ችሎ ማደር!
አሁን ገና ጨዋታ መጣ :: አስቲ የት ላይ ነው መፍለጡ መቁረጡ :: ሐላፊነት የለም አንዴ ; ቤት አይከበርም አንዴ : ዞሮ ለቤተስቡ አንደመርዳት አርግዝ አርጎ ማረፍ :: የአጎቴ ጥፋት የቱ ላይ ነው
ልጅቷ ተሳስታ አንዴ አርግዛለች! በቃ! ከዚ ተነስና መፍትሄ ፈልግ! ወደዋላ ተመልሰህ ለምን አረግዝሽ ብትላት ብትዘል ብትፈርጥ የተጎዳዉን የልጅቷን ስሜት ጨምረህ ነው የምትጎዳው እንጂ ምንም የምታመጣው ነገር የለም::
አጎትህም ይህን መረዳት አለምቻላቸው ነው እንዲበሳጩና በግትርነት ልጅቷን ከቤት ዉጪልኝ የሚሉት! ረጋ ብለው ምን ላድግ ብለው ቢያስቡ ትልቅ ጥፋት ደግመው እየሰሩ ያሉት አጎትህ ናቸው! የሰውን (ያዉም የልጃቸውን) ችግር ተረድቶ እንደ መርዳት በችግሯ ላይ ሌላ ችግር መደረብ ትልቅ ሀጥያት ነው:: ለዚ ነው ፈላጭ ቆራጭ ያልኩት::
በተጨማሪም አንድ ቤተሰብ የሚመሰረተው 50% ባል 50% ሚስት ነው እንጂ እንደጃንሆይ ዘመን ትዳር ያዉም በሰለጠነው አለም ትሁኖ አያምርም! ባል ከቤት ዉጪ ስላሉ ብቻ የአጎትህ ሚስት ሀሳብ ምን እንደሆነ ሳይታወቅ ልጅቱ ትዉጣለች ማለት አይደለም! ሁለቱም ተነጋግረው ከቤት ትዉጣ ካሉ ok! ልጅቷም ትልቅ ናት ራስዋን መምራት ትችላለች!!!
የቤተሰብ ክብር የምትለው ነገር በጣም ያስቃል! ልጃቸው ተቸግራ ከቤት ዉጪልኝ እያሉ አባት ስለቤተሰብ ክብር ሲጨነቁ! ይህ ነው የአጎትህ ትልቅ ጥፋት! ከሁሉም የከፋው የሳቸው ትፋ ነው! ልጃቸውን እኔ አለዉልሽ ብሎ እንደአባት ተጋፍጦ እንደመመከት እራስን በቤተሰብ ክብር ስም ከልሎ ከችግሩ ማምለት ምን የሚሉት ነገር ነው::
እሳቸውስ በድሮው አስተሳአሰብ ሄደው ስለሆነ ለመፍረድ ያስቸግራል! ግን ያንተ ይገርማል! በዚ ሁኔታ ላይ ላለች ልጅ የቤተሰብ ክብር ብሎ ጣጣ ምፍትሄዋ አይሆንም!!!