የወንዜ ልጅ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የወንዜ ልጅ

Postby ኦኑፈያሮ » Mon Nov 28, 2005 11:13 am

****በዚይዝ በጨለማ ወያኔ ደለማ******

አልገናኝ ሲለው ነቢብ ከገቢሩ

እየተማታበት ውሉና መስመሩ

ያዘመረው ሁሉ እያሻሻረበት

የከመረው ሁሉ እየፈረሰበት

ጥርት ያለው ውሀ አንፎርሻ ጭቃ

ጥልሉ በጥሀ ጉሮሮ እሚያነቃ

እንዲህ እየሆነ እንዲህ ሲያስቸግረው

ይህ የወንዜ ልጅ ይህ ያገሬ ሰው

ከእህህ ወዲያ ሆድ ይፍጀው እንጅ ነው

ከዚህ የተሻለ የሚናገርበት ምን ቁዋንቁዋ ነበረው

****************ምንም***************
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Sat Dec 03, 2005 9:25 am

ሠው ሁሉ ሰልጥኖ ስልጣኔ ሲረክስ

ሌላ አለም ፈልጎ በአየር ላይ ሲፈስ

ደስታ አይደለም እንዴ ለታሪክ መቅረቱ

አንደኛ ደንቆሮ ሆኖ መገኘቱ

ከፊት የቀደመ የፊት አንደኛ ነው

ከሁዋላም የቀረ የሁዋላ አንደኛ ነው

ጊዜ እና አቅጣጫውን መርጦ እንዳደረገው

ማን ያውቃል ምናልባት አንደኛ ሆነን

ያገኙን ይሆናል እውቀት ሳይደፍረን
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Mon Dec 05, 2005 7:36 am

አንዲት ጦጣ ያረጀች
አይኑዋ ታሞ ታወከች

ከሰዎችም ሰምታ ወሬ
መፍትሄ አለው ብላ አጅሬ

ግማሽ ደርዘን መነጸር
ገዝታ ሄደች ወደ ዱር

በጅራትዋም ሰካቻቸው
በምላስዋም ላሰቻቸው
አያሳዩም ምን ነካቸው

ሰው ሁሉ ያለውን ያመነ
እርሱ እንጅ ነው የታለለ

ብላ ጦጢት በግና ጡዛ
ወደል ድንጋይ በእጅዋ ይዛ

ያንን ሁሉ መነጸር
ሆቤ አለችው በድምር
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests