ለካስ BYONCE ለረመዳን ጾም መፍቻ ነው የምትመጣው::

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ለካስ BYONCE ለረመዳን ጾም መፍቻ ነው የምትመጣው::

Postby leflafiw » Sun Aug 26, 2007 11:50 am

ሼኩ ምናቸው ሞኝ ነው ለካስ ሸራተን ያምያሰራው ጊዜያዊው ኪትዮጵያ ትልቁ አዳራሽ ለረመዳን እና ለአውሮፓውያን ዘመን መለወጫም ዝግጅት ነው ::

ሼኩ በጾም ምድር የብዮንሴን ቂጥ ማየት ትርጉም የለውም ብለው በዛውም ጾሚዎች ሚሌንየሙን ክጾም መፍቻ ጋር እንድያከብሩ oktober መጨርሻ ላይ ነው የውጭ ዘፋኞች የሚመጡት ::

በዐገራችን ይዘመን መለወጫ ላይ ግን የ ኢትዮጵያ ዘፋኞች ብቻ ናቸው የምያዝናኑት ::

Byonceን ለሚለንየም አያለሁ ብሎ ያሰበ ካለ ተሳስቷል::

ሚሌንየሙን ከአስቴር አወቀ ጋር እህህ እያሉ መላቀስ ነው :( :(

በከፊል ይዜና ምንጩ

http://www.addisfortune.com/Sheraton%20Addis%20Hiring%202,000%20Crew%20for%20Millennium%20Bonanza.htm

እንደው ግን ለብዮሴ ብሎ ለሚሌንየም ጎዞ ያሰበ ነበር :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
leflafiw
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 48
Joined: Sat Dec 24, 2005 2:01 pm

Postby መልከጻዲቅ » Sun Aug 26, 2007 12:58 pm

ለፍላፊው!! እንደምን:ከረሙ:
ይሀውልዎ:የጻፉትን:ማጣቀሻ:(link), አየሁት::በሚለንየሙ:አንጻር:ለሚዘጋጀው:ኮንሰርት:እንዲረዱ:እስ
ከ:ሁለት:ሺ:ሰራተኞች:ለስድስት:ወራት:በኮንትራት:መልክ:እንደሚቀ
ጠሩ:ይዘግብና:መሰናዶው:በሶስት:ታላላቅ:ቀናቶች:ላይ:እንዲውል:
መታሰቡን:ይተነትናል::እነዚህም: በሚለንየሙ:አዲስ:አመት:መግቢያ: አንድ:ይበሉ, በጥቅምት:ወር:መጨረሻ:በሚውለው:የእስልምና:ወገኖቻችን:የጾም:መግደፊያ:
እለት: ሁለት, ከዛም: የፈረንጆቹን:አዲስ:አመት:በማስመልከት:
ታህሳስ:ወር:መጨረሻ:ላይ:የሚደረግ:መሆኑን:አዲስ:ፎርቹን:ያስነ
ብበናል::ውድ:ለፍላፊው:እርሶ:የጠቀሷት:ዘፋኝ:በዚህ:ቀን:ትዘፍናለች:
የሚል:ሀረግ:የለም::እስኪ:ጽህፉዎን:አንዴ:ይገርቡት, final touch,እንደሚባለው:አይነት... ሰላም:ይሁኑ::
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ቆቁ » Sun Aug 26, 2007 2:18 pm

ዘፈን ምን ያረጋል ? ምንስ ይፈጥራል ?
ብሎ ፈላስፋው ይጠይቃል ::
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4027
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby መልከጻዲቅ » Sun Aug 26, 2007 8:07 pm

እንደምናሉ:አቶ:ቆቅ:
ጥያቄዎ:ቀላል:ይመስላል:እንጂ:ከባድም:ነው::መልስ:ባይሆንም:
የመሰለኝን:ልንገርዎ:ዘፈን:ጥሩ: ነው:ያለፈ: ትዝታን:የምናስታውስበት:መስታወትን:ይመስላል::የጉርምስና:ዘመ
ናችንን:የምንቃኝበት:መነጽርም:ይሆናል::ዘፈን:በቀረርቶና:በሽለላ:
ሲታጀብ:ደግሞ:ወኔን:ይቀሰቅሳል,ያበራታል::ሰዎች:በደቦ:ስራ:ሲሰሩ:
ገበሬዎች:እህል:ሲያበራዩ:እየዘፈኑም:አይደል! ቆቁ:እንዴት:ነው:
አይበሉኝ:እንጂ:ዘፈን:እኮ:አንዳች:መግነጥሲያዊ:ሀይል:አለው::
ውስጣዊ:ህሊናችንን:መኮርኮር:የሚችል:,በህዋ:የሚያዞር:በአየር:
ላይ: የሚያንሳፍፍ..... ግድየለዎትም:የዘፈን:ነገር :ጉዳዪ:ቡዙ:ነው::በሰርግ:ጊዜ:ዘፈን:ይዘፈናል:ሙሽራና:ሙሽሪትን:
ደስ;ያሰኛል:ቤተዘመድን;ያስፈነድቃል::ይህ;ሁሉ:የዘፈን:ጥሩነትን:
በተመለከተ;ነው::ዘፈን:መጥፎ:የሚሆነው:ታዲያ:በኛ:ላይ;መሰልጠን:
ሲጀምር:ነው....ይህም:ማለት:ዘፈን:ካልሰማሁ:ቀኑን:ሙሉ:እደበራለሁ,
ማለት:ስንጀምር, ዘፈን:ከሌለ;ፍቅር:መስጠትም:መቀበልም:አልችልም:የምትል:ፍቅረኛ;ካለችዎት:
ዘፈን:ከሌለ:ጥናት:አይገባኝም:የሚል:ጉብል:እቤትዎ:ካለ:የዘፈኑ;ተጠቃሚዎች:
ሳንሆን:ምርኮኞች;ሆነናል:ማለት:ነው::አቶ: ቆቁ:ዋርካ:ቡዙ;አድባሮች;አሉዋት:: እነሱም;የሚሉትን:እናድምጥ...... መልስ:ነው:ብዬ:ሳይሆን: ሰው: ያለውን:ከወረወረ: በሚል:ነው....ደህና:ይሁኑ::
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ቆቁ » Mon Aug 27, 2007 7:50 pm

ዘፈናችን: አበባየሆይ::
ጨፈራችን: ሆያ ሆዬ::

አበባየሆይ: ሲዘፈን: ልጅነቴ: ጉርምስናየ::
ሆያ: ሆየ: ሲጨፈር: ልጅነቴ :ኮረዳነቴ: ትዝ: ይሉኛል::
ሜዳው: ሸንተረሩ: ሸለቆው: የጅራፍ: ግርፊያው: ሙሉሙል: ዳቦው: አምባሻው : አደይ አበባው : ችቦው :
ሳር ጉዝጉዋዙ : የዶሮ ወጡ: ጠላው ጠጁ :የቀንዶዋ አረቄ : ባርማሽላው : ወሰራ እና ገብስማ ዶሮው: የብይ እና የጠጠር ጨዋታው : የቆርኪ ጨዋታው : የጢቢጢብ ጨዋራው እረ ስንቱ ልበልህ መልከ ጼዴቅ :!: :!: :!:


እንደ ጃኒት ምን ይሰራሉ እነ ብዮንስስ ምን ይፈጥራሉ :?: የአሜሪካንን ትዝታ ለማስታወስ ? ወይስ ... ?

ሐምበርገር እንዴት እንደሚገመጥ ለማስታወስ ?
ሆት ዶግ እንዴት እንደሚሰለቀጥ እና እንደሚዋት ለማስታወስ :?:


እሺ እነ ጃኒት ዘፈኑ እነ ብዮንስ ተጫወቱ እንበል
ምንድነው ትዝታው ምንድነው ትውስታው ?

ዳንሱ : መጠጡ : አዳራሹ : እነ ጃኒት እና እነ ብዮንስ :?: :?: :?:

አሁንስ ጥያቄዬ ከባድ ነው ወይስ ቀላል ?

ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4027
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby መልከጻዲቅ » Tue Aug 28, 2007 2:54 am

ሰላም:ዋሉልኝ:አቶ:ቆቅ:
የኑሮ:ጉዳይ:ሆኖ:ቶሎ:መልስ:አልሰጠሁም::ጥያቄዎ:አሁን:ግልጽ:
ይመስላል::የግራሞት:አያስኬድም:መንዙማ:የለውም::
ግጭት:ፍጥጫዎ:ጸብ:አምባጋርዎ:ከዘፈን:ትርጉም:ጋራ:ሳይሆን:መድረኩን:
እነማን:ይውረዱበት:ሠገነቱን:ማንኛቸው:ያዳምቁት:የሚል:ስር:ሀረግ:
አለው:: ኢላማዬን:አልሳትኩም:አይደል!
ይሀውልዎ:ቆቁ:እርሶ:ባሉት:ሀሳብ:ላይ:በፉጹማዊ:አንድነት:እስማማለሁ::
አሁን:ማ:ይሙት:ለወ/ሪት:ጃኔት:የኢትዮጵያ:ምእተ:አመት:ምን:
ፋይዳ:አለው?ቢዎንስም:ብትሆን:ኢትዮጵያን:ከካርታ:በዘለለ:
የምታውቃት:አይመስለኝም::
የኢትዮጵያ:ታላቅ:ክብረ:በአል:በኢትዮጵያውያን:ተወዛዋዦች:
በኪነ:ጥበብ:ሰዎች:ይከበር:ዘንድ:ታላቅ:ምኞቴ:ነው::ታላቁን:
የክፍለ:ዘመናችንን:የሙዚቃ:ሰው:ጥላሁንን:ጨምሮ:አለማየሁን:
ታምራትን:መሀሙድን:አስቴርን:ሸበሌዎችን:ሸገኔዎችን:አምባሰሎችን:
ዘመነኞችን:ከየብሔሩ:የመጡ:ድንቅ;የባህል:ሙዚቃ:ተጫዋቾችን:ተወዛዋዦችን:
ሁሉንም:አፍርታለች:ይህች:ሀገር::አዘጋጆቹ:ለታላላቆቹ:የኢትዮጵያ:
ልጆች:በዚሁ:የእሥራ:አመት:መከበሪያ:ላይ:የክብር:ስፍራቸውንና:
የመክፈቻውን:ስርአተ-ቁልፍ:ይሰጣአቸው:ዘንድ:እኔም:እንደእርሶ:
ኢሮ:እላለሁ::ዘፈን:ለምን:ተዘፈነ? አይደለም:ሰጣ-ገባው! ያገሩን:
ሰርዶ:ባገሩ:በሬ:ይሁን:ነው:ማሳረጊያው::
ፈላስፋው:ሆይ:ነገሬ:ሚዛን:ባያነሳም:የምችለውን:ሞክሬአለሁ:
ታላቁ:መጽሀፍም:እንደሚል:እግዚአብሄር:ያልሰጠውን:አይጠይቅም:
እናም:ይህው:ነው:ያለኝ......
በነገርዎ:ላይ:ጽህፉዎን:ሳነብ:በትዝታ:ሳቡኝ:...."ቀንዶ:አረቄ:ነው:"ያሉት?
.........እሷ:እኮ:ዋና:ነገር:ናት!!ፈረንጆች:የማያውቁት:ለሆድ:የሚሆን:
ቡዙ:መድሀኒት:አላት:ይባላል:ይበሉ:እንግዲህ,የሚያውቁት:
ግሮሰሪ:በሰፈርዎ:ካለ:ቀስ:ብለው:በቴሌግራም: ሹክ:ይበሉኝ:ካልሆነም:
ግድ:የለም:አይጨነቁ:ለማንኛውም:ደህና:ይሁኑልኝ::
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ቆቁ » Tue Aug 28, 2007 10:21 am

መልከጼዴቅ ወዳጄ አስከአሁን ከተስማማን እስኪ ደግሞ ወደ ምንለያይበት መንገድ ደግሞ እንሂድ


ጃኒትም ሆነ ብዮንስ :ይምጡ : ነገር: ግነ: እነዚህ: ዘፋኞች: እንዲመጡ :የጋበዙት: ኢትዮጵያውያን: ናቸው: ወይስ: አሜሪካኖች? :?:

ወዳጀ: መልኬ: ጸዴቅ :የአሜሪካን: እና: የአውሮፓ: የዲያስፕራው: ወገን: ሐገሩ: እንጂ: የሚናፍቀው : የሐገሩ ባህል: እንጂ: ሰውነቱን :የሚነዝረው: እነ: ጃኒት: እና: ብዮንስማ: እዛው: በዲያስፕራው ዓለም : በራዴዮ: የሚዘንፉለት: አጥጋቢ :ነው
ታዲያ :ለምን: አስፈለጉ: እነዚህ :ዘፋኞች? :?: :?:

የጋባዞቹ : እና :የአስተናጋጆቹ : የሐገር :ወዳድነት : ሐገር: ባህል: ወዳድነትስ: ምን: ያህል :ነው ?

እሺ: የሽማግሌው: ወገን: ለምሳሌ: እነ ፕሮፌሰር: ኤፍሬም: እና :ሐይሌ: ገብረስላሴ: ምን: ይላሉ: በዚህ: ሁኔታ ?


ለመሆኑ: ይህ :ጉዳይ: የቅኝግዛት: ምልክት: አይደለም?

ለመሆኑ: አንድ :ኢትዮጵያዊ: ዘፋኝ: በአሜሪካ: ተጋብዞ: ለአሜሪካኖች ዘፍኗል :?:

ጃኒትም: ሆነ: ብዮንስ: ሌላ: የሙዚቃ: ዝግጅት: በኢትዮጵያ :ለማድረግ :መብት: አላቸው:: ነገር: ግን: ይህንን: የኢትዮጵያ: አዲስ :ዓመት: 2000 :ለማክበር: የግድ: የአሜሪካ: ዘፋኞች: መምጣት: አለባቸው?

ለመሆኑ: የአዲስ: አመት: በፈረንጁ: ሐገር: ሲከበር: ከሌላ: ሐገር :ዘፋኝ :እየመጣ: ነው: የሚያከብረው ?

ባህላችን :በውጭ: ባህል: ሲወረር: ለዛውም: በተለይ: ይህ: አዲስ: አመት: በቀጥታ: ሳይሆን: በተዘዋዋሪ: መንገድ: በነ: ጃኒት: ጃክሰን: እና: በብዮንስ :ሲወረር: እንዴት: ዝም: ብለው: ያዩታል?


ዘፈናችን: አንድ: ጊዜ: በሪጌ: ሲወረር: አሁን: ደግሞ: በራፕ: ሲወረር: ዝም: ብሎ: የሚመለከት: አስተናባሪና: አዘጋጅ: ምንድነው: ብለን: ብንጠይቅስ ?

እንደውም: እርቀ: ሰላሙ :በዚህ :በአዲስ :መንገድ: መቀጠል :ከፈለገ: እርስዎ: እንዳሉት: ወደር: የሌላቸው: ዘፋኞቻችን:ወደር: የማይገኝላቸው: ቀልደኞቻችን: ወደ: ሐገራችው: ጎራ: ብለው: ያንን: ወገናችንን: ቢያዝናኑት: ከዛም: አልፈው: ለዲያስፕራው: ወገንና: ለሐገር: ወገን: የመጉዋጉዋዣ: ድልድይ: ቢሆኑ: ምን: ክፋት: ነበረው ?

ብሎ ፈላስፋው ይጠይቃል

ሌላም ጥያቄ አለው
ከነጃኒት ጃክሰን በሁዋላስ ማን ይመጣ ይሆን ?
መቸ ?

የነጃኒት ጃክሰን ግብዣ በጣም ውድ ሲሆን
የሐገራችን ዘፋኞች ግብዣ ደግሞ ብዙ ገንዘብ የማያስከፍል እንደውም በነጻ : ብዙ ውጣ ውረድ የሌለበት : ታዲያ አትራፊዎች እንደት ነው ነገሩን የተመለከቱት ?


ተንሸዋሮ ገንዘብ መቁጠር ብቻ ሌላ ነገር እዚህ ጭንቅላት የምንለው ውስጥ የለም ማለት ይሆን ?

ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4027
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby BRUKYIRGA » Tue Aug 28, 2007 1:49 pm

ዥግና ደህና ከረማችሁ ወይ?
በዚህ መልኩስ ብታዩትስ? ትልቅ ግብዣ ኖሮ ገበታው ላይ የያገሩ አይነት ምግብ ቢቀርብ ማን ይጠላል ? ከያይነቱ እየቀማመሱ ማጣጣም እንጂ ያም ማለት በዋናነት የሚወዱት የምግብ ምርጫዎ እንደተጠበቀ ሆኖ ............ በዚሁ ቀመር መሰረት የሙዚቃ ድግሱም ላይ ቢያንሴም ሆነች ማንትስ ቢግኙ ........እንዲያውም ተየ አለሙ ማእዘን ቢመጡስ>>>? እውነት ያ ህዝብ ለመዝፈን ተታደለ!!!!!!!
BRUKYIRGA
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 218
Joined: Sat Nov 26, 2005 12:36 am
Location: minnesota/usa

Postby ቆቁ » Tue Aug 28, 2007 6:07 pm

BRUKYIRGA wrote:ዥግና ደህና ከረማችሁ ወይ?
በዚህ መልኩስ ብታዩትስ? ትልቅ ግብዣ ኖሮ ገበታው ላይ የያገሩ አይነት ምግብ ቢቀርብ ማን ይጠላል ? ከያይነቱ እየቀማመሱ ማጣጣም እንጂ ያም ማለት በዋናነት የሚወዱት የምግብ ምርጫዎ እንደተጠበቀ ሆኖ ............ በዚሁ ቀመር መሰረት የሙዚቃ ድግሱም ላይ ቢያንሴም ሆነች ማንትስ ቢግኙ ........እንዲያውም ተየ አለሙ ማእዘን ቢመጡስ>>>? እውነት ያ ህዝብ ለመዝፈን ተታደለ!!!!!!!


ጀግናው የሐገሩን ሰርዶ በሐገሩ በሬ ሲባል የምታውቅ መሰለኝ::

ስማ እኛ ኢትዮጵያውያን ሳንሆን ራሳቸው ፈረንጆች ናቸው ይህንን የ2000 ዓመት በናፍቆት የሚጠባበቁት
ሲጠባበቁትስ እንዴት ነው ብለህ ራስህን ጠይቅ እስቲ ?

በጃኒት ጃክሰን ዘፈን !!!!!!!
በብዮንስ ዘፈን !!!!!

ስማ ለፈረንጆች የሚያስቅ ነው ምክንያቱም ""የተውሶ ልብስ አያደምቅ"" ዓይነት ነገር ስለሚሆን

2000 አመተ ምህረትን በጃኒት ጃክሰን እና በብዮንስ ? :!: :!: :!: :!:

የ2000 ዓመተ ምህረት አከባበር ዓላማ ምንድነው ?

የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር እና የኢትዮጵያን ባህላዊ ትርኢት እንዲሁም የኢትዮጵውያንን የምግብ እና የመጠጥ ዓይነት ከዛም የኢትዮጵያን ሕዝቦች እና ምድሩዋን እንዲሁም ወንዙዋን ለማስተዋወቅ መስሎኝ ?

አይደለም እንዴ ?

ነገሩስ እውነትህን ነው ሉሲ አሜሪካ ስለሄደች ነው መሰለኝ እነ ጃኒት በልዋጩ ኢትዮጵያ የሚመጡት ?

ያ ከሆነ ምንም አይደለም 8) 8) 8)


ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4027
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby መልከጻዲቅ » Sun Sep 02, 2007 1:02 am

ፈላስፋ
ው:ቆቁ:ሁለተኛም:የሚኖሶታው:ብሩክ:ይርጋ:ሰላም:
ሰነበታችሁ:ወይ!!የቆቁን:አላውቅም:እንጂ:ብሩክ:ይርጋ:ያሉበት:
ሀገር:ለምለም:ናት:ይባላል::የወተት:የማር:ምድር:ናት:ዳግማዊ:ሀገርዎ:: ታዲያ:ለአዲሱ:አመት:ሙክት:ብጤ:አርደው:ይጥሩና!!እርግጠኛ:
ነኝ:ፈላስፋው:ግብዥአዎን:በደስታ:ይቀበላሉ::እኔም:የአክፋይ:የምትሆን:በጋዜጣ:
ጠቅልዬ:እመጣለሁ:አላሳፍርዎትም::
ፈላስፋው:ቆቁ:የጠፋሁት:በቴክኒክ:ችግር;ምክንያት:ነው::ለጠየቁኝ:
ጥያቄ:ደጎስ:ያለ:ኤሮግራም:አዘጋጅቼ:ነበር::ጽሁፌን:ለአየር:ከማብቃቴ:
በፊት:ታዲያ:ለመገረብ:የምታስችለኝን:ጠቆአሚ:(peview button)
አንድ:ጊዜ:ብቻ:ነካሗት:ጠላትዎ:ጎርደሜ:ገደል:ይግባ!ጽሁፌ:
እያየሗት:በአናቷ:ገባች::ያ:ሁሉ:ድካም:ከንቱ:ሆነ:ጽሁፌ:ጠፋ::
ኮምፒይተር:ውስጥ:የመሰገ:ዘንዶ:ዮናስን:የዋጠ:አሳ:የኔንም:ጽሁፍ:ሰለቀጠው::
ፈላስፋው:ጥያቄ:ልጠይቅዎ:ነው:እርስዎ:ጋ:እውቀት-ብልሀቱ:አይጥፋም:ብዬ:
አስባለሁ:
1.በአማርኛ:የጻፉትን:መልክት:ከመላክዎ:በፊት: save:ማድረግ:
ይችላሉ:ወይ?ጥበቡን:ይጻፉልኝ.....
2. ከኮምይተር:ውስጥ:የጠፉ:ጽሁፎችን:አሳዳ:የምትይዝ:መድሀኒት:
ያውቃሉ:ወይ?እባክዎን:ያፋልጉኝ!!
አለበለዛ:ኮሚይተሬን:ኮሶ:በጥብጬ:ላጠጣት:ነው:እንዲያሽራት!!!!
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ጎማ እግሩ » Sun Sep 02, 2007 3:07 am

መልከፃዲቅ

በመጀመሪያ የፃፉትን ሃይላይት ያድርጉ በመቀጠል
save ለማድረግ Ctrl እና C አንድ ላይ ይጫኑ:: ፅሁፍዎ ከጠፋ እንደገና Ctrl እና V አንድ ላይ ይጫኑ:: መልሰው ፅሁፍዎን ያገኙታል
Rights go hand in hand with responsibility, with dignity, with respect for oneself and for the other.
ጎማ እግሩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 864
Joined: Wed Jun 20, 2007 1:49 pm

Postby መልከጻዲቅ » Sun Sep 02, 2007 3:54 am

ጎማ:እግሩ:እንደምን:አሉ:ፈላስፋው:በምርምር:ላይ:ናቸው:መሰል:
መለክቴን:ያዩት:አይመስልም.... ለፈጣን:ምላሽዎ:እግዚሀብሄር:ይስጥዎ:: ሰላም:ይሁኑልኝ!!!
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests

cron