ባልቻና መዶሻው ግሮሠር=> ተጠፋፋን

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ዘኪዮስ5 » Mon Dec 04, 2006 1:25 am

እዚህ ግሮሠሪ ውስጥ ባማላጅነት የፍቅር ደብዳቤ እንደምንፅፍ አስቀድመን ገልፀንላችሁ ነበር::
እነሆ ቃላችንን ለመጠበቅ ስንል ዛሬ ወንድማችን ክርስቲያን ለ konjit ያለውን ፍቅር ካማከረን በኌላ የግሮሠሪው አገልግሎት ማማለድና ደብዳቤ በመለዕክት መፃፍ መሆኑን አበክሮ ጠይቆን እኛም ጥያቄውን ያቅማችንን ጥረን እንደዚህ አቅርበነዋል::


ይድረስ ፍቅርሽ ላጃጃለኝ ቆንጆዋ የቆነጃጅት ቆንጂት እነኚያ የብር ፍልቃቂ የጨረቃ ፍንጥቅጣቂ የሚመስሉት ጥርሶችሽ በተኛውበት እየታወሡኝ ሕልሜን ሁሉ በፈገግታሽ እንዳጀብኩት ነው የሚነጋልኝ:: ቆንጂዬ እኔ'ኮ እዚህ ባልቻ ግሮሠሪ በየቀኑ ምመጣው ያንቺ ፍቅር ስ__ክ__ር አድርጎኝ'ንጂ የዋናውን በአሕያ ሲጓጓዝ የከረመ የሞቀ ቢራ ፈልጌ አይደለም ይሄው ሞኒካ'ንኳን በበሬ ሹክክ በለህ ታልፋለህ እያለችኝ የትዝብት ቁጣዋን ስታዘንብብኝ አንገቴን ደፋው::

ጠግቤ'ንኳን ከበላው ስንት ጊዜዬ የጉዱ ሥጋ ቤት ጮማ'ንኳን ኣልበላ ብሎኛል ሠዎች ባለፈው ለቅሶ ቤት አይተውኝ ምነው ከሳህ ቢሉኝ ምን ለበላቸው? ቆንጂትዬ ያ የሚያንሆልል ፈገግታሽን ከጅምሩ አሳይተሽኝ በዛ አስማታዊ ዕይታሽ እንደኮብራ ነድፈሽ አስለምልመሽ የተውሽኝ ምን ብበድልሽ ነው? .....ያፍቃሪ ዕጣውስ ይሄ ነውን????

ባለፈው ሠብለ ፀጉር ቤት ጠብቀኝ ብለሽኝ ደጃፉን እንደዘበኛ ስንጎማልለ ቆይቼ ሠዎች ሁሉ ስራ አገኘህ ወይ እያሉ ተሳልቀብኝ ያንቺ ሠሃታት የፈጀ ፀጉርሽ አብቅቶ ስትወጪ በፀሃይ የጠየመ ፊቴን አይተሽ ''ውይ እስካሁን አለህ?'' ብለሽ በሙሉ ዓይንሽ ሳታዪኝ ወዲያው ዲቦራ ቡቲክ ገባሽ::
የዛን ዕለት ወይዘሮ ደብዚ ጠጅ ቤት በንዴት ስጠጣ አድሬ ጠዋት የሞኒካ ካፌ ቡና ነው የፈወሠኝ እስት እባክሽ ፍቅሬን አክብሪና መላ በዪኝ ያንቺ ፍቅር የሌለብኝን ሡስ እያመጣብኝ ነው ይሄው አሁንማ እዛ ግሮሠሪ ከገባሽ ጀምሮ አስሩ ሲያናግርሽ በቅናት ብግን ብዬ መሞቴ ነው::
ቆንጂት ንፅሑ ልቤን አይተሽ መጎዳቴን ተገንዝበሽ ፍቅሬን ትቀበዪኝ ስል እማፀንሻለው:: ................ካንድም ሁለት ሦስት ጊዜ ሚሚ ላቭ ጋር ዘፈን ባስመርጥልሽ በባሕልና ስነፅሑፍ ላይ በግጥም ባወድስሽ አንቺ ግን
ምንም ጭጭ ዝም እባክሽ ቆንጅትዬ ብዙ ምሑራን አማክሬ ብዙ ብዙ ዶክተሮች ጋር ተመርምሬ በሽታዬ አንቺን ማጣት ብቻ መሆኑን ነገሩኝ:: እነሱስ ምን ያድርጉ እንደታብሌት ሪፈር አያደርጉኝ ....የራሤ ነፍ ሪፈር አድርጎኝ እዚ ባልቻና መዶሻው ግሮሠሪ ቀረውልሽ :: አሁን አሁንማ እዚሁ ሠፈር ከመብዛቴም ቢራ ሁሉ ተጭኖ ሲመጣ ና! አግዘን እያሉ ይጠሩኝ ጀምረዋል:: እነ ተድባ እና እነ ማሪቱ ባማክራቸው ጭራሽ ለታሕሳስ ገብሬል ባለወርቅ ዘርፍ ጥላ ተሳሉልኝ እነሱስ ምን ያድርጉ ፍቅር መስጠት ቀላል መሆኑን በነደበበ አይተውት ያንቺ ንፉግ መሆን ገርሟቸው ነው::

እና ቆንጂትዬ ምላሽሽን በዋርካው አድባር እየተማፀንኩኝ እንድታሳውቂኝ ስል እለምንሻለው የፍቅር አምላክ ይርዳኝና [/color]

ተፃፈ በ''ባልቻና መዶሻው ግሮሠሪ የፍቅር አማላጆች''

_________________________________________________::


_________________________::
[/list]
ዘኪዮስ5
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 42
Joined: Sun Aug 13, 2006 12:00 am

Postby ዋናው » Mon Dec 04, 2006 1:53 am

ክቡራን እና ክቡራት ደንበኞቻችን በፍቅር ተበድለናል ለምትሉ አፍቃሪያን በሙሉ የፍቅር ደብዳቤ ባማላጅነት እንደምንፅፍ በዚህ አጋጣሚ በድጋሚ አናሳውቃለን ዘርፈ ብዙው ነፃ አገልጎታችን እንደሚደሰቱ ተስፋ እናደርጋለን::

ሌላ ማስሳሰቢያ

ዘውትር ኃሙስ ምሽት በዲጄ እንቅልፍ አልባዋ(slee pless girl) የሚቀርብ ፓርቲ መጀመራችንን በደስታ እንገልጻለን::

አስተዳዳሪው_____________________________________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ክርስትያን06 » Mon Dec 04, 2006 4:22 pm

እንደኔው አይነቱ ልቡ በፍቅር ፍላጻ ለተወጋና ሁለት የተለያዩ ካልሲዎች አድርጎ በሸፋፋ ጫማ በየግሮሰሪው. በየስጋ ቤቱና ቡና ቤቱ ...ቆንጂትን ለማግኘት ለሚንከራተተው ጉብል የዋናው ግሮሰሪ ፍቱን መድሓኒት ነው::

ዛሬም ""አንችን መጠበቅ አይሰለቸኝም"" የሚለውን የሙሉቀንን ዘፈን እየዘፈንኩ ከግሮሰሪው ተጎልቻለሁ::

አብየ ዋናው ግን እጁ እሳት ሆነብኝ... የሚቀጥለውን ደብዳቤየ ላይ ቅናሽ ብታርግልኝ ፈንጥዝያየ ልክ አይኖረውም::

አንች ሞኒካ ባልሽው መሰረት ሹልክ ብየ ቅምስን እጎበኛለሁ::
ክርስትያን06
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 601
Joined: Fri Sep 08, 2006 5:15 pm

Postby እንቆጳፂዮን1 » Mon Dec 04, 2006 11:39 pm

ስትሪፕ ደናሽ እንድምትፍልጉ ሰምቸ ነው የመጣውት ሽንቅጥቅጥ ያልኩኝ ነው ሰዉ ሁል በኔ ሰውንት ዓይኑ እንደሚጎለጎል ተስፋ አልኝ እናም አፕሊከሽኔ ይታይልኝ ስል እጠይቃለው::

ቅቅቅ
እንቆጳፂዮን1
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 10
Joined: Wed Oct 11, 2006 7:05 pm

ወይ ኑሮ

Postby እሪኩም » Tue Dec 05, 2006 2:20 am

ሠላም ዋናው!

ኑሮ እንደ ኑሮነቱ ያዘግማል ወይ?
ግሮሰሪህ ዘሎ ፍቅር አንባ ሲገባ - አብረው ሲንደፋደፉ ማዬቱ ሰልችቶኝ - ቀስ በቀስ ይዤዐቸው ወደ ሠፈርህ ተመልሼ አጻጻፍ ወይንም አረጋገጥ እንዲችሉ ብዬ ቀይሻቸዋለሁ - አንተም አይተህ - ተጨማሪ ከመስጠት እንደማትቆጠብ ነው::

Image

ወይ ኑሮ - እንበርታ
እሪኩም
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby ዋናው » Tue Dec 05, 2006 11:18 pm

ክሪስ

እንዴት ነው konjit ጨከነችብህ'ንዴ ቅቅቅ ለነገሩ ፍቅር ትንሽ ሲያንገላታ ነው ሚጣፍጠው ብላ ይሆን እኔንንጃ ቅቅቅ ካልሆነ ሌላ ቦምብ የሆነ ደብዳቤ ደግሞ እንፅፋለን ያኔ ፍቅሯ ወደሷ ይዞራል አይዞህ ለሂሣቡ አጽጋ ዋጋችን ተመጣጣኝ ይሆናል::
እንቖጳ እስቲ ያንድ ሳምንት ሙከራ እንሠጥሻለን ሌሎች የስትሪፕ ደናሾች ሲበራከቱ እናሳውቅሽና ግን ልበሙልነትሽ ጥሩ ይመስላል::

እሪኩም ደረደርከው'ኮ ይሄን ቢራ ቅቅቅ ተባረክ አቦ ገበያው ደርቶ አልቆብኝ ሠዉን በደረቅ ጅን አሳርሬው ነበር::

እስቲ እየጠጣቹ


ዋናው_______________________________________________________________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby Monica**** » Wed Dec 06, 2006 9:45 pm

ዋናችን
እስኪ ደብል ብራንዲ ቅዳልኝ ከዛ በፊት ሁለት ጠርሙስ ቢራ አምጣልኝ እዚህ ቤት ስርቪስ መቼም ፑር ነው!!!
ብርዱ ጆሮዬን ሳይቆርጠው ቶሎ በል!!!!
ደሞ የፍቅር ደብዳቤ መጻፍ ጀመርክ? በል ለኔም አንድ 20 የምጽፍላችው ስዎች አሉና አስቤ ስማችውን እስክነግርህ ድረስ ብራንዲውን ድገመኝ
ያxኢ የግልነስ እንደሆን አዝማሪነቱን ትታዋለች( አዝማሪ ስድብ ከሆነ ዘፋኝነቱን)
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby Konjit » Thu Dec 07, 2006 5:38 am

ሰላም ለቤቱ ደምበኞች በሙሉ

እዚህ ግሮሠሪ ውስጥ ባማላጅነት የፍቅር ደብዳቤ እንደምንፅፍ አስቀድመን ገልፀንላችሁ ነበር ::
እነሆ ቃላችንን ለመጠበቅ ስንል ዛሬ ወንድማችን ክርስቲያን ለ konjit ያለውን ፍቅር ካማከረን በኌላ የግሮሠሪው አገልግሎት ማማለድና ደብዳቤ በመለዕክት መፃፍ መሆኑን አበክሮ ጠይቆን እኛም ጥያቄውን ያቅማችንን ጥረን እንደዚህ አቅርበነዋል ::


ውዱ አለቃዬ ምነው ገበናዬን ባደባባይ ሲሆን ሲሆን መጀመሪያ ለኔ በድብቅ ይነገርና ከዛ ጸሀይ እንዲመታው ለህዝብ ይለቀቃል አፍቃሪው ክሪስ ተፈቃሪዋ እኔ, ምንስ እኮ ቢሆን የዚህ ቤት ገበያ በኔ ነው እኮ ያለው መነካህ እሳ ወይ ደሞዝ ቢጤ ጨምር ወይ ደሞ እድገት ይሰጠኝ.

ይድረስ ፍቅርህ ላሳመረኝ የጻፊዎች ጻፊ የወንዶች ወንድ እነኛ ኪቦርድ ስትመታባቸው ሚያሳሱት እጆችህ እንዲው በህልሜ እየመጡ ግጥም ስትገጥምልኝ ሚነጋልኝ አንተ ግርማ ሞገስህ ያማረ ምለሎ ጎምላላ እንዲት ነህልኝ. የፍቅርህ ሚዳቆ ልቤላይ ፈንድቆ አላስቆም አላስቀምጥ ቢለኝ ይህን የፍቅሬን መግለጫ ደብዳቤ ካለህበት ላደርስ ቆርጬ ተነሳሁ:: ክሪስዬ እዚህ ባልቻ መዶሻ ካየሁህ ቀን ጀምሮ እንዲሁ ልቤን እንደ ሌባ ሳታንኳኳ ዘው ብለህ ገብተህ ሰርቀህው ከሄድህ ሰነበተ እንዴት ብዬ እንደምገልጽልህ ቢያቅተኝም እ/ር ብድሩን ይከፈለውና ዋንሽ አለቃዬ ብቻ ሳይሆን የስሜቴ ተካፋይ በመሆን ላንተ ይህችን ደብዳቤ እንድጽፍ ሲገፋፋኝ ቆይቶቷል:: ምንም እንኳን ሞኒካ በበሬ በላም ምትለው ነገርዋ እኔ ባውቅባትም አስተያየትዋ ግን በጎሪጥ መሆኑ ደስ አላለኝም የስዋ እንኳን አያበሳጨኝም ያቺ የግል ግን ዝም ብላ ካንተ ጋር ያበዛችው ሰፋጣ እንዲሁ ሲያንገበግበኝ ነው ሚያመሸው የንጀራ ነገር ሆኖብኝ ግን ምን እናገራለሁ::
ሚያሳዝነኝ ግን አንተ ትመጣለህ እያልኩ ያቺን ኮርነር ቦታ ማንም እንዳይቀመጥ እያልኩ ዋንሽ ሚቆጣኝ ነው አንተ ግን መች ይገባህና ዝም ብለህ ይቺ ሞኒካ ቤት ገብተህ ስትሰልቅ ታመሽና ቤቱ ሊዘጋ ሲል ትመጣለህ እረ ተው ግፍ አለው:: የሄ እንደበረዶ የተንገጠገጠው ጥርሴ እኮ ላንተ ብቻ እንጂ ለማንም ሚፈታ አይደልም እሱ አይደልም የጉዱን ጥሬ ስጋ የሀረር ሰንጋ እንኳን በልተህ አያረካህም, ግን እደው እንደልማድህ የኔን ፈገግታ ስታይ ሰሶስት ወር ጮማ አያሰኝህም ልክ እንደ ጮማ ነኛ:: ? ደሞ አንተን ደስ ይበልህ ብዬ ሰብሊ ጋር ጸግሬን ብሰራ አንተ መቼስ ጥሩ ነገር መውደድ ካቆመልህ ሰነበተ እንዲሁ ያልቀ መወልወያ እያስመሰልኩ ፍሪዝ እያልኩ ብሄድ ምርጫህ ነው:: እረ ተው የኔ ማማር እኮ ላንተ ጌጥ ነው:: (በየት በኩል እንዳተልኝ ብቻ) ዲቦራ ቡቲክ መግባቴ አንተን እንደዛ ያከረረች ጸሀይ እኔን ከማድረቅዋ በፊት ሰን ስክሪን ለመግዛት ብዬ እንጂ አፈር የመሰለውን ፊትህን ማየት መች ጠልቼ አንተን ስወድ እኮ እስከተንሻፈፈው ጫማህ ነው:
እማዝነው ግን የዛን እለት ደብዚ ጠጅ ቤት ከምትሄድ አብረን ግሮሰሪ እንምጣ ስልህ እንዲሁ የደብዚን ጠጅ ስትጋት አደርክ ሞኒካ እማ እኔን ለማናደድ የዶሮ አይን የመሰለ ቡና አፍልታ ሰጠችህ አልሆነልሽም በላት:: እኔ ልጅት እንደሆን እንዲሁ በቀላሉ አልቀናም:: አንተ ተቃጥለህ ከምትሞት ግፋ ቢል ቢቀር ሚቀረው ቲፕ ነው እሱም ደሞ ደጎስ ያለ ቲፕ ሚሰጥ ዘርሽ ነው እሱን ማስተናገድ አቆማለሁ ሚዬቲ ታስተናግደው ላንተ ስል ማልከፍለው መስዋትነት የለም::
ለማንኛውም ንጹሁ ልብህን አይቼ መጎዳትህን ተገንዝቤ ፍቅርህንም ተጋርቼ ልቀበልህ እየተዘጋጀሁ ነው ዘፈኑ ግን አልደረሰኝም::ተፃፈ በ ''ባልቻና መዶሻው ግሮሠሪ የፍቅር ተማላጅ ''
Faith is putting all your eggs in God's basket, then counting your blessings before they hatch. ~Ramona C.
Konjit
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 473
Joined: Sun Sep 07, 2003 6:59 am

Postby ክርስትያን06 » Thu Dec 07, 2006 4:16 pm

ይከርከር ክራሩ ይደለቅ ከበሮው
ይነፋ ዋሽንቱ ይመታ ማሲንቆው
ወፎች ይዘምሩ ሆነው ከዛፍ ላይ
አማልክት ይውረዱ ከሰማየ ሰማይግዋዝሽን ጠቅልለሽ ገብተሽ ከልቤ ውስጥ ተንዘራፍጠሽ የፍቅር ድውርሽን ለምትደውሪብኝ ቆንጂት

አንችን ለማግኘት ያልዞርኩበት ምን አለ:: ጫማየ ምስክር ነው:: የዛሬ ሶስት አመት ከደነበኛየ ባልቻ ዘንድ የገዛሁት ጫማ ይህው አንችኑ ለመፈለግ ስዋትትበት ያለእድሜው እርጅቷል:: ሰሞኑን ተመልሸ ባልቻ ዘንድ ሄጄ ሁለት ደህና ደህና ምስማር ከጎኑና ከጎኑ አስገብቶልኛል:: ታድያ ምን ያረጋል ያ ምስማር በጎን በኩል ጥርሱን አግጥጦ እያወጣ ያስነክሰኝ ጀመር:: አይ ዘንድሮ ባልቻ ደግሞ እጁ አልቀመስ ብሏል:: ቢብስብኝ ሰሞኑን የ10 ብር እቁብ ገብቻለሁ:: እንዲያ ሽቅር ቅር ብለሽ ሳይሽ መቸም በበረባሶ መምጣቱ አሳፍሮኝ ነው እንጂ ሳልናፍቅሽ ቀርቸ አይደለም::

ቆንጂትየ

ያች ሞኒካ ጋ ከሰሞኑ ጎራ ብየ ቆንጂትየን አየሽ ወይ ብየ ብጠይቃት ቡና ተፈልቷል ተቀመጥ የኔ ጎብላላ እያለች ልታማልለኝ ሲሞክራት እኔ ያንች አንበሳ ምኗ ሊታየኝ አይኔን ጨፍኘልሽ ከቤቷ ወጣሁ:: እንዲያው ከየት አምጥታ ነው እንዲህ ያጋጌጠችው? ቡና በመቸርቸር ብቻ ነው ብለሽ ነው? ለነገሩ እንደው ቡናዋስ የዋዛ አይደለም:: አንችን ስፈግል ናላየ ዞሮ ጎራ ብየ አንዱን ብታቀምሰኝ አይኔ ቦግ ነው ያለው;; ምህታት አለው ቆንጂትየ አያድርስ ነው::

ያ ዘሪሽ የምትይው ሰው አላማረኝም... ሰሞኑን አንድ ሽህ ብር እቁብ ደርሶታል መስለኝ አስሬ ኪሱን እየደባበሰ በቲፕ ሊያነሆልልሽ ይሞክራል:: ቆንጂትየ ሁለቱን ወደል አህዮቸን ብሸጣቸው እኮ ካንድ ሽህ ብር በላይ ናቸው:: ደግሞ ለገንዘብ.. እረ አንበሸብሽሻለሁ:: ለጠጉርሽ ማስሪያ ገንዘብ ጠፍቶኝ መሰለሽ.. እኔ ቀልቤን የሚወስደው በሻሽ ግጥም አርገሽው ሳይሽ ነው:: ቅባትም አታብዥ ምን ያረጋል... ሰው አይን መግባት ነው ትርፉ::

እረግልኝ ሰሞኑን አልሜሽ ሳልነግርሽ... ቆይ እሱን ብቻሽን ነው የምነግርሽ::

ያንችው ተከራታች

ተጻፈ ከባልቻ ግሮሰሪ
ክርስትያን06
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 601
Joined: Fri Sep 08, 2006 5:15 pm

Postby ክርስትያን06 » Thu Dec 07, 2006 4:23 pm

ግዋዝሽን ጠቅልለሽ ከልቤ ውስጥ ተንዘራፍጠሽ የፍቅር ድውርሽን ለምትደውሪብኝ ቆንጂት

አንችን ለማግኘት ያልዞርኩበት ምን አለ:: ጫማየ ምስክር ነው:: የዛሬ ሶስት አመት ከደነበኛየ ባልቻ ዘንድ የገዛሁት ጫማ ይህው አንችኑ ለመፈለግ ስዋትትበት ያለእድሜው እርጅቷል:: ሰሞኑን ተመልሸ ባልቻ ዘንድ ሄጄ ሁለት ደህና ደህና ምስማር ከጎኑና ከጎኑ አስገብቶልኛል:: ታድያ ምን ያረጋል ያ ምስማር በጎን በኩል ጥርሱን አግጥጦ እያወጣ ያስነክሰኝ ጀመር:: አይ ዘንድሮ ባልቻ ደግሞ እጁ አልቀመስ ብሏል:: ቢብስብኝ ሰሞኑን የ10 ብር እቁብ ገብቻለሁ:: እንዲያ ሽቅር ቅር ብለሽ ሳይሽ መቸም በበረባሶ መምጣቱ አሳፍሮኝ ነው እንጂ ሳልናፍቅሽ ቀርቸ አይደለም::

ቆንጂትየ

ያች ሞኒካ ጋ ከሰሞኑ ጎራ ብየ ቆንጂትየን አየሽ ወይ ብየ ብጠይቃት ቡና ተፈልቷል ተቀመጥ የኔ ጎብላላ እያለች ልታማልለኝ ሲሞክራት እኔ ያንች አንበሳ ምኗ ሊታየኝ አይኔን ጨፍኘልሽ ከቤቷ ወጣሁ:: እንዲያው ከየት አምጥታ ነው እንዲህ ያጋጌጠችው? ቡና በመቸርቸር ብቻ ነው ብለሽ ነው? ለነገሩ እንደው ቡናዋስ የዋዛ አይደለም:: አንችን ስፈግል ናላየ ዞሮ ጎራ ብየ አንዱን ብታቀምሰኝ አይኔ ቦግ ነው ያለው;; ምህታት አለው ቆንጂትየ አያድርስ ነው::

ያ ዘሪሽ የምትይው ሰው አላማረኝም... ሰሞኑን አንድ ሽህ ብር እቁብ ደርሶታል መስለኝ አስሬ ኪሱን እየደባበሰ በቲፕ ሊያነሆልልሽ ይሞክራል:: ቆንጂትየ ሁለቱን ወደል አህዮቸን ብሸጣቸው እኮ ካንድ ሽህ ብር በላይ ናቸው:: ደግሞ ለገንዘብ.. እረ አንበሸብሽሻለሁ:: ለጠጉርሽ ማስሪያ ገንዘብ ጠፍቶኝ መሰለሽ.. እኔ ቀልቤን የሚወስደው በሻሽ ግጥም አርገሽው ሳይሽ ነው:: ቅባትም አታብዥ ምን ያረጋል... ሰው አይን መግባት ነው ትርፉ::

እረግልኝ ሰሞኑን አልሜሽ ሳልነግርሽ... ቆይ እሱን ብቻሽን ነው የምነግርሽ::

ያንችው ተከራታች

ተጻፈ ከባልቻ ግሮሰሪ
ክርስትያን06
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 601
Joined: Fri Sep 08, 2006 5:15 pm

ምን ይሻላል?

Postby እሪኩም » Thu Dec 07, 2006 11:22 pm

ሠላም ዋናው!

ባለፈው የላክልኝ ቀዝቃዛ ባቲ ቢራ ልዩ ጣዕም ስለነበረው እንግዶቼ ተደስተው በሥነ ሥርዕቱ ከተስተናገዱ በኍላ ሞቅ ያለ ሠላምታ እና ምስጋና አስተላልፈዋል:: ይኽው ተቀበላቸው::
Image

ብፈልግ ባስፈልግ የምወዳት እና የምትወደኝ ጦቢያ ከተሰወረች ጊዜያት አስቆጥራለች::
ምን ይሻላል?
Image

መልካም ወቅት
እሪኩም
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby sable » Thu Dec 07, 2006 11:27 pm

ዘኪዮስ5 wrote:ባለፈው ሠብለ ፀጉር ቤት ጠብቀኝ ብለሽኝ ደጃፉን እንደዘበኛ ስንጎማልለ ቆይቼ ሠዎች ሁሉ ስራ አገኘህ ወይ እያሉ ተሳልቀብኝ ያንቺ ሠሃታት የፈጀ ፀጉርሽ አብቅቶ ስትወጪ በፀሃይ የጠየመ ፊቴን አይተሽ ''ውይ እስካሁን አለህ?'' ብለሽ በሙሉ ዓይንሽ ሳታዪኝ ወዲያው ዲቦራ ቡቲክ ገባሽ::
ተፃፈ በ''ባልቻና መዶሻው ግሮሠሪ የፍቅር አማላጆች''
_________________________::
[/list]


ሄይይይይ ዋናው እንዴት ነህ?
ክርስ እንደዛ ቤቴ ጋ ሲመላለስ ግርም ብሎኝ በመስኮት ስከታተለው ነበር እንዳውም ምን እየሰራህ ነው ግባና ተቀመጥ ጸሀይ ነው ስለው ሰው እየጠበኩ ነው እዙሁ ይሻለኛል ብቻ የሚጠጣ ውሀ ብቻ ስጪኝ ጸሀዩን አልቻልኩትም ብሎኝ ነበር....... ከዛ ማንን እንደሚጠብቅ ስጠይቀው ለመናገር ፍቃደኛ ስላለነበር እኔም ብዙ አላስቸግረውም ብዬ ወደ ስራዬ ተመለስኩ ቆንጂትም ሄደ አልሄደ እያለች ስተከታተል ነበር መች ገባኝ እኔ ለካ አንፎቃቂው ፍቅር ነው...............በል እስቲ መልካም እድል ክርስ ቆንጂትን አሳምሬልሀለሁ :lol: :lol: :lol: ::

ዋናው የሀሙሱን ብሮግራም ሰምቼ ነው የመጣሁት ቴብል ያዝልኝ አራት ሆነን ነው የምንመጣው:: ስሊፒ Go Girl ይመችሽ 8)
Love is the Magic Key of Life!.
sable
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 168
Joined: Fri Jun 09, 2006 5:31 am
Location: next door! :)

Postby ዋናው » Fri Dec 08, 2006 1:46 am

Monica**** wrote:ዋናችን
እስኪ ደብል ብራንዲ ቅዳልኝ ከዛ በፊት ሁለት ጠርሙስ ቢራ አምጣልኝ እዚህ ቤት ስርቪስ መቼም ፑር ነው!!!
ብርዱ ጆሮዬን ሳይቆርጠው ቶሎ በል!!!!
ደሞ የፍቅር ደብዳቤ መጻፍ ጀመርክ? በል ለኔም አንድ 20 የምጽፍላችው ስዎች አሉና አስቤ ስማችውን እስክነግርህ ድረስ ብራንዲውን ድገመኝ
ያxኢ የግልነስ እንደሆን አዝማሪነቱን ትታዋለች( አዝማሪ ስድብ ከሆነ ዘፋኝነቱን)

ሞኒካዬ ይሄ ብርድ ቅቅቅቅ በግል የሳቅሽው አንቺ ላይ ደረሰ ቅቅቅ ደብል ብራንዲ ደብል ቢራ ...ኸረቀስ በይ ምንም ንግድ ቢሆንም ያንቺን ውልቅ ማለት አልፈልግም ቅቅቅቅ በደብል ብራንዲ.....? ብለሽ ባልሳቅሽብኝ ...
ጠፋሽ ሠሞኑን ምነው ቤትሽን ትውሽው ልበል ሂሳብ ልትረከቢ ብቻ ነው ብቅ ብለሽ በዛው ላጥ የምትዪው ቅቅቅ
እንግዲ ሞኒካለም ያልሻቸውን ፍቅረኞችሽ ንገሪንና ደብዳቤውን እንፅፍልሻለን::በተመጣጣኝ ዋጋ::_______________________________________________________________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Dec 08, 2006 1:57 am

Konjit wrote:
ለማንኛውም ንጹሁ ልብህን አይቼ መጎዳትህን ተገንዝቤ ፍቅርህንም ተጋርቼ ልቀበልህ እየተዘጋጀሁ ነው ዘፈኑ ግን አልደረሰኝም::ተፃፈ በ ''ባልቻና መዶሻው ግሮሠሪ የፍቅር ተማላጅ ''

ውድ ታዳሚያን አማላጅነታችን እንደዚህ ሃሳብ እንደሚያስቀይር ምስክር ይሆናቹ ዘንድ ከላይ ያነበባችሁት የሁለቱ ፍቅረኞችን ወግ ትኮመኩሙ ዘንድ ግብዣችን ነው ታዲያ ሳያዙ መቀመጥ አይቻልም አሁንም አስፈላጊውን ሁሉ ደብዳቤ እንፅፋለን ፍቅር እናማልዳለን:: ባገልጎታችን ይደሰታሉና ችግሮን አማክሩን....ይላልል ''የባልቻና መዶሻው ግሮሠሪ''

ቆንጂት
የደሞዝ ጭማሪ መጠየቅሽ ሚስጥሩ ዘግይቶ ቢገባኝም ለክሪስመስ ያልኩሽ ጭማሪ በዚህ ሳምንት እንደሚጀምርልሽ ልነግርሽ እወዳለው ....ይሄም አላማዬ የቤታችን ቋሚ ደንበኛ ሁለቱን አሕያዎቹን ከመሸጥ ይድናል በማለት ነው::

ምክኒያቱም አሕያዎቹን ከሸጠ ነገ ሚጠጣበት ስለሌለ ዞሮ ዞሮ ችግሩ ወደኔ ነው ብዬ ነው::ቅቅቅቅ_____________________________________________________________________________:[/list]
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Dec 08, 2006 2:06 am

ክርስትያን06 wrote:
ያ ዘሪሽ የምትይው ሰው አላማረኝም... ሰሞኑን አንድ ሽህ ብር እቁብ ደርሶታል መስለኝ አስሬ ኪሱን እየደባበሰ በቲፕ ሊያነሆልልሽ ይሞክራል:: ቆንጂትየ ሁለቱን ወደል አህዮቸን ብሸጣቸው እኮ ካንድ ሽህ ብር በላይ ናቸው:: ደግሞ ለገንዘብ.. እረ አንበሸብሽሻለሁ:: ለጠጉርሽ ማስሪያ ገንዘብ ጠፍቶኝ መሰለሽ.. እኔ ቀልቤን የሚወስደው በሻሽ ግጥም አርገሽው ሳይሽ ነው:: ቅባትም አታብዥ ምን ያረጋል... ሰው አይን መግባት ነው ትርፉ::

እረግልኝ ሰሞኑን አልሜሽ ሳልነግርሽ... ቆይ እሱን ብቻሽን ነው የምነግርሽ::

ያንችው ተከራታች

ተጻፈ ከባልቻ ግሮሰሪ


ውድክሪስ
እንዴት ነህ በዘሪሽ ዕቁብ መቅናት መጀመርህ ትንሽ ከፍቶኛል ምክኒያቱንም የሱ እቁብ መግባት ለእኔ ይጠቅማልና ነው ብቻ ስጋትህ ገብቶኛል አይዞህ ቅቅቅቅ
የባልቻና መዶሻ ግሮሠሪ ብዙ ችግሮቹን ስለሚፈታ ያንተን አሕዮች ወደበቅሎ የምትቀይርበት መንገድ በማመቻቸት ላይ ነው::
በተረፈ መልካም
ፍቅር ደንበኝነትህ እንደፀና ይሁን በዋጋችን ተመጣጣኝነት መቼም እንደረካህ ተስፋ አለን::

______________________________________________________________:[/list][/list]
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 9 guests