እስኪ ተጠየቁ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

እስኪ ተጠየቁ

Postby ማርስ » Thu Oct 20, 2005 11:33 am

እስኪ ልጠይቃቹ
የምታውቁት መልስ ካላቹ
የዚህ አለም ንሮ ሚስጢር የገባቹ
ንገሩኝ እናንተየ አንድ በሉኝና
አካፍሉኝ ለኔም በሉኝ መላው ይሄውና
I dreamed of some one like you
you see too marvelous for it to be true.
-
-
Image
ማርስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 44
Joined: Sat Jan 03, 2004 12:54 am

ሚስጢሩ...ቅቅ

Postby ዋኖስ » Thu Oct 20, 2005 4:14 pm

:roll:

የዚኅ ዓለም ኑሮ ሚስጢሩ ቀመሩ

<U>መብተክተክ ማሰቡን</U> መተዉ ነው ባጪሩ

ሌላ ምንም የለዉ እንደ ገባኝ ድረስ

<U>ባለን ተደስተን</U> ከተዉነ ማግበስበስ::

~~~~~~ዋኖስ~~~~

ቅቅ አለሽ ለመሆኑ በኃገር?
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ትትና » Mon Oct 24, 2005 8:18 am

እኔም እስማማለሁ በዋኖስ ቀመር
እግዜር የሰጠንን አክብሮ መኖር
ሺ አመት ላይኖር መብከንከን ማሰብ
አንዱን ሳይጨብጡት ላንዱ መስገብገብ

የከንቱ ከንቱ ነው እንዳለው ሀዋሪያ
ንፋስንም መከተል ላይሞላ ከጉያ
መሮጥ መብከንከኑን ላይጨበጥ አንዱ
ፍላጎት ሳይሞላ ዘመን መተካቱ

አስቢበት እቴ ማመስገን ለሁሉ
ጨምሮ ይሰጣል እንዳለ በቃሉ
ሁሉን ለሱ ትቶ ደስታንና ሀዘንን
መጠበቅ ይሻላል የማይቀረውን (ሞት)


አቤት ብቻ አዋቂዎቹ ግጥሜን አይተው እዚህ ቤት አንገባም እንዳይሉ!!

አክባሪያችሁ
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

ትህትና!

Postby ዋኖስ » Mon Oct 24, 2005 4:38 pm

ለትኅትና:-

:roll: ትኅትናእንኳን ግጥም ፅፈሽ መልዕክት ጨምረሽ

<U>ግብርን</U> አስተማሪ ሥያሜ እያለሽ

ምነዉ ምን? አስፈራሽ በግጥሙ ትዬባ

ጫሪዉ እንደ ዶሮ እንታጠብ በዕምባ

እኔ ደስ ብሎኛል አንኳር ይዘት ዉስጡ

ሥምሽን ወዳጆች ታዳሚሽ ሲመጡ

ፃፊላቸዉ በእዉነት ከእዉነታው ከጪብጡ::============ዋኖስ=============
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ትትና » Wed Oct 26, 2005 7:49 am

አይ ዋኖስ ወንድሜ!

አይ ዋኖስ ወንድሜ ቢቸግርህ እንጂ
መች አውቄው ኖሮ ስዘላብድ እንጂ :D
ግጥሙንማ ነበር ብተወው ለናንተ
መልካም ሆኖ ቢኖር እንዳለ በናንተ :D
መች ይሆን ነበር እንዳይሆን እንዳይሆን
በንደኔ አይነቷ ባይደፈር ጥንቱን
ሲባል ሰምቻለሁ በዘይቤ ፊቱን
አላዋቂ ሳሚ.... ቢያደርግ አስቀያሚ
ጥፋተኛው ማነው? ዝም ብሎ ተሳሚ
ቆማጣን ካላሉት ነህ ብለው ቆማጣ
ገብቶ ይፈተፍታል ሳይፈራ ባአይናውጣ
እንደኔ አይነቱ የግጥም ቀበኛ
ቶሎ ቦታ ቢለቅ የመረጣል ባአንደኛ

አሁን በህውነት! በል እስኪ አልሳክብኝም?

አክባሪህ
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

አካፋን አካፋ

Postby ወለላዬ » Wed Oct 26, 2005 11:07 am

አካፋን አካፋ

ስሚኝ ትህትና ላጫውትሽ ቁም ነገር
ስለድርሰት ስራ ትንሽ በመቆንጠር
ባሳብሽ ያለውን በአይምሮሽ ጓዳ
መጻፍ ትችያለሽ ማንንም ካልጎዳ
ግለጪው አስፍሪው ንደፊው ቃል በቃል
ችሎታሽ ታፍኖ ለምን ይደበቃል
የግጥሙም ሁኔታ እያደር ይጠራል
ይልቅ ይሄ ያልሻው ቆማጣን ቆማጣ
ሰምቻለሁ ብዙ እንዳመጣ ጣጣ
ቢተካው ተብሎ ቃሉ ተሻሽሏል
አካፋን አካፋ ካላሉት ተብሏል
ወለላዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 403
Joined: Wed Jan 26, 2005 11:20 am
Location: united states

...

Postby ዋኖስ » Thu Oct 27, 2005 4:58 am

ቅቅቅ


ከዚህ በላይ ግጥም ከየት ከአዩ ፀኃፍት

ደረደርሽዉ እኮ አስነካሽዉ በእዉነት::

ጋሼ ወለላዬ እሱ እንደነገረሽ

እኔም በጥቂቱ ልጨምርሽ ትንሽ

ስትወጪ ስትገቢ በሌጣ ቀረቀት

እየጫርሽ አኑሪ ሲመጡ በድንገት::

ከዚያም ሰዐት ወስደሽ አቀናጂዉና

ተመልከችው እስኪ ጪብጡን በጥሞና::

ፍሰቱን... ዉበቱን... ብሎም ጥንካሬ

ቃላት አመራረጥ ትርጉምና ፍሬ

ኃሳብ አሳሳሉን የዉስጥሽ ስሜትን

መልዕክቱ መድፋቱን አንኳር ቁም ነገሩን

ያኔ ፈትሺበት ራስሽን ዕይና እንደ ፊት መስታዉት

በ ቀለሙ-ቅያስ በሌጣው ወረቀት::

እንዲህ እንዲህ ብለሽ "ቋት-ብዕር"ሽ ሲሞላ

ጥበብን- በቀለም አዋኅደሽ መርጠሽ አምስለሽ አለላ

<U>ትኅትና</U>ን አሳይን አንቺ የማር-ወለላ::

======ዋኖስ ከደብረ-ዳሞት=====
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ትትና » Fri Oct 28, 2005 10:14 am

ወገኖቼ ሁሉ

ወገኖቼ ሁሉ አሉኝ በቺ በጣም
ሲሞከር ነው ከቶ የሚቻለው መቆም
እንግዲህ ካሉማ ከመጣ ከነሱ
እኔም ተቀበልኩኝ ምክሩን እንደውርሱ

ባይሆን ይሉኝ ነበር ይቅር እንዳይሆን
ሀሳቤን ለመግለጽ የተናገርኩትን
በዋናነት ይዘው ወለላውን
አጥበቀው ደገፉኝ ወገናቸውን

እኔም ቃሌን ሰጠሁ የመጨረሻውን
ሁለቴ ላልደግም በፊት ያልኩትን
ቆማጣን ቆማጣ 'ተባለው ጉዳይ
ማምጣቱን ባላውቅም እንዲህ ያለ ግዳይ

ወረቀቱም ይህው ብዕሩም እንዳለ
ተዘጋጅቻለሁ የሚወርድ እንዳለ
ላሰፍረው አስቤ እንዳወራወሩ
ተዘጋጅቻለሁ ዳሞት እንደምክሩ

አክባሪያችሁ
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

ቅቅቅ

Postby ዋኖስ » Fri Oct 28, 2005 2:09 pm

:roll:

ከዚህ በላይ ግጥም መልዕክቱ ሚያኮራ

ማን ይወዳደራል ቲቲ ከ አንች ጋራ!!

የሚያስብል አይደለ! አጀብ ነዉ ግሩም ነው::

እሄንንስ ታዲያ የግጥም አባትሽ ክቡር ወሌ ባዬዉ::

ምንም እርግጠኛ ባልሆን ለሽልማት

ሲገዙ አይቻለሁ አንድ ነገር በኩራት

ሊሰጡሽ መሰለኝ ግጥም ለማበርታት::

ይህ ነገር ሚስጢር ነዉ ዝም ብለሽ እያቸዉ

ከደጂሽ ሲመጡ ተርፏቸዋልና በረከት ከእጃቸዉ

የፃፍሽዉን ግጥም ለእርሳቸዉ ስጫቸው

እንዲያከናንቡሽ መክሊት ከኪሳቸዉ::

=====ዋኖስ ====
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

ሰሞኑን ልመለስ

Postby ወለላዬ » Tue Nov 01, 2005 10:40 am

ሰሞኑን ልመለስ

ምንም ባይኖረኝም የማከናንባት
ሁኔታው ባይፈቅድም ደግሼ ለመጥራት
ያለኝን እንድሰጥ ከተጠየኩማ
ፍጹም ቅር ሳይለኝ ምንም ሳላቅማማ
ፈልጌ አስፈልጌ ወጥቼ ከተማ
አመጣላታለሁ ለሷ የሚስማማ
እንደተረዳሁት ጽሁፏን መርምሬ
እንዳገላበጥኩት ከበፊት ጀምሬ
ውይይት በመክፈት ወይንም በመሳተፍ
ያሳብ ልውውጡን ቃሉን ሳታዛንፍ
እዛም ቤት እዛም ቤት ሳትል ጥልቅ ትልቅ
የምትታውቅ ነች ቁምነገር በማፍለቅ
የድርሰት ለግጥም እንዳላትም ፍቅር
ስራዋን ስላየሁ አልሻም ምስክር
የስም አወጣጡ እራሱ ትትና
ከሷ ጋር ተስማምቶ ቁጭ ብሏልና
ምን እንደሚሻላት እስቲ ላስብና
ሰሞኑን ልመለስ እዚሁ እንደገና
ወለላዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 403
Joined: Wed Jan 26, 2005 11:20 am
Location: united states


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest