠቃለው
በዛ ያለ ዳቦ ይቆራረስና
ጎድጎድ ያለ ሳህን ከሱቅ ይዋስና
በላይ የፉል መረቅ ይደፋበትና
ጨውም ሆነ ዘይት ጠብ ይደረግና
ስሙ ማይታወቅ
ግማሹ እረጠብ ሌላው ያለ ደረቅ
ለሰው ነው ለእንስሳ ተብሎ ያልታወቀ
በአፍ ማይነገር ለልብ የጨነቀ


ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ


በጣም ትዝ ያለኝ ነገር ስላለ ማለት ስለምግቡ መጻፍ አልቻልኩም ከምር ነው ግን

ሽቁል ማለት በአረብኛ {ስራ ማለት ነው}

ይቀጥላል:-
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

ስደተኛው:በአፍሪቃ::

Postby ARERU » Sat Oct 29, 2005 2:48 pm

ቁጥር 12 ከቁጥር 11 የቀጠለ:-

ምግቡ:-

ቀለሙ አይታወቅ ቡና አይነት ግራጫ
ወየም አረንጓዴ ነጭ ነው ወይ ቢጫ
ሳይንቲስት ያልጻፈው ቫይታሚን ኤቢሲ ያተመረቀለት
ለጉልበት እንደሆን ወይም ለጤንነት ታስቦ ለውበት
ያነ ይመጣና ከእነሳህኑ ጉብ ይደረግና
ያም ያም ሁሉም እጁን ገባ ያደርግና
በአንዳንድ ውርወራ የሳህኑ ውስጥ ታይቶ
ሁሉም ብድግ ይላል አንድ አንድ ሹት መትቶ
ከዛማ:-
አወይ ደስ ማለቱ
ወሬው በየፈርጁ ከዛማ ይደምቃል
ቀልዱ ቁም ነገሩ ሁሉም በየተራ ይነሳል
ይወድቃል
ሳቅና ጭዋታው አቤት ደስ ማለቱ
ፍቅር እያለበት ማን ይሆናል ከንቱ
የልጅነት ጊዜ ያበባው ጊዜአችን
የማይደገመው ያ እንቁ ወቅታችን
ከዜሮ ጀምሮ ከቃቃ ጭውታው
የእንቆቅልሹና የንካ ስላንትያው
ቦቻና እቴሜቴ ሰኞና ማክሰኞው
ገበጣና ብዩ
የገመድ ዝላዩ
ቦሊቦል እገር ኳስ እርግጫና ዋናው
ያ ሁሉ ተነገሮ ሁሉም በይተራው
ወድያው ይዘፈናል ትዝ አለኝ የጥንቱ
ያሳለፍነው ዘመን የቀረው በከንቱ
ጥላሁን ገሰሰ ሳይነሳ አያድር
የእሱ ዘፈኖች ልክ እንደሚያወፍር
እንደ ምሳ እራት አብረን እየበላን
ውስጣችን ሁል ጊዜ ደስታ ይሰጠናል
ይህ ሁሉ ተብሎ መለስ ይባልና ወደዘመናችን
ያም ያም ይናገራል የደረሰበትን
ሀገሬ ሀገሬ ባልኩ ምን አገባህ ብለው
እነሱ የገዝዋት የግላቸው አረገው
ከሁለት ሶስት ጊዜ እያሰሩ ፈትተው
እግሬን በጉማሬ ጀርባየን ተልትለው
ባልተወለደ አንጀት እንደ እንጀራ እናት
ዱላ አልበቃ ብሎ በርሀብ መቀጣት
በውሀ ቀጠነ በማይመስል ነገር
እነሱ አሳቢ ላገር ሚቆረቆር
እሚሰሩት ስህተት ሚናገሩት ውሸት
ሁሌ ሚጠብቁ እንዲንጨበጨብለት
አጥፍተሀል በግድ ላቅመ አዳም ደርሰሀል
ግባ ዱላ ቅመስ መታሰር ያንስሀል
አትብላ አትጠጣ የነሱስ ለቅል ነው
አተንፍስ ያሉትን ጊዜ አልፎ ይቁጠረው
በዚም በዛም ብለው ቅጥቅጥ አድርገውኝ
እሚሉትን ሲያጡ አስጠንቅቀው ፈቱኝ
ይላል ለላው ደግሞ የእነሱ እንድሆን
ነገሩን አውቄ ወገን እንዳሰቃይ ሀገር እንድበድል
አንዴ አናርኪስት ነህ
ሌላ ጊዜ ደግሞ አንተ ከቡርዣው ነህ
ወይም አቢወቱን ውስጥ ውስጥ ከሚበሉት
ካድርባዮች ጎራ አንተም አለህበት
መኖርን ከፈለግክ እኛን ምሰልና
ምትፈለገው ነገር ይሟላልህና
መኪናውም ቪላ ጥሩ ደሞዝ ኖሮህ
ተከብረህ ተፈርተህ አንቱ እየተባልህ
መኖር ትችላለህ አብዮታዊ ተብለህ
ይልቅ ተሎ ፍጠን ጊዜ እንዳያመልጥህ::

እምቢ አልስማማም ይቅርብኝ በውነት
ሆኖ አግኝቸዋለሁ ምላስችሁ ሁለት
ትናንት ለህዝብ ነን ስትሉ እንዳልነበር
ጉልበት ሲኖራችሁ ዛሬ እንዲህ ሲቀየር
ሆ ብሎ ተነስቶ አብሯቹሁ ተጉዞ
በጉያው ደብቆ አብልቶ አጠጠቶ ለናንተ አግዞ
ሞራል ገንዘብ ልጁን ሁሉን አበርክቶ
እናንተ እንዳትሞቱ ቀድሞ እሱ ሞቶ
ለውጥ ይመጣል ብሎ ለውጥ እየጠበቀ
ወጣት ሽማግሌው አይዟቹህ እያለ
ሸሁና ካህኑ ባንድ እየመረቀ
ለዚህ አድርሷችሁ ገና ሳቅ ሳይጀምር
ደስታውን ወስዳችሁ በምትኩ ችግር
ተቀመጥ ተነሳ እንደወፍ ላይ ብረር
ስትጠያይቁጥ የማይቻል ነገር
ሰላም በተኛበት ባድባሩ በቀየው
ና ውጣ ና ግባ ያን ልቀቅ ያን ያዘው
ለናንተ የሞተው ገና ስጋው ሳይፈርስ
ጉድጉዋድ እንደገና ከበላዩ ሲማስ
እሬሳ በሬሳ ስታጨናንቁት
ቦታ መቀበርያ ስታሳጡት መሬት
ሞራሉ ደንዝዞ አንገቱን ሲደፋ
ዝም ለምን አለ ተብሎ እንድጠፋ
አንዱን አስሮ መግረፍ
የቆጡን የባጡን የግድ ማስለፍለፍ
በፊት ያልነበረ ያልሆነውን ነገር
እኔ አርግዠ ወለድኩ ሚስቴ እንዳትቸገር
ታንክ ቀብሬለሁ አውሮፕላን ከቤት
አባቴ ይናገር አውጥቶ ይስጣችሁ ከተቀበረበት
እናቴ ትመስክር ዶማ የሰጠችኝ
እህቴ ትናገር አፈር ያዋጣችኝ
ወንድሜም ነበረ አብሮ ያጓተተኝ
ያክስቶቸ ልጆች ድንጋይም ያናሱኝ
ብሎ ይናግራል እሚባል ከለለ እማይባል ብሎ
ከዱላ እንዲላቀቅ በጣሙን ተቻኩሎ
ሴትዋን እንደንሰሳ ያም ያም ሲወጣባት
እንመርምር ተብሎ እስዋ የት ጎራ ናት
በጨለማ መብራት
ሰው በማያይበት
ሶስት አራት በተራ ሁሉም ሲገናኝዋት
እየተጉዋተቱ ሲቀረማመትዋት
ያ አልበቃ ብሎ በዱላ መነረት
የሞተች እንደሆን ስቃይ ሲበዛባት
እንደውሻ ጎትቶ ጉድጓድ ውስጥ መክተት
ይሄስ ለብቻው ነው ሰይጣናዊ እምነት::
እየዘረዘረ ተናግሮ ሳይጨርስ
የደከመው ገላ በዚያው ፍንድስ ፍንድስ
የነገውን ማለም ያው ነው እንደዛሬው
ምንም ማይቀየር አዲስ ተስፋ የለው
እንዲህ እንዲህ እያልን እየተንጠባጠብን
በድፍረት በእድል ወይም እየታሰርን
ቀስ ቀስ እያልን ሁላችን ተሟጠን
ካርቱም ዘልቀን ገባን::

ይቀጥላል:-
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

Postby ARERU » Thu Nov 10, 2005 4:23 pm

ሰሞኑን እኮ የሀገሬ ሁኔታ አንገብግቦኝ ምንም ሳልጽፍ ቀረሁ ታላቅ ይቅርታ ስምትከታተሉ ለነበር ወገኖች::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

ስደተኛው በአስሪቃ::

Postby ARERU » Thu Nov 10, 2005 7:49 pm

ቁጥር 13 ከቁጥር 12 የቀጠለ:-

ካርቱም:-

ያ ትልቅ ከተማ የተወራለቱ
ሁለቱ አባዮች ሚገናኙበቱ
ገና ትምህርት ቤት ጆግራፊ ስንማር
እንዲህ እንዲህ ተብሎ ሲነገር
ካርቱምን ለማየት እናፍቀው ነበር
አያስገርምም ወይ ዛሬ ባንድ ጊዜ ፍላጎት ሲቀየር
ሙቀቱ ያለቅጥ ጽሀይ ከነዘርዋ የሰፈረችበት
ተፈጥሮ ባንድ ላይ ሁሉም የጋለበት
አቡዋራው እንደ ጉም ሚተራመስበት
ካልታጠቡ መዋል የማይቻልበት
በእየደቂቃው ውሀ ሚጠማበት
ሰው ሰይንቀሳቀስ ተሎ ሚደክምበት
እየታጠቡ ላብ ጅረት የሆነበት
እቤት ውስጥ ማደር የማይቻልበት
ይህ ሁሉ ተዳምሮ ሰው የሚኖርበት
እንድምንም ብየ ካርቱምን አየሁት
ስለ አመጣጤ ባይወራ ይቅር
እኔማ አልችልም ያገዘኝ አግዚአብሄር
ያመጡኝ ሹፌርች አምላክ ያግዛቸው
አንድ ቀን መኪና ስላጠብኩላቸው
ፍላጎትህ ምን ነው ብለው ጠይቀውኝ
ወደ ካርቱም መሄድ ብየ ስለአልኩኝ
ያለ ይለፍ ወረቀት ያለምንም ገንዘብ
እኔን ውስጥ አቃ በላይ ደረብ
አድርገው አመጡኝ እግዚአብሄር ይስጣቸው
ጊዜ ሰጥቶኝ እኔም እስከማግዛቸው
ካርቱም ገባሁና ዴም እሚባል ሰፈር
አንድ ሀበሻ ባገኝ ብየ ስደናበር
መጠየቅ አቅቶኝ ግራ ገብቶኝ ውየ
ሆን ጭንቅ ብሎኝ ተለይቶ ቋንቋየ
ደከመኝ አረፍ አልኩ ጥላ ስር ፈልጌ
ቀኑም እየመሸ እኔም በጣም ደክሞኝ
እርሀብ ጥማቱ ተቀላቅለውብኝ
በጣም ጭንቅ ብሎኝ የማደርገው ጠፍቶኝ
ሚያልፈው ሚያገድመው ሸርመም አርጎ እያየኝ
ካሁን ካሁን አንዱ የት መጣህ የሚለኝ
እያንከለከለ እስር ቤት ሚወስደኝ
ያለጠያቂ እዛ የሚያበሰብሰኝ
ሳልተኛ እንዲሁ ቅዥት ቅዠት ሲለኝ
ሰው እየቀነሰ ውሻው ውር ውር ማለቱን ጀመረ
ተስፋየም ከውስጤ ክንፍ አርጎ በረረ
የሰው ያለህ ተበሎ የማይጮህበት
ቋንቋው ማይሰማ ግራ በሆነበት
ምን ሆነሀል ቢባል ምን ሆንኩ ለማለት
ቃላት ተፈልገው በማይገኙበት
ወዳክስቴ ልሂድ ወይ ወዳጎቴ ቤት
ወይም ወደዘመድ በማይባልበት
ምድረ በዳ ቀረሁ
ሰው ሳለ ሰው አጣሁ
ቤት ሞልቶ ማደርያ ለጎኔ እንኩዋን ጀንዴ
አፈር ላይ ተጋደምኩ ወድጀ በግዴ
የሌሊቱ አጋማሽ እየተቃረበ
ሰውነቴ ፍርሀት እየተደረበ
ሀሞቴ ተሟጦ ልቤ ተሰለበ
ለሊቱ እንዴት ይንጋ መቶ አመት መሰለኝ
ስአቱ አልሄድ አለ ቆሞ እየጠበቀኝ
አምላኬን እባክህ ብየ ተማጸንኩት
ሌሊቱ ይንጋና ሰው አሳየኝ አልኩት
እንዲህ እንዲህ እያልኩ ይነጋ አይነጋ
አንድ መአት ፈረስ መጣ እየተንጋጋ


ይቀጥላል:-
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

Postby ARERU » Wed Jan 25, 2006 5:31 pm

እንደገና ስደተኛው በአፍሪካ ባልታወቀ ምክኒያት ለብዙ ጊዜ ተቁዋርጦ የነበረው ታሪካዊ ግጥም ሊቀጥል ነው::
አረሩ::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests