አገባው

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

አገባው

Postby ወንድም » Mon Aug 28, 2006 7:41 am

ከዚህ በፊት ጥሩ ስራ ቢኖረኝም እኔ ጥሩ ሰው ብሆንም እድሜየም early thrites ፋራ ሳልሆን እዚህ አሜሪካ ያሉ ያበሻ ሴቶች እድል እንዳልሰጡኝ ስሞታየን ለናንተ አሰምቼ ነበር
እኔ ወንዱ እንዴት እንዴት ሚስት አጣለው ብየ ሳስብ ሳስብ የዛሬ ዘጠኝ ወር ገደማ አገር ቤት ሄጄ እያለው የጎረቤታችን ልጅ ተግባቢዋ ትዝ አለችኝ ብዙም ሳልዘጋጅ ለማዘርም ሳልነግራት ወደ አዲስ አበባ አመራው ማዘር ምነው በደህና ነህ የመጣሀው አለችን ናፈቅሽኝ አልኩዋት መምጣቴ ደስ ቢላትም ግን በጣም ገርሞዋታል በመጣው በሁለተኛው ቀን ልጅትዋና ማንም ሳይሰሙ ከባድ ታላቅ እህቴን የመጣውበትን ጉዳይ ነገርኩዋትና ለሌላ ሰው እንዳትናገር አስማልኩዋት ምክንያቱም ወረኞች ከሰሙ በሆነ ምክንያት ሀሳቤን ብቀይር የሰዋ ሞራል ይነካል.እህቴ በታም ደስ አላት ሰለልጅትዋ ጥሩ ጸባይ ስለትህትናዋ ሁሉ ከነገረኝ በውሀላ ለማንኛውም ሳምንት ስጠኝና የበለጥ ላጥናት አንዳንድም ወሬ ላጠያይቅ አለችኝ .ይቀጥላል
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ወንድም » Tue Aug 29, 2006 2:23 am

እኝ ቤት ቤተኛ ስለሆነች ወጣ ገባ ባለች ቁጥር አተኩሬ አያታለውና በሀሳብ ጭልጥ በዬ እሃዳለው ጭንቅላቴ እስኪበጠበጥ ነበር የማስበው እንቢ ብትለኝስ ካገባዋት በውሀል ጸባይዋን ብትቀይርስ እዛ ሄዳ ዞር በል ብትለኝስ የሆነ ያልሆነውን እያሰብኩኝ እፈዝ ስለነበር ማዘርም ሳትጨነቅ አልቀረችም አንድ ቀን ማዘር ቡና ልታፈላ ከሰል ስታቀጣጥል አሁንሽ ደክሞሻል ያቺ ጎረቤታችን ታግዝሽ ስላት አተኩራ አየችኝና "' እውነትህን ነውኮ እስዋ የተባረከች ባለሙያ ቆንጆ ደግ ልጅ ሲደክመኝ የምትረዳኝ እውነትህን ነው ልጥራት'' አለችና ይዛት መጣች እኔ በዚ ሰአት በሀሳቤ ምን እያደርኩኝ ነው ከአፌ ባመለጠኝ ነገር ቆጨኝ ልጅትዋ ቡና እያፈላች እያለች ማዘር ፊትዋ ላይ የደስታ ምልክት አይባታለው ልጅትዋን እንዴት እንደማያት ታጠናለች እኔ ደግሞ ኖርማል ለመሆን እሞክራለው ግን አልቻልኩም ቡና ካለቀ በውሀላ ልጅትዋም ቤትዋ ሄዳ ምርጫህ በጣም ጥሩ ነው ሳትቀደም ቅደም አለችኝ እማዬ ተይኝ ባክሽ የወደዳት ያግባት አልኩዋትና ከቤት ወጣው .
እህቴ በአምስተኛው ቀን አካባቢ አግባት ምንም ነገር ፈልጌ አጣውባት አለችኝ እኔም ከመምጣቴ በፊት የኤድስ ምርመራ አድርጌ ማለፌን ነገርኩዋትና ደስ አላት
የዛኑ ቀን ማታ እኔና እህቴ ሆነን የመጣውበትን ጉዳይ ስነግራት ማዘር በጣም ከመደሰትዋ የተነሳ ቤቱን በእልልታ አቀለጠችው ጎረቤቶቻችን አንድ ሶስት የሚሆኑ ምን ተገኘ ብለው መጡ ከመጡትም አንድዋ ያች ልጅ ነበረችና ማዘር አገላብጣ ጉንጭዋን ሳመቻት እህቴ በሳቅ ሞተች እኔ በአፍረት የት ልግባ ምን ተገኝቶ ነው እልልታው እኔንስ መሳሙ ሎተሪ ደረስዎት እንዴ አለች አጅሪት ማዘር ነገር ከማበላሸትዋ በፊት እሕቴ ''አይ ጠፍቶ የነበረው የማዘር ወርቕ ስለተገኘ ነው አለች ኦ ለዛ ነው አልች
ይቀጥላል
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ቸኮሌት1 » Tue Aug 29, 2006 6:17 am

:lol: :lol: :lol: አይ ወንድም'' የማዘር ወርቅ ነው ''አላቹ :lol: :lol: ግን ያልገባኝ ልብወለድ ነው የጀመርከው ወይስ የራስህ እውነተኛ ታሪክ?
ONE LOVE
ቸኮሌት1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 158
Joined: Sat May 20, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

Postby ህይወት » Tue Aug 29, 2006 9:00 am

ጠፍቶ የነበረው የማዘር ወርቅ ስለተገኘ ነው??? ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ይገርማል...እውነተኛ ታሪክ ነው ወይስ ልብወለድ??? የኛ እናቶች እኮ ስያሳዝኑ....ፍቅር....መመቻቸት....ኢንተረስት...ምናምን የሚባሉት ነገሮች እኮ የትዳር መስፈርት ዉስጥ አይገቡም በቃ እነሱ....የሆነ ጎታታ ቀሚስ ለብሳ እቤት ዉስጥ ቡና ምናምን ስትቀቅል ከዋለች በቃ ለትዳር ተስማሚ ናት ብለው ነው የሚገምቱት.....ለነገሩ አንተም እኮ ወንድም ከናቶቻችን በምንም አልተሻልክም....ልጅትዋን ዴት ሳታረጋትና ጠልቀህ ሳታውቃት በቃ እቤት ዉሥጥ ስትንደፋደፍ ስለምትውል ሚስት ትሆነኛለች ብለህ ያሰብከው??? አንተ እኮ መፈለግ የተያያዝከው ሚስት ሳይሆን የሳሎን ጌጥ ነው
ህይወት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 167
Joined: Mon Dec 15, 2003 5:11 pm

Postby ወንድም » Wed Aug 30, 2006 1:48 am

ቸኮሌት ታሪኩ እውነተኛ የኔ ታሪክ ነው
ህይወት ማዘር እኮ እችን ልጅ ከህጻንነትዋ ጀምሮ ነው የምታውቃት ትላልቅ ሰዎች እንደ አላዋቂ አትቁጠራቸው በጣም አስተዋዮች ናቸው ለዛም ነው በብዛት በቤተሰብ ተፈልጋ የተገኘች ከሆነ ትዳሩ የሚዘልቀው እኔም ያለፈው የመጣው ጊዜ በደንብ አጥንቻታለው ለምንም አላሰብኩዋትም ነበር ግን ni the back of my mind i loved her but i was not honest with my self may be because i thought it wouldent work የግድም አብረን መውጣት አላስፈለገኝም ሁለት ሶስቴ እህቴ ነይ እያለቻት አራት ሶስት ሆነን ኬክ ቤት ምናምን ሄደናል የአልጋ ሙከራ የምትል ከሆነ ከሌላ ሴቶች ጋር ከሆነ ቀድሞ ነገር መቸ ነው የምወስባት ነው ጥያቄዬ በጣም ችኩል ነኝ ከዚች ጋር ግን በፍጹም ለዛ አልተመኘዋትም
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ወንድም » Wed Aug 30, 2006 3:06 am

በሚቀትለው ቀን ጠዋት ስነሳ ያባቴ ወንድም አጎቴ ከማዘር ጋር ቁጭ ብለው ቡና እይጠጡ የድሮውን ምናምን እያነሱ ይቀዳሉ ከሳመኝ በውሀላ
እናትህ የምስራቹን ነገረችኝ ከቤት ከመውጣትህም በፊት ብዬ ነው በጠዋት የመጣውት እሁን ገና የወንዶች አሰብክ ያለፈው የመጣህ ጊዜም ብመክርህ አሻፈረኝ አልክ አንተ ለካ የሆድህን በሆድህ ይዘህ ነው አየህ ነብሱን ይማረውና ወንድሜ አባትህም እናትህን የመረጠለት ሰው የለም አባታችን ለሌላ ሴት ሊድረው ፈልጎ እሱ ደሞ እስዋ ካልሆነች ሞቸ እገኛለው አባታችንም ብዙ አልተከራከረም እንደዛ ነው የምልህ ምናምን ሲል እናቴ የአባቴ ስሙም ሲነሳ እንባዋ ስለሚመጣ ተነስታ ጉዋዳ ቆይታ መጣች .
እናም በአባትህ ፈንታ እኔና እናትህ ሽማግሌዎች እንልካለን የውሸታቸውን እናስብበት ስለሚሉ ቶሎ እንጠይቃቸው ልጅትዋንም አቃታለው ጨዋ ነች '' አጎቴ ነገር ለነገ አያውቅም ችኩል ያዘው ጥለፈው ነው
እኔ በዚህ ሰአት ልክ ብለሀል አጎቴ ሽማግሌ ትልካለህ ግን መጀመርያ የልጅትዋን እራስዋን ልጠይቃት'' ስል
''እንደትልቆቹ ጀምረህው አሁን ደግሞ ወደ ልጆች ቀየርከው አለኝ'' በአዘኔታ
''ቤተስቦችዋ እሺ ብለው እስዋ እንቢ ብትልስ በቤተሰብ ግፊት እሺ ብላ ያለምኞትዋ ትዳር እኔም አልፈልገውም ስል
አጎቴ እራሱን ነቀነቀና ''እንኩዋን አንተ ካሜሪካ የመጣሀው ይቅርና ምሳውን በልቶ እራቱን ለማይደግም ምስኪን እሺ ይላሉ''
እሱን ማሳምንበት መንገድ አጣው ከዛ እህቴ ''ለወደፊት እንኩዋን መጀመርያ ለምን ግን እኔን አልጠየከኝም ብላ እንዳትወቅሰው'' ስትለው
''እንዳላቹ እሺ'' ብሎ ተመለሰ
የዛኑ ቀን ከሰአት በውሀላ እኔ እህቴና አጅሪት ኬክ ቤት ሄድን ቁጭ ብለን እያለን ሲስተር መጸዳጃ ብላ ሄደች በዛ ሰአት ኮምፒይተር እንደምትማሪ አውቃልእው ከዛስ ምን ታስቢያለሽ ስላት እኔ እንጃ ከትገኝ በዛው ስራ ባገኝበት አለችኝ
'' ትዳር ነው የሚሻለው'' አልኩኝ ድምጼን ቀነስ አድርጌ ''ምን አልክ'' አለች
አፌ ተለጎመ ስንትዋን ጀንጅኜ መስማት የሚፈልጉትን ሁሉ አስረድቼ ገልጻ አድርጌ በአፍ ካራቴ ጥዬ በቡፋ ድር ጠፍንጌ አስሬ የፈለኩትን እንዳላገኘው እዚች ጋር ስደርስ ግን አፌ ተለጎመ አሽነፈችኝ
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ደንቢያ1 » Wed Aug 30, 2006 5:38 am

ታሪክህ በጣም ይስባል ቀጥልበት አላህ ይርዳህ::
ደንቢያ1
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 13
Joined: Sat Aug 26, 2006 5:46 am

Postby ወንድም » Thu Aug 31, 2006 2:35 am

እና አንዳልኩዋችሁ i have lots of game when it takling to chicks i am on the top of my game it is not like yew baby yaw baby i make them lough by telling them some bs phony story but this one i didnit know what to tell har
ቢያንስ ቢያንስ የግድ ዳር ዳር ማለት አለብኝ በዬ አስብክ ስምዋን ለመጀመርያ አቆላምጬ ጠራውና
''እኔን የሰለቸኝ ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ""? ብየ ጠየቅዋት
ምንድነው ንገረኝ አለች
''እስኪ አንቺ ገምቺው አልኩዋት''
በግርምታ ነገር አየችኝና ''እኔ ምን አውቃለው ምን እንደሰለቸህ አሜሪካ ኖረህም ስልቸታ ብሎ ነገር አለ ስልችቱን ብስጭቱን ከቤተሰብ ጥገኝነቱን ስራ አጥነቱን ለኛ ተወውና በስራችን ገብተህ አታማርር የደላው ሙቅ ያኝካል አሉ'' አለችና ሳቀችብኝ ስትስቅ ጉንጭዋ ይሰረጎዳል ጥርስዋ በጣም ያምራል. በጣም ፈገግ ብዬ አይዋትና አሁንም በቁልምጫ ጠራዋትና
''አሜሪካ እሄን ያህል እናንተ እንደምታስቡት ሁሉ ነገር የተሙላበት አይደለም እርግጥ ነው የስራ ፈቃድ ካለሽ ሰርተሽ መኖር ትችያለሽ ግን እዚ ያላቹት አሜሪካ ሲባል እንደ መንግስተ ሰማይ ነው የምታስቡዋት'' ስል.
''አቁዋረጠችኝና እኔ በበኩሌ ከዚ ያን ያህል አላደንቃትም ከዚህ ግን ይሻላል ለምሳሌ እዚው ቁጭ ብለን ስንት የኔ ብጤ ነው የለመነን እነዚህ ብዙዎቹ እውነት ልመና ይወዳሉ መስሎህ ነው ግን ሌላ አማራጭ አጥተው ነው እንጂ''አለች
እኔ በሆዴ ''ለዚህም ነው እኮ ያፈቀርኩሽ የኔ አስተዋይ የኔ እንደበተ ርቱእ አልኩኝ'' በሆዴ
እሱስ ልክ ነሽ የጠየኩሽን ግን አልነገርሽኝም ምን እንደሰለቸኝ
'' ሆ..... አንተ ሰው እኔ ምን አውቃልው ብለህ ነው ለምን ግን አንተው እራስህ አትነግረኝም እኔ የሚያስጨንቀኝ ነገር ካለ ለስው ሳማክር ይቀለኛል ስለዚህ አንተም ተንፍሰውና መፍትሄ እንፈልግለት አልችኝ''
ልክ ብለሻል እኔን የሰለቸን ብቸኝነቴ የኔ ነች የምላት አጋሬ የደስታዬና የሀዘኔ ተካፋይ የምትሆን የምወዳት ሚስት ስለሌለኝ ለብቻዬ እሄን አስልቺ መንገድ ማዝገሙ እጅ እጅ ብሎኛል ለዛም ነው ቶሎ ተመልሼ የመጣውት እሺ ካለችኝ የወደድኩዋትን ልጅ በወግ በማእረጉ ለማግባት ስል
በጥርጣሬ አይን አየችኝና አፍራ ወደ መሬት እያያች ዝቅ ባለ ድምጽ ''
""እሱስ ልክ ነህ'' አለች በዚህ ሰአት ሲስተር መጥታ ስለነበር ""ወይኔ ረስቸው እማዬን እልቆይም ብያት ነው ከቤት የወጣሁት ብላ ተነሳች ሲስተርን እንሂድ'' አለቻት
""አንቺ ደሞ ቆዪ ማዘር ከኔ ጋር እንደሆንሽ ካውቁ ምንም አይሉሽም'' ስትላት
''ዛሬስ ትቆጣለች የግድ መሄድ አለብኝ'' ስትል
ከዛ እኔ አይ ግድ የለም ሂዱ እናንተ እኔ በዚው ሌላ ቦታ ስለምሄድ እናንተ ሂዱ አልኩኝ አጅሪት ለምን መሄድ እንደፈለገች ገባኝ አፍራለች እንደማያስቸኩለኝ ስለማውቅ

''ደግሞ ስትዞር ውለህ ማታ እንዳትመጣ ስለዛ ነገር በውሀል እንጫወታለን ብላኝ ሄደች አጅሪት ቻው ብላኝ ፈንጠር ብላ ቆማ ሲስተርን ስትጥብቃት ስለነበር አልሰማችም
ይቀጥላል
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby እድላዊት » Thu Aug 31, 2006 7:02 am

ትላልቅ ሰዎች እንደ አላዋቂ አትቁጠራቸው በጣም አስተዋዮች ናቸው ለዛም ነው በብዛት በቤተሰብ ተፈልጋ የተገኘች ከሆነ ትዳሩ የሚዘልቀው

ሰላም ላንተ ይሁን ወንድም

ታሪኩን በጉጉት ከሚከታተሉህ አንዱዋ ነኝ ደስ የሚል ነው ግን በዚ ባሰፈርከው ነገር ላይ ካንተ የበለጠ ስላንተ ህይወት ባላውቅም ትንሽ ጥንቃቄ ብታረግ መልካም ይመስለኛል በርግጥ እናት አባት ቤተሰብ አስተዋይና ከኑሮ ልምድ ከኛ የተሻለ ምርጫ እና አስተሳሰብ እንዳላቸው አልክድም ነገር ግን በገዛ ፋሚሊዬ በማውቃቸው ወንዶች ላይ ይህ በቤተሰብ ጋብቻ የእከሌ ልጅ የጨዋ ልጅ ተፈልጎ ተድረው ግን ትዳሩ ሳይሰምር ብዙ ጭቅጭቅ እና በሽታ ያመጣባቸው ካለእድመያቸው የደም ብዛት የስኩዋር በሽተኞች የሆኑ ስለማውቅ ጥንቃቄ አይለይህ ብዙ ሰው የሚፈልገውን እስኪያገኝ አንተን መስሎ መኖር እንደሚችል አትዘንጋ እና እያጠናው ነው ብለሀል በተገቢው መንገድ በደንብ አጥና ትዳር ቀላል ነገር ስላልሆነ
በተረፈ ግን አሪፍ ጽሁፍ ነው እስቲ መጨረሻውን በመልካም ያሰማን
ሶሪ ግን ጥልቅ ብዬ ይህንን አስተያየት ስለሰጠው ብዙ ችግር የደረሰባቸው ሰዎችን ስላየው ነው
አክባሪህ እድል
hany
እድላዊት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 283
Joined: Sat Nov 27, 2004 12:49 pm
Location: united states

Postby ወንድም » Thu Aug 31, 2006 9:05 pm

ደንቢያ አመሰግናለው ለጥሩ አስተያየትሽ(ህ)

እድላዊት ብጉጉት ስለተከታተልሽው አመሰግናለው ቤተሰቦችሽ ከማይሆን ሰው ጋር ገጥመው ያልነበራቸውን ህመም በመግዛታቸው ከልቤ አዝናለው.የኔም በጣም የምወደው ጉዋደኛዬ አንዲት ወረቀት ከሌላት መጥፎ ልጅ ጋር ለወሲብ ብቻ በሎ ተጠግቶ ልጅትዋ ማርገዝ ከዛ አማራጭ አልነበረውም አብረው ቤት ተከራዩ ግን በጣም ደስ የምትል ቆንጆ ሴት ልጅ ወለደች ልጅትዋ ከተወለደች ከሁለት አመት በውሀላ ጨቅጭቃው በግድ ፈረመላት ትዳር በግድ ይሉሻል እሄ ነው ሢጣሉ ይመጣና ያላዝንብኛል ሲታረቁ ደግሞ የስደብኩዋትና የመከርኩትን ይነግራታል ስለዚህ ስለስዋ ከሆነ የፈለገውን ቢል ዝም ነው የሚለው የሚገርመው ልጅትዋ አሁን አስር አመትዋ ነው እኔን uncel ብላ ነው የምትጠራኝ ፈልፈላዋን በጣም ስለምወዳት እኔም ለዛች Bitch i have to show happy face
እቺ ያገርቤትዋ ግን ከላይ እንዳልኩት እኔም ሆንኩኝ ሆሉም ፋሚሊ አብጠርትረው የሚያውቁዋት ከድሮ ብዙ አወራው የዛች ቢች ነገር ሲነሳ ነውኮ ያ ከረፈፍ እንዳይሰማና ደሞ እንዳይነግርብኝ እናንተም አትንገሩት ሳቅ በሳቅ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ የንዴት ሳቅ አሁንም ሳቅቅቅቅቅቅቅቅ ወደ ዋንው ታሪክ በውሀላ እመለሳለው የምሳ እረፍቴ አልቀ
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ወንድም » Fri Sep 01, 2006 2:45 am

እነሱ ከሄዱ በውሀላ አስተናጋጅዋ ስታልፍ አየዋትና የኔ እህት ሂሳቡ ስንት ነው አልኩዋት በጣም የደስ ደስ ያላት ቀላ ያለች ወጣት ነች ""ቆይ አንዴ'' ብላኝ ከኔ በፊት የነበሩሩትን ሰዎች ሂሳብ ተቀብላ መጣች
''ሻይያችንን ወደድከው'' አለችኝ አነጋገርዋ ድሮ እንደምንተዋወቅ ነው
ሻይውስ በጣም ደባሪ ነው ለዛ አይደል በየቀኑ የምመላለሰው
አሁንም በጣም ፈገግ ብላ
''አንተ ደሞ ትገርማለህ አዎ ጥሩ ነው እንደማለት ለዛ ነው በየቀኑ የምመላለሰው ከአጠጣጥህ እኮ ጠብታ ጭላጭም አላስቀረህም እረ እንዳውምኮ አለቃዬ ብርጭቆ መላስ ክልክል ነው በይው ብሎኝ ነበር ""
እውነትም የጠጣውበት ብርጭቆ ንጹህ ያልተቀዳበት ይመስላል ብርጭቆውን አይቸ ከልቤ ሳቅኩኝ
""በጣም ተጫዋች ቀልደኛ ነሽ ለምን ኮመዲያን አትሆኝም አልኩዋት''
''የግብ እደል የልሽም ብለው አልቀጠሩኝም
ለመሆኑ ከየት አገር ነው የመጣሀው''
''ለምን እንደዛ አልሽ ከውጭ የመጣው እመስላለው አልኩዋት
''በደንብ'' አልች''
''በምኔ'' አልኩኝ እራሴን ከላይ ወደ ስር ዝቅ ብዬ አይቼ ስትነገር አንድ አንድ ጥራዝ ነጠቅ እንግሊዘኛ ጫማህ ሰውነትህ.....'' እያለች ስትዘረዝር
''ስው ከውጪ እንደመጣ ታውቂያለሽ ከየት እንደመጣስ ማወቂያ ዘዴ ታውቂያለሽ?'' ስላት
ቀዥቃዣ ነገር አይደለችም በችኮላ
''አዎ አዎ ብዙ ጊዜ ከአውሮፓ የመጡት ከጫማቸው በስተቀር አለባበሳቸው ጸጉራቸው አጭር ነው ጢማቸውን በየቀኑ ይላጫሉ መሰለኝ ብቻ ሁሌ ኒት ናቸው ግን ገንዘባቸው ላይ በጣም ይጠነቀቃሉ''
""ገብጋባ ናቸው ልትይ ፈልገሽ ነው?'' አልኩኝ
ገብጋባ ብልህስ አባህና አልች
""ከአሜሪካ የመጡትስ'' ብላት
''እነሱ ደግሞ ጥሩ ስኒከር ጫማ ያደርጉና ልብሳቸው ግን ንጹህ ሆኖ መናኛ ነገር ነው ሲናገሩ ደግሞ ይቸኩላሉ ግን ደጎች ናቸው ሁላቸውም ከአውሮፓም ይሁን ከአሜሪካ የመጡት ሴሰኞች ናቸው ልበል አንዳንዶቹማ በየቀኑ ሴት መቀያየር እነዚ የኛዎቹ ደግሞ ገና ለገና ከውጭ መጣ ብለው ነገ ጥልዋት ለሚሄድ ና ግባ ቀሚሴም እግሬም ክፍት ነው ይላሉ እዛ ሴት የለም እንዴ እዚ ስሰራ ስንቱን አየው መሰለህ'' አለች በአ
እንደቅድሙ አትስቅም ነበር
እኔም ሆዴ ተነካና
''እውነትሽን ነው ስንት ወሮበላ አጭበርባሪ አበሻ አለም ላይ አለ መሰለሽ ነውረኛነታቸውን እዚህ መጥተው ይፈጽማሉ''
ብዬ የሆነ ሂሳቡን ሰጠዋትና
''መልሱን ውሰጂው አልኩዋት''
ገንዘቡን ከተቀበለችኝ ብውሀላ
እሄማ ይበዛብኛል አለች
ግድ የለም ይገባሻል ለጫወታሽ ጭምር ነው አልኩዋትና ከዛ ወጣው
ከመጨለሙ በፊት ቤት ገባው እናቴ ገና ስገባ ''ይልመድብህ ጎሽ ተባረክ ልጄ በጊዜ መጣህ'' አለችኝ
ደህና ዋል እማዬ አልኩዋት
ደህና እግዚአብሄር ይመስገን ልጄ አለችኝ በስስት እያየችኝ
ከአጅሪት ጋር ተጋብተን የናቴን ግማሽ ከወደደችኝ በቂዬ ነው ብዬ አስብኩ ቴዲ እውነቱን ነው የናቴን ምትክ ስጠኝ ያለው
ብዬ ሳስብ እናቴ ''ጀመረህ ደግሞ ለብቻህ በቀን ህልም ትዋዥቃለህ ሳታገባ ሳትወልድ የምን ሀሳብ ነው ልጄ''
''እማዬ አንቺ ይመስልሻል እንጂ እኔኮ ካንቺ ጋር ቁጭ ብሎ መጫወት ሌሎች ቅቤ ነክረው ከሚሰጡኝ አንቺ እንጀራ ነስንሰሽ የሰጠሽኝ እንደሚጣፍጠኝ ታውቂያለሽ እማዬ'' አልኩዋት
እውነቴን ነው በናቴ የምጠላው ነገር ያለ አይመስለኝም i am crazy about this women i love her so much she feels the same way about me i get guarante motherly love but we never tell one onother i love you action speak better than word i guess
በነገራችን ላይ እንዚህን ሁለት ቃላቶች ውድፊትም ወደው ሁዋላም አንብቡ ትኩሥ ብሥኩት

ይቀጥላል
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby እድላዊት » Fri Sep 01, 2006 6:56 am

ወንድም wrote:
እውነቴን ነው በናቴ የምጠላው ነገር ያለ አይመስለኝም i am crazy about this women i love her so much she feels the same way about me i get guarante motherly love but we never tell one onother i love you action speak better than word i guess


ወንድ ልጅ እናቱን እንደዚ ሲወድ እንዴት ያረካል አምላክ ያኑርልህ እኔም እናቴን እንዳይኔ ብሌን ስለምወድ ነው አቴንሽን የሰጠውት :)

ወንድም ታሪክህ እንደልብ ወለድ ጉጉት የሚያረግ ነው እስቲ ልባችንን አትስቀል ቀጥልበት

እድል
hany
እድላዊት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 283
Joined: Sat Nov 27, 2004 12:49 pm
Location: united states

Postby ትትና » Fri Sep 01, 2006 8:14 am

ወንድም:- በጣም በጣም የሚስብ ነው! መጨረሻው ምን ይሆን? ብቻ የተሳካውና የተቃናውን ይስጥህ!

የናትን ነገር ተወው!! ሁፍፍፍፍፍፍ እንደሷ በምድር ላይ ማን አለ?

እየጠበኩ ነው::
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Postby ሜሪያን » Fri Sep 01, 2006 3:04 pm

ወንድም በጣም ደስ የሚል ታሪክ ነው መቼም እውነተኛ ታሪክ ነው? መሆን አለበት በጣም ልብ እሚሰቅል ታሪክ ነው መቼም የፊደል አመራረጥህ እራሱ እሚያስገርም ነው ግን ግን ቶሎ ቶሎ ጣፍልን እሚጠባበቁ ስንት ታዳሚዎች አሉ መሰለህ እኔ በበኩሌ ቸኩያለሁ እና በርታ በርታ.....

አክባሪ
ሜሪያን
ሜሪያን
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 68
Joined: Thu Jun 29, 2006 6:09 pm
Location: ethiopia

Postby ሜሪያን » Fri Sep 01, 2006 3:39 pm

ትትና... እድል... ወንድም... እንዲሁም ለሌሎቻችሁ በሙሉ ልክ ብላችሆል እናትን የመሰለ ማን አለና እኔ እናቴን ካጣሆት 2 አመት ሆነኝ ሁል ግዜ እናቴ በመራብና በመጠማት አለሁት በሰው አገር ላይ እንከራተታለሁ ይህ የዘላለም መጠማት ነው አንዱን ስል አንዱን እያደራረበ የህይወት ጣአምና ሽታው ከኔ ከራቁኝ አመታት ተቆጠሩ አሁን እናንተ ስለእናት ስታወሩ በጣም አስደሰታችሁኝ ባንድ በኩል ደግሞ ቀናሁ ለማለት የምፈልገው በህይወት ያሉትን እናቶችን ከምንም በላይ ከማንም በላይ እነሱን መንከባከብ ሁሉም ሰው አለበት......እስቲ ይሁን

አክባሪ
ሜሪያን
ሜሪያን
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 68
Joined: Thu Jun 29, 2006 6:09 pm
Location: ethiopia

Next

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 4 guests