Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)
by yammi » Fri Jun 29, 2007 9:01 pm
ሞካሪ........አንተም እንኳን በሰላም ተመለስክ :D
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Fri Jun 29, 2007 9:23 pm
.......
ወዳጅ እንደወነጀላት ቢሰማ
ጥሩ ቀን እንደራቃት
ጠላቷ እያቆላመጠ ቀርቦ
ጥቁር ወተት አለባት::
29/6/2007
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Fri Jun 29, 2007 9:33 pm
እንቆቅልሽ
ምን አውቅልሽ
.
.
አንቺ ለንዋይ ስትሰግጂ
እኔ ለፍቅር ስዋረድ
ያንቺ መንገድ ሲቃና
የኔ መቀመቅ ይዞኝ መውረድ
ምክንያቱ?..................
29/6/2007
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ቅራሪ » Fri Jun 29, 2007 9:37 pm
ልሞክር ያሚቲ መልሱ
ምክንያቱም ቀርፋፋ ስለሆንሽ ወይም ቶሎ ቶሎ መራመድ ስለማትችይ.... እንግዲ እንዳጽቁብኝ ከሰብዬ ት/ቤት አንደኛ ነው የወጣሁት ሰብየ ይጠየቅ.....
-
ቅራሪ
- ኮትኳች

-
- Posts: 247
- Joined: Wed May 10, 2006 4:42 am
- Location: adiss abeba
-
by ሀምሳለ » Sat Jun 30, 2007 12:22 am
ያሚዬ ምክኒያቱ :D ምክኒያቱ :D
እኔ ምን አውቃለሁ ብለሽ ነው :D :D ጥቅም የሚገዛት ሴት ወዶ መሰለኝ የማይወጣው ችግር ገብቶ
ቅራሪ ሰሞኑን ተገኘሽ ይልመድብሽ
ድውውውውውው
-
ሀምሳለ
- ኮትኳች

-
- Posts: 243
- Joined: Fri Oct 13, 2006 8:43 pm
- Location: America
by ዋናው » Mon Jul 02, 2007 2:51 am
yammi wrote:እንቆቅልሽ
ምን አውቅልሽ
.
.
አንቺ ለንዋይ ስትሰግጂ
እኔ ለፍቅር ስዋረድ
ያንቺ መንገድ ሲቃና
የኔ መቀመቅ ይዞኝ መውረድ
ምክንያቱ?..................
29/6/2007
ያሚ
አንቺ ነገን ቀጥ ማለት ስታስቢ
-እኔ ስንገዳገድ
ቡቃያዉን ቀድመሽ ወስደሽ
-እኔ አረም ሳጭድ
ምክኒያቱማ
ልቦናችን ላይቀና ሲንጋደድ
ሁለትነታችን ከአንድ ርቆ
-ፍቅር ከእኛ ሢሠደድ
እዛም አመድ
እዚህም ሠደድ
ያሚያችን እንቆቅልህን በእንቆቆልሽ ሞከርኩኝ ልበል?
አድናቂሽ
ዋናው________________________________________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2804
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by ሀምሳለ » Tue Jul 03, 2007 3:35 pm
ዋናው ወንድሜ የታሰረን ነገር መልሰህ አስረህ ትሄዳለህ :(
-
ሀምሳለ
- ኮትኳች

-
- Posts: 243
- Joined: Fri Oct 13, 2006 8:43 pm
- Location: America
by ሾተል » Fri Jul 06, 2007 1:41 pm
yammi wrote:እንቆቅልሽ
ምን አውቅልሽ
.
.
አንቺ ለንዋይ ስትሰግጂ
እኔ ለፍቅር ስዋረድ
ያንቺ መንገድ ሲቃና
የኔ መቀመቅ ይዞኝ መውረድ
ምክንያቱ?..................
29/6/2007
ያሚ
ምክንያቱማ....
ከርስ ካልሞላ በንዋይ
እንዴት ይነካል ስቅለተ ሰማይ
እንደዘመኑ ለኪስ ማደለብ ካልኖሩ
ለፍቅር ብለው በባዶነት ከተቸገሩ
እንደ አሻሮ ይኖራሉ መቀመቅ ውስጥ ሲያሩ
ላልተከሰተ ስውር ፍቅር
ለጠፋው ዘመን በልብ ማደር
በቢሆን የፍቅር አለም መኖር
ሞኝነት ነው ላላወቀበት ከምር
እንግዲህ ይሁን ብለው ለልብ ከኖሩ
ያሻውን ያድርገኝ ብለው በፍቅር ከታሰሩ
ቀኑም በእከክ እየተፎከተ ያልፋል
ጥልቀ መቀመቅ ውስጥ በግለት ይቀልጡዋል
ታድያ
ዘመኑጋ መስላ ያልኖረች ነፍስ
ትኖራለች ከድህነትዋ ጋ ስታለቅስ
ያ ነው ዘመኑን የዋጀው
ፍቅርን አጥቁሮ-
የንዋይን መውደድ ያበራው
ሰውን ከሰው ያጣላው
በመግደል መክዳት ወንጀል ደም ያጠበው
እናትን ከልጅ ያከዳዳው
እህትን ከወንድም ያጋደለው
የልብ ፍቅር በኖ የንዋይ ፍቅር የበቀለው...
ሾተል......ቃለህይወት ያሰማኝ-አሜን
-
ሾተል
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 9653
- Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
- Location: Vienna-Austria
by ሀምሳለ » Tue Jul 10, 2007 3:19 pm
ያሚን የበላ ጂብ አልጮህ አለ :cry:
-
ሀምሳለ
- ኮትኳች

-
- Posts: 243
- Joined: Fri Oct 13, 2006 8:43 pm
- Location: America
by yammi » Sat Jul 14, 2007 10:51 pm
ያሚን የበላው ጅብ ለ ሀምሳለ የተወው መልእክት
አውውውውውውውውውውውውውውውውውውውውው
:lol: :lol: :lol:
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ባቲ » Mon Aug 13, 2007 5:02 am
ቅና! ቅና! ብላኝ
ቅናቴን ተጠምታ
ቅናት ሲነግሥብኝ
ጠፋች ለሰላምታ?
SaQ _Be _SaQ.....That's what I wish 4 all of Us
ስምየ ውዕቱ ክንዴ ባቲ
-
ባቲ
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 942
- Joined: Tue Jul 06, 2004 8:18 pm
- Location: ethiopia
-
by ሚላግሮ » Mon Aug 13, 2007 9:11 am
ጊዜን መሻማቱ
ክፋትን ማብዛቱ
ስንት ነው ህይወቱ
በስብሶ እትብቱ
ልክ እንደቀፈቱ
እሱን ብቻ ማሰብ.......
ለእሱ ብቻ መድለብ....
ንዋይ ነዋይ ሆኖ ሁሉንም ካልገዛ
ለምን ተስፋ መቁረጥ ባለም ላይ አይብዛ
ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም
-
ሚላግሮ
- አዲስ

-
- Posts: 28
- Joined: Mon Feb 21, 2005 1:16 pm
- Location: united states
by ሚላግሮ » Mon Aug 13, 2007 9:28 am
ለጥሩ ነገር ሳስብ...
ልቤ ተነሳስቶ
አድርጎ...
አድርጎ...
ላይደላኝ ልይመቸኝ
የእጄን ላያሳየኝ
አሳመመኝ.....
አቆሰለኝ....
ልቤ ነው ያስጠቃኝ
በአለም ያስናቀኝ
አእምሮዩ ነው መሰል
እንዲህ ልል ያረገኝ
ዳሩ ግን ዳር አለው
አፈር ለሚበላው
አፈርን ሲበላው
ሲበላው ... ሲበላው.....
አሁን...? በዋላ...? ማምሻ...?
..... መቼ...........?
ስሄድ አገነሁት
ስመለስ አጣሁት
ሞትህን አታውቃት
መኖርን እወቃት
መታሰቢያነቱ____________
ለእንቆቅልሹ ሙከራ
-
ሚላግሮ
- አዲስ

-
- Posts: 28
- Joined: Mon Feb 21, 2005 1:16 pm
- Location: united states
by ክርስትያን06 » Wed Aug 15, 2007 8:50 pm
ያሚቲ ..
እውነትም አንችን የበላ ጅብ አልጮህ አለ :shock:
-
ክርስትያን06
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 601
- Joined: Fri Sep 08, 2006 5:15 pm
by ቤቲ_13 » Sat Sep 22, 2007 6:25 pm

ያሚታ እንኳን አደረሰሽ
መጪዉ አመት የሰላም ፍቅርና ተድላ ያድርግልሽ
ብዕርሽ የማይነጥፍበት አመት ::አሜን!!
አድናቂሽ
-
ቤቲ_13
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 795
- Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
- Location: ethiopia
-
Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
Who is online
Users browsing this forum: No registered users and 3 guests