by ቃኘው » Wed Dec 07, 2005 4:40 pm
በእርግጥ ነው ህወኃት ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያዊነት አመለካከት ቢኖረው ነበር ወደ ኤርትራ መሄዳቸው ይወገዛል::
ፈረንጅ አገር ተሰዶ በመንፈስ ስቃይ ተሰቃይቶ ከመንቀሳቀስ ይልቅ ራሱ ወንድም እህት ከሆኑት ህዝቦች ዘንድና የደም ጽስርና ወንድም አማቺነትን የሚሰማበት አካባቢ ለጊዜው መሆኑም ያስደንቃቸዋል እንጂ አያስወቅሳቸውም:: ቢያንስ አማቺ አበልጅና የሃይማኖት ዕምነቶቻቺን አመላቺንና ፍላጎታቺን ቋንቋቺን ታሪካቺንና ባሕላቺን ከሚመሳሰልህ ህዝብ ጋር መቆየት ደግሞ ነውር አያስመስልም:: እንዲያውም ለወደፊቱ ቀጣይነት ላለው ግንኙነቶች ድጋፍ ይሰጠዋል:: በክፉ ግዜ ኢትዮጵያን ስለረዷት አብሮ መኖርና ብሎም መዋኃዳቺን የማይቀር መሆኑን ጊዜው ሲደርስ አዲሱ ትውልድ የሚፈርደው ጉዳይ ነውና::
አሁን ማሰብ ያለብን:: ህዝባቺንን በሔሊኮፕተር ጋን ሽፕ መደብደብ የለብንም ብለው ያሉትማ ወደ ጂቡቲ ሄደው ጉሌ አሳልፎ ለህወኃት ሰጣቸው:: እነኝህም ህዝባቺንን ለመጨፍጨፍ አይደለም ለኢትዮጵያ ቃል የገባንላት በሚል ተቃውሟቸውን በሰከነ ብልኃት ተወጡ እንጂ ሊወቀሱ አይገባም::
አሁንም ለወደፊቱ የበለጠ ይሰራሉ ተብሎ ይታመናል:: ወጣቶች ናቸው 8 ፓይለት እያንዳንዱ ቁምነገር ይሰራል እኮ ያንን መርሳት የለብንም::
ቤላ ሩስ የነበሩት እንዲሁ 8ቶቹ ወደዚያው ወደ ኤርትራ ሄደው በተለያዩ ወታደራዊ ተግባሮችን እንዲመለከቱና ቢለማመዱ አይከፋም:: ጀግና በየትም ቦታ አላት ኢትዮጵያ ነገር ግን አንዱ ሲራመድ ሌላው እየጎተተና የራሱንና የቤተሰቦቹን ጥቅምና ፍላጎት ከሥልጣኗ ጋራ እያገናኘ በማስቸገሩ ነው አገራችን እስከዛሬ ጀግና ዓልባ ልትሆን የቻለቺው::
አሁን ግን እያበቃለት ይመስላል:: ልክ ወያኔው ሕወኃቱ የሄደባትን መንገድ ሌላው ተጻራሪው የማይሄድበት ምክንያት የለም:: አገራቺን ጦርነት ሳይሆን ሠላምና ዴሞክራሲ ብታራምድ የበለጠ ህዝቦቿ የሚጠይቋትን ልታሟላ ትቺላለቺ በሚል ነበረ እስከዛሬ ት ዕግስቱ:: ነገር ግን ወያኔ ህወኃትና መለሰ እነዚህ አንድም ሶስትም ጋንጩሮች የህዝባዊ ትግስት ሊዋጥላቸው ባለመቻሉ ወደሌላ ምክንያቶች እየገቡ ስላስቸገሩ ህዝብ ሊያድምባቸው ሊያገላቸው ይገባል::
ድምጻቸውም የገድል ማሚቶ ይሆናል:: የሚደርስላቸው ሊኖር አይቺልም::
ጀግናው? ያሰደነቀኝ ቢኖር አንተ ራስህን ጀግና ብለህ ሰይመህ በመጨረሻ አገራቺን ጀግና አጣቺ ስትል ደነቀኝ? ለዚያም ቢሆን ቀጥለው የጻፉልህ ወገን መልሰውታልና ልብ በል አይዞህ ጀግኖች እየመጡልህ ነው::
"ውድቀት ለወያኔ" ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ቃኘው
ከ(ሰሐሊን)
tank you