እድል wrote:ለዛ ባለው ጠምዛዛ አሽሙር
አውቆ እውነቱን በማሳከር
ጎሸምሸም - ሸንቆጥ በነገር:
ተረብ ጥሎ መፎጋገሩ
ተሞጋግሶ መደራደሩ
ተዘራጥጦ መነጋገሩ
በስላቅ ቧልት መጠጋገሩ:
ማን አለ እኮ ከፋ
ጨዋታነቱ እስካልጠፋ::
በአዝናኝ humor በተሞላ
ጭውውት ቁም ነገር ሲብላላ:
Sarcasmሙን እየተረተሩ
ሲዋዛ ቀደዳው - chatteሩ
አቤት ወጋችን ማማሩ!!!
ክርክሩ በውስጠ-ወይራ
ቅኔ ነክ ቃላት ውርወራ
ተጋግሎ ሲያንሰራራ
ተውቦ ወሬው ሲደራ:
መንፈሳችን በተሃድሶ
ከድካም ጭንቀቱ ተፈውሶ
ዘና ይላል ተመልሶ::
ግና ሁሌም አይሞላማ
ጥልቅ ይላል አንዱ ጠማማ:
ባፈጠጠ ስድብ ዜማ
ወጋችንን እያግማማ
አጨማልቆ ሊያገለማ::
አድፍጦ እያደባ
አለአግባብ እየገባ
ጨዋታን ሊያደፈርስ
አቆርፍዶ ሊያፋርስ::
ሞያው የሱ ነው መራቀቅ
በ profanity መመጻደቅ
በራቁት ብልግና መሞሻለቅ:
'ዝቅ" ባለ ጸያፍ ወሬ
መበርገድ እንደ አቦሬ::
ሸፈንፈን አርጎ በለበጣ
ለመባለግ 'ሳያስጠጣ'
መች ያውቃል ቃላት መረጣ
ማቀርሸት እንጂ እንደመጣ::
የሚያውቀው እሱ ከፍጥረቱ
መለጠፍ ብቻ እንደንፍጡ
መቅዘን ነው Vulgar በጠጡን::
እድል
እድል wrote:ዋርካ ፍቅር
ፍቅር ትሆን እውን ከምር?
ወይስ ናት መደበሪያ
የስራ ፈት መናሀሪያ:
አሊያም ናት መናገሻ
የአበሻ ሆደ ባሻ
የልቡን መተንፈሻ::
ያስቀኛል አንዳንዴ
የዋርካ ''ፍቅር'' መንገዴ
እንደው ያሰያየሙ ዘዴ::
የ''ፍቅር'' መድረክ ግብግቡን
መናናቁን ጥላቻውን
ካየሁ ከታዘብኩ በኍላ
Oolala!! እንዲያው ዝም ብዬ Oolala!!
የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ
ቅቅ ቅቅ ቅቅቅቅ
ድንቄም የለ መተዋወቅ
ቢሉት ይሻል ነበር ይልቅ
የኔ ፉንጋ እንተናነቅ
ተያይዘን እንተላለቅ::
የሆነውን ቢሆን መድረኩ
መቼም ከመጎብኘት አልቦዘንኩ::
በፍቅር ሰይፍ የተቀላ
የነፈዘ ነሁላላ
አሊያም አታላዩ ሁላ:
ገርል ፍሬንዴ ኮብልላ
ሚስቴ በdollar ተደልላ
አልጠጣ እህል አልበላ:
እ...
የባሌ እቃው እ-ን-ስ ብላ
መሄዴ ነው ወደሌላ
ልብ ከሚያርስ ሸበላ
እያሉ ይጭሩብናላ
መንጋ የሴሰኝነት ንክ ሁላ::
ሚስቴ ሆዴ የኔ ገላ
ባታውቅም እኔን በድላ
ልተዋት ነው ይለናላ:
ምን ላርግ ታዲያ....እቃዋ ቦርቅቋላ
ሞኒካ ወይ ትትና በሉኛ እስቲ መላ
መፍትሄ አምጡ blah blah blah blah
የምክሩ አይነት አበዛዙ
ታጅቦ በንዝንዙ
በስድብ ጥዝጥዙ
አርስት ለቀው እየናወዙ::
ቃላት አክርረው ሊጠመዝዙ
ልጅ ደጉ ሲቅበዘበዙ:
በኩሩሩ እሹሩሩ
ካልተዘነጋው ነገሩ
አይቀር ከቶ ሳያቅራራ
የዋርካው አቶ ቀብራራው
እያለ ''ወንድሜ በል ኮራ""
""ዝም ብለህ አትደንብራ"'
በነ ት(ህ)ትና ትንተና
ባለጉዳይ ሲል ዘና:
የሞኒካን ወግ ጥረቃ
ሲከታተል ብሎ ነቃ:
እንዲያ ቢሆን ደሞ እንደዚ
ስትለው ማድሞዜል? ደብዚ:
ይላታል thank you! now I see!
Oh now I really really see!
ጥያቄክ ከሆነ ከምርክ
አየከው ወንድሜ ምን መሰለክ
እኔ እህትክ የምመክርክ
ብላ ስትገባ sweet ሲትራ
ነገሩን ልታብራራ:
ይመጡና ሴጣኖቹ
አባትና ልጆቹ
እናታቹን ል...ዳላቹ
F--k you! ምን ትሆናላቹ!?
ምንስ ታመጣላቹ?
በስድብ በቅሎ ቹ! ቹ! ቹ! ቹ!
ከች ይልና አስተማማኝ
""አንቺ ለማኝ""! ""አንተ ቂጥኝ""!
አንድ አገር የስድብ ቋጥኝ
ሊያወርድብን ውርጅብኝ
ይላላ ያዙኝ ልቀቁኝ
በገጽ ሙሉ እኝ እኝ እኝ እኝኝኝኝኝኝ::
ያች ፈጣጣ አይነ ደረቅ
ናፍቆት ቆቋ ስትራቀቅ
ነገር ስትፈለቅቅ
ስታደርገው ይህንን ጠቅ ያንንም ጠቅ:
ስትፈትል አማርኛ
ስትጠልፍ ከፈረንጅኛ:
ሲነገር አርስት መክፈቷ
ጎራ ነዋ ወደ ቤቷ
ወዳጇም ሆነ ጠላቷ
እሷም አትቦዝን የታባቷ
ናፍቆት አክሮባቲስቷ
ፊለፊት ከመማታቷ
ይቺን ቷ! ያንንም ቷ!
ወይ መዘባረቅ........ በሉ ቻው!!
እድል
ያስቀኛል አንዳንዴ
የዋርካ ''ፍቅር '' መንገዴ
እንደው ያሰያየሙ ዘዴ ::
የ ''ፍቅር '' መድረክ ግብግቡን
መናናቁን ጥላቻውን
ካየሁ ከታዘብኩ በኍላ
Oolala!! እንዲያው ዝም ብዬ Oolala!!
የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ
ቅቅ ቅቅ ቅቅቅቅ
ድንቄም የለ መተዋወቅ
ቢሉት ይሻል ነበር ይልቅ
የኔ ፉንጋ እንተናነቅ
ተያይዘን እንተላለቅ ::
የሆነውን ቢሆን መድረኩ
መቼም ከመጎብኘት አልቦዘንኩ ::
በፍቅር ሰይፍ የተቀላ
የነፈዘ ነሁላላ
አሊያም አታላዩ ሁላ :
ገርል ፍሬንዴ ኮብልላ
ሚስቴ በ dollar ተደልላ
አልጠጣ እህል አልበላ :
እ ...
የባሌ እቃው እ -ን -ስ ብላ
መሄዴ ነው ወደሌላ
ልብ ከሚያርስ ሸበላ
እያሉ ይጭሩብናላ
መንጋ የሴሰኝነት ንክ ሁላ ::
ሚስቴ ሆዴ የኔ ገላ
ባታውቅም እኔን በድላ
ልተዋት ነው ይለናላ :
ምን ላርግ ታዲያ ....እቃዋ ቦርቅቋላ
ሞኒካ ወይ ትትና በሉኛ እስቲ መላ
መፍትሄ አምጡ blah blah blah blah
Debzi wrote:እድል wrote:
እንዲያ ቢሆን ደሞ እንደዚ
ስትለው ማድሞዜል? ደብዚ
ይላታል thank you! now I see!
Oh now I really really see!
እድል
የኔ ስም mentioned የሆነበትን አርስት አይኔ እያየ ወደ ሁለተኛ ገጽ አላስኬደውም መቸም::
በተጨማሪም የእድልን የፈጠራ ስራ ለማመስገን ያህል ነው::
Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር
Users browsing this forum: Google [Bot], Google Adsense [Bot] and 4 guests