by ወንድም » Fri Sep 01, 2006 2:45 am
እነሱ ከሄዱ በውሀላ አስተናጋጅዋ ስታልፍ አየዋትና የኔ እህት ሂሳቡ ስንት ነው አልኩዋት በጣም የደስ ደስ ያላት ቀላ ያለች ወጣት ነች ""ቆይ አንዴ'' ብላኝ ከኔ በፊት የነበሩሩትን ሰዎች ሂሳብ ተቀብላ መጣች
''ሻይያችንን ወደድከው'' አለችኝ አነጋገርዋ ድሮ እንደምንተዋወቅ ነው
ሻይውስ በጣም ደባሪ ነው ለዛ አይደል በየቀኑ የምመላለሰው
አሁንም በጣም ፈገግ ብላ
''አንተ ደሞ ትገርማለህ አዎ ጥሩ ነው እንደማለት ለዛ ነው በየቀኑ የምመላለሰው ከአጠጣጥህ እኮ ጠብታ ጭላጭም አላስቀረህም እረ እንዳውምኮ አለቃዬ ብርጭቆ መላስ ክልክል ነው በይው ብሎኝ ነበር ""
እውነትም የጠጣውበት ብርጭቆ ንጹህ ያልተቀዳበት ይመስላል ብርጭቆውን አይቸ ከልቤ ሳቅኩኝ
""በጣም ተጫዋች ቀልደኛ ነሽ ለምን ኮመዲያን አትሆኝም አልኩዋት''
''የግብ እደል የልሽም ብለው አልቀጠሩኝም
ለመሆኑ ከየት አገር ነው የመጣሀው''
''ለምን እንደዛ አልሽ ከውጭ የመጣው እመስላለው አልኩዋት
''በደንብ'' አልች''
''በምኔ'' አልኩኝ እራሴን ከላይ ወደ ስር ዝቅ ብዬ አይቼ ስትነገር አንድ አንድ ጥራዝ ነጠቅ እንግሊዘኛ ጫማህ ሰውነትህ.....'' እያለች ስትዘረዝር
''ስው ከውጪ እንደመጣ ታውቂያለሽ ከየት እንደመጣስ ማወቂያ ዘዴ ታውቂያለሽ?'' ስላት
ቀዥቃዣ ነገር አይደለችም በችኮላ
''አዎ አዎ ብዙ ጊዜ ከአውሮፓ የመጡት ከጫማቸው በስተቀር አለባበሳቸው ጸጉራቸው አጭር ነው ጢማቸውን በየቀኑ ይላጫሉ መሰለኝ ብቻ ሁሌ ኒት ናቸው ግን ገንዘባቸው ላይ በጣም ይጠነቀቃሉ''
""ገብጋባ ናቸው ልትይ ፈልገሽ ነው?'' አልኩኝ
ገብጋባ ብልህስ አባህና አልች
""ከአሜሪካ የመጡትስ'' ብላት
''እነሱ ደግሞ ጥሩ ስኒከር ጫማ ያደርጉና ልብሳቸው ግን ንጹህ ሆኖ መናኛ ነገር ነው ሲናገሩ ደግሞ ይቸኩላሉ ግን ደጎች ናቸው ሁላቸውም ከአውሮፓም ይሁን ከአሜሪካ የመጡት ሴሰኞች ናቸው ልበል አንዳንዶቹማ በየቀኑ ሴት መቀያየር እነዚ የኛዎቹ ደግሞ ገና ለገና ከውጭ መጣ ብለው ነገ ጥልዋት ለሚሄድ ና ግባ ቀሚሴም እግሬም ክፍት ነው ይላሉ እዛ ሴት የለም እንዴ እዚ ስሰራ ስንቱን አየው መሰለህ'' አለች በአ
እንደቅድሙ አትስቅም ነበር
እኔም ሆዴ ተነካና
''እውነትሽን ነው ስንት ወሮበላ አጭበርባሪ አበሻ አለም ላይ አለ መሰለሽ ነውረኛነታቸውን እዚህ መጥተው ይፈጽማሉ''
ብዬ የሆነ ሂሳቡን ሰጠዋትና
''መልሱን ውሰጂው አልኩዋት''
ገንዘቡን ከተቀበለችኝ ብውሀላ
እሄማ ይበዛብኛል አለች
ግድ የለም ይገባሻል ለጫወታሽ ጭምር ነው አልኩዋትና ከዛ ወጣው
ከመጨለሙ በፊት ቤት ገባው እናቴ ገና ስገባ ''ይልመድብህ ጎሽ ተባረክ ልጄ በጊዜ መጣህ'' አለችኝ
ደህና ዋል እማዬ አልኩዋት
ደህና እግዚአብሄር ይመስገን ልጄ አለችኝ በስስት እያየችኝ
ከአጅሪት ጋር ተጋብተን የናቴን ግማሽ ከወደደችኝ በቂዬ ነው ብዬ አስብኩ ቴዲ እውነቱን ነው የናቴን ምትክ ስጠኝ ያለው
ብዬ ሳስብ እናቴ ''ጀመረህ ደግሞ ለብቻህ በቀን ህልም ትዋዥቃለህ ሳታገባ ሳትወልድ የምን ሀሳብ ነው ልጄ''
''እማዬ አንቺ ይመስልሻል እንጂ እኔኮ ካንቺ ጋር ቁጭ ብሎ መጫወት ሌሎች ቅቤ ነክረው ከሚሰጡኝ አንቺ እንጀራ ነስንሰሽ የሰጠሽኝ እንደሚጣፍጠኝ ታውቂያለሽ እማዬ'' አልኩዋት
እውነቴን ነው በናቴ የምጠላው ነገር ያለ አይመስለኝም i am crazy about this women i love her so much she feels the same way about me i get guarante motherly love but we never tell one onother i love you action speak better than word i guess
በነገራችን ላይ እንዚህን ሁለት ቃላቶች ውድፊትም ወደው ሁዋላም አንብቡ ትኩሥ ብሥኩት
ይቀጥላል
God bless america and the rest of the world.