አንዱ ሌላውን የማጥፋት ሩጫ ለምን ይሆን ?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: አንዱ ሌላውን የማጥፋት ሩጫ ለምን ይሆን ?

Postby ራስ ንጉስ » Thu Dec 14, 2006 11:21 am

ምን ይሽላል ? wrote:እንደምን ሰነበታችሁ ወገን ?

http://www.ethiopianreporter.com/module ... &sid=10569

http://www.ethiopianreporter.com/module ... &sid=10572

ይህንን ዘገባ አይታችሁታል ?

ለእኔ የታየኝ ! በፎቶ ላይ የሚታየውን የቀድሞ {ደርግ} መንግስት ባለሥልጣኖች ፎቶና የፍርድ ሂደት ብቻ ሳይሆን : ያለፈውና የሚቀጥለው አጠቃላይ ታሪካችን ነው ::

እኔ የዚህች አገር መጨረሻዋ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ከአእምሮዬ በላይ ሆኖብኛል ::

መደማመጥና መከባበር የጠፋበት ሕዝብ : አንዱ ሥልጣን ሲይዝ : በዕውር ዳበሳ ጉዞ ቀና ብሎ ያየውን ሁሉ ጠላቴ ነው እያለ መጨፋጨፍ ለምን እንደሚጠቅም ምንም ሊገባኝ አልቻለም ::

የሩቁ ዘመን ይቆይና : እስኪ ትንሽ ወደኍላ ሄደን ታሪካችንን እንመልከተው ::

በታሪክ እንዳነበብነው

1. ዐጼ {እምዬ} ሚኒልክ ዐጼ ዮሐንስን : ባህታዊ መሰል ሰላይ ልከው ብውድውርቡሾች ተደብድበው እንዲሞቱ አደረጉ ::

2. ዐጼ ኃይለ ስላሴ ልጅ ኢያሱን በተንኮል አስረው አስገደሉ :: በመቀጠልም : እነ በላይ ዘለቀን የመሰለ የቂርጥ ቀን ጀግና አታለው : እነ መንግስቱ ንዋይን የመሰሉ በወቅቱ ለአገሪቱ የሚያስፈጓትን ምሑራን : ከሳቸው የተለየ አሳብ ስላቀረቡ ብቻ በአደባባይ ሰቅለው ገደሉ ::

3. ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለ ማርያምና መሰሎቻቸው የጦር መኮንኖች ያስተማሯቸውን ሽማግሌ አባት ጃንሆይን : በሳቸውም ሰበብ : አገሪቱ በብዙ ወጪ ያፈራቻቸውንና መተኪያ የሌላቸውን : ታላላቅ ባለስልጣናት : የጦር መኮንኖች : በአንድ ቤት ሰብስበው ሲረሽኑ : ምሑራንና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የነበሩትን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ሳይቀር ለረጅም ዐመታት በጽኑ ካንገላቷቸው በኍላ በገመድ እያንጠለጠሉ ፈጇቸው :
በመቀጠል : ለአገር ተረካቢ የነበረውን ትኩስ ኃይል {ወጣት} ቀይ ሽብር እያሉ : እግዚአብሔር የፈጠረውን ክቡር ሕይወት እንደቀልድ በጠራራ ሜዳ ሲጨፈጭፉት : ከዚያ የተረፈውም : በውጭ አገርና በጫካ በመረባረብ : ጨካኙን የደርግን መንግስት ለውድቀት አበቃው ::

እንደገናም ለደርግም ይኸው አልበቃ ብሎት : በየጊዜው ደስ ሲለው በግልጽም በድቅም ከሚረሽናቸው በተጨማሪ : 66 መኮንኖችን በአንድ ቀን ወታደራዊ ፍርደ ረሸናቸው ::

4. ከዚህ ሁሉ በዙ ምውሰድ የሚገባቸው የአሁኑ ጠቅላይ ሚንስቴር አቶ መለስ ዜናዊ ደግሞ :: ያለፉትን መሪዎች መመሪያ በበለጠና በረቀቀ ስልት : በቡድን ላይ በተመሰረተ ፖለቲካ ማለትም በስልጣን : አንዱን ታማኝና ምርጥ ዘር : ሌላው የማይታመን : ጉልበቱና እውቀቱ ብቻ የሚፈለግ እንጅ : በጥቅምም ሆነ በማንኛውም የአገሪቱ ወሳኝ ጉዳዮች ውስጥ ምንም ቦታ የሌለው ዓይነት አስተዳደር መስርተው : ከምንም የህዝቡ ብቸኛ ሀብት የነበረውን : ተስማምቶና ተከባብሮ የመኖር አኩሪ ባህሪውን : የስልጣን ዕድሜ ለማራዘም ሲባል ብቻ : የልዩነት ነጸብራቅና ፈርጥ የሆነውን የቋንቋ የጎሳ ልዩነት መሳሪያ አድርጎ በመከፋፈል : ከምንጊዜውም በከፋ ሁኔታ በሕዝባችን መካከል መርዝ ነዛበት ::

በሌላም በኩል የውሸት ዲሞክራሲ ብሎ አወጀና : የጫካ የትግል አጋሮቹ : ከነበሩት ሻዕቢያና ዖነግን መካከል ዘር ቆጥሮ : እንዲ በአጭሩ ለሚቀጨው ፍቅራቸው ለሻዕቢያ ኤርትራን በማስገንጠል አግራችንን ያለወደብ በር አስቀርቶ አፏን ከዘጋ በኋላ ኦነግን ስልጣን በማካፈሉ ላይ ሳያሳትፍ ስላባረረው ወደ ጫካ ለመግባት ተገደደ ::

ከዚያ በኍላም : እውነተኛ ዲሞክራሲ ያለ መስሏቸው ተከታዮቻቸውን በማስተባበር የነበሩትን እነፕሮፌሰር አስራትን እና ሌሎችንም ምርጥ ለነጻነት ታጋዮች : የውሸት ክስ እየፈጠረ በስር ቤት ዓይናቸው ጠፍቶ እንዲሞቱ ከማድረጉም በላይ : የትግሉን እንቅስቃኤም : በህቡዕ ላደራጃቸው የወሸት ተቃዋሚ ተብዮዎች ለነ ልደቱ አያሌው አስተላለፈው ::

በራሱ ውስጥም ቢሆን የኢሐዲግን መሰሪ ተንኮል የሚያጋልጡትንና : በተለይ በኤርትራ ጉዳይ ትክክለኛ አቋም የነበራቸውን : እነ ሐየሎ ያሉትን በረቀቀ ስልት በውስጥ በማስገደል : እንደነ ስዬ አብርሃ ገብሩ አስራት ያሉትን ደግሞ አስቀድሞ ባዘጋጀላቸው ወጥመድ ሳይቀድሙኝ ልቅደማቸው በማለት ጠላልፎ ሽባ ደረጋቸው : ወይም ከአገር አሰደዳቸው ::

ከሁሉም የሚከፋውና የኢትዮጵያን ሕዝብ እጅግ ያስቆጣው ግን : ኢሐዲግ በዲሞክራሲ ያምናል መስሏቸው : እንደማንኛውም የሰለጠነው ዓለም ተደራጅተውና የሕዝቡን ቀልብ ስበው የተነሱትን : ከሞት የተረፉ : ብርቅዬ ምሑራን : የፖለቲካ ሰዎች : የህግ ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች : የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎችን : ለምን ሕዝብ መረጣቸው በማለት ተናዶ : በማን አለብኝነት ሰብስቦ በስር ቤት አጎራቸው ::
እነሱን ደግፎ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣውን ሕዝብ : በገዛ ገንዘቡ በተገዛ ጥይት: በጠራራ ጸሀይ ግንባር ግንባሩ እያለ ረሸረነው ::

የቀረውንም ወደ የማሰቃያ ቦታ ወሰደው : ለዚህ ሰልፍ የተባበረው ነጋዴው የንግድ ፈቃዱን ተቀማ : ሰውራተኛው ከስራ ተባረረ : የታክሲ ሾፌሮች ሳይቀሩ መንጃ ፈቃዳቸው ተነጠቀ :: ሕዝቡም መግቢያ መውጫ ቢያጣ : በፍርሃትና በጭንቀት ተውጦ አንገቱን ደፍቶ : ጀርባውን አጎብጦ መሄድ ጀመረ ::

በአንድ ላይ ሲሰባሰቡለት : ለቃቅሞ ያሰራቸው ምሑራንም እንደነ ፕሮፌሰር አስራት ጤናቸው እየታቀወሰ ተስፋ ቆርጠው ያልቁለታል ::

ይህን የግፍ እርምጃና አገዛዝ ያወገዙ ምዕራባውያንም የእርዳታ እጃቸውን በመሰብሰባቸው : እየው ሕዝቡ ከመቸውም ጊዜ በባሰ ሁኔታ በኑሮ ውድነት እየታመሰ ይገኛል ::

ታዲያ ዲሞክራሲ ማለት የቱ ነው ? ዜግነቱ ባጎናጸፈው ነጻነት ተጠቅሞ : የማያምንበትን መቃወም : የሚያምንበት መደገፍ ካልቻለ : የዲሞክራሲ ትርጉሙ ምኑ ላይ ነው ?

አብዛኞቻችን የምንኖርበትን የሰለጠነ ዓለም በማየት : ዲሞክራሲ ምን ማለት እንደሆነ በሚገባ ተትረድተናል ::

ኢሐዲግ ዲሞክራሲን የሚጠቀመው : ተቃዋሚ ሆነው የተነሱትን ለመለያ እና ለማጥፊያ መሳሪያነት መሆኑ እየተረጋገጠ ነው ::

ምክንያቱም ቀጥተኛ ተቃዋሚዎች የሆኑ ሁሉ : አንዳቸውም በሰላም መኖር አልቻሉም :: እንደኔ እምነት : የኢሐዲግ ስርአት ከደርግ ቢከፋ ምንም አይሻልም ::

አፈናውም : ጭቆናውም : አሰራውም : በአደባባይ መረሸኑም : ማሳደዱም የበለጠና የረቀቀ ሆኖ ከመሰራቱ በቀር ምንም የቀነሰ ነገር የለም : እንዲያው በዘር ያነጣጠረ : ማለትም የአንድን ዘር ልይቶ ለመጥቀምና ሌላውን የበይ ተመልካች ለማድረግ ::

ይህን ሁሉ ነገር ለማለት የፈለግሁት : የነዚህን በዘር ማጥፋት ወንጀ ተከሰው የሞት ቅጣት የሚጠብቃቸውን ሰዎች : የፍርድ ሂደት ባነበብሁበት ወቅት በውስጤ አንድ ነገር ስለተሰማኝ ነው ::

በስልጣን የወጣው ሁሉ : ከሱ በፊት የነበረው መንግስት : የገነባውን ሲያፈርስ : የተከለውን ሲነቅል : የፈረደውን ሲሽር :

ይህ ነገር እስከመቸ ነው የሚቀጥለው ?
መቋጫውስ የቱ ጋ ነው ?

ወደፊት ይመጣል ብለን የምናስበውስ : ለአገራችን ወደ ምንመኝላት ዓይነት አስተዳደር እንዴት ሊመጣ ይችላል ?

ለመሆኑ ዛሬ በውጭ የሚገኘው ዲያስጶራ የሚከተለው በተቃውሞ ላይ ያነጣጠረ :

የአርቆ አሳቢነት ነገሮችን ሁሉ በሰላማዊ መንገድ ለማስተካከል ጊዜ ያጠረው ሆኖ : አግኝቸዋለሁ ::

ያለፈው አልፏል :ተመልሶ አይመጣምና
ምናለ አንድ ጊዜ ሁላችን ይቅርታ ብንባባል ?

ኢሕዲግም ለሞት ያቀረባቸውን ባለስልጣናት : ህዝቡ ይቅር እንዲላቸው : ለሕዝቡ ያቅርብ :
እሱም ያጠፋውን ጥፋት ይመንና : የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ይጠይቅ : ያሰራቸውንም ይፍታና በፈለጉበት የትግል ጎራ ገብተው መንቀሳቀስ እንዲችሉ ያድርግ :

እስኪ በመጪው አዲስ ሚሊኒዬም አዲስ አኗኗር እንመስርት ::
ምዕራብና ምስራቅ በመባል በጠላትነት ይተያዩ ጀርመኖች አነድ የሆኑት : እርስ በርሳቸው ሲጨፋጨፉ የነበሩት ኤሮፖች አንድ መንግስት ለመስረት በሂደት ባሉበት :
ዓለም ወደ አንድነት እየተቀራረበች ባለበት ዘመን ላይ ሆነን እንዴት አርቆ ማሰብ : መቻቻል : መተዛዘንና ከልብ አንድ መሆን አቃተን ?

ወደ አንድነት ለመምጣት እኮ : ሁሉም የራሱን ግትር አቋም መተው አለበት ::

ስለዚህ ሁላችንም ከእኛ የተለየ አቋም ያለውን : የጎደለንን ነገር እንደሚነግረን እንጅ እንደ ጠላት መቁጠር ይብቃን ::

የፖለቲካም ሆነ : የዘር : የሃይማኖት : ልዩነት : ተቻችሎ አብሮ በመኖር ተምሳሌት እንጅ ለመጠፋፋት : ምክንያት ሊሆኑ አይገባም ::

ሁላችን አንድ ሆነን እንደ አንድ ሕዝብ ማሰብ ከፈለግን : የሌላውን ልዩነት : በቅንነት ማስተናገድ አለብን ::

ከእኔ የተለየ ሁሉ ከሰይጣን ነው የምንል ከሆነ ግን : ምናልባት ነገ ከቤተ ሰቦቻችንም ጋር ወደ መጠፋፋት እየሄድን እንዳይሆን ::

እንኳን አገር : አንድ ፋሚሊ እንኳን በአንድ ሰው ህሳብ ብቻ አይመራም :: ዓለም የጋራ ድካም ውጤት ነች ::

ስለዚህ መንግስት ለእውነተኛ ተቃዋሚዎች በሩን መክፈተና : ከተሸነፈም ስልጣኑን መልቀቅ አለእበት ::

በሚሸነፍበት ጊዜ ስልጣን ለህዝብ ለማስረከብ ከወሰነ : ሚዲያዎችን : ሚሊተሪውን : ምርጫ ቦርድን : እና የመሳሰሉትን ከፓርቲው አባልት አንጽቶ : ለባለሙያዎች በማስረከብ ለህዝብ አገልግሎት ብቻ እንዲውሉ ማድረግ አለበት ::

ተቃዋሚን የማስተናገድ የመጀመሪያ እርምጃዎች እነዚህ ናቸው ::

አለበለዚያ ግን በቀድሞ ባለስልጣናት ላይ የፈረደው ፍርድ : ሳይውል ሳያድር : በሱም ላይ ይዞርና :

የኢሕአዲግ ባለስልጣናትም በተመሳሳይ ወንጀል ተመሳሳይ ፍርድ ተፈርዶባቸው ፎቷቸውን የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ::

ኢሕአዲጎች : እስኪ በትክክል ማሰብ ጀምሩ :

ደርግ ያደረገው : እናንተ ያላደረጋችሁት ምን አለ ?

ደርግ ጸረ አብዮት እያለ ይረሽን ነበር
እናንተም ጸረ ሰላም ኃይሎች እያላችሁ ትረሽናላችሁ: በቃ : ሌላ ምን አዲስ ነገር አመጣችሁ ?

ዲያስጶራዎችም እስኪ ቆም እንበልና የነገዋን አገራችንን ሁኔታ እናስብ ::

የነገን ለማሰብ ደግሞ : ከዛሬ ጭፍን አድማስ መውጣት አለብን ::

በእርግጥ ደምተናል : አዝነናል : ተከሰናል : ተሳደናል ::
ግን እግዚአብሔር ይመስገን : አልከፋንም : አገር ቤት ካሉ ወገኖቻችን የተሻለ ኑሮ እንኖራለን ::

ለነገዋ አገራችን : ለነገ ልጆቻችን : እናስብ :
ያለፉት ነገስታም አልፈዋል : ኢሐዲግም ያልፋል : እኛም እናልፋለን ::
ትውልድና አገር ግን : ይቀጥላልና አያልፍም :

ስለሆነም በሚያልፈው ዕድሜያችን የማያልፍ ስራ እንስራ ::

ጦርነት ብቻ መፍትሔ ይሆናል አናስብ :: ሌላም መንገድ እንፈልግ : እንመካከር : እንደማመጥ : እንከባበር : እንቻቻል : ይቅርታን እንልመድ ይቅርም እንባባል ::

የደርግ ባለስልጣናትን የሞት ፍርድ ስሰማ : ደርግ የገደላቸውንና የወደፊቶቹን ባለስልጣናትም እጣ ፈንታ አሰብሁ ::

የሰላ ሂስና አስተያየት ካለ እቀበላለሁ
ስድብም ካለ በጸጋ

ብቻ: በውነት ላይ የተመሰረተና አስተማሪ ይሁንበተራ ቁጥር 1 እና 2 ያስቀመጥከው በተለይ ቁጥር 1 ያንተው ፈጠራ ካልሆነ ቅንጣት እውናትነት የለውም ወይስ ሁሉም አጥፍተዋል መለስ ብቻ አይደለም ለማለት ነው :?: :?: ከየትኛውስ የታሪክ መዛግብት ነው ያገኘህው :?: ወይስ አንተው አሁን ፈጥረህ ታሪክ ልታረገው ነው :?: አንድ ወንድማችን በሌላ ረእስ ያለውን ልዋስና እዚህ የሚጻፍን የሚያነቡ ብዙ ወጣቶች አሉና የሌለ ፈጠራ ከማስተማር ብትታቀብ ይመረጣል:: ለምን ይሆን በሬ ጥጃ ወለደ ያሰኘህ :?:
Etiopia Tikdem!
ራስ ንጉስ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 376
Joined: Mon Dec 08, 2003 8:10 pm
Location: Jupiter

Postby ራስ ንጉስ » Thu Dec 14, 2006 11:22 am

ወዴት? ወዴት?......

Postby ዘማች » Thu Dec 14, 2006 11:54 pm

አያ ምን ይሻላል.... ራስ ንጉስ ለጥየቀህ መሰረታዊ ጥያቄ ተገቢውን መልስ በማስረጃ መስጠት እንደሚጠበቅብህ የዘነጋህ መሰልከኝ:: ይህንን የሚያህል እውነትም ወሬ ወለደ መዋእለ ዜና እንደተማላ ወርውረህ ወዴኤት ነው ሽሽቱ?....ቅቅቅቅ!... የተጻፈ የተነጎተ ነገር ካለ ምንጩን ጥቀስና የሁላችንንም ልብ ማርክ!... ያለበለዚያ ይህንን መሰሉ የታሪክ ሽውረራ የነጎይታና ታክቲክ ነችና ሀቃችንን አትስረቀን:: ልጅት, እንኩዋን ሲሸጡኝ ሲያስማሙኝም ይገባኛል ነው ያለችው? ነገሩ እንዲያ ነውና እየተራረምን እንጓዛ ዐለሜ!!!!!!!!!!!!!!! መረጃ ከሌለህ ግን ለተሳሳተ ዜናህ ይቅርታ መጠየቅ ባንተ አለተጀመረምና እነሆኝ ሜዳው....

ዘማች አባዱላ
ያገር ፍቅሩ ቤተኛ

ምን ይሽላል ? wrote:ራስ ንጉሥ እንደጻፈ (ች)ው

በተራ ቁጥር 1 እና 2 ያስቀመጥከው በተለይ ቁጥር 1 ያንተው ፈጠራ ካልሆነ ቅንጣት እውናትነት የለውም ወይስ ሁሉም አጥፍተዋል መለስ ብቻ አይደለም ለማለት ነው ከየትኛውስ የታሪክ መዛግብት ነው ያገኘህው ወይስ አንተው አሁን ፈጥረህ ታሪክ ልታረገው ነው አንድ ወንድማችን በሌላ ረእስ ያለውን ልዋስና እዚህ የሚጻፍን የሚያነቡ ብዙ ወጣቶች አሉና የሌለ ፈጠራ ከማስተማር ብትታቀብ ይመረጣል :: ለምን ይሆን በሬ ጥጃ ወለደ ያሰኘህ

ታሪኩን በሚገባ አብቤዋለሁ :

ከታሪክ መዛግብት ያገኘሁትን እንጅ ከኪሴ አውጥቼ እንዳታስፍሁ ላረጋግጥልህ እወዳለሁ ::

ታሪክ በታሪነቱ ይነገራል እንጅ : ለራሱ የሚያደስተውን እና የሚያስከፋውን ብቻ እየመረጠ : ጥሩና መጥፎ የሚል ሰው : ስለ ታሪክ እያወራን እንዳልሆነ መረዳት አለበት ::

የጻፍሁት በሙሉ : ተቀንሶለት ካልሆነ አንድም ሀሰት የለበትም ::

ከአሁን በፊት ባነበብኸው እና ያንተን ሀሳብ ብቻ በሚደግፍልህ : ሳትወሰን ሌሎችን የታሪክ መዛግብቶችን አገላብጥ አንድ ቀን ታገኘዋለህ ::

በተረፈ : የጽሁፌ ዓላማ : ጥፋተኞችን ለማወዳደር በማሰብ ሳይሆን ::

ሁሉም : ሰው በመሆናቸው ተሳስተዋል : አንዱ በሌላው ፍርድ ለመስጠት የሚያበቃው :ሞራል የለውም : ለማለት መሆኑንና : አንዱ የሰራውን : ሌላው ከሚነቅል : አንዱ የሚናገረው ለሌላው ኮሶ ከሚሆንበት : መደማመጥ : መቻቻልና አርቆ ማስተዋል ይኑር ለማለት ነው ::

ደግሞ የማውቀውን ተናገርሁ እንጅ : ፍርድ ሰጪ አይደለሁም ::

ምንም አትነገር ከሆነ : ማንንም መከልከል የሚቻል አይመስለኝም ::

ለማንኝውም : አንተም እኔን መንቀፍህን ተወውና : ሰለወደፊቷ ኢትዮጵያችን እናስብ ::

በትክክል ተፈረደ : አልተፈረደም : የሞቱት ሞተዋል : የሚገደሉትም ይገደላሉ ::

እኛም የተሰማንን እየተናገርን ጊዜው ያልፋል ::

ምናልባትም አንድ ቀን ለወገናችን መልካም ቀን ይወጣ ይሆናል ::
ዘማች
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 88
Joined: Wed Aug 18, 2004 7:02 pm
Location: ethiopia

ምንይሻላል

Postby ልጁነኝ1 » Fri Dec 15, 2006 12:08 am

ምን ይሻላ!
አዎ የጻፉት በትክክል አስቀምጠውታል:: ፊታውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ በታሪኩ ውስጥ ያሉት ነገር አለ:: ያም ጃንሆይን ሲተቹ! "ቁጭብለን የሰቀልነው ቆመንም ማውረድ አልቻልንም"
ማለታቸው::

ቀጥሎም አቤቱ ኢያሱ አጼ ምኒልክ ስለ ዛሬዋ ኤርትራና ወይም ከመረብ ወዲያ ስለቀረችው አገራቸው ሲያሳድጓቸው ሁሉ ሙሉ ትምህርትና ምክር ሰተዋቸዋል:: በዚያም በሚዘጋጁበት ጊዜ ይጠቀሙበት ዘንድ ካርቱ ሱዳን ውስጥ በሚገኘው የእንግሊዝ ባንክ ውስጥ 25 ሚሊዮን ጠገራ ብርና ወርቆች አስቀምጠው ነበር:: ያም ገንዘብ ኢትዮጵያ ያሰበቺውን የምታስፈጽምበት ችግርም ሲያጋጥመት ቆንጥራ ችግሮቹዋን የምትወጣበት የሚል::

ይህን ሁሉ ለአቤቱ ኢያሱ ነው የተናገሩት ያስረዱት:: ከዚያም በጃን ሜዳ ልጆን አቤቶ ኢያሱ ምኒልክን ያልከተለ አሸከሬና ሕዝቤ ጭምር ካልተከተላቺሁት ጥቁር ውሻ ውለዱ ብለው ተናግረዋል:: ያም በጳውሎስ ኞኞ የታሪክ መጽሐፍ ላይ በስተመጨረሻውጋ ተጽፎ የገኛል::

ልጅ ኢያሱ ወይም አቤቶ ኢያሱ የሶሻል ሰው ናቸው ቅድሚያ የሚሰጡት ለህዝቡና በህዝቡ መሐልም ዘወትር መገኘትና ህዝቡን ወደራሳቸው ልብ መሣብ ነበር:: ያንም ምክንያት አድርገው ወነጀሉዋቸው ሁኔታዎቹን አሁን አላነሳቸውም:: ይቅርብን::

ልጅ እያሱን ይዘው በሰላሌ እስርቤት አኖሩዋቸው:: ከዚያም ልጅ እያሱ እስር ቤት ሰብረው ጎጃም ገቡ እንደገናም ተይዘው ጋራ ሙለታ ታሰሩ ለብዙ አመታት:: በመጨረሻ ጣሊያን ኢትዮጵያን ወረረች:: ጃንሆይ ቀ.ኃ.ሥ. ልጅ ኢያሱን ከጋራ ሙለታ አይሻና ደወሌ በዘበኞቻቸው እያስጠበቁ እንዲቆይ አድርገዋል:: ከዚያ ጃንሆይ ለሥደት ቤተሰባቸውንና ገንዘባቸውን የቅርብ ዘመዶቻቸውን ታላቅ መኳንቶቻቸውን ሹሞቻቸውን አስቀድመው ጂቡቲ ላኩና በመጨረሻ እሳቸው!

እነ ደጃዝማች ታከለ ወልደሐዋያት በፍጹም ልማዳቺን አይደለም ቤተመንግሥቱ ወደ አርባ ምንጭ ተስተላልፎ እርም እዚያ ሆነው አርበኞችን መምራት ይገባዎታል በሚል ከፍተኛ ክርክሮች አድርገዋል:: በመጨረሻ ንጉሡ ወደ ጂቡቲ ጉዟቸውን ሲቀጥሉ ልጅ እያሱን ቆመው አሳርደው መቃብሩም ሳይታወቅ እስከዛሬ እንደሚኖር ነው::

አሁን ግን ግዜይ DNA የሚባል ቴክኖሎጂ ስለተፈጠረ የልጅ እያሱን አጽም ማግኘት እንደሚቻል ነው የሚታሰብ አስፈጻሚ ከተገኘ::

የጎጃሙ ንጉሥ ተክለሃይማኖትና ምኒልክ መዋጋታቸው:: ከዚያም የጎጃሙ ንጉሥ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መሆን ሲገባቸው ደጃዝማች በዝብዝ ካሣ ተሽቀዳድመው ንጉሠ ነገሥት መሆናቸው:: ራሱ ምስክር ይሆናል::

ከቀድሞ ጀምሮ ቺግሮች እንዳሉ ያመለክተናል:: ድርቡሾች ጎንደርን ሲያቃጥሉዋትና 44 ታቦት ሲዘርፉ ወርቅና መስቀልን ሰባብረው ሲወስዱ ታቦቱን በሜዳ ሲጥሉ አጼ ዮሐንስ ድንጎሎ ላይ ሆነው ያንን በመስማታቸው በቀጥታ ለንጉሥ ምኒልክ ነው ትዛዝ ያስተላለፉት ባስቸኳይ ወደ መተማ እንድትወርድ ጎንደርን ድርቡሾች ስላቃጠሉዋት::

ዮሐንስም ኢጣሊያ ወደ ደጋው ወደ አስመራ ወይም ምድሪ ሃማሴን እንዳይመጣ አድፍጠው ከበው ለማድቀቅ የቀየሱት ዓላማቸውን ትተው ወደ መተማ በንዴት ዘምተዋል:: ጣሊያንም ያለማንም መካች ኃይል ኤርትራን ተቆጣጠራት:: በ1884 ዓ.ም. ከዚያ የሸዋው ምኒልክም በጎንደር አካባቢ ወይም አዘዞ የጦር ልምምድ ሠራዊታቸውን እያስተማሩ ቆይተዋል:: የተነገራቸው ግን ቀድመኸኝ ድረስ እኔ ያለሁት እሩቅ ነው ነበር:: ያንን ለምን አልፈ
ታሙም? ያንን ለታሪክ ከታቢዎች እንተወው::

ዮሐንስ በንዴት ራሳቸው ንጉሠ ነገሥት ሆነው ሳሉ እንደተራ አርበኛ ፈረሳቸው ላይ ሆነው ጎራዴአቸውን መዘው በመጋለብ ጦርነቱን ጀመሩ:: እስከ ገደአሪፍ ድረስ አካባቢው ድረስም ነበር የሄዱት በመጨረሻ የድርቡሾች ኃይል በመጠንከሩ ወደ ኃላ አፈግፍገው ጦራቸውን ሲመለከቱ እንዲህ አሉ ይባላል! "እንዴ ጦሬን ሁሉ እኮ ገለባት " አሉ:: ያቺ ቦታ ከመተማ ባሻገር ያለቺዋ ከተማ እስከ ዛሬ ገላባት ትባለለች::

የየዮሐንስ ሰውነት የወደቀባት ቦታ የመተማዋ ማርያም ተሰርታበታለች:: ውኃም በውስጡዋ በመቅደሱዋ ውስጥ ፈልቆባታል:: ውሃ ከውጪ አይቀዱም አገልጋዮቹዋ ከመቅደሱዋ ነው::

የማርያም ቤተክርስቲያን ልክ ያቺ ትንሽ ወንዝ ነው የምትለያት ከዚያ በስንዝር ሱዳን ነች:: ቤተክርስቲያኑዋ እንደዚያ ነው የሠሩዋት:: ስለዚያ ሁኔታ ሄዶ አጥንቶ ስለ መተማ ማርያም መጻፍ ይኖርበታል ታሪካዊ ታቦት ነችና::በመጨረሻም በምንም ዓይነት ወደ ኢትዮጵያ ክልል አልፌ አላፈገፍግም በማለት ሞትማ እዚህቺው ነው አሉ ይባላል:: በዚያ የተነሳ ነው "መተማ" የተባለቺው ብዙ አባቶች ይናገራሉ::

የአጤ ቴድሮስንም ታሪክ ብንመለከት የኢትዮጵያ መኳንቶች ንግሥናም ፈላጊዎች ሻጥር ሰርተውባቸው እንጂ ያንን ጀነራል ናፔዬርን ማሸነፍ ይቻላቸው ነበር:: በማያውቃት አገር መጥቶ ንጉሥ ሊገድል ወይም ሊወጋ በቀጥታ አይቭቺልም ነበር::

እንግዲህ ምን ይሻላል ያስቀረሁትን አስተካክለህ እንድትሞላው የአነበብኩዋትን ያህል እውነቱን ነው የተናገርኩት ማንም ለመደገፍ ማንንም ለማሳጣት ወይም ለማጉድፍ ሳይሆን::

ከይቅርታ ጋራ ካጠፋሁ.

አክባሪዎ

ልጁነኝ1
ከ(ሰሐሊን)

ምን ይሽላል ? wrote:ራስ ንጉሥ እንደጻፈ (ች)ው

በተራ ቁጥር 1 እና 2 ያስቀመጥከው በተለይ ቁጥር 1 ያንተው ፈጠራ ካልሆነ ቅንጣት እውናትነት የለውም ወይስ ሁሉም አጥፍተዋል መለስ ብቻ አይደለም ለማለት ነው ከየትኛውስ የታሪክ መዛግብት ነው ያገኘህው ወይስ አንተው አሁን ፈጥረህ ታሪክ ልታረገው ነው አንድ ወንድማችን በሌላ ረእስ ያለውን ልዋስና እዚህ የሚጻፍን የሚያነቡ ብዙ ወጣቶች አሉና የሌለ ፈጠራ ከማስተማር ብትታቀብ ይመረጣል :: ለምን ይሆን በሬ ጥጃ ወለደ ያሰኘህ

ታሪኩን በሚገባ አብቤዋለሁ :

ከታሪክ መዛግብት ያገኘሁትን እንጅ ከኪሴ አውጥቼ እንዳታስፍሁ ላረጋግጥልህ እወዳለሁ ::

ታሪክ በታሪነቱ ይነገራል እንጅ : ለራሱ የሚያደስተውን እና የሚያስከፋውን ብቻ እየመረጠ : ጥሩና መጥፎ የሚል ሰው : ስለ ታሪክ እያወራን እንዳልሆነ መረዳት አለበት ::

የጻፍሁት በሙሉ : ተቀንሶለት ካልሆነ አንድም ሀሰት የለበትም ::

ከአሁን በፊት ባነበብኸው እና ያንተን ሀሳብ ብቻ በሚደግፍልህ : ሳትወሰን ሌሎችን የታሪክ መዛግብቶችን አገላብጥ አንድ ቀን ታገኘዋለህ ::

በተረፈ : የጽሁፌ ዓላማ : ጥፋተኞችን ለማወዳደር በማሰብ ሳይሆን ::

ሁሉም : ሰው በመሆናቸው ተሳስተዋል : አንዱ በሌላው ፍርድ ለመስጠት የሚያበቃው :ሞራል የለውም : ለማለት መሆኑንና : አንዱ የሰራውን : ሌላው ከሚነቅል : አንዱ የሚናገረው ለሌላው ኮሶ ከሚሆንበት : መደማመጥ : መቻቻልና አርቆ ማስተዋል ይኑር ለማለት ነው ::

ደግሞ የማውቀውን ተናገርሁ እንጅ : ፍርድ ሰጪ አይደለሁም ::

ምንም አትነገር ከሆነ : ማንንም መከልከል የሚቻል አይመስለኝም ::

ለማንኝውም : አንተም እኔን መንቀፍህን ተወውና : ሰለወደፊቷ ኢትዮጵያችን እናስብ ::

በትክክል ተፈረደ : አልተፈረደም : የሞቱት ሞተዋል : የሚገደሉትም ይገደላሉ ::

እኛም የተሰማንን እየተናገርን ጊዜው ያልፋል ::

ምናልባትም አንድ ቀን ለወገናችን መልካም ቀን ይወጣ ይሆናል ::
ልጁነኝ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 641
Joined: Tue Dec 30, 2003 2:17 pm
Location: united states

Re: አንዱ ሌላውን የማጥፋት ሩጫ ለምን ይሆን ?

Postby ካሳ ኃይሉ » Fri Dec 15, 2006 1:12 am

ምን ይሽላል ? wrote:
በታሪክ እንዳነበብነው

1. ዐጼ {እምዬ} ሚኒልክ ዐጼ ዮሐንስን : ባህታዊ መሰል ሰላይ ልከው ብውድውርቡሾች ተደብድበው እንዲሞቱ አደረጉ ::

የትኛው ታሪክ ነው እንደዚያ የሚለው እባክህ? መለስ ዜናዊ የጻፈላችሁ?
ዮሀንስ ተብየው ከሀዲ ሆዳም ርካሽ ሰው እንደነበር ነው ታሪክ የሚያስረዳው እድሜ ለሱዳኖች ያንን ባንዳ አንገቱን ቀልተው አሳረፉት ደግሞ አጼ ሲባል ነው የሚገርመኝ

አስመሳይ የዎያኔ ተላላኪ መሆንህን ማንም መገንዘብ ይችላል ርካሽ
ካሳ ኃይሉ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 83
Joined: Fri Dec 08, 2006 2:21 am

Re: አንዱ ሌላውን የማጥፋት ሩጫ ለምን ይሆን ?

Postby መኖርደግ » Fri Dec 15, 2006 5:04 am

ምን ይሽላል ? wrote:
1. ዐጼ {እምዬ} ሚኒልክ ዐጼ ዮሐንስን : ባህታዊ መሰል ሰላይ ልከው ብውድውርቡሾች ተደብድበው እንዲሞቱ አደረጉ ::የአፄ ዮሓንስ አሟሟት የሆነው አንተ እንደምትለው አይደለም!! ይህን ታሪክ ማን እንደፈጠረው ብታመላክተን ለሁላችንም ጥሩ ነው::

የአፄ ዮሓንስ ወታደርቻቸውን እና መኳንቶቻቸውን አስከትለው ማርች 10፣ 1889 ዓ.ም. መተማ ላይ ደርቡሽን ገጠሙ::
የኢትዮጵያ ጦር እያጠቃ ነበር: የደርብሽን ምሽግ እየደረመሰው ነበር: የአፄ ዮሓንስ ከጦራቸው ግንባር ሆነው መዋጋት ይወዳሉ: ወደኋላ እንዲሆኑ ቢጠየቁ አሻፈረኝ አሉ:: ይህ ለዚያች እለት ታላቁ ቁልፍ ስህተት ነበር::
የደርቡሽ ተኳሽ ጥይት ንጉሡን ነደፋቸው:: ቁስሉ ከፍተኛ ነበርና ወደድንኳናቸው ተወሰዱ በዚያም ሕይወታቸው አለፈ::
የታላቁ ጀግና የአፄ ዮሓንስ አሟሟት ይህ ነው:: ከዚህ የተለየ ታሪክ ማን እንዳስተማረህ አላውቅም:: ብዙ የታሪክ መጽሐፍ አንብቤአልሁ ይህን ግን አላገኘሁትም::

የፈረደበት እምዬ ሚኒልክ ገዳይ እሱ በቅኝ ያዥ እሱ ባሪያ ሻጭ እሱ ............................................................
ምን ያለተባለው አለ?
እረ ደግ አይደለም ታርክን ማጣመም!!!!!

ታሪኩን በሚገባ አብቤዋለሁ :

ከታሪክ መዛግብት ያገኘሁትን እንጅ ከኪሴ አውጥቼ እንዳታስፍሁ ላረጋግጥልህ እወዳለሁ ::

እኔም ለማንበብ ጓጉቻለሁን እባክህን የመጽሀፉን ስም ንገረኝ:: መወያየት የሚጠቅመው እርስ በርስ ለመማማር ነውና::
አመስግናለሁ
ቅወሥ
ሰላም ለሁላችን
መኖርደግ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 292
Joined: Thu Aug 17, 2006 5:51 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests