Mo's coffee house!!!

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Re: Mo's Coffee House(MCH)

Postby ጌታ » Thu Dec 29, 2005 1:52 am

Monica**** wrote:
አንድ ነገር የምትጠየቁት እዚህ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ስትገቡ አንድ የሚያስቅ ነገር የደረስባችሁን ወይም የምታውቁት ስው ላይ የደረስውን እንድታጫውቱን ስጠይቅ በደስታ ነው::


እኔው ላይ የደረሰውን ላውጋሽ........................

አሜሪካ በመጣሁ በተወሰኑ ቀናት ውስጥ ነው:: ጊዜው ሰመር እንደመሆኑ እጅጌ ጉርድ ቲሸርቴን አድርጌ ለወክ ወጣሁ:: ካረፍኩበት አፓርትመንት ብዙም ሳልርቅ አንዲት ጥቁር አሜሪካዊት "Do you have time?" አለችኝ::

እኔ ደግሞ ይህቺ ጀሆቫ ዊትነስ ልታደርቀኝ ነው አልኩና "አአይ እቸኩላለሁ" አልኳት:: በመበሳጨትና ግራ በመጋባት "ምንድነው የምታወራው?" አለችኝ:: "እ.... የሆነ ቦታ ቶሎ መድረስ አለብኝ" ብላት

"I'm just asking you what time it is' ብላ ድሮ መምህር አብራራው ሰዓት ሲጠየቅ ኋት ታይም ኢዚት ነው ያሉኝ እዚህ እንደማይሰራ ገባኝ::

ከላይ አለባበሴን የገለጽኩት ያለምክንያት አይደለም:: ሰዓት ማድረጌን አስቀድማ ማየቷን ለማሳየት ያህል ነው::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3117
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ባብ » Thu Dec 29, 2005 3:25 am

ሰላም ሞኒካዬ.......የጌታን ገጠመኝ ሳነብ በራሴ ላይ የደረሰውን ተመሳሳይ አጋጣሚ አስታወሰኝ ...ጊዜው ትንሽ ቆየት ብሏል ለአሜሪካ እንግዳ ነበርኩ...አስታውሳለሁ የመጀመርያ ስራዬን የጀመርኩ ጊዜ ኢንተርቪው ያደረገችኝ ሴት ነበረች...ስራውን ማግኘቴን ካበሰረችኝ በህዋላ ስለ ካምፓኒው ዩኒፎርም ስትነግረኝ you must have to wear a black pant, no jeans please ስትለኝ I was like ይቺን ይወዳል የሰውዬው ልጅ ! እንዴት እንዴት ነው ነገሩ ? ሙታንታዬ ደግሞ ነጭ ይሁን ጥቁር ምን ይሰራላታል.......የተቀጠርኩት ለዋና ውድድር ቢሆን እሺ ! ዋናተኞቹን ለመለየት ነው ይባላል....እንደገረመኝ እንደተመራመርኩ ቤት ደርሼ ትራውዘርስ ፓንት አንደርዊር....የሚባሉትን ነገሮች አንድነትና ልዩነት ለማወቅ በቃሁ እልሻለሁ.....

ስለ time ጉዳይ ደግሞ ሌላ ጊዜ አወጋሻለሁ ዋርካዎች ከፈቀዱልኝ ::ከኮምፒተሬ ወደ ዋርካ እንድገባ አልፈቀዱልኝም በማላውቀው ምክንያት IP ዬን አግደውታል መሰለኝ በጓደኛዬ ኮምፒዩተር ነው የምጠቀመው ከስራ ቦታዬም ሳይበርን እንደልቤ መጠቀም እችላለሁ ሎግ ኢን ማድረግም እችላለሁ....ከቤቴ ግን ምንም ማድረግ አልችልም........አንዳንዴ ሲመቸኝ በጓደኛዬ ወይም በስራ ቦታዬ ፒሲ እየተጠቀምኩ ብቅ እያልኩ አወራሻለሁ

የሚወድሽ ወንድምሽ
ባብ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 62
Joined: Wed Mar 23, 2005 11:27 am
Location: united states

ሩሜት

Postby ወንድም » Thu Dec 29, 2005 5:34 am

አንዴ ናይት ክልብ ገባውልሽና ሆነ ብዬ ዛሬ ከኔጋ የምታድር
ሴት ስፈልግ በመጨረሻ በለስ ቀናኝና አንድዋን ንጭ አገኝው
ልሽ ቤትዋ እንድንሄድ ተስማምተን ቤትዋ ስገባ ያ ጉረኛ ግዋ
ደኛዬ ቤቱ በጣም ደስ የሚል አፓርትመንት ከከተማ ወጣ ያለ
seburb ፔንት ሀውስ ይሽበርቀ እንደሆነ ይነግረኛል ግን አል
ፎ አልፎ እኔ ጋር ያድራል ቤትህን አሳየኝ ብለው ዛረ ነገ እ
ያለ ይፎግረኛል አጅሬው ሶፋው ላይ ትኝቶ ያንኮራፋል ሳየው ደነገጥኩ እሄ ማነው ብላት እሱማ ሩሜት (ደባል) ነው አልችኝ ታውቀዋልህ አለችኝ አዎ አልኩዋት በሚቀት
ለው ቀን እዛ ክልብ ሄደህ ነበር እንዴ አለኝ ኖ አልሄድኩም
ብለው እዚ ከተማ ወረኞች ሞልተዋል በሬ ወለደ ብልው
ያወራሉ አለኝ ገና ለገና ይወራብኛል ብሎ እኔ ደሞ የሰው
ቤት ስፋ ላይ እንደምታድር እንዳያስወሩብህ ነው ብለው
እንባው መጥቶ እብክህን እችን እለፈኝ ሌላስው እንዳይሰ
ማብኝ ብሎ እግሬ ስር ሊወድቅም ፈለገ አይዞህ ሚስጥርህ
ሚስጥሬ ነው አልኩት ከዛን ቀን ብወሀላ ጉራውን ተወው
ያ የኔ አጋጣሚ ነው ሌላ ጊዜ ሌላ ጨምራልው ቻው በይ
የኔ ቆንጆ ማለትም ሞኒካ ብቻ
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ሜዳ » Thu Dec 29, 2005 8:48 am

ሰላም ለዚህ ቤት ሞኒካ ቢና ቤትሽ ይመቻል በኦርደር ነው
ወይስ ዝም ተብሎ ይገባል እኔግን የመጣው ይምጣ ዘው

የጌታን ገጠመኝ ሳነብ እኔም አንድ ትዝ አለችኝ ታድያ እኔ ቡና የተቆላውን ካላሸተትኩ በማንከሽከሻ አልወድም ካስጨመረም ሂስሳብ ደብተሩላይ ይጻፍ

ይኽውልሽ ለረፍት ሀገርቤት ሄጄ ነው እዚህ ሰመር ላይ የማደርጋት ቲሸርት አድርጌ ነው (ቲሸርትዋ ጉርድ ናት ከትከሻዋ ጀምሮ እጅጌ የላትም) እስዋን አድርጌ ከጭፈራ በለሊት ነው ከታናሽወንዴሜና ከአንድ ጉዋደኛዬ ጋር ወዴበት ስንመለስ የሰፈራችን ልጆች በዛ ሰአት ምን እንደሚያደርጉ አላቅም ሰብሰብ ብለው ያወራሉ ይሳሳቃሉ እኛም ስናልፍ በመኪና ሰላም ብለን አለፍን ወንድሜ ወርጄ ሰላም ልበል ብሎ ወረደና እየሳቀ ተመለሰ ምነው ስንለው,
እኔን መሆኑ ነው ብራዘርሽ ደሞ በዚህ ሰአት ጉርድ ምታደርገው መጋኛላይ ነው እንዴ ምትነፋፋው ከመምጣትሽ ብርድ እንዳይዝናናብሽ ደርብ በለው ብለው መልክት ላኩ እልሻለሁ

በይ ሰላም ሁኚ
ሜዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 47
Joined: Sun Feb 27, 2005 12:28 am
Location: united states

Postby Monica**** » Thu Dec 29, 2005 9:27 am

እንዴት አደራችችችችች ሁሁሁሁ
የቡና ማህበርተኞቼ ሁሉ!
ማነሽ?..........ዘቢደሩ? እረ ቡናውን ቶሎ ቶሎ በይ ጠዋት ተነስተሽ ስትድፈነፈኝ ቡናውን እንክዋን ሳትቆይ ትጠብቂኛለሽ ቤቴክሲያን ስሜ ስመጣ?????
ምን የዞረባት ናት ባካችሁ........ደሞ ውሀ እያንጠፈጠፍሽ እቃ አታቅርቢ........ስራውን የማትፈልጊው ከሆነ መሄድ ትችያለሽ እኮ.........ስንት ስው ልጄ ስራ የሚፈልግ አለ! ወቸ ጉድ!!
( እናቴ የቤታችንን ስራተኞች ከምር እንደዚህ ነበር የምትናገራችው.......እረ ተይ ስንላት እናንተ ናችሁ አጉል ውጭ ትምህርት የልብ ልብ የምትስጧቸው ስትል.........አቤት የስው መብት ብሎ ከማዘን ሌላ ምን እላለሁ........)
ዘቢደሩ አይዞሽ እኔ ሻሼ እንደእናቴ ሀይለኛ አይደለሁም የማታ ተምሬ 4ኛ ክፍል ደርሻለሁ የተማርኩ ነኝ!! :wink: :wink:
እስኪ ለእንግዶቼ ቡናውን ቶሎ ቶሎ ብዬ ላቅርበውና እራሴ ከዛ እየካደምኩ ላጫውታችሁ!!! የዘንድሮ ስራተኞች እኮ በወር 100 ብር መቀለጃ ነው.......ድሮ የመጀመሪያ ባለቤቴ( የጩኒ አባት) 50አለቃ ደሞዙ ነበር የዛሬን አያድርገውና! አሁንማ ብር ወረቀት ሆነ እኮ!!!
በይ ከሰሉን እያራገብሽ :roll: :roll: :roll:
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby Monica**** » Thu Dec 29, 2005 9:55 am

ጉዱ ካሳ
ታጠቅ ብሎ ፈረስ ካሳ ብሎ ስም
አርብ አረብ ይሽበራል እየሩሳሌም
እንደው ትርጉሙ ምን ይሆን??????
እንክዋን ደህና መጣህልኝ የጥንቱ!!! የውልህ የስው ልጅ ጥሮ ከስራ እንክዋን ሞ ካፌ ሽራተንም የኛ ይሆናል :wink: :wink: :wink:( አባባ አላሙዲን እንዳይስሙኝ ደሞ)!!!
እስኪ ይልመድብህ ያገር ልጅ :wink:


**************************
4get.this
አንተም እንደማልጨክንብህ ስላወቅክ አይደል ፍቃድ የጠየቅከኝ :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: እስኪ አንድ ገጠመኝ ያንተም ባይሆን ጣል አድርግ ከዛ ጌታ ሽምግልና ሳይገባ ታረቅን ማለት ነው :lol: :lol: :lol:


*************************
ጌታ
የኔ ቆንጆ ምነው ስሞኑን እንደዚህ ጠፋህ??? አገራችሁ እንክዋን ተርኪ የምትበሉት ለ Thanksgiven መስሎኝ ነበር.....እሱን ስትበላ ከርመህ እንደሆን ብዬ ነው! :lol: :lol:

ጌታ ጥሩ ጨዋታ አምጥተሀል የቁዋንቁዋ ነገር......እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም እንደዛ አይነት ነገር አጋጥሞናልና ለመስማት ዝግጁ ነኝ እኔም ትዝ ሲለኝ እመለስበታለሁ!
የደብዚዬ ጠጅ ለአርብና ለቅዳመ ማታ ይበቃሀል! ቀን ቀን የሻሼ ካፌ ከአገር በሀል እስከ ዘመናዊ የቡና አፈላል ያለን ነንና አትጥፋ!
በጥያቄህ መስረት ቢጫ ቀለም አጥፍቻለሁ! ያው በሆነ ባልሆነው የኢትዮጵያን ባንዲራ የማይበት ሰበብ መፍጠሬ ነበር....ለካ የሽማግሌዎቹንና የአሮጊቶቹን( እኔንም ጨምሮ) እያጠናበርክዋችው ኖሯል? :lol: :lol: :lol:
በል ይልመድብህ
የምትወድህ እህትህ


*************************

ባብ የኔ ቆንጆጆጆ
ለካ ዋርካዎች አላስገባ ብለውህ ነው የጠፋህው??? እረ ዋርካዎች የምወደውን ወንድሜን ካላስገባችሁ ኔም ድማ አድርጌ እንዳልቀር! :twisted: :twisted: በይ አንቺም ቅሬ ካሉኝ ምን አደርገዋለሁኝ :oops: :oops: :oops: ዋናው ነገር ቤት ለእንግዳ!
የፓንቷ ነገር አሁን በመከራ ነው የለመድኩት እንግሊዞች Trouser ነው የሚሉት pant እኛጋ እናንተ underwear እንደምትሉት ነው! ግራ የገባ ቁዋንቁዋ ነው ደግነቱ አንተ ብላክ ፓንት ብቻ አድርገህ( አንደርዌር) ስራ አለመሄድህ ነው :lol: :lol: :lol:
ይልመድብህ የኔ ቆንጆ
ውድድድድድድድድድድ


********************************

ወንድም
ስላም የኔ ቆንጆ!
ጥሩ ጨዋታ ነው.......ግን በደባልነት ይኑር እንጂ ቤቱ ልክ እሱ እንዳለው ነው ወይስ ዝም ብሎ ሲያጋንን ይሆን?
አንዳንዴ ዋሽተን እራሳችንን ስናታልል ስው ያታለልን ይመስለናል......አለማወቃችን እኮ ነው!
ከዛ በህዋላ መቼም ሁለተኛ አይዋሽም!
በል ያገር ልጅ ይልመድብህ ቡናውም ደርሷል ቶሎ ቶሎ ፉት እያልክ ይሄ የመጀመሪያህ እንጂ የመጨረሻህ እንደማይሆን ነው :wink:


********************

ሜዳ ያገር ልጅ
እረ ምን ፍቃድ ያስፈልገዋል ቤትህ ቤቴ ገንዘብህ ገንዘቤ የኔ ገንዘብ ግን የራሴ ነው :lol: :lol: :lol:
የመጋኛዋን አባባል ወድጄያታለሁኝ.......እረ ልብ ብለህ እንደሆን አገራችን እኮ እንደዛ አይነት ነገር የተለመደ ነው....መጋኛ መቶት ወይ ብርድ መቶት ሞተ ሲባል ነው የምስማው ቀዝቃዛው አየር ከዚህ በረዶ የተለየ ሆኖ ነው ወይስ እውነት የኛ አገር ብርድ ስው ለበሽታና ለሞት አሳልፎ የሚስጠው አይነት ነው????
እስኪ የምናውቀውን አንድ እንበል.....
መዳ በል ይልመድብህ ያገር ልጅ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby SUAVE » Thu Dec 29, 2005 10:22 am

ባገራችን ቡና ሲፈላኮ ዋናው ቡና ቁርስ ሀሜት ነው:: እኔ ሀሜት የሌለበት ቡና, ምንም አይጥመኝም:: ኧረ ባካችሁ ሀሜት አምጡ?

የቤቱ ባለቤት ቤተስኪያን ሊስሙ ወጣ ብለዋልና እስኪ ትንሽ እንማቸው:: ይሄ አሁን ኮፊ ሀውስ ብለው ባንድ ሲኒ ቡና አዳሜን ገንዘብ የሚዘርፉበትን ቤት አሉ አንዱ ነው የሰራላቸው:: ሰውየው ከሳቸው ጋ ቅልጥ ያለ ፍቅር ውስጥ ነበሩ አሉ:: ሴትዮዋ ታዲያ ይህን አይተው በቁማቸው ዝርፍ አርገው ጨረሷቸው አሉ::
Last edited by SUAVE on Thu Dec 29, 2005 1:10 pm, edited 1 time in total.
SUAVE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 475
Joined: Sat Sep 03, 2005 8:42 am
Location: ethiopia

Re: Mo's Coffee House(MCH)

Postby ጭምት » Thu Dec 29, 2005 1:01 pm

ጌታ wrote:"Do you have time?"


Do you have time? = ስንት ሰአት ነው?

እንግሊዝኛውን ከኔቲቮቹ እኩል ባናውቀውም እቺኛዋ ትርጓሜ ትክክለኛነቷን ለመቀበል ተቸገርኩ:: ዱ ዩ ሀቭ ታይም ስትልህ አይ አም ቢዚ አልካትና መንገድህን ቀጠልክ:: That was correct english. You know what must have happened? Originally she planned to talk to you as you correctly undestood it. But when she new you let her down, she acted smart and played some tricks on you. She didn't want to be embarrassed by your rejection. A little bit of maneuvering changed the situation, she saved herself from the embarrassement and you were left cursing your poor english!
ጭምት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 403
Joined: Sun Jul 31, 2005 7:42 am
Location: ethiopia

Re: Mo's Coffee House(MCH)

Postby ጌታ » Thu Dec 29, 2005 3:35 pm

ጭምት wrote:
ጌታ wrote:"Do you have time?"


Do you have time? = ስንት ሰአት ነው?

እንግሊዝኛውን ከኔቲቮቹ እኩል ባናውቀውም እቺኛዋ ትርጓሜ ትክክለኛነቷን ለመቀበል ተቸገርኩ:: ዱ ዩ ሀቭ ታይም ስትልህ አይ አም ቢዚ አልካትና መንገድህን ቀጠልክ:: That was correct english. You know what must have happened? Originally she planned to talk to you as you correctly undestood it. But when she new you let her down, she acted smart and played some tricks on you. She didn't want to be embarrassed by your rejection. A little bit of maneuvering changed the situation, she saved herself from the embarrassement and you were left cursing your poor english!


ወንድሜ ጭምት

ጥቁር አሜሪካዊ መሆኗን የጠቀስኩት ያለምክንያት አልነበረም:: እነሱ የሚናገሩት እንግሊዘኛ እና እኔና አንተ የተማርነው አራምባና ቆቦ ነው:: ለምሳሌ ያህል

He/she don't
ask ለማለት aks
an እና a የሚጠቀሙት ቦታማ ግራ ነው የሚገባህ
በተረፈ ደግሞ የዶማው2005ን እንግሊዘኛ ብታይ የበለጠ ግልጽ ይሆንልሀል:: It's typical Ibonix. የጥቁር አሜሪካውያኑ ቋንቋ ኢባኒክስ ነው የሚባለው::

Do you have time? እና

What time you have? እማ ቀን ተቀን የምሰማቸው 'ሰዓት ስንት ነው? ማለት ናቸው:: እንዲያውም እኔ አስተካክዬው ነው እንጂ እንሱ የሚሉት You have time? ነው:: በትክክለኛው እንግሊዘኛ ከሄድን እኔና አንተ ነን ትክክል:: ቋንቋ ግን አንዳንድ ጊዜ እንዳካባቢው ነዋሪ ስምምነት ስለሚወሰን በዚያ ኅብረተሰብ መሃል እስከኖርን ድረስ ተቀብለን መኖር ነው::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3117
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby እማማ እርጎየ » Thu Dec 29, 2005 3:58 pm

እንዴት ዋላችሁ? አረ ቤቶች...ወይ ጉዴ....እንግዲህ ልጄ ሞኒካዬ የለችም ማለት ነው....አንዴ? አናንተ

አረግ አረግ አረግ ....ነይ እስኪ እምፑዋ እምፑዋ እንዴት ነሽ ልጄ? እ እንዴት ነሽ? ደና ነሽ , አንዴት ሰነበትሽ...እንደው ይሄ ቡና ገበያ እንዴት ነው? እሰይ እሰይ

እኔ አለሁ አንድየን አይክፋው:: ትላንትም እኮ መጣሁና በትእዛዝሽ መሰረት እንዴት ያለ በሶ በልቼ ሄድኩ:: ልጄ ቀኑን ሙሉ ስመርቅሽ ነው የዋልኩ...ታውቂ የለ በሶ እኮ ከገባ አይነቃነቅም ...ብረት ነው...ገብስም አይደል:: ሙሉ ቀን ይዞኝ ዋለ:: እድሜ ላንቺ::

የለም የለም ዛሬ እንኩዋን ትንሽ እቆያለሁ:: ቤተክሲያንም አልሄድኩ....ባይሆን ስመለስ እመጣለሁ:: ላንቺም እጸልያለሁ:: በይ ሰላም ዋይልኝ,,, አምላኬ በቸርነቱ ይጎብኝሽ.....አንዲህ እኔን እንደምትመግቢኝ....እሱ ደሞ በጎደለው ነገርሽ ይድረስልሽ ልጄ:: ዲግሪሽን እንዳበላኝ ደሞ ሰርግሽን ያብላኝ የኔ ልጅ:: ውለጂ ክበጂ...ቃሌ ነው..እኔ እናትሽ...የመጀመሪያ ልጅሽን ስትወልጂ አጠገብሽ እሆናለሁ.....30 ቀን ሙሉ አገለግልሻለሁ:: /አርስሻለሁ/

ልጄ ....ወንድም...አሳቢ...መከታ...መኩሪያ የሆነ ባል ይስጥሽ::

ሞኒካዬ እንደዛሬ ልጆች መልክና ቁመና አይማርክሽ ልጄ....የውስጥ ነገር ነው ዋናው....ቁምነገር ..ቁምነገር ልጄ....ቅን ከሆነ...የሚወድሽ ከሆነ...ዘመዶችሽን የሚወድ ከሆነ .....ገንዘብ የማይወድ ከሆነ.....በቃ እሱ ነው ባልሽ...ታዲያ የኔንም ነገር ንግሪው...ይቺን የለመድኩዋትን ቁርስ እንዳይነፍገኝ:: አዎ...ደግ ባል ነው ባል ማለት:: አይይ የኔ ባል.....መሬቱ ይቅለላቸውና...መቸም ባል ብሎ ዝም ነበሩ:: ኤዲያ ትዝታየ ተቀሰቀሰ .. :(

ልሂድ ልጄ..ከቤተክሲያን ስመጣ ብቅ እላለሁ::

ቸር ይግጠመን::
Last edited by እማማ እርጎየ on Thu Dec 29, 2005 4:00 pm, edited 1 time in total.
እማማ እርጎየ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 279
Joined: Wed Dec 21, 2005 7:25 pm

Postby አሰግድ » Thu Dec 29, 2005 3:59 pm

ለጌታ ና ለጭምት
እንግሊዘኛና ህልም እንደ ፈቺው ነው ሲባል አልሰማችሁም :wink:
Last edited by አሰግድ on Thu Dec 29, 2005 4:03 pm, edited 1 time in total.
አሰግድ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 33
Joined: Sat Jul 31, 2004 11:39 pm
Location: ethiopia

Postby SUAVE » Thu Dec 29, 2005 4:01 pm

እኔ አዲሳባ በጣም የሚናፍቀኝ መርካቶ ነው:: ልጅ ሆኘ በሆነ አጋጣሚ ስሄድ ግርግሩ እንዴት ፍቅር እንደሚያሲዘኝ! ግርግር, ትርምስ ሩጫ, ክርክር, አንዳንዴ ደሞ ቅሚያ, ዱባይ ተራ, ጭድ ተራ, ቦምብ ተራ, ሚሊቴሪ ተራ, ምንያለሽ ተራ....

አሁንም እንደመጣሁ መርካቶን ለማየት በፍቅር ነው የናፈኩት የነበረው:: ሄድኩ- እዛው መርካቶ! በመጣሁ በሶስተኛ ቀን::

ምንያለሽ ተራ የማይሸጥ ነገር የለም:: ሰከንድ ሀንድ አንደርዊር, ካልሲ, የተሰባበረ የሸክላ ድስት, የጃንጥላ ሽቦዎች.....ምንም አይቀርም

አንድ ጥግ ደሞ ጉርሻ መሸጫ አለ! ቀልድ አይደለም:: ከተለያዩ ሆቴሎች የሚመጡ የተራረፉ ምግቦች እንደመጡበት ሆቴል ደረጃ አላቸው::ዋጋቸው እንደደረጃቸው ይለያያል:: የሸራተን, ሂልተን, ጊዮን,...ግን በሁለት አይነት ያሻሻጥ ስታይል ነው ሹያጩ የሚካሄደው:: አንደኛው እንደማንኛውም የጉልት ንግድ በመደብ ሲሆን ሌለኛው በጉርሻ ነው::

እንደምታቁት መርካቶ የሩጫ, የጥድፊያ ቦታ ነው:: ጥቂት ጊዜ ብዙ ያወጣል:: እናም እዚህ የሚሰሩ የጉልበት ሰራተኞች, ሬስቶራንት ገብተው, እጅ ታጥበው, ሜኖ መጥቶላቸው አዝዘው, እስኪበስል ጠብቀው መብላትን አፎርድ አያረጉትም:: ይህንኑ ችግራቸውን ያገናዘበ "ሬስቶራንት" ግን አላቸው:: የጉርሻ ስቶር:: ከተለያዩ ሆቴሎች የሚመጡ ትራፊ ምግቦች, የሆቴሉን ደረጃ እንደጠበቁ, በጉርሻም ይሸጣሉ:: ሻጭ ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆኖ እጁን በማሾለክ ለገዥ ያጎርሳል:: የጉርሻ መጠኑ አይለያይም-ስታንዳርድ አለው:: የጉርሻው ብዛት ግን እንደክፍያው መጠን ነው:: የአጉራሽ (ሻጭ) ከመጋረጃ በስተጀርባ ሸፈን የማለት ሚስጥር ገዥን ፊት ለፊት በማየት የጉርሻን መጠን ላለመወሰን (ፌር ለመሆን) ነው አሉ::
SUAVE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 475
Joined: Sat Sep 03, 2005 8:42 am
Location: ethiopia

Postby SUAVE » Thu Dec 29, 2005 4:17 pm

ባለቤቷ ደሞ የት ሄዱ? አሁን ቤተስኪያን መሳም ይህን ያህል ያቆያል? ህምምምም አቤት እሳቸው....
SUAVE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 475
Joined: Sat Sep 03, 2005 8:42 am
Location: ethiopia

Postby Monica**** » Thu Dec 29, 2005 5:30 pm

አቤት ሲታሙ አድርስኝ
ሲጣሉ መልስኝ ይል የሌ ያገሬ ስው :lol: :lol: :lol:

SUAVEዬ
በተክሲያን ስሜ በዛው የባላምባራስ አለባችውን ለቅሶ ልደርስ ጎራ ብዬ እዛው ዋልኩኝ::
አሁን ያንን ወሬ የነዛችብኝ ያችው ጠላቴ ማናለብሽ ናት በቅናት!!! :twisted: :twisted:
እኔ ይሄን ግዛ ይሄን አትግዛ ብዬ ጠይቄው አላውቅ...... ያው ልጆቼን ተባህርማዶ የትምህርትቤታችውን ብቻ ክፈል ብዬ ጠይቄለሁ አልዋሽም! ተዛ ሌላ ወዶኝ ብሩን ቢያፈስ ሙልጭ አድርጋ በልታ ያስብለኛል? :lol: :lol: አበስኩ ገበርኩ አለኝ እትዬ ደብዚ ወዳ እኮ አይደለም!
በል የኔ ቆንጆ አንተ ብቻ በስው አሉባልታ አትቅር በል ቡናውን ፉት እያልክ ለመሆኑ ምሳ በልተሀል?


**********************
ጭምት የኔ ቁምነገረኛ
የትላንትናው ጨዋታችን ስለጭ መስለኝ መልስ አልስጠህኝም :lol: :lol: :lol: ሁለቱም የለኝም ስልህ ፋይዳም የላት ብለህ ነው አይደል? :lol: :lol: :lol: ከጌታ ጋር የያዛችሁት ጨዋታ አስቆኛል.....ልጅቷ ሌላ ጉዳይ ኖሯት ነው ለካ ጌታ ምስኪኑ አላወቀ :lol: :lol: :lol: ያቺ ዘቢደሩ ለመሆኑ ሻይ ቡና ብላህ ይሆን? እሷ እኮ ምድር ስማዩ የዞረባት ናት :roll: :roll: ትንሿ ትሻላለች :lol: :lol: በል ቡና ላቀራርብ


***************

ጌታ የኔ ቆንጆ
ይሄ ቀለም አይንህን ከያዘው ሂድና አይንህን ዶክተር እንትናጋ ተመርመርና መነጥር ያዝልሀል :lol: :lol:
ከጭምት ጋር የያዛችሁትን ጨዋታ አላቆርፍድ! ቡናህን ልድገምህ የኔ ጌታ? :wink: :wink: :wink:


*********************
አስግድ እኔ አላምንም!!!
አንተ ልጅ እንደው ከምድር ገጽ ላይ እንደዚህ ቫኒሽ ያደረግከው እንድትናፈቅ ነበር? :lol: :lol:
ዋናው ነገር እንክዋን በስላም ተመለስክ ተናፍቀህ ነበር እኔን በተመለከተ!!! በል ትኩስ ቡናህን እየጠጣህ የት ጠፍተህ እንደከረምክ አቻውተኝ :lol: :lol:
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby Monica**** » Thu Dec 29, 2005 5:43 pm

SUAVEዬ የኔ ቆንጆ
እኔው ነኝ በድጋሚ!! ይቺ ስለመርካቶ ያልካት ነገር ከዚህ በፊት ዋርካ ጄኔራል ላይ ተጽፎ አንብቤ....መርካቶ ጉርሻ ቤ እንዳለ ታውቁ ኖሯል ነው የሚለው ብዙ ዲቴል ሳይጻፍ!!
እኔ ደደቧ እህትህ ደሞ የመስለኝ ሴቶቹ እንጀራ ጥፍራችው ውስጥ እንዳይገባ ለሀይጂን ሲሉ ያደረጉት መስሎኝ ወይ ገንዘብ እንዲህ ያጠግባል ብዬ ትንሽ ገርሞኝ እንደውም ይሄንኑ ጥያቄ ጠይቄ ልጁ አባራርቶ ነገረኝ ከድህነት እንጂ ከቅንጦት እንዳልሆነ!!!
ይሄ ታዲያ አያሳዝንም?????????
SUAVE wrote:
አንድ ጥግ ደሞ ጉርሻ መሸጫ አለ! ቀልድ አይደለም:: ከተለያዩ ሆቴሎች የሚመጡ የተራረፉ ምግቦች እንደመጡበት ሆቴል ደረጃ አላቸው::ዋጋቸው እንደደረጃቸው ይለያያል:: የሸራተን, ሂልተን, ጊዮን,...ግን በሁለት አይነት ያሻሻጥ ስታይል ነው ሹያጩ የሚካሄደው:: አንደኛው እንደማንኛውም የጉልት ንግድ በመደብ ሲሆን ሌለኛው በጉርሻ ነው::

እንደምታቁት መርካቶ የሩጫ, የጥድፊያ ቦታ ነው:: ጥቂት ጊዜ ብዙ ያወጣል:: እናም እዚህ የሚሰሩ የጉልበት ሰራተኞች, ሬስቶራንት ገብተው, እጅ ታጥበው, ሜኖ መጥቶላቸው አዝዘው, እስኪበስል ጠብቀው መብላትን አፎርድ አያረጉትም:: ይህንኑ ችግራቸውን ያገናዘበ "ሬስቶራንት" ግን አላቸው:: የጉርሻ ስቶር:: ከተለያዩ ሆቴሎች የሚመጡ ትራፊ ምግቦች, የሆቴሉን ደረጃ እንደጠበቁ, በጉርሻም ይሸጣሉ:: ሻጭ ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆኖ እጁን በማሾለክ ለገዥ ያጎርሳል:: የጉርሻ መጠኑ አይለያይም-ስታንዳርድ አለው:: የጉርሻው ብዛት ግን እንደክፍያው መጠን ነው:: የአጉራሽ (ሻጭ) ከመጋረጃ በስተጀርባ ሸፈን የማለት ሚስጥር ገዥን ፊት ለፊት በማየት የጉርሻን መጠን ላለመወሰን (ፌር ለመሆን) ነው አሉ::
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests