አገባው

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ሶርርይ » Thu Sep 07, 2006 6:05 am

cooool
plz move on ወንድም
and write more
...........................
ሶርርይ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Thu Aug 31, 2006 8:23 am

Postby ወንድም » Thu Sep 07, 2006 6:56 am

በሚቀጥለው ቀን የተቀጣጠርንበት ቦታ እኔና ተድላ ቀድመን ገነት ሆቴል ሄደን ሀላፊውን አስጠርተን እንግዳ ስለሚመጣብን ዘዋራ ቦታ እንዲያዘጋጅልን ብንጠይቅው
''ሁሉም እዚህ ቤት የሚመጣውኮ እንግዳ ነው ለምንድነው ለናንተ በልዩ የምናዘጋጅላቹ'' አለ ገርሞት
ተድላ እንዳመሉ ቸኩሎ ከሞሞጣሞጡ በፊት ሰውየውን ውደ ጎን ስቤ አየህ ዛሬ እኔ ልዩ እንግዳ ስላለብኝ ነው ስለተቸገርክልን ደሞ እሄውልህ''
ብዬ ሀምሳ ብር አሳይቼ ኪሱ ላይ ጨመርኩለት
ጮክ ብሎ ''ድሮም ቢሆን እንግዶቻችንን አስቀይመን አናውቅም ስራችን እናንተን ማስደሰት ነው ብሎ አጨብጭቦ ሰራተኞችን ጠራቸውና ምቹ ቦታ ላይ ቁጭ ብለው የነበሩትን ሁለት ሰዎች በቅድሚያ ተይዞ የነበረ ቦታ ነው ያ ደንቆሮ አስተናጋጅ ሊነግራቹ ይገባ ነበር የተይዝዋል ምልክት ሊያደርግበት በተገባ ከይቅርታ ጋር ቦታ ትቀይሩ ሲላቸው ምንም አይደለም ብለው ተነሱልን ከዛም ከወንበሩና ከጠረፔዛው ስር ውድ ስጋጃ አስነጠፈበት የጠረፔዛውንም ጨርቅ ቀየረው
የነበረውን ወንበር ወስደው ሌላ ቆንጆ ወንበሮች አመጡልን
''እዚጋ ለነበሩት ሰዎች የሚጠጡትን ሁለት እኔ ነው የምከፍለው'' ስል
''አንተ ገንዘብ በዝቶብሀል እዚህ ቤት ቂጥ ቆራጮች መሆናቸውን ተዘነጋህ''
እህቴና አጅሪት እስኪመጡ ቢራ ይዘን ጠበቅናቸው
ትንሽ ደቂቃ እንደጠበቅን ያቺ ከሆነች ገቢናዋና ካሶኒዋ (body) ወደር የለውም ዋናው ግን ሞተሩ ነው አለኝ ከሩቁ አይትዋቸው.
ከመቸውም የበለጠ ተውባለች
ይቀጥላል
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ማኖር » Thu Sep 07, 2006 8:51 am

ወንድም

በጣም ጥሩ ታሪክ ነው::እውነቴ ነው የምልህ ይህ ራሱ የቻለ ጥራዝ እንደሚወጣው አምናለሁ::በጣም አስተማሪም ነው:: አንድ ትዳር ፈላጊ ትዳር አለም ከመግባቱ በፊት ምን ምን አይነት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት አቅጣጫ የሚጠቁም አቀራረብ ነው:: በበኩሌ ታሪኩን እየቆራረጡ ማንበብ የታሪኩን ሂደት ለዛ ስለሚያሳጣው ብዙ ፖስት ካደርክ በኋላ ቢነበብ ጥሩ መስሎ ስለ ታየኝ እንደዛ አደርጋለሁ::አንተም ታድያ ተሎ ተሎ እያልክ አስነብበን::
"Great minds discuss ideas;Average minds discuss events;Small minds discuss people" Eleanor Roosvelt
ማኖር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 300
Joined: Mon Feb 13, 2006 6:14 am
Location: US America

Postby ቆንጂቲና » Thu Sep 07, 2006 9:14 am

ምነው ወንድም እንደዚህ ልቤን አስጨነካት ከምር መጨረሻውን ለመሰማት ጓጉቻለሁ Please በዛ አድርገህ ጻፍ እሺ ወንድምዬ.

አክባሪክ
ቆንጂቲና
ቆንጂቲና
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Mon Sep 04, 2006 5:47 am
Location: n/a

Postby ቅራሪ » Thu Sep 07, 2006 5:51 pm

ውንድም ከራሴ ጋር ሙግት ይዜ ነበር ምንም ላለመጣፍ ታሪኩ እስከሚያልቅ ድረስ ነገር ግን ምንም አላስቻለኝም ብቅ አልኩልህ በጣም ልብ አንጠልጣይ ነው በተቻለህ መጠን በርከት ያለ ጣፍልን ያጎጎል በጣም በሞቴ እንደው በሞቴ ሳትጨርስ እንዳታቁአርጠው አደራ.

አክባሪ
ቅራሪ
ቅራሪ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 247
Joined: Wed May 10, 2006 4:42 am
Location: adiss abeba

Postby ወንድም » Fri Sep 08, 2006 8:53 pm

thank you ሶርሶይ

ማኖር you are so nice ድሮምኮ የሚያበረታታኝ አጥቼ ነውጂ የራሴን ጥፋት በሰው ላላክክ እንጂ

ቆንጂትና እንደ ስምሽ የሆንሽ ቆንጂዬ ነገር አይዞሽ ልብሽን እንደተንጠለጠለ አይቀርም አወርደዋለው

ቅራሪ አይዞሕ (ሽ) አስደግፌህ(ሽ) አልጠፋም cut and run no way


ልጆች በአጠቃላይ ትላንት በአንድ ጊዜ ብዙ ጻፍኩላቹና submit የሚለውን ስነካ ለካ ኮምፒይተሩ ተበላሸ መሰለኝ
ብላክ አውት ሆኖ በጣም አብሽቆኝ ያ ሁሉ ልፋት በነጻ ተናድጄ ተኛው ዛሬ በስራ ኮምፒይተር ነው የጻፍኩት ከስራ ስመለስ እንተርኔት ካፌ ጽፋለው የምሳ እረፍቴ አለቀ ቻው i will beback just like arnold on terminator
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby አብቹ1 » Fri Sep 08, 2006 10:22 pm

ወንድም, በጣም ደስ የሚል ታሪክ ቐጥልበት, አጣጣፍህ በጣም ጉሩም ነው አደንቓሀልሁ
አብቹ1
አብቹ1
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Fri Sep 24, 2004 10:20 pm
Location: united states

Postby ወንድም » Fri Sep 08, 2006 11:13 pm

አብቹ ጭሱ ለሙከሻው ሳላመሰግንህ ላልፍ አልፈልግም ወደ ትረካው ልመልስ
ሰው በየቀኑ ውበቱ እየጨመረ ይመጣል በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው የአጅሪት ግን በተቃራኒው ነው ቆንጆ አጠር ያለ ቀይ ቀሚስ አርጋ እንዲመሳሰል ነው መሰለኝ ነው ቀይ ታኮ ጫማም ተጫምታለች ያ ለስላሳ ቆንጆ ጸጉርዋ ዛሬ ተሰርታዋለች መሰለኝ ጫፍ ጫፉ ጠቅለል ብሎ እንደጠገበ አንበሳ ኮራ ብሎ ግምለል በማለት ተጋድሟል.
አጠገባችን ሲደርሱ ተነስተን የሚገባቸውን ሰላምታ ሰጥተን ተድላንና አጅሪትንም አስተዋወቅናቸው
እኔ መጣው ብዬ ጓዳ ገብቼ ለህቴ ውደ ሞባይል(ሴሉላር) ስልክ ደውዬ ወደ ጓዳ እንድትመጣ ነገርኳት
''ለምን እንደጠራሻት ነገርሻት እንዴ''
''አይ አልነገርኩዋትም''
''ምነው ታድያ ጨረቃ መሰለች አንቺም የቀልድ አይደለም የዘነጥሽው''
''ለሰርግ ብለን ነዋ''
''ሰርግ? ሰርግ? የምን ሰርግ? አመጣሽብኝ ምን ነካሽ አደራ ብዬሽ እሺ ብለሽ አሁን ለሰርግ ነው እንደዚ የለበስነው ትያለሽ!!'' ብስጭትጭት ባለ አነጋገር እጆቼንም እያወናጨፍክኝ
''ረጋ በልጂ አየህ ጠዋት አልጋዋ ላይ እየለች ቤቷ ሄጄ
ዛሬ የቅርብ ዘመዳችን ሰርግ ስላለ አንቺም ስለጠራሽ አደራሽን እንቢ እንዳትይኝ የዛሬን ብቻ አውጭኝ አልኩልህና በግድ ስሎኔ ውስጄ አሳምሬ አመጣውልህ''.
''አስሞነሞንሽልኝ እንጂ ውለታሽን እንዴት እንደምከፍለው እንጃ''
''አንተን ብቻ ይቅናህ''
''እንደአፍሽ ያርግልኝ
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby meote » Fri Sep 08, 2006 11:47 pm

ስላም ለውንድም
ምንም አልናገርም ብዬ ነበር ግን አላስቸል አለኝ እር ፐሊስስስስስ ቶሎ ቶሎ ጻፍልን ምንላይደርሳቸሁ:
ወይይይይ ልቤን አንጠለጠልካት እኮ ወቸጉድ በል ይቅናህ
እግዛብሔር ካንተ ጋር ይሁን እውነተኛ አፍቃሪ ትመስላለህ: በል ቆሎ በል አቦ :wink: :wink:
አክባሪህ meoteዬ
meote
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 443
Joined: Sat Apr 22, 2006 8:08 pm
Location: warka

Postby ወንድም » Sat Sep 09, 2006 12:09 am

ውደ መቀመጫችን እንደተመለስን አስተናጋጁን በጆሮው አበባውን እንዲያመጣ ነግሬው እንዳመጣልኝ ለአጅሪት ጎንበስ ብዬ እሄ ላንቺ ነው በማለት ጉንጉን አበባ አስታቀፍኳት እህቴም አይን አይኔን ስታየኝ ''አንቺንም አልረሳሁሽም በማለት ለስዋም ጉንጉን አበባ ሰጠዋት ሁለቱም በደስታ ፊታቸው በርቶ ነበር ሴቶች አይደሉ አበባና ዳይመንድ ዋና ጓደኛቸው ነው ይባላል.
''ተድላ የቀልዱን ወደኔ እያፈጠጠ ለኔስ እኔ አበባ አያምርልኝም'' ያለው ማነው ሲል
''አንተ ደሞ ምን አበባ አስፈለገህ አርፈህ ቢራህን ከጠጣህ ምን አነሰህ.
''አጅሪት ከኔ ትካፈላለህ'' ብላ ከጉንጉኑ አንድ አበባ መዝዛ ስትሰጠው ለኔም ሌላ አበባ መዛ ሰጠችኝ
''ጎሽ ተባረኪ አንቺ ትሻያለሽ'' ብሎ ተቀበላት
''ሰዎች እኔ በጣም ርቦኛል ብዬ አሰላፊውን ጠራውትና
''እናንተም እዘዙ''
''ሰርግ ቤት ሄደን ስለምንበላ ጭማቂ ነገር ይበቃኛል'' አለች አጅሪት
''ነብስዋ መብላት አለብሽ እዛ ከሺ ሰው ጋር ተጋፍቶ ከመብላት እዚው አጠናቀን የወንድማችንን ግብዣም እንቀበለው'' ሲላት
''እህቴም እውነቱን ነውኮ እዛ እስክንደርስ ይተናል ቦታው ደሞ ሩቅ ነው ግድርድር ጎንደሬ አትሁኚ''
''እሺ ካላቹ'' ብላ ሁላችንም አዘን ምሰችንን በላን
ከምሳ በውሀላ ጭማቂ እየጠጣን ሳለ ተድላ እግሬን እየረገጠ አስቸገረኝ ጠይቃት ለማለት.
''ሰዎች ተኛንኮ ወደተባባልነው ሰርግ አንሄድም እዚ የመጣነውምኮ እስዋ እነሱ ገነት ሆቴል ስላሉ እግረመንገዳችንን ጎራ ብለን አብረን ተያይዘን እንሄዳለን ብላኝ ነው ሙሽሮች ሳይወጡ ብንደርስ ምን ይመስላችሗል
''እነሱ ለተጋቡት እኛ ምን አጨብጫቢዎች ነን አንዱ ላገባ ሌላው ገገባ የነሱን ትተን የራሳችንን እናድርግ ሺ ሰርግ በላን በተለይ እኔማ በየሳምንቱ ሰርግ ሰርግ እነሱ ተጋብተው አለማቸውን ሲያዩ እኛ ቆመን ቀረን እኔ የምትሆነኝን የማፈቅራትን ባገኝ ዛሬ በጠለፍክዋት ለዛ ግን አልታደልኩም ስለዚህ እናንተ ተጋቡ''
ብሎ የኔንና የአጅሪትን እጅ አያያዘው
''ልጁ ምንድነው የሚያወራው ልጁ አለች''
ገርሟት እኔን እያየች በእጅዋ ወደ ተድላ እያመለከተች
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ወንድም » Sat Sep 09, 2006 1:25 am

Meote እውነተኛ አፍቃሪ ትመስላለሕ? አጭቤ ብሆንስ ያ ድሮ ቀረ አንቺም ወይም ላንተም ይቅናህ(ሽ)ከኔ ትይዩ ስለተቀመጠች አሻግሬ ሁለት እጅዋን ይዤ ''ፍቅሬ ነብሴ ምን ያህል እንደማፈቅርሽ ታውቂያለሽ ኑሮ ያላንቺ አይሆንም ብዬ ነው እንደገና የመጣሁት. ያለፈው ጊዜ አንቺን ለማግባት እንዳሰብኩኝ ለናቴ ብነግራት እልልታውን ለቀቀችው አንቺም ታስታውሻለሽ በጣም ስለምትወድሽ ነውኮ አንቺ ደሞ ሎተሪ ደረሰሽ ወይ ብለሽ ጠየቅሻት የደረሳት ግን ከሎተሪ የበለጠ አንቺ ፍቅሬ ነሽ''
''እኔኮ ለርካሽ ለጊዜያዊ ፍቅር አይደለም የምጠይቅሽ ለዘለቄታው አግባብ ባለው ሁኔታ ቤተክርስትያን ሄደን እንድንጋባ ነው እኛም እንደ ሰዉ የራሳችንን ጎጆ እንድንቀይስ ካንቺ ጋር ሲሆን ዳገቱ ሜዳ ሆኖ ይሰማኛል ትዳር የሚባል ነገር እንደጦር ነበር የምፈራው ማንንም ሴት ለማግባት አስቤ አላውቅም ነበር ከማይስማማኝ ሰው ጋር ኑሬ አባጨጉዋሬ እንዳይሆን ስለምሰጋ አንቺ ከጎኔ ካለሽ ምንም አይሳነኝም ምክንያቱም የኔ በሽታ አንቺን ማጣት ነው. ዞረሽ ተመልከቺ የት እንዳለን እንደዚ አይነት ትልቅ ሆቴል አላዘወትርም ቢጤዎቼ እዚ ስለማይገቡ ምን ለማለት ፈልጌ መሰለሽ እሄ ሁሉ ላንች ክብር ነው እና ነብሴ ምን ትያለሽ ታድያ''
ሊቆም የማይችል እንባ ከአይንዋ ይወርድ ጀመር እህቴና እኔ አባበልናት እህቴም እንባዋን በመሀረብዋ ጠረገችላት እኔም ሳግ መጣኝ''
''እኔም እኔምኮ በጣም በጣም ነው የምወድህ ሁሌ ስላንተ ነው የማስበው አለች እኛን ሳታይ እንዳቀረቀረች.
''እናስ ታገቢኛለሽ''
ቀና ብላ ላለመሳቅ እየሞከረች
''እሺ አገባሀለው'' አለች
''አይዞሽ በዚ ውሳኔሽ አትቆጪም በደንብ እንከባከብሻለው''
''እኔም እንደዛው ለዘላለሙ ከጎንህ እሆናለው''
የደስደስ ተነስቼ እጮኛዬን ጥብቅ አርጌ አቀፍኩዋት አለምን በቁጥትሬ ስር ያደረኩኝ ሆኖ ተሰማኝ አስዋም ከኔ የጠበቀ አቅፋ ሳመችኝ
አራታችንም በየተራ ተሳሳምን
እነዛ ወሬ ጠቢ የቤቱ አስተናጋጆችም እየመጡ እንኩዋን ደስ አላቹ አሉን.
እንደተመኘዋት አገኘዋት የሚለውን ዘፈን መዝፈን አማረኝ
ቀስ ብላ በጆሮዬ
''ወደ ቤተሰቤ ሽማግሌ መለክ አለብሕ አልብህ''
ሽማግሌዎቹ በተጠንቀቅ እንዳሉ ነገርኳት
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ሶርርይ » Sat Sep 09, 2006 8:24 am

Hello ወንድም
You have good gift.Realy!
It do not seem fiction,you just play it in our mind.
Please write similar(not marrage only) things.Even you can write Jaki Chan's action movei.
Excellent!!!
keep it up bro
with respect
...........................
ሶርርይ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Thu Aug 31, 2006 8:23 am

Postby ሶርርይ » Sat Sep 09, 2006 8:30 am

Hello ወንድም
You have good gift.Realy!
It do not seem fiction,you just play it in our mind.
Please write similar(not marrage only) things.Even you can write Jaki Chan's action movei.
Excellent!!!
keep it up bro
with respect
...........................
ሶርርይ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Thu Aug 31, 2006 8:23 am

Postby ወንድም » Sat Sep 09, 2006 11:12 pm

ሶርሶይ do you realy think i have a gift i realy thank you from the bottom of my heart for your encourajment
do you want me to write action flick me and you are body action heros your line
ሶርሶይ wendm are you going to let them get away with this crime we have to chase them where ever thay are and kill them just like thay kill full bar of people
my line
ወንድም look sorsoy you think i donit want to shoot them between there eyes but instead of being crimnal like them lets bring them to justice we are better than them
your line
ሶሮሶይ stob this mambo jambo justice shit remeber eye for eye tooth for tooth get your man hood together act like angry man and i know you are
my line
ወንድም i load my my 12 gage shut gun i will say to you ok lets do them your way
your line
ሶርሶይ that is what i am talking about my partner partner for life and you load m14 rifile gun and we give fife and we take the law on our hnds

i am just clawning bro just fattassy
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ወንድም » Sun Sep 10, 2006 12:55 am

የኔና የእጮኛዬ መፈቃቀድ ሽማግሌም እንደላክን በሰፈርም በቤተዘመድም ያደባባይ ሚስጥር ሆነ እኔና እጮኛዬ ከመቸውም የበለጠ ተቀራረብን
ጠዋት ከቤት ወጥቼ ታክሲ ልሳፈር ስል በጣም አርጌ የድሮ ዘንብል ፎልስ ዋገን መኪና የተደገፉ በግምት የ ሀምሳ አምስት አመት የሚሆናቸው ቀጭን ሰውዬ ስሜን ጠርተው ጠሩኝና
''ደህና አደርክ''
ማን እንደሆኑ አውቃቸዋለው የድሮ ያባቴ ጉዋደኛ የጮኛዬ አባት ናቸው
''ደህና እግዚአብሄር ይመስገን''
''ና እኔ ልውሰድህ ና ግባ''
''እረ ግድ የለም እንዳላስቸግሮት በታክሲ እሄዳለው''
''ና ግባ እያልኩህ''
ትእዛዝም ይመስላል ሰውየው በጤና አይደሉም የኔ ጣጣ አያልቅም ስለ እጮኛዬ አንድ ነገር ሊሉኝ እንደሆነ አላጣሁትም
''እሺ'' በማለት መኪናዋ ውስጥ ገባው መኪና ሳይሆን ተንቀሳቃሽ ኩሽና ነው የምትመስለው እሳቸውና ቤተሰባቸውን ግን ከሀያ አመት በላይ አገልግላለች ወዴት እንደምንሄድም አልጠየኩም
የሆነ ቁርስ ቤት ነገር አቆሙና ገባንና ቡና አዘን እይጥጣን
''ከኛ ቤተሰብ ጋር መዛመድ መፈለግህን በጣም ደስ ብሎኛል ድሮም ቢሆን ቤተሰብ ነን ልጄም ሽማግሌዎችን እንዳላሳፍር በጣም እንደምታፈቅርህ ሳትነግረኝ አልቀረችም ሽማግሌውችም የኛን መልስ ለማጝኘት ሳምንት ቀርትዋቸዋል.
''በናትዋ በኩል እንዳጣራውት እንዳልነካሀት ነው ልጄን ብቻ ሳይሆን አንተንም ከምር ከማመስገንም አልፌ አደንቃሀለው''
''ልጆትን ከልቤ ስለማፈቅራትና ስለማከብራት ስንጋባ እደርስበታለው ብዬ ነው ጌታዬ ሳልፈልግ ቀርቼ አይደለም.
''እሺ እኔ ድብብቆሽ አልችልበትም ለምን ዛሬ ፈለኩህ መስለህ እቺን ልጅ ከተወለደች ጀምሮ የሚገባትን ፍቅር ሰጥተን እንደ አይናችን ብሌን ተንከባክበን ነው ያሳደግናት
በጣምም እንወዳታለን በተለይ ለኔ ነብሴና ስጋዬ ናት እና አንተም እሄን ልትረዳልን ይገባል........
ብሀሳቤ ሰዉ እንዴት ወርዱዋል ዘንድሮ ገንዘብ በጎን ካልሰጠህኝ ልጄን አልሰጥህም ሊሉኝ? ነው ስንት ብርስ ሚሆን የሚጠይቁኝ ወይም የዚችን ከርካሳ መኪና መቀየርያ ገንዘብ ይሆናል የሚፈልጉት ምን ጣጣ ነው እሱ.
''እየሰማሀኝ ነው''
ብርግግ በማለት ''አዎ እየሰማዎት ነው''
''ለሽማግሌዎች እሺ ከማለቴ በፊት እንድትመረመርልኝ ፈክጋለው''
ምንድነው እኚ ሰውዬ የሚቀባጥሩት ብዬ
''ምንድነው የምመረመረው''
''ከኤድስ በሽታ ነጻ መሆንህን''
''ኤድስ አለበት ብለው ጠርጥረዋላ!!''
''በፍጹም አልወጣኝም''
''ታድያ ምንድነው ተመርመር ምናምን የሚሉኝ''
''ቅድም እንዳልኩህ ልጃችንን ስለጠየቅ በጣም ደስ ብሎናል እንቅጩን ልንገርህ ግን ካልተመረመርክ ግን ልጃችንን እንደማታገኝ እወቅ ከጃፓንም ምጣ ካሜሪካ!!''
ፊታቸውን ወደ ፊቴ አስጠግተው ጠረፔዛውን በሌባ ጣታቸው እየቆረቆሩ.
ሰውየው በልጃቸው አይቀልዱም እኔም በስዋ ቀልድ የለም እኚ ሰውዬ እውነት አላቸው አልኩኝ ለራሴ
''ፋዘር እኔምኮ እራሴን አበላሽቼ የሰው ልጅ ይዤ ልጅ በበሽታ ላጠፋ አልፈልግምና እሺ እመረመራለው.ተጨባበጥንና ከነገ ወድያ ወስደው ሊያስመረምሩኝ የምንገናኝበትን ሰአትና የክሊንኩን አድራሻ ሰጥተውኝ ተለያየን.
ተመርምሬ እንዳለፍኩ እጮኛዬ ስለ ተመርምሬ ማለፌን እናትዋ እንደነገረቻትና እስዋ እዚህ ነገር ውስጥ እንደሌለችበት አስረዳችኝ አመንኩዋት አባትዋ እውነት እንዳላችው ብነግራት ግን አልሰማም አለችኝ ሳልጠይቃትም አስገድዳ ወስዳኝ በፊቴ ተመርምራ የለብሽም አልዋት
ነገ የመጨረሻው ክፍል
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests