ውድ ዲጎኔ ብዙ ጊዜ የምጸጣቸውን አስተያየቶች አነባለሁ በዕውነት በጌታ ላይ ባለህም እምነትና መመካት አደንቅሀለሁ
ጌታ አሁንም አብዝቶ ይባርክህ አንድ ነገር ግን ልል ዕወዳለሁ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች አንተ የምሰጣቸውን አስተያየቶች ከዕምነት ግሩፕ ጋር እያያያዙ የጠጣመመ ወይም ወደ አንድነት የማያመጣ አስተያየት ሲሰጡ አያለሁ
ይህ መልካም አይደለም አንተን ማለቴ አይደለም ግን አንተን ለማለት የምወደው ነገር ቢኖር እንደዚህ አይነት አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ሲነሱ መልስ ከመስጠት ብትቆጠብ መልካም ነው ሰዎች በዚህ ዘመን የጌታን ቃል እራሳቸው በሚፈልጉትመንገድ እንጂቃሉ እንደሚለው አይወስዱትምና
ዋናም ደግሞ የዕምነት ግንብ ሰርቶ እኔ ኦርቶዶክስ ስለሆንኩ ወይም ካቶሊክ ወይም ደግሞ ፕሮቴስታንት ስለሆንኩ በማለት ሳይሆን መዳን የሚገኘው በአንድ ልጁበክርስቶስ ኢየሱስ እንደሆነ ማመኑ ስለሆነ የየትኛው ድርጅት አባል መሆን እንደማያድን በማወቅ በዚህ መልኩ የሚመጡብህን ባታስተናግድ መልካም ነው
አቡነ ተጋዳላይ ጳውሎስንም ማንም ሰው የሚያወግዘው በእምነት አባትነቱ የሚፈለግበትን ባለማድረጉና እንዲያውም ከፋሽስቶች ስለወገነ ይህ ሁሉ ህዝብ ሲጨፈጨፍ በዝምታ በማለፉ እንደ ግለሰብ እንጂ በኦርቶዶክስነቱ አይደለም ስለዚህ የካቶሊኩ ድርጅት በዚህ በድፍረት ወጥተው መናገራቸው ይበሉ የሚያሰኛቸው ነው አሁንም በግልጽ እንዲታወቅ የምፈልገው የምተቸው አባ ተጋዳላይ ጳውሎስንና የርሱን ተከታዮች እንጂ ኦርቶዶክስን አይደለም
ወንድም ዲጎኔ በዕምነት ድርጅቶች መካከል ባለ ልዩነት ክርክር ሊያነሱብህ የሚሹትን ወደ እግዚአብሔር ቃል (መጽሀፍ ቅዱስ) ምራቸው እንጂ መልስ አትስጣቸው
አክባሪህ አቡዬ
በቸር እንሰንብት