Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)
by ዋናው » Tue Mar 28, 2006 5:27 pm
ሠላም አንባቢያኖቼ እንኳን ወደ አቆማዳዬ በሠላም መጣችሁ:
እዚች አቆማዳዬ ውስጥ
=>ግጥሞች
=>መጣጥፍ
=>ወግ
=>እንዲሁም የተለያዩ የእርሳስና የከሠል ንድፎች, የቀለም ቅቦች (በርግጥ አሁን ዋርካ ምስል ማሳየት አቋርጣለች)
ያገኛሉ::
አስተያየቶቻችሁ ይጠቅመኛል:
የአምዱ መግቢያ ርዕስ ላይ የተፃፈዉን ለማግኘት ወደመጨረሻው ገፅ ይዝለቁ
መልካም ንባብ
ከብዙ ብዙ ማክበር ጋር
ዋናው
Last edited by
ዋናው on Sun Nov 20, 2016 2:18 pm, edited 69 times in total.
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by ዋናው » Tue Mar 28, 2006 6:09 pm
ሌሊቱ_________________________________
ራሱን አጥቁሮ
ንፋስን አክርሮ
ጀንበርን አይቶ ላይውቅ
-በጨረቃ ብርሀን ተማሮ
ሰካራሙን አስወግሮ
ነጣቂውን አስኑሮ
ህልማለም ቀኤዬውን
-በወሲብ አደናብሮ
ገመድ አልባ ውሻን
-መንደሩስጥ አጉሮ
አያሌ ድርጊትን በስልጣኑ አድርጎ
ዝንታለም ጨልሞ
ከጥቀርሻ ጠቁሮ
ንጋትን ላይፋለም
ጀንበርን ላያጭልም
ትላንት እንደመሸው ዛሬንም ጨልሞ
የጸሀይን ጭላንጭል አፍሮ ተሽኮርምሞ
ነውርን ሊጋብዝ ጀንበርን አክትሞ
ይመጣል ሌሊቱ
አይቀርም መምጣቱ
የማታ ውላጁ በዛ በጡቅረቱ
ኦገስት 30 2002-ደቡብ ኮሪያ
ዋናው
________________________________
የረፈደ ፍቅር
ሲጥወልግ አበባው
-ሲሙዋሽሽ ቅጠሉ
በእምባ የራሱት ቃሎች
-ደብዳቤዎች ሲጣሉ (ጣ-አይጠብቅም)
ፎቶሽን አውርጄው
-ስሕሎች ሲሰቀሉ
አንቺን ልርሳ ብዬ
ሲጋራዬን ጠቅልዬ
ቢራዬን ጨብጬ ሆዴን ሁሉ ጥዬ
ፊቴም ቀጭሞልሽ ያረጀው መስዬ
ወዳንቺ ላልዞር
-ከጊዜ ጋር ምዬ
.
.
.
ዛሬ ድምጽሽን ብሰማው
ፈገግታሽን ባየው
ጥላነትሽን ባስተውለው
የትላንት መዳፍሽ
-እጄን ቢጭብጠው
ልቤም አስተውሎሽ
-ጠረንሽን ቢያወሳው
.
.
.
እውነት እልሻለሁ
በጣም ነው
የ
ረ
ፈ
ደ
ው..............................::
ብሪታኒያ
ዲሴምበር 20 2004
ዋናው____________________________________::[/list]
Last edited by
ዋናው on Mon Oct 06, 2008 9:57 pm, edited 1 time in total.
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by ዋናው » Wed Mar 29, 2006 4:24 pm
ደሜን የቀዱኝ ለት
ሽንቴን የወሰዱ ለት
አልጋው ላይ ጋድሜ
-አየር ስመጠምጥ
የልቤ ሩጫ በመስመሮች ሲያምጥ
ዶክተሩም አፍጥጦ
-ትርታዬን ሲያዳምጥ
ጢጥ
ጢጥ
ጢጥ
ጢ________________________ጥ
ስጋዬ መሬት ስቦት
ነፍሴም ተሰናብቶት
ደምና ስጋዬ 'ማይፈራርስ መስሎት
አንደበቴም ጠፍታ
ኑዛዜንም ትታ
ብቻ ዓይኔ ብርሀን አይታ
ፈጣሪን መላክታ
መኖር መኗኗርን
-ለነገ ጎምጅታ
ተመለሰች ነፍሴ
-ልመናዬን ሰምታ
ዋናው______________________________________::
Last edited by
ዋናው on Wed Mar 29, 2006 6:38 pm, edited 1 time in total.
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by ዋናው » Wed Mar 29, 2006 6:28 pm
ላልቃሽ ማን ያለቅሳል?
ሙሾ ሲደረድር ደረት እያስመታ
ራስ አስመልጦ ሀዘን ሲያበረታ
ነጠላ አስዘቅዝቆ ፎጣን እንደኩታ...
ዝናተለም ሲያስነባ
ያዘን ሰውን ሲያባባ
ጊዜ ተገላብጦ
-ዛሬ ቀኑ ሆነና
ያዜመለት ሞት እርሱንም አየና
እሱም ሞተ ተራውን
-ቀኑ ደረሰና
ታዲያ ማን ሙሾ ያውርድ?
ማን ያዚም
-ማን ያስኪህድ ?
ያፈር ግብሩን አፈር
-ያለ ዜማ እንዴት ይስደድ......?
ዋናው__________________________::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by በጎሲያ » Thu Mar 30, 2006 8:03 pm
ዋው...............................ዋናው
እቺ ሰፈር ደግሞ መቼ ተከፈተች አላየዋትም ነበር
አሪፍ ትመስላለች ከቀጠለች
........ጎሲያ
-
በጎሲያ
- ጀማሪ ኮትኳች

-
- Posts: 93
- Joined: Mon Dec 29, 2003 8:48 pm
by ዋናው » Fri Mar 31, 2006 12:33 pm
የሎከስነው ሻማ ካልደመቀ
ወይ በንፋስ ኪልኪላ ካልሳቀ
ለራሱ ብቻ አምብቶ ካለቀ
ኪሳራ በኪሳራ
አለቀ
ደቀቀ::
ዋናው______________________________::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by ዋናው » Fri Mar 31, 2006 12:57 pm
በየኔታ ጉሮሮ ጠጅ ይንቆርቆር ብለን
በኛ ጾም ጉሮሮ
-ፊደል አንቆርቁረን
አሀዙንና ሆሄውን
-በስንጥር ፈልቅቀን
አርብን ሳናደርስ
-ስንፍናን መንግለን
ፈተናውን ከወደቅን
-"እኔን ያየህ" ብለን
ዳዊትና አቦጊዳን
ደግመን አስቆጥረን
ትላንት እንዲህ አልፎ
ዛሬን ደረስንና
ሳይንስና ጂኦግራፊን
መማር ግድ ሆነና
የትላንቱን ፊደል
-ወዲህ ብናቀና..............
ፊደልም መጣ አሉ
-ላቲን ተሄደና
ያ ሁሉ ከንቱ ትምርህርት
-ባክኖ ተረሳና
ያፍሪካ ጌጥ ፊደል
-በቁቤ ቢቀየር
እንደ ቄስ ተማሪ
-እኔም ብደናገር
አ.ባ.ዳ.ጫ ብለው
ፊደላት አንጋግተው
ቢያስጠኑኝ የሰዉን
-የኔን እንዴት ልተው?
ውስጤ የበቀለውን
ከኔጋር ያደገውን
.
.
.
ላቲኑ አበሻ መባሉን ጠልቼ
በማላውቀው ፊደል
መማሩንም ትቼ
እየው ዳዊት ላይ ነኝ
ሁሉንም ፈርቼ
=======(ቁቤ ላበሳጨው የኦሮሚያ ተማሪ)=======
ዋናው____________________________::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by ዋናው » Sun Apr 02, 2006 5:50 pm
____ቀዝቃዛ ጸሀይ____
ሰማይ ደማናን አስቃ
ምድርን አብረቅርቃ
ዓይንን ወግታ
-ጨረሯን አተልቃ
ጉምድማጅ ጉሞችን
-በብርሀን መስመር አንቃ
ምነው ታዲያ ያልሞቀች?
ቆዳን ያላሳቀች
ዓይንን እየወጋጋች
"ለብ" እንኩዋን ያላለች?
እቺ ጸሀይ ናት ስዕል ነች?
ውርጭን እያዘነበች
.
.
.
ምነው እዛው ጠፍታ
-ዳምና በቀረች
እርጥብ ልብሴን 'ንኩዋን
-ማድረቅን ካልቻለች
ፌብርዋሪ 20 06
(ብሪታኒያ)
ዋናው___________________________::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by አብዮት » Sun Apr 02, 2006 7:09 pm
ገብሬልን ሸላይ ናት::
-
አብዮት
- አዲስ

-
- Posts: 18
- Joined: Thu Dec 18, 2003 12:44 pm
by ዋናው » Mon Apr 03, 2006 2:21 pm
ዱባ ጡት አጉጠው
ዱቄት ተነስንሰው
ቅንድብ ከናፍርትን
-ቀለማት አጊጠው
ጭንና ባታቸው
-አይኖቻችን ላይ ፈጠው
ሸቀጥ ወሲባቸውን
-በመስኮት አስተዋውቀው
ስሜት ሊያከራዩ
ዘሙተው እጅ ሊያዩ
.
.
.
ሜይ 29 2003
ሴንት ፖል መንደር
ሀምቡርግ__ጀርመን
ዋናው___________________________::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by ዋኖስ » Mon Apr 03, 2006 4:08 pm
ሸላይ ነች! አለ ሰዉየዉ:: ሸላይ-ሥንኝ::
-
ዋኖስ
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1552
- Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
- Location: Mars
-
by ዋናው » Mon Apr 03, 2006 5:06 pm
ሐቅ ምንድነው ዘልዓለምስ ምንድነው እግዚያብሄርስ____? የሚሉት ዋላ ቀር ሙግቶች ተፈላሳፊው ማነው ይህንን የማወቅ አቅም አለው ወይን? ኗሪስ ነው ወይ ከኖረስ መኖር ምንድነው? በሚሉት ጥያቄዎች ተትክቶም አያሌ ዘመናትም ከየት እንደመጣንና ወዴት እንድምንሄድ የምናውቀው ነገር የለም::(absurd) ጨለማ ነው በዚህ አንኩዋር ሀስብ ፍለጋ አኪያሄድ
ለነገሩ ኮተት ነውም የስራ አጥ ጭቅጨቃ መኖር መደሰት ለየሰዉ እንዴትና ምን ነው? ይሄንን ያሰብኩኝ ቀን ያገሬ ድሀ ታዛው ስር ተኝቶ የዛሬን እህሉን ሳያውቅ ብቻ እንቅልፍና ድብርቱ ከላዩ ላይ እንደሌቱ ጨለማ ሲገፈፍ
ፈገጋትው ይበራል ደስተኛ ነው ለርሱ ኑሮ ቀላል ነው ዛሬን ማምለጥ ከዛም ነገ የራሱ ጉዳይ ________---
ተስፈኞችና ነገን አስቢዎችስ ሳቁ? እኔንጃ ምናይነት ሳቅ? በርግጥ ነግን ይተነበያሉ(ፕሪዲክት) ያደርጋሉ ለነርሱ ኑሮዋቸው በጋር የተወጣጣ ቅንብር ነው ታዲያ ውበት አለው? በውነት ይሄንን አላቅም::
የማውቅና የዕውቀት አድማስን ማስፋት ደስ ይላል በርግጥ ግን ሁሉም ዳቦን ቢጋግርንጂ ፈገግታን አይሰራም ቢሰራም ....እኔንንጃ
ኤግዚሽቲያኖች ምን አሰቡ ምንስ አረጋገጡ? ያ ቅድም ስላልኩት አብታም የድሀ ሰው ሳቅ ያገኙት አለ? ሚስጥር ነው ወይም አይገባንም::
መቀዣበር ደስ ስለሚለኝ ነው በዚች የቁጭ ምድር ቅቅቅቅቅ
ዋናው ነኝ በራሴው ሰፈር____________________::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by ዋኖስ » Mon Apr 03, 2006 5:53 pm
እስኪ ሥለ "አብሰርዲስት" አልበርት ካሙስ ትንሽ አዉጋን ቅቅ
-
ዋኖስ
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1552
- Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
- Location: Mars
-
by ዋናው » Wed Apr 05, 2006 2:04 pm
ዓ
ይ
ን
__________
ልቡ ያፈቀረ ሲጠቃቅስበት
ውስጡ ሕ ዝ ን ያለ
-ከፍቶት ሲያለቅስበት
በለሱ የቀናው በሳቅ ሲያገጥበት
በደስታ በርቶለት.....
ንዴት የሸተተው
-ሰብቆ ሲቆጣበት
ሁሉም ያላማረው
-ሲገላምጥበት
ምሁርነት ያማረው
ፊደል ሲቆጥርበት
.
.
.
የባ_____ሰበት መጣ
ዓይኑን መንግሎ ያወጣ
ዕራቱን ለመድገም
-ብ ር ሀ ኑን ያጣ
በዱላ ተመርቶ
_ጭለማ ውስጥ የመጣ
እነዚህን ዕይታዎች ባይ
-ዓይኔም ተጨፈነ እንቅልፌ ሳይመጣ
::
ዋናው___________________________::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by አብዮት » Wed Apr 05, 2006 7:49 pm
ቅቅቅቅቅ
አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም አሉ
እስቲ ለጥቀው አባ ተመችቶኛል ያንተ ሰፈር
የአቢዮት አደባባዩ
አብዮት
-
አብዮት
- አዲስ

-
- Posts: 18
- Joined: Thu Dec 18, 2003 12:44 pm
Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
Who is online
Users browsing this forum: No registered users and 2 guests