ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር በተመላለሰባቸው ቀናት እጅግ አድርጎ የገሰጻቸው ግብዝ የሀይማኖት መሪዎችን ሲሆን ዛሬም መንፈሱ የሚያነጣጥረው እነርሱን በመሰሉ ግብዝ ጳጳሳትና ሆድ አምላኩ ተከታዮቻቸው ላይ ነው::
በእርግጥ በሀገር ቤት በጥቂቱ በስደት ደግሞ በመጠኑ ከፈሪሳዊነት የራቁ መኖራቸው ባይካድም አብዛኛዎቹ ስልጣን የያዘውን ሁሉ ሺ አመት ያኑር እያሉ ሲመርቁ እንደነበርና ዛሬም አረመኔው ኢሀዲግን "ያሰንብትልን" ያሉትን የሲኖዶስ ተብዬው መሪዎችን ስም እየተጠቀሰ ከለፈፉበት ስፍራ ጭምር ማቅረብ ይቻላል::
ርእሱ "ጳጳሳት" ስለሚል ህዝባችን ጳጳስቱ እነዚያ ግብዝ የጭቆናና የአፈና ተባባሪዎች ሳይሆኑ አንድ ሚሊዮን የማይሞሉትና በጳጳስ ብርሀነኢየሱስ የምትመራው የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን መሆናቸው ተለይቶ መታወቅ ስላለበት"ኮተለኩ" "ተኩላ" እየተባሉ የተነቀፉትን ካቶሊኮችን እንድንቀበል ያቀረብኩት መጣጥፍ ነው::
ይህ ሰናይ ግብር የሚያቃጥለው የደብተራዎቹ አፈቃላጤ እኔን ለእናት ኢትዮጵያ በጎ ምግባርን ከየትም ቢከሰት የምዘግበውን አንዴ የካቶሊኮች ወገንተኛ አድርጎ ሲከሰኝ ሌላ ጊዜ ደግሞ "ተዋህዶን"መሰልክ እያለ ያንጉዋጥጠኛል እኔ ግን በዋርካ ላይ ያለአንዳች ልዩነት ለኢትዮጵያ በጎ መንፈሳዊም ሆነ ስጋዊ ተሀድሶን ለመዘገቤ ይህው ግለሰብ ያወጣው ፋይሌ ያረጋግጣል::
እጅግ አሳፋሪው ታሪካቸው ቄስ አበበ ፈንቴ የተባሉ የቆሬ አርሲ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ካህን በጀርመን ድምጽ ያቀረቡትን ተማጽኖ ሰምተው ለወገኖችና ለአለም ሰብአዊ ድርጅቶች ከማሳወቅ ይልቅ የሌላውን እምነት ለመሳደብና ለማውገዝ ሲተጉ ይገኛሉ:እኔ ግን በዋርካም ሆነ በግሌ የእነዚህ የአርሲ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ወገኖቼን የብሶስት ጥሪ ለአለም አስተጋብቻለሁ:: ይህ ቅን ተግባሬ ወይም በሀገሬም ሆነ በባህር ማዶ በኢ/ኦ/ቤ/ክ ፕሮግራሞች መካፈሌ "ተዋህዶን ለመምሰል" የሚል ጮርቃ ግንዛቤ በዚሁ ግለሰብ አሰጥቷል::
ለማጠቃለል ኢትዮጵያዊ አጀንዳችንን በእምነት መለያየታችን እንደማይገድበው ከብዙ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ወገኖች ጋር በሚኖረኝ ስብሰባና እንቅስቃሴ ሁሉን የሚያውቅ ጌታና ወገኖቼ ስለሚረዱ አሁን ይህ የክርስቶስ ቤተሰቦችን ካቶሊክ ኦርቶዶክስ ፕሮቴስታንት በማለት የሚከፋፍል ግለሰብ ሊነቅፈኝ አንዳች ብቃት ከቶ የለውም::
በተረፈ መከራዋ ለበዛው ሀገራችን የግፈኛ ጨቁዋኞች መሳሪያ በመሆን የህዝቡን ሰቆቃ ጆሮ ዳባ ልበስ ያሉትን "የቅዱስ ሲኖዶስ"ጳጳሳትህን እንድናስተናድ ላቀረብከው ጥያቄ ንስሀ ገብተው እስከተስተካከሉ ድረስ የጌታ ቤት በግዝት ሰው ለዘለአለም የሚታገድበት ያለመሆኑንና የምህረትና የፍቅር አምባ መሆኑን እገልጽልሀለሁ::
ዲጎኔ ሞረቴው ከፍቅር ምህረትና ሰላም ተሀድሶ አደባባይ