Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)
by yammi » Tue Apr 24, 2007 5:16 pm
ለመሪ ወንዝ
እንኳን በሰላም ቆየኸኝ..........ከፎቶ ስብስቦችህ ጋር :D
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Tue Apr 24, 2007 5:49 pm
ሰው ከንቱ
ከግብአተ-መሬት በኍላ
ቀባሪው እንደተሰበሰበ
የተቀባሪው አዛውንት መልእክት
እንዲህ ሲል ተነበበ..................
"በአፍላነት ዘመኔ
ወጣት ጉልበቱን በገንዘብ ሲመነዝር
ነገን ከዛሬ መኖር ሊጀምር
ለነገ ዛሬ ሲ-ደ-ረ-ድ-ር
እኔ ጉልበቴን ""በእድሜ ይስጥህ"" ምርቃት ለወጥኩ
እድሜዬን በቁና ልሰፍር
ምርቃቴ ሰመረ ስል
ታሪክ በአንደበቴ ተዘከረ
ድህነትም አብሮ
በእድሜዬ ቁና ተሰፈረ
እድሜ አይበላ ነገር ሆኖብኝ
አሳር በትከሻዬ ተሸክሜ
አይታችሁኛል እንግዲህ
የእድሜዬን ግማሽ ቁልቁል ስኖር
በምርቃቴ ተረግሜ......
እናም ውድ ወገኖቼ
"እድሜ ይስጥህ" ከሚለው
ምርቃተ ጎደሎ ተጠበቁ
"እድሜ ከጧሪ ወይም ከሀብት ጋር ይስጥህ ብላችሁ
ሙሉ ምርቃትን መርቁ::
"እድሜ ጸጋ ነው"
ብለው ሲተርቱ እንኳን ብትሰሙ
"እድሜም ያለጧሪ አሳር ነው" ብላችሁ
ተረተኛ ወገኔን አርሙ::
ከሞት ጋር ትንቅንቅ ይዘው የጻፉት
የተቀባሪው መልእክት
በቀባሪው አንድ ጆሮ ገብቶ
በሌላኛው ጆሮ በመውጣቱ
ከተጫናቸው አፈር ጋር
መልሰው እንደእድሜያቸው ተሸከሙት
የእድሜ ባለጸጋው አዛውንቱ::
ምጽ......
24/4/2007
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ቤቲ_13 » Wed Apr 25, 2007 4:00 pm
ልዕልት-ያሚቲ እንኳን በደህና መጣሽልን
-
ቤቲ_13
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 795
- Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
- Location: ethiopia
-
by yammi » Fri Apr 27, 2007 5:42 pm
ቤቲ
በጣም አመሰግናለሁ የኔ ቆንጆ...........እንኳን በሰላም ቆየሽኝ:: ለእንኳን አደረሰሽ ምኞትሽ ዘግይቼ በመመለሴ ይቅርታ ::
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Fri Apr 27, 2007 7:10 pm
የአዛውንቱ ውሎ
አቡነ በሰማያት
በእንተ ማርያምን እያልጎመጎሙ
ከጀንበሯ ለጥቀው
ከእዳሪ ሊሰየሙ
በከዘራቸው ጫፍ
መሬቱን እየኮረኮሙ
...............አዘገሙ
ምሽት እስኪገላግላቸው ድረስ
ተቀምጠው ከደጃፉ
ያዘመመ ጎጇቸውን
በደከመ እይታቸው ሊደግፉ::
27/4/2007
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Wed May 02, 2007 10:35 pm
2/5/2007
ያሚ
Last edited by
yammi on Tue Mar 04, 2008 5:08 am, edited 3 times in total.
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by መሪ ወንዝ » Thu May 03, 2007 12:54 pm
ሠላም ያምሮት!
በጣም ውብ ግጥሞች ናቸው::
yammi wrote:ይድረስ ለመስቀል ወፍ
አይኖቼ ጭልፊትን ሲጠብቁ
ከእንቅልፍ እንደራቁ
ስታውቂ.......
ጆሮዎቼ ኮሽታን ሲበትኑ
መሽቶ እንደሚነጋ ቀኑ
ስታውቂ........
በላባዎችሽ ውበት
ወፋዊ ቅናት ስዘናጋ
ሙቀቴን አጋርቼ የቀፈቀፍኩት
የጭልፊትን ልጅ ጉሮሮ እንዳይዘጋ
ምናለ ለአፍታ ካጠገቤ ብትርቂ.......
ጠማማ ቀኔን ብታርቂ?
ለ ሚሳ
2/5/2007
ያሚ
ሠም እና ወርቅ
መሪ ወንዝ ከተከዜ (ጎርፉ)
-
መሪ ወንዝ
- ኮትኳች

-
- Posts: 470
- Joined: Sat May 06, 2006 5:13 am
- Location: ኢትዮጵያ
by ሾተል » Thu May 03, 2007 2:03 pm
..........
ሾተል
Last edited by
ሾተል on Thu May 10, 2007 3:21 pm, edited 1 time in total.
-
ሾተል
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 9647
- Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
- Location: Vienna-Austria
by ሾተል » Thu May 03, 2007 2:24 pm
......
ሾተል......
Last edited by
ሾተል on Thu May 10, 2007 3:22 pm, edited 2 times in total.
-
ሾተል
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 9647
- Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
- Location: Vienna-Austria
by yammi » Fri May 04, 2007 6:40 pm
እፍረት
የሞቱት ሳይታወሱ
የቆሙት እንደተረሱ
..
..
በቁም የሞቱት ሲወቀሱ
በቁም የገደሉት ሲወደሱ
ይኸው...................
የኔ ዘመንና ግሳንግሱ
የኔ ዘመንና ትርምሱ::
4/5/07
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Sat May 05, 2007 9:58 pm
ዘመኔ
ዘመኔ?
ዘመኔማ...............
እምነት ያሳቀቀበት
ክህደት ያጸደቀበት
ጻድቅ የኮሰሰበት
ሀጥእ የገዘፈበት
ዘመኔማ..............
ፍቅር የከሰመበት
ሽንገላ የዘየረበት
ቅናት የካደመበት
እውነት የሰገደበት
ዘመኔማ................
ዘመኔማ.. ዘመን ነው
ዘመን የነቀዘበት::
05/5/2007
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by meote » Sat May 05, 2007 10:41 pm
ስላም ያሚዬ: ሁሌ ግጥም እሞክር እና: እንቢ ይለኛል .......
ይኢትዩጽያ ምደር
አንቺ ይደም ጎዳና
መስክሪ አፍ አውጪና
መስክሪ አንች ምድር ኑሪ ግድ ይለሽም
እኛ ብንሞት እንጂ
አንቺን አይጉዱሽም................... :shock: ከተሳሳትኩኝ አርሚኝ ቅቅቅቅ
LIFE IS A WOUNDERFUL THING.....
-
meote
- ኮትኳች

-
- Posts: 443
- Joined: Sat Apr 22, 2006 8:08 pm
- Location: warka
by ሀምሳለ » Sun May 06, 2007 12:44 am
ምኦት በጣም ቆንጆ ነው ግን ማንን ሀጥያት ለመክተት ነው አይጥ ውድድድድድድ
ያምዬ ሰላም ቆንጆ ተናፍቀሻል ባክሽ ቶሎቶሎ ጣፍ ጣፍ አርጊ ቤቲን ሰላም በይልኝ :D
ሀምሳለ
-
ሀምሳለ
- ኮትኳች

-
- Posts: 243
- Joined: Fri Oct 13, 2006 8:43 pm
- Location: America
by yammi » Sun May 06, 2007 10:40 pm
meoteዬ..................ደግሞ ለግጥም እንቢ ሲልሽ አንቺም አለቅ ብለሽ እንቢ ማለት ነው:: አታይም ውጤቱን ::ሁላችንም እንዲህ እያልን ነው የጀመርነው ቆንጆ :: ከአንዳንድ ቃላቶች ግድፈት ሌላ ግጥምሽን ወድጄዋለሁ: እስቲ ጨመርመር አድርጊና ..........
ሀምሳልዬ......... እድሜ ለዋርካ ቻት ስንት ነገር አምጥቼ እንዳላቀብልሽ ጥርቅም ብሎ ጠበቀኝ::ተያይዘን ሱባኤ እንግባ መሰለኝ :roll: ...... ጨዋታሽ እንዴት እንደናፈቀኝ::
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
Who is online
Users browsing this forum: No registered users and 0 guests