Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)
by yammi » Thu May 17, 2007 10:04 pm
..........
Last edited by
yammi on Tue Mar 04, 2008 4:57 am, edited 2 times in total.
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ጦምኔው » Thu May 17, 2007 10:21 pm
ሠላም ለቤቱና ለቤቱ ባለቤት::............ሙድ መያዝ አይቻልም...........አስተያየት እንፈልጋለን :lol:
ከወንዙ ዳር ከዛፍ ጥላ
የበቀለች የጅብ ጥላ
ከብሳና ተቀጥላ
አገኘኍት ትክዝ ብላ
ለብቻዋ..........
ወገን የላት በዙሪያዋ
የሚያጽናናት በሀዘኗ
አለሁ 'ሚላት በችግሯ
የሚሆንላት አጋሯ
ሆድ ሲብሳት..............
ብቸኝነት ሲያንገላታት
በሰመመን ሲመስጣት
ትዝታዋ.........
የተጻፈ ከህሊናዋ
ከነፍሷ ነፍስ ውሳጠዋ
ስንቅ የሆናት መጽናኛዋ
የማይጠፋ በዘመኗ
እሷን ሳያት አወይ አልኩኝ
ሕይወቷ ሕይወቴን ቢመስልብኝ............::
ጦምን ዘአራዳ.............05/17/07
-
ጦምኔው
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1529
- Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
- Location: Right here
by ጦምኔው » Thu May 17, 2007 11:04 pm
ሠላም ያሚ..............
ሰማይ ቧጦ ምድር ጠልቆ
ከዓለማት ወዲያ መጥቆ
አየራትን ሰነጣጥቆ
ከፍጡራን ተራ ርቆ
ተራሮችን እየናደ
ዓለቶች እያነደደ
ደርሶ ታየ ወዲያ ማዶ
ከሕልም ዓለም ደስታ ቦታ
እንስቲቱን ያየ ለታ
ተወጥሮ በእሳት ንዳድ
በገሞራ በነጎድጓድ
እስኪተከል መሰረቱ
እስኪሰክን ያ ግለቱ
ፈሳሽ እሳት ትኩሳቱ............::
ጦምን ዘአራዳ................05/17/07
-
ጦምኔው
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1529
- Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
- Location: Right here
by yammi » Thu May 17, 2007 11:27 pm
ጦምዬ-----------ዋውውውውውውውውውውውውውው
ይህንን የመሰለ ችሎታ ይዘህ እሰከዛሬ መደበቅህ ከምር ያስቀስፋል:: በጣም ነው ግጥሞችህን የወደድኳቸው በጣምምምምምምምም:: ቅኔን የተላበሱ ናቸው::ወደፊት ብዙ እንደምታስነብበን ተስፋ አደርጋለሁ::
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ሞካሪ » Fri May 18, 2007 12:32 pm
ሰላም ለባለቤት ሰላም ለታዳሚው
እጄን እግር ጥሎት ይህው እዚህ ገባሁ::
እስኪ ይሁን ብየ አድናቆቴን ልቸር
ገባሁ ባህል አምባ ከጣፊወች ሰፈር::
የተደበቀውን ያምሮቴን ልወጣ
ሲሉ እየሰማሁ ነው ሰው ከገባ አይወጣ
ምስጢር ሚስጥር ይሁን ለባእድ አይውጣ
ይሄው ታዛዣለሁ ዛሬ በዚህ ላብቃ::
መሞከር ለካ ጥሩ ነው :D
-
ሞካሪ
- ጀማሪ ኮትኳች

-
- Posts: 81
- Joined: Thu Sep 07, 2006 11:07 pm
by ሞካሪ » Sat May 19, 2007 9:57 am
እረ እዚህ ቤት ...ባለቤት የለም?... :(
ባህላችን አይደለም አለመደብንም
እንግዳ ሲመጣ ወደ ውጭ የለም:
ይግቡ ይቀመጡ ቡናም እንዲጠጡ
ይላል ያገሬ ሰው ቤቱ ለሚመጡ::
ይሁና ይሁና
...
-
ሞካሪ
- ጀማሪ ኮትኳች

-
- Posts: 81
- Joined: Thu Sep 07, 2006 11:07 pm
by yammi » Sat May 19, 2007 6:53 pm
ውድ ሞካሪ
በጣም ይቅርታ:: ከአሁን አሁን መልስ እጽፋለሁ ስል ተመልሰህ መጣህብኝ::አዲስ እንግዳ ኸረ ደስ ብሎን እንቀበላለን......እንኳን ደህና መጣህ::
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ጦምኔው » Sat May 19, 2007 10:31 pm
ሰላም ያሚቲ.............
ያሉኝን ጥቂት" ግ ጥ ሞ ች ".......ከተባሉ..................አራግፌ ልጨርስ ነው የመጣሁት ................ሰው እንደት አራት ጥይት ይዞ ጦርነት ይሄዳል :?: ...............አራትዋን ድው ድው አርጎ ከዚያ ሽሽት :?: ............................... :lol:
የሚቀመስ የሚበላ
ጠፍቶ ሳለ ከማጀቴ
ገመናዬ ባደባባይ
ተዘርግፎ ውስጠ ቤቴ
ሆዴ ተነፍቶ ቢታይም
ተጣብቆ ሳለ አንጀቴ
የሰዉን ኑሮ እያየሁ
ትርጉም ቢያጣብኝ ሕይወቴ
እስቅ ጀመርኩ እገለፍጥ
ያልፍ መስሎኝ መራቤና መጠማቴ
ልደብቀው ልሸሽገው
ፈጦ ሳለ ባዶነቴ
የሆዴ ኦና መሆኑ
የአእምሮዬ መራቆቱ
ታየኝ ጎልቶ ድህነቴ...................!!!
ጦምን ዘአራዳ...........05/19/07
-
ጦምኔው
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1529
- Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
- Location: Right here
by yammi » Mon May 21, 2007 5:20 pm
ጦምዬ ዘአራዳ
ከጓሮ የቀበርካትንም ቢሆን ታወጣታለህ እንጂ ማንም አይለቅህም :lol: ማንገራገር አይቻልም:: ግጥምህ ግን እንደሁልጊዜው ሸላይ ነው(ከዋናው የተወሰደ)::
ያሚ ከውቤ በረሀ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Mon May 21, 2007 8:30 pm
ፍረጂኝ
እኔ የምድር ኮስማና
ያልሞላለት ብላቴና
አንቺ የሰማይ ቀይ እንቁ
አይኖችሽ ፍቅርን የሚያፈልቁ
ውበትሽ አይኔን ነጥቆ
ዝምታሽ ቀልቤን ሰርቆ
ከነገስሽበት ጥቁር ሰማይ
መሽጓልና
እንዳይታይ
የጽልመቷ ንግስት
አጉራሽ ጠናኝ
በግዛትሽ ክሴ ይቃኝ
በዙፋንሽ ቅጥር ልዳኝ::
21/5/07
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ጦምኔው » Sat May 26, 2007 2:17 pm
ያሚዬ ተመልሼ መጣሁልሽ..............ቤትሽን ገጽ 2 ላይ ሳያት ከጋቢናው ዱቅ ትበል ብዬ ነው የመለስኳት..............
ልጅ ሳለሁኝ ገና ጮርቃ
ለቁም ነገር የማልበቃ
የዕድሜ ጸጋን የታደሉ
በማስተዋል የተሞሉ
አያቴ እመት ታደሉ
ራሴን እየደባበሱ
አንዳንዴም እያለቀሱ
ሲመርቁኝ ጠዋት ማታ
" እደግ" ሲሉኝ ሰው ሁን በርታ
መስሎኝ ነበር ማደግ ለኔ
ለቁመቴ ለአካሌ
.
.
ለካስ ነበር ገባኝ ዛሬ
በማስተዋል ለመኖሬ
ለሕሊና ለማደሬ:;
ጦምን ዘአራዳ..............05/26/07
-
ጦምኔው
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1529
- Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
- Location: Right here
by yammi » Thu Jun 21, 2007 7:52 pm
አራምባና ቆቦ
ያቺን የአንተን አለም
በአንተ አይን አይቼ
በአንተ አፍንጫ አሽትቼ
በአንተ እግር ገስግሼ
በአንተ እጅ ዳስሼ
አዬ ውበት...................ጀመርኩ::
ይቺን የኔን አለም
በእኔ አይን አይቼ
በእኔ አፍንጫ አሽትቼ
በእኔ እግር ገስግሼ
በእኔ እጅ ዳስሼ
................አይ ልዩነት:: ጨረስኩ ::
21/6/2007
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ዋናው » Sun Jun 24, 2007 1:27 pm
ያሚያችን
ጠፍቼ ከርሜ ደጅሽን ብቃኘው
ያጌጡ ያበቡ ግጣጥሞች አየው
መልካም አበቦች ንቦችን ከሩቅ የመሣቡ ዓይነት .................'ንዲሉ::
አድናቂሽ
ዋናው_________________________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2802
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by yammi » Sun Jun 24, 2007 11:44 pm
ዋንሽ..................እንኳን በሰላም ተመለስክልን:: ከዋርካ ነጠል ማለትህ ብሩሽህን ብቻ ሳይሆን ብእርህንም አሹሎ እንደላከለን ተስፋ እናደረጋለን............:: ጣል ጣል አድርግብን::
ያንተው አድናቂ
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ሞካሪ » Mon Jun 25, 2007 12:12 am
ሰላም እዚህ ቤቶች እንዴት ከረማችሁ?
ብቅ ብሎ የጠፋው ደግሞ መጣላችሁ::
....
አይ የምድር ኑሮ ... ሩጫ ... መታከት
ያለፈው ተረስቶ ከፊት ብቻ ማየት::
አይደርስ የሚመሰለው ተደርሶበት ሲታይ
ርካታና ደስታ ራቁ እንደ ሰማይ::
ከንግዲህ ይቅርብኝ...
... ነገን መጠበቁ የቀጠሮ ኑሮ
ዛሬንም ሳልኖረው ነገም ዛሬ ሆኖ
ሳንገናኝ ልናልፍ እኔና ያ ኑሮ::
አይ አንቺ ምድሪቱ ክፉ አታላይቱ
ተስፋየ ሰማይ ነው ተውኩሽ አንቺ ከንቱ
ጭንቀቴን ተውኩልሽ ወጣልኝ ጉጉቱ::
ከሚያጉጉዋ ነገር ጉጉቱን ለማጥፋት ሞካሪ :wink:
-
ሞካሪ
- ጀማሪ ኮትኳች

-
- Posts: 81
- Joined: Thu Sep 07, 2006 11:07 pm
Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
Who is online
Users browsing this forum: No registered users and 3 guests