ሸዋ ባላመጠ.................

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ይድረስ ለወንድሜ ነቅንቄ

Postby ዲጎኔ » Thu Jan 26, 2006 8:02 am

ይድረስ ለወንድሜ ነቅንቄ

ስለበጎ ምላሽህ እኔም በተራዬ አሪክቡን ብያለሁ::
በዚህ ምላሽህ ላይ አሁን ያለአግባብ ስለታሰሩት የቅንጅት መሪዎች የገለጽከውን በተለይ እያደነቅሁ በሌሎች ጉዳዮች የምንጋራቸው ሲኖሩ ለእናት ኢትዮጵያ ፍትህ ያለን መሻት ከሁሉ ቀዳሚ ነው::

በትግል ጉዞ ላይ ምኞትና ስሜት ሲከሰቱ መንስኤው የድል ናፍቆት ስለሆነ ለቀጣዩ ትግል ትምህርት ተወሰዶበት ይታለፋል:ከዚህ የከፋው ግን ድብቅ አላማ ይዞ የህዝብን ትግል ለራስ ዝናና ጥቅም ማዋል ነው::

የቅንጅቱ መሪዎች ህልም አላቸው ህልሙም የተማሩትንና በረጅም ዘመን ያዳበሩትን እውቀት ለእናት ኢትዮጵያ ወገኖቻቸው ለማካፈል ብዙዎቹም በውጭ ሀገር የነበራቸውን የተሻለ ጥቅም በመሰዋት ለባእዳን የሚፈሰውን ጉልበትና ጥበብ ለሀገራቸው ለማዋል ስላልቻሉ ተጨናገፈ እንጂ ፍሬያቸውን ሳያዩ ክንዳቸውን እንደማንይንተራሱ ጸሎቴም እምነቴም ነው::

ወሎ በትክክል እንዳልከው ለኢትዮጵያ ትክክለኛ አወቃቀር የሚመች ጂኦግራፊን ያቀፈ ሁሉም ጎሳና እምነት ያለበት ሲሆን ከወያኔ በመፋለምም ከማንም ባልተናነሰ መልኩ አስተዋጽኦ ያደረገ የጀግና ምድር ነው::
ሪፖርተርንም ሳላይ የአንዳርጋቸውንም ቃለመጠይቅ ሳልሰማ ወያኔ ምን ያህል አቶ ልደቱን ከትግል አጋሮቹ ለመለየት እንደሚደክር ሰሞኑን ዋልታ ላይ ወያኔ ከምርጫው ፉክክር ሰሞን ውጭ አድርጎት የማያውቀውን የኢዴፓ-መድህንን ጉባኤን ከቤን አምድ ጠልፎ ያቀረበው ብቻ ይበቃኛል::ግን ምናለበት አቶ መለስ ይህንን ልዩ የተንኮል ጭንቅላት ከጥፋት ይልቅ ለልማት ቢያውሉት?

ልማድ ሆኖብን ያኔ ህዝባዊው ትግል በኢህአፓ አመራር ስር በወደቀበት ሰአት ብርሀነ መስቀል በተገኘው መድረክ ከደርግ ጋር መስራት በምንችልበት አቅጣጫ እንሳተፍ በማለቱ የተለጠፈበት"አንጃ" ታፔላና የሀ እና ለ የእርስ በእርስ እልቂት ገና ከአእምሮዬ አልጠፋም :: ይህን ስልህ ብሄራዊ ግንባርን በተለጣፊ ቡትቶ ከሚሰበስብ ወያኔ ጋር በምርጫ በተሸነፈበት ፓርላማው ገብተን እናሟሙቅለት ማለቴ አይደለም በጸረወያኔ ግንባር ያለነው አንባላ እንጂ::
ለማጠቃለል የምልህ ቅንጅቱ እንደ ትግል ግንባር የሚቆጠር የህዝባዊ ሀይሎች አንድነት ስለሆነ በግንባር አባላት ዘንድ ችግሮች ሲፈጠሩ ከማፈንገጥ ይልቅ" ብዙሀን ይመውኡ" እንደሚለው ለብዙሀን ድምጽ በመገዛት በመተናነጽ ጉልበታችንን ማፈርጠም እንጂ በመከፋፈል እጅ መስጠት እንደሌለብን ነው::እስኪ አሁን ወያኔ ግንባር ብሎ በውሸት ጎሳዎችን እየሸነገለ የግፍ አገዛዙን በህዝባችን ላይ ሲያራዝም እውነተኛ የህዝብ ግንባር ያላቸው ቅንጅቱና ህብረቱ ከአባል ድርጅቶች ጋር የሚያደርጉት ጥል "የአለም(ሰይጣን) ልጆች ከብርሀን(ህዝባዊ)ልጆች ይልቅ ለትውልዳቸው ያስባሉ" እንደሚለው ቅዱስ ቃል እንዳይሆንብን እጸልያለሁ::

ዲጎኔ ሞረቴው ከእናት ኢትዮጵያ ቅንጅታዊ አንድነት ዲሞክራቲክ ግንባር
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

ነቅንቄ

Postby ዉዱያያ » Thu Jan 26, 2006 8:25 am

እስኪ ለነዚህ በኢትዮጵያዊነት ስም ለሚነግዱ የሀገር ነቀርሳዎችና የብራና ብሎች ቢገባቸው እንደኮሶ መድሀኒት ጋታቸው - ከርሞ ጥጃ ሁላ!!!
TRUTH IS THE SAFEST LIE; AND THE TRUTH IS NOT ALWAYS WHAT WE WANT TO HEAR
ዉዱያያ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 16
Joined: Wed Nov 30, 2005 2:15 pm

Re: ነቅንቄ

Postby ነቅንቄ » Tue Feb 07, 2006 11:39 pm

ዉዱያያ wrote:እስኪ ለነዚህ በኢትዮጵያዊነት ስም ለሚነግዱ የሀገር ነቀርሳዎችና የብራና ብሎች ቢገባቸው እንደኮሶ መድሀኒት ጋታቸው - ከርሞ ጥጃ ሁላ!!!


ከፈልጉም ከነበከተ አስተሳሰባቸው መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቸው. በምናዉቀው በቆየው ባህላችን ወያኔን እናነጋግረዋለን. ይህ የነጻነት ትግል ጣምራ ጦርነት ሲሆን አንዱ ከወያኔ አምባገነነት ሁለተኛው ከሸዋ እርምጥምጥ አስተሳእብ እና የገዢነት አባዜ ጋር ይሆናል. ቢዘገይም አቸናፊነታችን አይቀሬ ነው.

ንቅንቄ
ግሼን ማርያም
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
ነቅንቄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 269
Joined: Tue Mar 01, 2005 10:57 pm
Location: bet-amhara

Postby ዋቆ » Wed Feb 08, 2006 12:51 am

ሰላም የአገር ልጆች በያላችሁበት

ድንገት ዋርካ ብቅ ብል ደግሞ ሸዋ ምን ሆነ? ብዬ ይህን ተመለከትኩ:: እፎይ ተመስገን!!!

በእውነት እላችሁዋለሁ ወያኔዎች እጅግ ይሉኝታ የሌላቸው ሲያስፈልጋቸውም መሰሪ የሆኑ የፖለቲካ ቁማር ተጫዋቾች ናቸው:: እኛ አቶ ልደቱን አጅበን ጥረቱን እያደነቅን አብረን ወድቀን ስንነሳ እነሱ ደግሞ የጽላት ሌባ ይሉት ነበር:: አሁን ቅንጅትን የሚያላላቸው ሆኖ ሲያገኙት ደግሞ ህሊና ቢሶቹ አይጋዎች ሪፖርተሮችና ዋልታዎች አቶ ለደቱን ጫንቃቸው ላይ ይዘው ሆ ሆ ሆ ይላሉ:: ምን አይነት ፋራዎች ናቸው አቦ!!!

ከዚያም አልፎ ዛሬ ነገሩን ልክ እንደሰገሌ ጦርነት የሸዋና የራስ ሚካኤል ግሩቦች ለመከፋፈል ለኢትዮጵያ በጎ ያሰቡ መስለው እሬታቸውን ማር እየቀቡ ለመጋት ይሞክራሉ:: እኔ በበኩሌ የዋቆ ግንባር የቅንጅት አባል ባልሆንም ነገር ግን ደሴ ልክ በከፍተኛ ድምጽ ልክ እንደአዲስ አበባ የመረጠው ቅንጅትን ነው:: ወሎም ልክ እንደሸዋ ያስባል ማለት ነው ቅቅቅቅ

አቶ ንቅንቄ ሸዋ ሽዋ እያለ ድንገት ለቅንጅቱ መፍረስ ቀዳዳ መርፌ ማስገባቱ ነው:: ሙከራው መልካም ነው:: ሆኖም ሸዋ ትርጉሙን እንኩዋ ያወቀው አይመስለኝም::

ሆኖም ዛሬ አማራውና ኦሮሞው የወያኔን መሰሪነት ተረድቶ በኦሮሚያ ከኦነግ ጋር መሳሳብን በፈጠረበት የትግል አንድነቱን ባቀናጀበት ወቅት ወሎንና ሺዋና ለማጣላት መሞከር ብዙም ባትደክሙ መልካም ነው:: አቶ ንቅንቄ ድንገት የማውቅህም መስልከኝ ልክ ሰባርጉማ የሚባል የአሺአ የዘረኞች ኮሙኒቲ ኮሌጅ ምሩቅ ሳትሆን አትቀርም:: ሙከራህ መልካም ነው ሆኖም ይህ ንግድ የተበላ እቁብ እኮ ሆነ ወዳጄ!!!

አቶ ልደቱን በተለመከተ አምና ስለሰውዬው ብዙ በጎ በተናገርኩት ዛሬ የምለው የለኝም:: ሰኔ የመጀመሪያ የሪፖርተር ልዩ ወዳጅ መሆን ሲጀምሩ ዘመድ መክሮዋቸው ከፖለቲካው ለሕዝብ ፍቅር ብለው እራሳቸውን ቢያገሉ ብዬ መክሬ ነበር:: ዛሬም ወገን ያለው ምርጫ ሰውዬውን ዝም ብሎ ቢተዋቸው መልካም ይሆናል::

እርግጠኛ ነኝ ወያኔና ወያላዎቻቸው የግድ ስለአቶ ልደቱ እንዲወራ ይፈልጋሉ:: ስደት የሚሉት ሕሊና ቢስ ወያኔ እንኩዋ አምና ብዙ ሰውዬውን እንዳላለ ሁሉ ዛሬ ከአይጋ ዘመዶቹ ስለልደቱ አይመጣ ዋርካ ላይ ይለጥፋል::

ወያኔ በሁሉም መንገድ ስለልደቱ እንዲወራለት የሚፈልገው ቅንጅትን ለማዳከም ነው:: ይህን ሁሉም መረዳት ይኖርበታል:: ወያኔ ለሁሉም ድርጅት ተለጣፊ ፈጥረዋል ለቅንጅትም ሌላ ቅንጅት እንዴት እንደሚፈጠር የማያገላብጡት ድንጋይ የለም:: የሸዋና ወሎ ጉዳይም ከዚሁ ነው::


ሰላም ሁኑልኝ ቻዎ ቻዎ

ዋቆ ነኝ
በዋርካ የአገር ፍቅር ግንባር
ዋቆ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 455
Joined: Sun Nov 16, 2003 2:12 am

Postby ወጥመድ » Wed Feb 08, 2006 9:44 am

ወጥመድ wrote
Code: Select all
ነቅንቄ!!
ቅ :lol: ቅ :lol: ቅ :lol: ቅ :lol: ቅ

አሁንም በድሮ በሬ እያረስክ ነው??
 ወሎ ጎጃም ጎንደር ሸዋ እያሉ ማላዘን ያኔ----ያኔ--- ቀረ እኮ :: ዛሬ ነገሩ ሁሉ እናንተ እንዳሰባችሁት ሳይሆን ቀርቶ የተገላቢጦሽ ሆኖ በግንባር ቀደምትነት ወያኔን የሚያርበደብደው የባህሕር ዳር, የደብረማርቆስ, የደሴ, የኮምቦቻ የባቲ--- የጎንደር ህዝብ---ወዘተ ሆነና እርፍ አለ:: እንግዲህ ነቅንቄ ነኝ  አዝብጤ ነኝ ብትል በስም የሚለወጥ ምንም ነገር የለም::

[b]ይልቅስ ከወሎ ክ/ሀገር ወደ ክልል 1 (ትግራይ) የተዘረፈውን ለም ለም መሬት በሰላም መልሱ::[/b]

ቅ :lol: ቅ :lol: ቅ 
አላርፍ ያለች ጣት----

ወጥመድ
ወጥመድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Fri Mar 11, 2005 1:52 pm
Location: Semen Walta

Postby ነቅንቄ » Wed Feb 08, 2006 10:35 pm

ወጥመድ wrote:ወጥመድ wrote
Code: Select all
ነቅንቄ!!
ቅ :lol: ቅ :lol: ቅ :lol: ቅ :lol: ቅ

አሁንም በድሮ በሬ እያረስክ ነው??
 ወሎ ጎጃም ጎንደር ሸዋ እያሉ ማላዘን ያኔ----ያኔ--- ቀረ እኮ :: ዛሬ ነገሩ ሁሉ እናንተ እንዳሰባችሁት ሳይሆን ቀርቶ
 የተገላቢጦሽ ሆኖ በግንባር ቀደምትነት ወያኔን የሚያርበደብደው የባህሕር ዳር, የደብረማርቆስ, የደሴ, የኮምቦቻ የባቲ--- የጎንደር ህዝብ---ወዘተ ሆነና እርፍ አለ:: እንግዲህ ነቅንቄ ነኝ  አዝብጤ ነኝ ብትል በስም የሚለወጥ ምንም ነገር የለም::

[b]ይልቅስ ከወሎ ክ/ሀገር ወደ ክልል 1 (ትግራይ) የተዘረፈውን ለም ለም መሬት በሰላም መልሱ::[/b]

ቅ :lol: ቅ :lol: ቅ 
አላርፍ ያለች ጣት----

ወጥመድ


አቶ ወጥመድ

ወጥመድህ አልያዘለህም. ባነሳሁዋቸው ነጥቦች ላይ አስተያየት ስጥ ወይ እንደሌለ ቆጥረህ እለፈው ብየህ ነበር.

ዛሬ ደግሞ አዛኝ ቅቤ አንጉዋች ሆነህ የተወሰደባች ሁን መሬት ከትግራይ መጀመርያ አስመልሱና ስለስልጣኑ ክፍፍል (ገና እጂ ባልገባ ስልጣን ቅቅቅቅ) ሁዋላ እንነጋገራለን የምትል ይመስላል.ነዉም.

ምክንያቱም ዛሬ ወያኔ በዉጪም በዉስጥም የተዳከመ ስለመሰላችሁ አገኘናት እንደተመኝናት አይነት የሸዋ አባዜ ነው የምታንጸባርቀው.

እኛ መሬታችንን ለማስመልሰ ወደስሜን ስንዘምት እናንተ ልትቀራመቱት ነው አይደል ምኞትህ??? አይሳካልህም. ቅቅቅ

ለነገሩ እኛ የሸፈትነው በወያኔ ላይ ብቻ ሳይሆን በደርግም--በሀይለስላሴም--በዮሀንስም--በቴዎድሮስም ላይ ነው. አማጺዎች ነን. አንገዛም--አንንበረከክም ባዮች ነን.
-ግራኝ አህመድ በሰይፍ እና ጎራዴ አልተሳካለትም
-ቴዎድሮስ ብዙ ጊዜ ሞክሮ አልተሳካለትም.
- ዮሀንስም በሰይፍ ሞክሮ አልተሳካለትም.
-ምኒልክ ብልጥ እና ብሩህ መሪ ናቸው. በዘዴ ጫማቸው ስር አስገብተውን ነበር እኛም እንወደዋለን የሳቸዉን ዘመነመንግስት. እዚያ ከመድረሳቸው በፊትም ቤዝ አምባቸው ወሎ ነበር.

ወርቂት ደብቃ ምኒልክን ባታስኮበልላቸው ኖሮ አንድ የምንኮራበት መሪ እንኩዋን አይኖረንም ነበር.

ከዚያም የቀጠሉት ደካማ መሪዎች ብዙ ሞክረዋል አልተሳካላቸዉም.

ዛሬ ደግሞ በሀያአንደኛው ክፍለዘመን ተንበርካኪው የሸዋ ስልጣን ጠማሽ ሊያንበረክከን አይችልም.

ተንበርካኪዎችን እያጸዳን ጸረወያኔዉን ትግል እናፋፍማለን.

ስለዚህ ትግላችን ጣምራ ትግል--ጣምራ ጦርነት--ጣምራ ግብግብ ይሆናል ማለት ነው.

በአንድ በኩል ስልጣን ጠማሹን --ተንበርካኪዉን የሸዋ ፖለቲከኛ በድሪትም--በፖለቲካም እየታገልን ወደሁለተኛው ከባድ ጸረ-ወያኔ ትግል እንሸጋገራለን ማለት ነው. ይህን ሳናደርግ ብንቀር---ወያኔን ወይ ንቅንቅ// :!: :!:

ነቅንቄ
አገው ምድር
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
ነቅንቄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 269
Joined: Tue Mar 01, 2005 10:57 pm
Location: bet-amhara

Previous

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 4 guests