[phpBB Debug] PHP Warning: in file [ROOT]/includes/bbcode.php on line 483: preg_replace(): The /e modifier is no longer supported, use preg_replace_callback instead

[phpBB Debug] PHP Warning: in file [ROOT]/includes/bbcode.php on line 112: preg_replace(): The /e modifier is no longer supported, use preg_replace_callback instead
[phpBB Debug] PHP Warning: in file [ROOT]/includes/bbcode.php on line 112: preg_replace(): The /e modifier is no longer supported, use preg_replace_callback instead
[phpBB Debug] PHP Warning: in file [ROOT]/includes/functions.php on line 4752: Cannot modify header information - headers already sent by (output started at [ROOT]/includes/functions.php:3887)
[phpBB Debug] PHP Warning: in file [ROOT]/includes/functions.php on line 4754: Cannot modify header information - headers already sent by (output started at [ROOT]/includes/functions.php:3887)
[phpBB Debug] PHP Warning: in file [ROOT]/includes/functions.php on line 4755: Cannot modify header information - headers already sent by (output started at [ROOT]/includes/functions.php:3887)
[phpBB Debug] PHP Warning: in file [ROOT]/includes/functions.php on line 4756: Cannot modify header information - headers already sent by (output started at [ROOT]/includes/functions.php:3887)
 WARKA ዋርካ • View topic - መፀሔተ-ዋርካ___________________________::

መፀሔተ-ዋርካ___________________________::

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ዋናው » Sat Sep 01, 2007 9:03 pm

ከባልቻ መዶሻ ድርሰት ውስጥ የተወሰደ ....ምልልስ

ባልቻ ፎዴን አራት ኪሎ የማያውቀው የለም ''...እኔ ባልቻ ያላቀናውት የመኩዋንንት ጫማ የለም ...'' ይላል ባለሙያነቱንና የስራ ልምዱን በኩራት ሲናገር ሽብሽብ የፊቱ ገጽ ስር የጠነገሩና ኑሮ 'ሀክ !' ያላቸው አይኖች አሉት ገብስማ ጢሙቹ ፊቱን እንደጉንዳን ቆንጥጠውታል የግራ ጆሮው ቀዳዳ ነው ተበስቶ ነበር ብቻ ሰፍና ቀዳዳ ሆነ ሁሌም ለሰላምታ እጅ ሲነሳ በቀር ከአናቱ የማትወልቀው ቅዱስ ገብሬልን ለማስፈራራት አትማ እዛው አናቱ ላይ ያረጀቸው የጨርቅ ኮፍያው መለያው ነች ::
ይገበዋል ጠጅ ቤት ገብቶ የመጀመሪያውን ብርሌውን በቁሙ አንቆርቁሮ ጠንጋራ አይኖቹን ሲማትር ባለንጀራው ጎበናን አየው ፈገግታ ሰጠው :: ጎበና መጥቶ አጠገቡ ተቀመጠ ::
...''እህሳ ባልቻ 'እንዴት ነህ ?'' አለው ብልጭልጭ ያለ ጥቁር ፊቱን ሁሉ ፈገግታ ሞልቶ
''አለው ቅዱስ ገብሬል የተመሰገነ ይሁን ...'' አለው ወደ ጣሪያው እጆቹን ዘርግቶ
''ስራስ እንዴት ነው ? ''
''አለው ይሄው የምድረ ሙጃሊያምን ፎዴ በውረንጦዬ እየወሰወስኩኝ ሸፋፋ ካለ ባልቻ ጾሙን አያድርም ....ጎበናዬ ''
ጎበና በመሀልና በሌባ ጣቱ ቆንጥጦ ያመጣትን ብርሌ በዜማዋ ወድጉሮሮው ዶቅ !ዶቅ !ዶቅ !... እያደረጋት ከንፈሮቹን ክብ አደረገና የወረዛ ጠጁን በሁለት ጣቶቹ አልቡ ጉልበቱ ላይ እያበሰ
''እንዴት ማለት ...?'' አለው ድምጹ እንደሰውነቱ ወፈር ያለ ነው ቢጫ ያይኖቹ ብሌኖች ተልቀው ጎበናን የሞኝ ገጽታ አላብሰውታል
'' በቃሀ ምን እንዴት አለ ሸፋፋ እንደሆን ጫማ ይቀዳል ሲቀደድ ደግሞ ውደባልቻ ...''
ጎበና ድጋሚ ሳቀና
''አይ ባልቻዬ ቅዱስ ግብሬልን እየተማጸንክ የሰዉ እግር ሁላ ቢጠማዘዝልህ ደስ ባለህ ....ቅቅቅ ''

''ታዲያሳ አንተስ ብትሆን ጠላ የሚያንቃርር ከሌለህ ስራ አጣህ ማለት አይደለ ? እቺ አለም 'ኮ እንዲህ ናት ያንዱ መከራ ላንዱ ጉራ አይደል ?...''

''አሀይ የኔስ አህያ አተላ ብታጣ የሆዳሞችን ጤፍ ታመላልሳለች ሞኞ ''
አለ ጎበና በኩራት ጠጁን 'የተጎነጨ

''...አይ አሁን በዛች ሸፋፋ አህያ ማን አምኖ እህል ይጭናል አተላውስ ቢደፋም አተላ ነው ...''

''ምነው ሸፋፋ አልካት እሱዋ 'ንድሆን ጫማ የላት ''
.''ቅቅቅ አይ ጎበና አንተ ኤኔትሬ ቢኖርህ ምን ትሆን ነበር በዚች አህያ እንዲህ የኮራህ ደሀ ወርቅ አይግዛ ....ነው የተባለው ''

ተፃፈ በዋናው
ፌብረዋሪ 26 2006
.
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sat Sep 08, 2007 10:05 pm

ጌታ ባንድ ወቅት መላጦችን እንዲህ ብሎ አፅናንቶ ነበር::

ድሮ ባዮሎጂ ስማር ከማስታውሰው ራሰበራነት በዘር ነው የሚተላለፈው :: ሴቶች ባብዛኛው በተሸካሚነት ወደ ልጆቻቸው ቢያስተላልፉም እነሱ የመመለጥ እድላቸው በጣም የመነመነ ነው :: ሌላ በቅርቡ የሰማሁት ደግሞ ራሰበራነት ቴስቴስትሮን ከሚባለው የወንድ ሆርሞን መብዛት ጋርም እንደሚያያዝ ነው :: ባገራችን ራሰበራ ወንድ አልጋ ላይ ኃይለኛ ነው የሚባለው ከዚህ ጋር ይያያዝ ይሆን ?

ለማንኛውም ያሁ ወይም ጉግል ሰርች ኤንጂኖች በመግባት baldness ብለህ ብትፈልግ ብዙ መረጃ ታገኛለህ :: ነገር ግን የተፈጥሮ ክስተት ስለሆነ በወጣትነትህም ቢከሰት ሳትጨነቅ እንድታስተናግደው እመክርሃለሁ :: ብዙ ወንዶች መላጣነት እንደሚያምርባቸውም አትዘንጋ ::

ተፃፈ በጌታ ሜይ 19 2006

_____________________________________________________________:[/b]
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sat Sep 08, 2007 10:36 pm

የ Oprahን ዝግጅት ካየሁ በኋላ በራሴም ጭምር ነው ያፈርኩት ማማ ትሙት :: እኛ ባልረባ ነገር አንተ ዘርህ ይሄ የእኔ እንደዚህ , የእኔ ቤት እዚህ ያንተ እዛ እያልን ስንባላ እኛው መቆጣጠር የሚገባንን : ወገናችንን ትምህርት መስጠት የሚገባንን : በቀላሉ መገታት በሚችል ነገር በብዙ መቶ የሚቆጠሩ እህቶቻችን ምን አይነት ኑሮ እየኖሩ እንደነበር እና እንዳለ ቤቱ ይቁጠረው :: እስኪ እራሳችን መፍታት የሚንችለውን ችግር ሌላው ስንትና ስንት አገር አቋርጦ : እኛ አጸያፊ ያልናቸውን ሲያቅፍ አያሳፍርም ?? በተለይ በተለይ ልቤን የነካኝ ከ Oprah ጋር አብረው ከተጓዙት መሀል ለህመምተኞቹ የእጅ አምባር ሰርታ ይዛ የሄደችው ሴት ናት :: ከእርሷ ሁላችንም እጅግ ልንማር እንችላለን :: ይህች ሴት በእነዛ ቅስማቸው በተሰበሩ ሴቶች ውስጥ የደስታን ፍንጣቂ ለማብራት ሚሊየን ብር ማውጣት አላስፈለጋትም :: ያላትን : ስለፍቅር ብላ የሰራችውን አካፈለች እናም ከሴቶቹ ያገኘችው "በጣም እናመሰግናለን :: የእግዚአብሄር ልብ ነው ያለሽ ::' የሚለው አስተያየት ከምንም በላይ ልብን የሚነካ ነበር :: እናም ጎበዝ ... ወገናችንን ለመርዳት የግድ ሚሊየን ብር መሰብሰብ አይስፈልገንም :: የግድ ስልጣን ገልብጠን ፕሬዝደንት መሆን የለብንም :: የግድ ታዋቂነትን ወይም እጅግ የተማረ መሆን አይጠበቅብንም :: በአንድ ሰው ህይወት ውስጥ ደስታን ለመዝራት : አስታዋሽ ያጡትን አለን ለማለት እቤት ውስጥ የተገጣጠም ትንሽ ብራስሌት ብዙ ትላለች :: ጤነኛ እስከሆንን አቅም እስካለን ድረስ ቢያንስ "አንድ " ማድረግ የምንችለው ነገር አለ :: እስኪ እናስብ !! ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልምና ::

ቸር ዋሉልኝ

ተፃፈ በማሜ ዲሴምበር 05 2005

__________________________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

ይፋ

Postby ወልዲያ » Tue Sep 11, 2007 1:57 am

ሠላም ልጅ ዋናው!

እንኳን ለኢትዮጵያ 2ኛው ሺህ በሠላም በፍቅር አብሮ አደረሰን::
Image
የምትጥላቸውን አማርኛ ሳደንቃቸው ጥራዝ ነጠቅነታቸውን ግን ሳልቃወም አላልፍም:: [ጓዳ በሩ ይመስክር]

ለቤቱ ይፋ የማላደርግበት ምክንያት አለኝ::

ለማንኛውም ተማር ---- መማር ኃጢያት አይደለም::

መልካም የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ዋዜማ
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Re: ይፋ

Postby ዋናው » Thu Sep 13, 2007 1:51 pm

ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Re: የግል

Postby ዘኪዮስ5 » Thu Sep 13, 2007 2:03 pm

ዘኪዮስ5
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 42
Joined: Sun Aug 13, 2006 12:00 am

Postby ዋናው » Sun Sep 23, 2007 1:18 am

እንደዝባዝንኬዉ አለም ... መልካም ልደት ብየ አልልም ... የልደትሽን ቀን እንዴት ና እንደምን እንደምትቀበይዉ አላዉቅምና !
እንደ ቀጣፊዉና ዋሾዉ አለምም አበባ አለጥፍም ... አበባን አበባ ለማለትሽ የማዉቀዉ ነገር የለምና !

ሻማም አላበራልሽም .... ቁጥሩ በመኖርና ለመኖር በመሞከር ተደበላልቋልና !

ኬክም አልቆርስልሽም .... የኬክ ጣእም አይገባኝምና !

ዳንኪራም አላስረግጥም ... የደስታ ምንጭ መሆኑን አላምንምና !

ሳትፈልጊ በሰዎች ምርጫ መጣሽ ... በዛሬዋ የልደት ቀን ማስታወሻሽ ላይ እስኪ ራስሽን እንደገና ዉለጂ ... አብቢ ... ዳግም ቆንጂ ..ቁንጂት በይ ... እደጊ ...ወደ ጎንም ...ወደ ላይም እደጊ ... እወቂ ... ራስሽን እወቂ ... አለምንም እወቂ ... እመኝ ... ራስሽን እመኝ ... ሌሎችንም እመኝ .... በእጂሽ ባለዉ ማጥፊያ ... የትናንትናዉን አጥፊዉ .... ለራስሽም ...ለአለምም ይቅርታን አድርጊ ... የተሰበረ ልብ ካለም ... ይጠገን ... ዳግም እንዳይሰበር ይሞከር ...

ትናንት ጥሩም መጥፎም ሆኖ ሊያልፍ ይችላል ... ነገን ግን የተሻለች ለማድረግ ሁሉም በእጂሽ ... ሁሉም በደጅሽ ነዉ ... እድሜሽን ከፍለሽ ያመጣሽዉ ትልቁ ንብረትሽ ተሞክሮሽ ነዉ ... ተሞክሮሽን አክብሪዉ ... ተመልከችዉ ... ትናንትን በዛሬ አስተካክይዉ ...

እኔ እስከዛሬ እንደምኖር ባዉቀዉ ኑሮ ለራሴ ትልቅ እንክብካቤ አደርግ ነበር ... ግን የስከዛሬዉንም ያክል ልኖር እችላለሁና እንክብካቤየን ጀምሪያለሁ ... ያለፈ የሚባል ጊዜ የለምና ! አለ እንዴ ? የእብድ ነገር ... ግን ጊዜ ያልፋል ... ይለፋ የራሱ ጉዳይ ... ግን አሁኑኑ ለራስሽ እንክብካቤ ጀምሪ ....

ወንድምሽ
ሙዝ 1

ተፃፈ በሙዘይድ
ሜይ 09 2007

____________________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon Sep 24, 2007 10:00 pm

ሠሞንኛ ትኩሡን የበርበሬ ወግን ትሸታለች ብዬ ነው እቺን ፅሁፍ ለዚች መፀሔት ያጨዋት::

ሐይ !!! ይቅርታ ..... በድጋሚ መጣሁ ......ሉህና አምሳለ ስለአለሙሜዳ ጀባ ልበላችሁ ብዬ ነው ::የአለሙ ሜዳ ሰፈር ሰዎች በርበሬ ገዝተው አያውቁም ነገርግን ማንም አልጫ ሲበሉ አይቷቸው አያውቅም .....ለምንድንው ??????መልሱ ......... የሜዳው ቀይ አፈር ወጡ ውስጥ ስለሚገባ ነው ......የሚል ካለ የፈረደበት ነው ::ያለሙ ሜዳ ጉልቤዎችን የረሳ ነው !!!!!!!!!!!

ተፃፈ በአዲስ ከተማው ልጅ ቶድ
ሜይ 17 2007____________________________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Oct 05, 2007 12:39 am

መቼም አባ ፈረዳ ቢራዉን ሲይዝ ጨዋታዉን ያመጠዋል ባንድ ወቅት ደጉ ቤት ውስጥ ካጫወተን .....

ደጉ ቀበሌ ታስሬ ባላውቅም ...አሳስሬአለሁ ....
ነገሩ እንዴት መሰለህ ..ከዛሬ ብዙ አመታት በፊት ..ለ 12..ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተዘጋጀሁ ..ሳለ ከወንድሞቼ ጋር የስራ ክፍፍል ነበረን ..አንዱ እንጨት ሲፈልጥ ሌላው ሌላ ሲሰራ ..የኔ ቀላል ነበረች ..ማምሻው ላይ ከእረኛ ከብቶቹን ተቀብሎ ...ሰፈር አካባቢ ማስጋጥ ነበር ...
እና ወደ ቁምነገሩ ልምጣና እንደሁሌው ከረኛው ላሞቻችንን ተቀብዬ ወደሰፈር ጠጋ ብዬ ከብቶቹ ለምለም ሳር እየቀራረሙ ሳለ እኔ የሆነ ነገር ማንበብ ያዝኩና ላሞቹን እረሳዋቸው ...ታድያ ላሞቹ የማታው እረኛ ፈዛዛ መሆኑን ተገንዝበው ..ወደ ለምለሟ ሳር በቀበሌ ጥበቃ ስር ባለችው ጫካ ጥልቅ ..ጠባቂዎችም እኔን እንኳ ሳይጠይቁ ..ላሞቻችንን ወስደው ቀበሌ ማጎር ...ከዛን ለት በላይ እራሴን እረግሜ አላውቅም ...ይታይህ እኔ በቅጣት እራት አልባ ሆንኩ ...ጥጆች በኔ ጥፋት ሳይጠቡ አደሩ ..ላሞችም ጥጆቻቸውን ሳይገናኙ በሚደብረው የቀበሌ እርቤት ሲያድሩ ቁንጫ አቅም ባይኖራትም ...ከሁሉም በላይ ጠዋት የተከፈለውን ገንዘብ ቤተሰብ እስከዛሬ ያስታውሱኛል ..በዝቶ አይደለም ...ቅቅቅቅቅቅየምርና የእውነት በኔ ላይ የሆነ ነገር ነው ...ቅቅቅቅቅ ግን ለምን ላንተ እናዘዛለሁ ወንድማችን ..ሰከርኩ መሰል ..ቢራው በዛ ...አይዞን የኤሌክትሮኒክስ ወንድሜ ስለሆንክ ብቻ ነው ...
ቻዎ

ተፃፈ በፓን ሪዝኮ
ረቡዕ ኖቬምበር 24 2004

____________________________________________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Wed Oct 17, 2007 7:04 pm

ለማስታወስ ያህል ብሎ ንዳቭ ካችዓምና ከጣፋት ያገኘሁትን እንካቹ::

ከንቱ :ከንቱ :የከንቱ :ከንቱ : ሁሉ : ከንቱ ነው ይላል :: ከጸሀይ በታች በሚደገምበት ድካም :
ሁሉ የሰው ልጅ ትርፉ ምንድነው ???

ትውልድ ይሄዳል : ትውልድ ይመጣል :

ምድር ግን ለዘላለም ነው ::
ጸሀይ ትወጣለች :ጸሀይም ትገባለች :
ወደምትወጣበትም :ስፍራ :ትቾኩላለች ::

ንፋስ ወደደቡብ :ይሄዳል ወደሰሜንም :ይዞራል
ዘውትር :በዙረቱ :ይዞራል :ንፋስም በዙረቱ :ደግሞ
ይመለሳል ::
ፈሳሾች :ሁሉ :ወደ :ባህር :ይሄዳሉ :
ባህሩ :ግን :አይሞላም :ፈሳሾች :ወደሚሄዱበት :ስፍራ :
እንደገና :ወደዛው :ይመለሳሉ ::

ነገር :ሁሉ :ያደክማል :ሰው ይናገረው :ዘንድ :አይችልም :

አይን :ከማየት :አይጠግብም :ጆሮም :ከመስማት :አይሞላምመጽሀፈ :መክብብ

ተፃፈ በንዳቭ
ኦክቶበር 28 20 05

________________________________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon Oct 22, 2007 12:36 am

..........ብቻ ሰው ማለት ቅናት መውደድ ተንኮል ሴራ ጦርነት አገም ጠቀም ያዝ ለቀቅ እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን ባይነት እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚሉት ሰብዐዊ አህያነት የሚስማማው ፍጡር ነው ....ለምን እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉት ጸባዮች ጥንድ ጥንድ በመሆን እንደሚስማሙት ለኔ ግልጽ ባይሆንልኝም ከስነ -ፍጥረት ጅምር ብንነሳም ያው ሰሪው ይሁን ብሎ ለራሱ የሚበጀውን የሚስማማውን አስቦ በክህሎቱ አዘጋጅቶ አጠገቡ ተቃራኒውን ግና የሚስማማውን ያኖረለት ምስክር ነው :: በተቃራኒ ማንነት ስጋው (ሰውነቱ ) በነፍሱ ወይም በማትታየው መንፈሳዊ (መግነጢሳዊ ) ኃይል ተሞልቶ የሚንቀሳቀስ ..ሲላቸው የሚጣሉ የማይስማሙ ጥላቸው ክርር ካለም ያው ባለቤቱን ሰው ተብዬውን ሰው ለጡዘት የሚዳርጉ እንዲህም ካልሆነ ሳይስማሙ እነዚያን ጥንድ ነገሮች በአቅቦ ሸክፎ የሚጓዝ ወይም ሽቅብ ታች እንደሚነጥር አየር የተሞላ የቆዳ ኳስ በመግነጢሳዊ ኃይል ሙላት የሚውተረተር የሚኖር ዝንተ አለሙን ለመኖር የሚኳትን ግንተፃፈ ኦክቶበር 19 2007
በአቡቲ
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Nov 30, 2007 1:23 am

ቀኑ ፀሀያማ ነው :: ፀሀያማ ሰኞ :: የስብሀት 'ሌቱም አይነጋልኝ ' ታትሞ ለገበያ መዋሉን ስሰማ እግሬ የመራኝ ወደ 'አሸናፊ መፅሀፍት መደብር ' ነበር :: አሸናፊ ግማሽ ክፍት በሆነችው የሱቁ በር አጠገብ ቁጭ ብሏል -ወጪና ወራጁን እያየ :: ለአዲስ ዘመን የሰጠው ቃለ -መጠይቅ ላይ

'አገራችን አንባቢ በዝቶ ሰዉ በብዛት መፅሀፍ እንዲገዛና እሱም በተዘዋዋሪ መኪና የመግዛት ህልሙ እንዲሳካለት ' የገለፀው አይረሳኝም ::

አሼ ያሰበው ተሳክቶ መኪና ገዝቶ ይሆን ???? እንጃ አራት አመት ሆነኝ ካየሁት ::

መፅሀፉን ገዝቼ ወደ አርቲስቲክ የሚወስደውን መንገድ ይጄ አመራሁ :: የስብሀትን መፅሀፍ ይጄ ስብሀትን ፍለጋ -ሰኞ አይደል ::አሸናፊን ሳስብ ጠይም ፊቱ እየታሰበኝ ; የሰኞ ቀን የስብሀት በአሸናፊ ቤት ወግ ትዝ ይለኛል :: የጠባብ ቤትዋን ግድግዳ ታከው የተጋደሙት አግዳሚዎች ወጣቶች ተቀምጠው ሸፍነዋቸዋል :: ቤቱ ግድግዳ ላይ የተሰኩት ስእሎች በስብሀት ልጅ የተሳሉ እንደሆኑ ነው የማውቀው (ነብስ ይማር ):: ስብሀት ብዙ አይናገርም :: ያዳምጣል :: የወጣቶችን ስሜት ፂሙን እያሸ በጥሞና ያዳምጣል :: አጠገቡ በኮዳ ወይም በጣሳ የተቀመጠ ውሀ ነገር ይታየኛል :: ቀስ እያለ ይጎነጭላታል :: ሲጠጣት በእርጋታ ; ሲናገር በእርጋታ ; ሲጓዝ በእርጋታ :: እድሜው ሙሉ ያነበበው እውቀት ደክሞት በእርጋታ የሚጓዝ ;የሚናገር ይመስላል ::

ጠይሙ ልኡል ሰኞ ሰኞ በወጣት ሀዋርያት ተከቦ እሱ ባለበት እውቀት ሲፈስ ይውላል :: ሀዋርያት ይናገራሉ :: ልኡል ይሰማል :: አድማጭ ልኡል ::.

ተፃፈ በ jossy1
ፌብሩዋሪ 1 20 06
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sat Mar 01, 2008 11:11 pm

::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Apr 11, 2008 9:36 pm

THIS IS MINE AND MINE ONLY So AM INTITELD TO IT

#291 " In the world where celebrity equals talent, and where make believe is called reality, it is important to have a real love, truth and stablity in your life" Bernie Bnillstein.

ተገኘ ከ ግራዴ ካርሜል ማኪያቶ ከፔ ላይ ......... አስ ዩዥዋል ኢት ስትረክ ሶም ቲንግ ኢን ሚ :: እውነት "እውነትን " የሚያሰኘው ነገር እንዲሁ ዝም ብሎ ለማለት ያህል ነው ? ወይስ በርግጥ የተረጋገጠ ነገረ ሆኖ ነው ? እውነተኛ ፍቅር , እውነተኛ ጓደኝነት እምም እውነተኛ ሰው እረ ብዙ እውነተኛ ነገር :: ታዲያ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግዑዝን ነገር የማይዳሰሰውን እና ሊጨብጥ የማይቻለውን ነገር እንዲሁ በምናቤ እያዋዛሁ ለራሴ በሚመቸኝ ሁኔታ እና መንገድ እያየሁት ከዚያም አልፎ እንደተመቸኝ እያብላላሁት መልስ ባጣለት እና እንዲሁ እንደነበረው ቢቀመጥ ጉዳቱ አይታየኝም ምክንያቱም ሁሉም እራሱን ቢመረምርና ቢጠይቀው መልስ ያማያገኝለት ብዙ ጥያቄዎች አሉትና .............ሰው በጠፋ ቀን ሰው ሚሆነኝ ሰው ፈልጌ አጣሁት ልክ "እውነተኛ " እንደጠፋ ሁላ ምክንያቱም ሁለቱም ስለማይገቡኝ ...............ለዚህ ነው ደሞ ለምን እንደማይገቡኝ ራሴን ስጠይቅ ለዚህም ጥያቄዬ መልስ ማጣው .........ወይ ጉድ አለሙ ግሩም ድንቅ ነው ሲሉ የሰማሁት እዚሁ ዋርካ ላይ ነው በርግጥ አለሙ ግሩም ድንቅ ነው በተለይ ደሞ የኔ አለም ምንም ሊወጣለት የማይችል ምክንያቱም እንዲወጣለት ስለማልፈቅድ :: ሶ ይህ በንዲህ እንዳለ ነበር real truth, love and stablityn የናፈቅሁዋቸው ሌላ መልስ አልባ ጥያቄ እና ኮንፊውሽን እንዲፈጥሩ ::

ተፃፈ በ konjit ኤፕሪል 07 20 08
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby በጎሲያ » Sun Jun 01, 2008 11:26 pm

ዋናው እንክዋን በሰላም ተመለስክ
እቺን ቤት ስለምወዳት ዛሬ የመራራውቀልደኛዉን ቀልድ አቅርቢያለው

በፖለቲከኞቻችን ስሌት 2+2 ሰንት ነው ?

አጼ ሓይለሰላሴ = ልጆች አትቸኩሉ የህዝባችንን ፍላጎት ጠይቀን እንነግራችዋለን ::

ገርማሜ ንዋይ == በትክክል መመለስ ያስቅላል
መንግስቱ ሐይለማርያም = ይህንን ለመጠየቅ ማን ፈቀደለህ ?
ለገስ አስፋው = 120
አባይ ጸሀዬ = ለብዙ ጊዜ ዝምታ ስለነበር ጋዜጠኛው ምንም
ሳይመዘግብ አልፎታል

ስብሀት ነጋ = ብቻዬን መመለስ አልችልም

መለስ ዜናዊ = 3 ወይንም 5 ሊሆን ይችላል ለትክክለኛው ውጤት ፖሊሲ ቀርጸን እየተንቀሳቀስን ነው ::4 ነው ብለው የሚናገሩ እንዳሉ እናውቃለን ::እነሱንም ቢሆን ግማሽ መንገድ ሄደን እንቀበላለን ::
በረከት ስሞእን = በንፋስ ካልሆነ በስተቀር ማንም 4 አያመጣም

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮሰ 4 ነው ብለን ነበር ይህንን ትተን በአማራጥ ሰሌት አቅርበናል

ልደቱ አያሌው = ሁል ጊዜ አንድ መልስ አትጠብቅ ሶስተኛ
አማራጥ አለ ;; 4 ነው የሚሉትን ተዋቸው ::የዲያስፖራ ወሬ ነው ::

አቶ ተመሰገን = ፎር ብለው አሜሪካኖች ሲናገሩ ሰምቻለሁ
ትክክለኛውን አላውቅም ::

አቶ ቡልቻ ደምቅሳ =እንጃ ብለው ዝም ሲሉ ጋዜጠኛው በኦሮምኛ ጃ (6) ብሎ መዝግቦታል

ብርሀኑ ነጋ (ዶ /ር ) 4 መሆኑ ቀድሞም ይታወቃል ነገር ግን መስማማት አልቻልንም :: ብቻህን 4 ብትል አይጠቅምም 3.99 ካመጡት መስማማት ;; ሰርተህ ማስየት ከቻልክ ምናልባት ተቀባይ ታገኝ ይሆናል :: ትራይ ሀርድ

አቶ ሀይሉ (ኢ /ር ) ማንኛውንም ውጤት አልቀበልም :: ካልተስረቀ በስተቀር 4 አይመጣም 5 ወይንም 3 የሚሉት ከየት እንዳመጡት አላውቅም

ዶር ነጋሶ :: ምን እንድሆን ይጠበቅብኛል ? የት ሄጄ ውጤት
ላምጣ ? ሞክሪያለሁ ! ተውኝ ሁሉም ዜሮ ነው

ጎሹ ወልዸ == አይደመርም

ዶር ታዬ == 4 የሚል አላነበብኩም

በመጠረሻ ጋዜጠኛው ትክክለኛውን እንዲንግሩት
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ አመት ተማሪዎች
ጠየቃቸው ::

ተማሪዎቹም

ገና ትምህርት እንዳልተጀመረ ግን እንድሚሞክሩ ሲነግሩት
ደሰ አለው

3.5 አሉ በአንድ ላይ
በጎሲያ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 93
Joined: Mon Dec 29, 2003 8:48 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest

cron