እዚህ ግሮሠሪ ውስጥ ባማላጅነት የፍቅር ደብዳቤ እንደምንፅፍ አስቀድመን ገልፀንላችሁ ነበር::
እነሆ ቃላችንን ለመጠበቅ ስንል ዛሬ ወንድማችን ክርስቲያን ለ konjit ያለውን ፍቅር ካማከረን በኌላ የግሮሠሪው አገልግሎት ማማለድና ደብዳቤ በመለዕክት መፃፍ መሆኑን አበክሮ ጠይቆን እኛም ጥያቄውን ያቅማችንን ጥረን እንደዚህ አቅርበነዋል::
ይድረስ ፍቅርሽ ላጃጃለኝ ቆንጆዋ የቆነጃጅት ቆንጂት እነኚያ የብር ፍልቃቂ የጨረቃ ፍንጥቅጣቂ የሚመስሉት ጥርሶችሽ በተኛውበት እየታወሡኝ ሕልሜን ሁሉ በፈገግታሽ እንዳጀብኩት ነው የሚነጋልኝ:: ቆንጂዬ እኔ'ኮ እዚህ ባልቻ ግሮሠሪ በየቀኑ ምመጣው ያንቺ ፍቅር ስ__ክ__ር አድርጎኝ'ንጂ የዋናውን በአሕያ ሲጓጓዝ የከረመ የሞቀ ቢራ ፈልጌ አይደለም ይሄው ሞኒካ'ንኳን በበሬ ሹክክ በለህ ታልፋለህ እያለችኝ የትዝብት ቁጣዋን ስታዘንብብኝ አንገቴን ደፋው::
ጠግቤ'ንኳን ከበላው ስንት ጊዜዬ የጉዱ ሥጋ ቤት ጮማ'ንኳን ኣልበላ ብሎኛል ሠዎች ባለፈው ለቅሶ ቤት አይተውኝ ምነው ከሳህ ቢሉኝ ምን ለበላቸው? ቆንጂትዬ ያ የሚያንሆልል ፈገግታሽን ከጅምሩ አሳይተሽኝ በዛ አስማታዊ ዕይታሽ እንደኮብራ ነድፈሽ አስለምልመሽ የተውሽኝ ምን ብበድልሽ ነው? .....ያፍቃሪ ዕጣውስ ይሄ ነውን????
ባለፈው ሠብለ ፀጉር ቤት ጠብቀኝ ብለሽኝ ደጃፉን እንደዘበኛ ስንጎማልለ ቆይቼ ሠዎች ሁሉ ስራ አገኘህ ወይ እያሉ ተሳልቀብኝ ያንቺ ሠሃታት የፈጀ ፀጉርሽ አብቅቶ ስትወጪ በፀሃይ የጠየመ ፊቴን አይተሽ ''ውይ እስካሁን አለህ?'' ብለሽ በሙሉ ዓይንሽ ሳታዪኝ ወዲያው ዲቦራ ቡቲክ ገባሽ::
የዛን ዕለት ወይዘሮ ደብዚ ጠጅ ቤት በንዴት ስጠጣ አድሬ ጠዋት የሞኒካ ካፌ ቡና ነው የፈወሠኝ እስት እባክሽ ፍቅሬን አክብሪና መላ በዪኝ ያንቺ ፍቅር የሌለብኝን ሡስ እያመጣብኝ ነው ይሄው አሁንማ እዛ ግሮሠሪ ከገባሽ ጀምሮ አስሩ ሲያናግርሽ በቅናት ብግን ብዬ መሞቴ ነው::
ቆንጂት ንፅሑ ልቤን አይተሽ መጎዳቴን ተገንዝበሽ ፍቅሬን ትቀበዪኝ ስል እማፀንሻለው:: ................ካንድም ሁለት ሦስት ጊዜ ሚሚ ላቭ ጋር ዘፈን ባስመርጥልሽ በባሕልና ስነፅሑፍ ላይ በግጥም ባወድስሽ አንቺ ግን ምንም ጭጭ ዝም እባክሽ ቆንጅትዬ ብዙ ምሑራን አማክሬ ብዙ ብዙ ዶክተሮች ጋር ተመርምሬ በሽታዬ አንቺን ማጣት ብቻ መሆኑን ነገሩኝ:: እነሱስ ምን ያድርጉ እንደታብሌት ሪፈር አያደርጉኝ ....የራሤ ነፍ ሪፈር አድርጎኝ እዚ ባልቻና መዶሻው ግሮሠሪ ቀረውልሽ :: አሁን አሁንማ እዚሁ ሠፈር ከመብዛቴም ቢራ ሁሉ ተጭኖ ሲመጣ ና! አግዘን እያሉ ይጠሩኝ ጀምረዋል:: እነ ተድባ እና እነ ማሪቱ ባማክራቸው ጭራሽ ለታሕሳስ ገብሬል ባለወርቅ ዘርፍ ጥላ ተሳሉልኝ እነሱስ ምን ያድርጉ ፍቅር መስጠት ቀላል መሆኑን በነደበበ አይተውት ያንቺ ንፉግ መሆን ገርሟቸው ነው::
እና ቆንጂትዬ ምላሽሽን በዋርካው አድባር እየተማፀንኩኝ እንድታሳውቂኝ ስል እለምንሻለው የፍቅር አምላክ ይርዳኝና [/color]
ተፃፈ በ''ባልቻና መዶሻው ግሮሠሪ የፍቅር አማላጆች''
_________________________________________________::
_________________________::
[/list]