by ሙትቻ » Tue Oct 31, 2006 6:16 pm
ሰላም ማንቼዎች
በአካባቢያችን ከአርብ ጀምሮ ኢንተርኔት ስላልነበረ በቦልተን ላይ በተቀዳጀነው
ታሪካዊ ድል የተሰማኝን ደስታ ሳልገልጥ ቀረሁ:: ቢሆንም አሁንም
ይደርሳል - እንኩዋን ደስ ያለን ማንቼዎች!!
ማንቼ ነገ ለቻምፒዮንስ ሊግ ፍልሚያ ወደ ዴንማርክ ዛሬ ጠዋት ሲጉዋዙ
ሪያን ጊግስ... ጋሪ ኔቭል እና ልዊስ ሰሀ በጉዳት የተነሳ
አብረው አልሄዱም:: በጣም አሳዛኝ ቢሆንም ዳረን ፍሌቸር... ብራውን እና ሶልሻየር የጎደለውን ቦታ ይሞሉታል::
ማንቼ የነገ ምሽቱን ተጋጣሚ ኮፓሀገንን 3 ለ 0 ማሽነፉ አይዘነጋም::
ፈርጊ ዛሬ ጠዋት በማንችስተር አውሮፕላን (ኤር ኤሲያ) ወደ ዴንማርክ
ሲጉዋዙ ይዘዋቸው የሄዱት ተጫዋቾች ዝርዝር ከዚህ የሚከተሉት ናቸው::
Van der Sar, Kuszczak, Brown, Ferdinand, Vidic, Silvestre, Heinze, Evra,
Lee, Ronaldo, Fletcher, Scholes, Carrick, O'Shea, Richardson,
D.Jones, Rooney, Solskjaer, Smith.
ፈርጊ ነገ ኖቬምበር 1 ማንቼን ማሰልጠን የጀመሩበትን 20ኛ አምት ያከብራሉ:: አንካን አደረሰዎ - ሰር::