አገባው

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ቆንጂቲና » Sun Sep 10, 2006 7:06 am

ወንድምዬ እስካሁን እጅግ በጣም ነው የተዋጣልህ የመጨረሻውን ክፍል ለመስማት በጉጉት ላይ ነኝ ብቻ አስደግፈኽን እንዳትጠፋ አደራህን::

አክባርህ
ቆንጂቲና
ቆንጂቲና
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Mon Sep 04, 2006 5:47 am
Location: n/a

Postby ወንድም » Sun Sep 10, 2006 10:47 pm

ቆንጂትና ነብሴ እንዴት ተደርጎ አስደግፌሽ ልጠፋ በተለይ የሰርጌ ቀን አይሆንም አላደርገውም ታሪኩን ስለወደድሽው አመሰግናለውቤታችንና የጮኛዬ ቤት የሰርጋችን ቀን ስለደረሰ ሽር ጉድ በዝቷል እናቴና አባትዋ ሰርጉ ቤት ካልሆነ አሻፈረኝ ብለው ነበር ከብዙ ውትወታ በሗላ ግን እጅ ሰጡና በሆቴል ተስማሙ.
ቤተስክያን ሄደን ቄሱ ጸሎት አድርሰው አስምለው አሁን ባልና ሚስት ናቹ ሲሉን ባለቤቴን አቅፌ ሳምኩዋት እስዋም ሳመችኝ እሄ ሁሉ ለኔ? ካለስዋ ሌላ ሴት ላልነካ በድጋሚ ለራሴ ቃል ገባው ከደስታዬም ብዛት ሳይታወቀኝ አይኔ ያነባ እንደበረ የነገረኝም ተድላ ነው.
''አንተ ምን ነካህ እንደ ሴት ታለቅሳለህ እየተቀርጽን ነውኮ ቪድዮውን ሲያዩ ቡና መጠጫ እንዳያደርጉን'' ብሎ ገሰጸኝ.
አዲስ አለም ውስጥ የገባው ሆኖ ተሰማኝ እውነት ከኔ በላይ የታደለ ሰው አለ ተሞኝተዋል ይመስላቸዋል እንጂ እንደኔስ ድርሻውን ያገኘ ካለ አርባ ጅራፍ ለጀርባዬ ብዬ የማስበው. ባለቤቴን ከጄ እንድምትጠፋ እንቁ እጅዋን አለቅም ሙጥኝ ብዬ ነበር የት ልትሄጂ ካሁን ብውሀላ እድሜ ልክሽን ከጎኔ ልትሆኝ ተፈርዶብሻል ሞት ነው የሚለየን. ቤተሰብና ቤተ ዘመድ ስመው እንኩዋን ደስ ያላች አሉን.
በሰርገኛ መኪና ታጅበን ከተማውን ስንዞር በጥቂት መኪና የታጀቡ ሰርገኞች ከኛ መኪናዎች ጋር ተቀላቅለው ሲሄዱ ለምን እንደዛ እንዳደርጉ ሾፌሩን ብጠይቀው
ከሰርጉ ካለፈ በሗላ ከማን አንሼ እኛም እሄን ሁሉ መኪና ደርድረን ነበር ለማለት ነዋ ብሎ አጫወተኝ
የሰርጉ አዳራሽ በሰው ሞልቷል ይበላል ይቆረጣል የባለቤቴ አባት ያገር ባህል ልብሳቸውን ለብሰው በሰዉ መሀል ይንጎራደዳሉ በኩራት ደረታቸውን ነፍተዋል ሊያቅራሩ የፈለጉም ይመስላሉ ወደኛ ሲያዩ ወየውልህ ልጄን ትበድላትና የሚሉ ያሉ ሆኖም ይሰማኛል እኔም በሆዴ የማላደርገውን እላለው.
እናቴም ቆንጆ ያበሻ ቀሚስዋን ለብሳ እየዞረች ምን ጎደለ እረ በደንብ ያዙ ትላለች አንዳንዶቹም ያጎርስዋታል ወደኛ ዞር ብላ ባየች ቁጥር አይ የኔ አንበሳ ጭራ ነው የጎደለህ እንጂ አንበሳዬ ነህ የምትለኝ ሆኖ ይሰማኛል አጎቴ ገና በጊዜው ክውሀዋ አብዝቶ ሞቅ ሳይለው አይቀርም እሱም በተቻለው መጠን ያባቴን ድርሻ ሊሞላ ደፋ ቀና ይላል

መጣው
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ወንድም » Sun Sep 10, 2006 11:56 pm

እህቴን የታለች እያልኩ በአይኔ ስቃኝ ልካ ከሚዜዎች ጎን ቁጭ ብላለች ወደኛ መጥታም እንዴት ነው ''እንዳሰብከው ነው'' አለችኝ ከዛ በላይ በዝግጅቱ እንደረካው ነገርኳት
በልተው ጠጥተው ሲጨርሱ ዳንኪራ ይረገጥ ጀመር እኛ ምን ቸገረን ማጨብጨብ ነው የኛ ተራ ደረሰ እኔና ባለቤቴ ተቃቅፈን ስንደንስ እልልታው በረታ ሲቃ ሲቃም እተነፍስ ነበር ስንትና ስንት ሴቶች ፓርቲ ቤትም ይሁን ሰርግ ቤት ለዳንስ እንቢ እንዳላሉኝ እችኛዋ ከዳንስ አልፎ እራስዋን ሰጥታኛለች. እንደነገሩ ተወዛወዝነው ማፈር ምናምን የሚሉት ነገር በመስኮት አውጥቼ ጥየዋለው በዛ ደባሪ በማልችለው ዳንሴ የፈለጉትን ይበሉ ይሳቁብኝ.
በሚቀጥለው ቀን ጎህ ሲቀድ ከንቅልፌ ነቃው ከአልጋዬ ውስጥ ግን ልወጣ አልቻልኩም ክንዴን ተንተርሳ ለጥ ብላ ተኝታለችና ቀስ ብዬ አንሶላውን ትንሽ ገልጬ መላ ሰውነትዋን አየሁት ምንም አልለበሰችም አቤት ሰውነት የደስታ ሳቄ እንዳይመጣም አፌን በቀኝ እጄ ሸፈንኩት
''ስትነቃ እ እቱ ታድያስ እንዴት ነበር ማታ?
አፍራ ነው መሰለኝ በመሽኮርመም እያየችኝ በእጅዋ ተደግፋ የነበረውን ደረቴን እንዳያሳምመኝ ቀስ ብላ በግራ እጅዋ በቦክስ መታችኝና እንጃልህ ብላ ከፊትዋ ግን ፈገግታ አልጠፋም [/url][/u]
''ለምንድነው ግን ልጃገረድ መሆንሽን ያልነገርሽኝ?''
''ጆሮህን ወይ አይንህን ታምናለህ''
''ልክ ብለሻል አይኔን ነው የማምነው አይቼም አምኛለው ካገር ቤት ከመጣው ገና ሶስት ወር ገደማ ቢሆነኝም ሳልደውልላት ሶስት ቀን ከቆየው ይጨንቀኛል አንዳንዴ ለሰአት እናወራለን እንድትመጣልኝም የሚግሬሽኑን ጠበቃ እንዴት ነው ሂደቱ ቆየ ስለው ረጋ በል ይለኛል.
ተፈጸመ
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ወንድም » Mon Sep 11, 2006 2:33 am

ቆንጂትና,ቸኮሌት,ህይወት,ደንቢያ,እድላዊት,ትትና,ሜርያን,ሜዳ,zizu,ቆንጅየው
ገላጋይ,ደብዚ,ndave,ሶርሶይ,ማኖር,ቅራሪ,አብቹ እናም meote
ሁላቹም ከዚህ በላይ ስማቹን የጠቀስኩት ታሪኩን ስትርክ
ስላበረታታቹሁኝ ጎንበስ ብዬ ከአክብሮት ጋር ከልብ እግዚአብሄር
ይስጥልኝ እላለው ጽሁፉን ስጀምር አረስቱ እንደሚለው አገባው
ብዬ በሁለት ጌዜ ብቻ ፖስት አድርጌ ጠቅለል ባለ መልኩ ልጽፍ
ነበር እናንተ ግን የልብ ልብ ስትሰጡንኝ ከሀይስኩል ጀምሮ የነበ
ረኝን የመጻፍ ፍላጎት በየቀኑ ብዙ ሰአትም እየፈጀው ጻፍኩት
ከልብ በጣም ደስ አለኝ ምክንያቱም ከአሁን በውሀላ አጫጭር
ልብ ወለድ እሞካክራለው ለማሳተም
በተረፈ ላላገባቹት እንደኔ ጥሩ እድል እንዲያጋጥማቹ እመ
ኝላችዋለው
print out ላደርግ ስሞክር ሁሉም ክፍል print አይሆንልኝም
ጫፉ ጋር ያለው ፕሪንት አልሆንም አለኝ መላውን ንገሩኝ

ሌላም ደግሞ እሄ ጽሁፍ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው ስለዚህ
የኔ ነው ብለህ አሳትማለው ብትል አ.አ ወፍራም ጠበቃ ቀጥሪያ
ያለው የምሬን ነው
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ቆንጂቲና » Mon Sep 11, 2006 3:30 am

ወንድምዬ አጨራረስህም አንደአጀማመርህ እጅግ ያማረ ነው በእውነት በጣም!! በጣም!!!! ተዋጥቶልሀል ደስ የሚል ታረክ ነው ጌታ ይባርክ ::

አክባሪህ
ቆንጂቲና
ቆንጂቲና
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Mon Sep 04, 2006 5:47 am
Location: n/a

ለ ወንድም

Postby zizu » Mon Sep 11, 2006 3:46 am

ዋውውው በጣም አሪፍ ነበር አሪፍ ብቻ... ከምሬ ነው የምልህ ወንድም ቤት ሄጄ ወደ ስራ ስመለስ መጀመርያ ፒሲዬን ኦን ሳደርግ ጓጉቼ የማየው ያንተን ጽሁፍ ነበር ምናለፋህ ተጀምሮ እስኪያልቅ በጣም በጉጉት ነው የተከታተልኩህ
አላህ አሳክቶልህ ውዷ ባለቤትህን በፍጥነት ከጎንህ እንዲያደርግልህ ምኞቴ ነው በርታታታታታ ብያለሁ ሌላም ቆንጆ ቆንጆ ልቦለዶችን እንደምታስነብበን ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ
zizu
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 98
Joined: Sat Aug 21, 2004 7:46 am
Location: saudi arabia

Postby ትትና » Mon Sep 11, 2006 10:07 am

ወንድም:- እንኳን ደስ አለህ ! ህልምህ እንኳን እውን ሆነልህ! አቀራረብህ ለታሪኩ ውበት ሰጥቶታል!!!


print
properties
orientation
change to landscape

የዋርካ ገጽ በጣም ሰፊ ስለሆነ በቁመቱ ሳይሆን በጎኑ ሙሉውን ያወጣልሀል::
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Postby እህምም » Mon Sep 11, 2006 1:47 pm

ሰላም ወንድም

በጣም ደስ የሚል ታሪክ ነው! እንኩዋን ደስ አለህ :)
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09 ... -darkness/


"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
እህምም
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2509
Joined: Mon Dec 19, 2005 10:36 pm
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

ውብ ነው!

Postby አፈ-ጉባኤ » Mon Sep 11, 2006 3:46 pm

ማለፊያ ትረካ እንደሆነ አድናቆቴን መግለጽ እሻለሁ:: እሚያስገርም የመተጣጠፍ (twisting) ክህሎት አለህ:: የኤድስ ውጤቱ እልልታ: የቅድስት ስልክ: ከተድላ ጋር ልትጋደሉ ነው ብለን ስንጠብቅ: የእህትህ ሰርግ አለ ብላ ይዛት መምጣት "አጅሪትን" ኸረ ስንቱ?

ትረካው ከጅምሩ አንስቶ መሳጭ ነው:: ጠንካራ ስእላዊ መግለጫዎች አሉት "ያጅሪትን" በሳቅ ጦሽ እያለች በጡቶቿ ደረትህን ስትዳስስ የመሰሉ::

ሌላው የጽሁፉ ውበት ወደ መቋጫው እሚያደርገው ግስጋሴ ነው:: ገጽ ለማብዛት ስትል ያላግባብ የዶልከው "የርጎ ዝምብ" ምእራፍ የለም::

ባትናዘዘውም ትረካህ ጀማሪ ደራሲ መሆንህን ያሳያል:: ርእሱ "አገባው" የታሪኩን ፍጻሜ ጠቋሚ ስለሆነ ቢለወጥ ይመረጣል:: ለምሳሌ ትዳር አቋመጠኝ:: ዋናዋ ገጸባህሪ ፍቅረኛህን "አጅሪት" ከማለት በፈጠራ ስም ብትለውጠው ይበልጥ እሚያምር አይመስልህም?

ጽሁፉ ብዙ የለቀማ (editing) ስራ ይሻል:: አልፎ አልፎ ግራ እሚያጋቡ አረፍተ ነገሮች ይታያሉ:: አላስፈላጊ ጉራማይሌ ቋንቋ ትጠቀማለህ:: ባንባቢ ታርሞ ሲቀርብ ጽሁፉ ምን እንደሚመስል ማየት ከፈለክ ያቅሜን ልሞክር ፈቃደኛ ነኝ:: ለሁሉም ተስፋ አለኝ በዚህ ድንቅ የትረካ መክሊትህ ላይ ልምድ ታክሎበት ለማየት::

ካድናቂዎችህ አንዱ
አፈ-ጉባኤ
አፈ-ጉባኤ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 302
Joined: Tue Mar 15, 2005 5:20 pm
Location: united states

Postby ህይወት » Mon Sep 11, 2006 5:53 pm

ቃላቶች ናቸው ያጠሩኝ ወንድም....በጣም የምያስቀና ፍቅር ነው!
ትዳራችሁን ሰላም ፍቅርና መከባበር የሞላበት ቆንጅዬ ልጆች ወልዳችሁ የምትስሙበት ያርግላችሁ!!!!!
ህይወት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 167
Joined: Mon Dec 15, 2003 5:11 pm

Postby አብቹ1 » Mon Sep 11, 2006 7:56 pm

መልካም ፍቅር ይሁንላቹ, ተፍቅራቹ አስከ መጨረሻው እንድትኖሩ እግዛብሒር ይጠብቃቹ
አብቹ1
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Fri Sep 24, 2004 10:20 pm
Location: united states

Postby ሰርቢሎ » Mon Sep 11, 2006 11:41 pm

ወንድም በዚህ ፍቀር እየቀነሰ በመጣበት አለም ራሷን የጠበቀች እና እንተም የምትወዳት እሷም እንባዋ እስኪፈስ ድረስ የምትወድህ ልጅ ማግኘትህ የሚያስደስትም የሚያስቀናም ነው :lol: :c
በል እንግዲህ መጨውን የትዳር ዘመንህን የሰላም እና የደስታ ያድርግልህ እልሀለሁ.

ወንድም ከዚህ በፊት ፓርቲና ዳንስ ቤቶች ያገኘሀቸው ሴቶች እምቢ ሲሉህ ያዘንከው ሀዘን በእግዜሩ ዘንድ ተሰምቶልህ ይሆን እንደዚህ አይነት ልጅና አጋጣሚ ያገኘህ? :D :D :D :D :D
መልካሙን ሁሉ እመኝልሀአለሁ
ሰርቢሎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Tue Nov 09, 2004 9:58 pm
Location: united states

Postby ቅዱሰ » Tue Sep 12, 2006 12:03 am

ሰማ ወንድም እህትህስ please if she is not married let me know her age and introduce us. i am not joking.
ቅዱሰ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 14
Joined: Sat Mar 18, 2006 1:57 am

Postby ወንድም » Tue Sep 12, 2006 1:32 am

ቆንጂትና you are to nice to me ሆዴ እግዚአብሄር ይስጥልኝ ከሌለሽ ላንቺም ይቅናሽ

Zizu ያን ያህል የኔን ጽሁፍ ትከታተል(ይ) ነበር ገረመኝ እሰየው ብዬ ላንተም(ቺም) ከሌለህ አላህ አጋርህን)(ሽን)ይስጥህ

ትትና እንኩዋን አብሮ ደስ አለን ንጥል ከሆንሽ ላንቺም እሺ እሺ የሚል ባል ይስጥሽ

እህምም እንኩዋን አብሮ ደስ አለን ላንተም እንደዛ

አፈ ጉባኤ ስለ ስነ ጽሁፍ ጠለቅ ያለ እውቀት እንዳለህ ታስታውቃለህ ግን ደግ ሀያሲ ትመስላለህ ቦንብ ታወርድብኛለህ ብዬ ነበር you take it easy on me እንጂ ሀያሲዎች ሊያጠፉህም ሊያለሙህም ይችላሉ.
እንዳልኩህ ስሙን አገባው ያልኩት ረጅም ጽሁፍ ልጽፍ አላሰብኩም በውሀላ እንዳልቀይረው በጀመርኩት ልቀጥል ብዬ ነው አጅሪት ያልኩዋት ከሌሎች ጸሀፊዎች ለየት ለማለት ነበር እንዳየህው አጅሪት እናም እጮኛዬ ከዛም ባለቤቴ.ልክ ብለሀል ታሪኩ ብዙ editing ያስፈልገዋል ለመጻፍ በጣም ረጅም ሰአት ነበር የሚፈጅብኝ አንዳንዴ ይሰለቸኝና እዲት ሳላደርግ submit ነካለው ጉራማይሌ ቋንቋ ያልከው የቱ ጋር እንደሆነ አልገባኝም በ pm ንገረኝ ለማንኛውም እኔው ራሴ areglhalew ጀማሪ ጸሀፊ?
haw dare you call me ጀማሪ ደራሲ እንን veteran ደራሲ ስቀልድህ ነው አንተ ጀማሪ ደራሲ ያ ለኔ ትልቅ ማእረግ ነው

ቅዱስ እውነቱን ለመናገር እህቴን በሳይበር እንጃ አይመስለኝም

ሰርቬሎ እነዛ ለአምስት ደቂቃ ዳንስ እንቢ ያሉኝ የናንተ ግፍ ፍቅሬን ሰጠኝ ላንተም እንደዚ መልካም እመኝልሀለው

አብቹ አሜን ይጠብቀን አንተንም ይጠብቅህ

ህይወት ለምርቃትሽ አሜን እያልኩኝ i wish you the same

ምስጋናዬ ለሁሉም ላነበባቹሁት ይሁን
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ጨላጣው » Tue Sep 12, 2006 3:36 am

ወ:ንድም.....ደህና ቀዳጅ ነህ በህልምህ ያየሕውን ነው ይጻፍከው ባይ ነኝ:: ለማንኛውም የሳይበር አንባቢዎችህን በምኞት አመረቀንካችው: ለዚህ ነው ጥሩ ትቀዳልህ ያልኩት:: ግን አንድ አልዋጥ ያለኝ ነገር አለ::

አጅሪት ለመሆኑ እዚህ እድሜ እስክትደርስ በልጃገረድነት እዴት ቆየች? ጠያቂ ያጣች አስቀያሚ ሆና ነው ወይስ አንተን ስትጠብቅ? እኔ ከድርሰትህ እድገመትኩት አጝጉል ቢጤ ሳትሆን አትቅርም ባይ ነኝ:: ምክንያቱም ያሁሉ የተቃናልት ግሪሳ በሞላበት አዲስ አበባ ከተማ አጅሪት በመጣጥፍህ አንደቀርጽካት ቆንጆ ከሆነች ድንግል ይቅርና ሌላም ሌላም አይኖራት: መቼ አጣናችው የአዱ ገነትን ልጆች:: ምናልባት ድንግል መስሎህ..........ይሆን እንዴ? ግን ጠዋት የምስራች ተናጋሪዎቹ: የደሙን ሸማ ይዘው ሄዱ ወይስ.....?
ለማንኛውም ድንግል ኖራትም አልኖራት ቆንጅም ሆነች ድስት ለአንት ከተስማማቺህ ይመችህ::
ጨላጣው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 434
Joined: Fri Mar 17, 2006 5:18 pm

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 2 guests