Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)
by yammi » Mon Oct 01, 2007 4:10 pm
ቤቲዬ.........
እንኳን አብሮ አደረሰን.........ለአንቺም እንዲሁ መልካም ዘመን ይሁንልሽ::
ለሁላችሁም መልካም ዘመን እመኛለሁ::
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Mon Oct 01, 2007 4:21 pm
.....................
ከምናብ ጦርሜዳ
ስሜት ተቀባብሎ
ሴትነት ሲከሸን
ወንድነት ሲፈተን
በምኞት ንቃቃት
በህልም አደባባይ
ወይ
............ጥሎ ሊፎክር
አሊያም
...........አፍሮ ሊያቀረቅር
በማይታይ ግዳይ
..
..
ልቤ ሽቅብ ስትጎን
በቃላት እሩምታ
ምርኮው ቢሰምርላት
ኮቴውን ልትገታ......
ጣቶቼ ካረንቋው
እግሮቼ ከድጡ
ገብተው ሲላቁጡ
ልከተለው ስድህ
መክኖ የቀረውን
በለስ ረምርሜ
ጆሮዬ አደመጠ
መጣሁ የቃጭል ድምፅ
ባለ መንፈቅ እድሜ::
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ጦምኔው » Fri Oct 05, 2007 2:39 pm
ግሩም ነው!!!!!!
:lol: Mucho Grasias :lol:
-
ጦምኔው
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1529
- Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
- Location: Right here
by yammi » Fri Oct 05, 2007 4:22 pm
ጦምን :D :D ምነው ጥፍት አልክ? ሰው ያስባል አይባልም :lol: :lol:
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by በጎሲያ » Fri Oct 05, 2007 6:43 pm
ያሚ እንኩዋን በሰላም ተመለስሽ::
-
በጎሲያ
- ጀማሪ ኮትኳች

-
- Posts: 93
- Joined: Mon Dec 29, 2003 8:48 pm
by yammi » Mon Nov 19, 2007 2:08 am
ምን ነበረበት
እማኞቼ እነዚያ ምሽቶች ናቸው
እነዚያ................
እንደ ህልም የታለሙ
እሳት በመሰለው ሰማይ
በተጋደምንበት
ግኡዝ መሬት
ፍቅራችንን የታደሙ
እማኞቼ እነዚያ ምሽቶች ናቸው
እነዚያ...........
ያጎጠጎጡ እንቡጦች
ያልጎመሩ ወይ ያልከሰሙ
እነሱ ናቸው እማኞቼ
እነሱ.............................
ብሰማ በወደደኩ ብዬ ስመኝ
አንደበትህ በፈቃድህ ቢፈታ
ከጣፈጡ ቃላቶችህ መሀል
ጆሮዬ ከሚጭር
እውነታ
የተበረዘም ቢሆን
የደፈረሰም ቢሆን
ይጠራልና የማታ ማታ
እማኞቼ እነዚያ ምሽቶች ናቸው
እነዚያ.................
19/11/2007
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ጦምኔው » Sat Jan 12, 2008 3:30 pm
.......????............
ምን ብለሻቸው ይሆን.....?
ላንቺ የታመኑ
እኛ የወለድናቸው
እነኛ ምሽቶች
እኚያ ልሳን ቢሶች
ላንቺ የወገኑ?
በኔ ክስ ሸንጎ
አላየንም.......
አልሰማንም ያሉ
ውስጤ አንቺን ሲራብሽ
ትዝታሽ ሲቀጣኝ
ተኝተው የዋሉ
የአፋፍ ላይ ጩኸቴን
የስቃይ ጥሪዬን
ቀብረው ያዳፈኑ
ምን አግኝተው ይሆን
ዛሬ ቀና ያሉ
አብረውሽ ተኝተው
መንቃትሽን ቢሰሙ
መስካሪሽ የሆኑ?
ጦምን ዘ አራዳ........01/12/08
-
ጦምኔው
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1529
- Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
- Location: Right here
by yammi » Thu Feb 07, 2008 1:56 am
ወይ ለሱ
ከሞኝ ሀገር
....ብልህ ውሎ
እጅ መንሻ
.....ዳስ አስጥሎ
እሸት ቆሎ
......አስፈልፍሎ
ሲሆንለት
......እየከካ
ሳይሆንለት
......እያቦካ
ሺ ደርድሮ
.......ከሞኝ ታዛ
እያበላ
.......ሹመት ገዛ::
ያሚ
Last edited by
yammi on Fri Feb 08, 2008 2:09 am, edited 1 time in total.
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ዋኖስ » Thu Feb 07, 2008 2:14 am
የዛሬዉን ልጂሽን ግን ሥም የማወጣለት እኔ ነኝ! ዘግይቼ በመድረሴ ግን ይቅርታ ምክንያቱም ከመገላገልሽ በፊት ነበር ና ስም የሚወጣዉ በርዝ-ሰርቲፊኬት ላይ የሚሰፍር ስም ሥለኆነ ቅቅ
ከሞኝ ታዛ!!
ከሞኝ ሀገር
....ብልህ ውሎ
እጅ መንሻ
.....ዳስ አስጥሎ
እሸት ቆሎ
......አስፈልፍሎ
ሲሆንለት
......እየከካ
ሳይሆንለት
......እያቦካ
ሺ ደርድሮ
.......ከሞኝ ታዛ
እያበላ
.......ሹመት ገዛ::
ያሚ
-
ዋኖስ
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1552
- Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
- Location: Mars
-
by yammi » Thu Feb 07, 2008 6:03 pm
:lol: :lol: :lol: አመሰግናለሁ ዋኖስ...እኔማ እንደምንም ተጣጥሬ ስም አውጥቼለት ነበር:: በቃ ያንተ ክርስትና ሲነሳ የክርስትና ስም ይሆነዋል :lol: :lol: :lol:
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ክርስትያን06 » Thu Feb 07, 2008 6:45 pm
እጹብ ድንቅ ነው ያሚቲ :lol:
ባለብዙ ፈርጅ ስንኝ::
-
ክርስትያን06
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 601
- Joined: Fri Sep 08, 2006 5:15 pm
by yammi » Thu Feb 07, 2008 10:45 pm
አመሰግናለሁ ክሪዬ......... ሽፍታው!! :D :D
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Thu Feb 07, 2008 10:50 pm
ስንብት
እንግዲህ..............
ሰማይም ሳሳ አሉ
ጨረቃም አረጀች
ምድርም አፈጀች
ነፍሴም..........ተ ሰ ላ ቸ ች::
ሂድልኝ አልልም
ናልኝም አይቃጣኝ
ግን ግን
ስቄ ባልሸኝህም
ዘለላም አይወጣኝ::
:( :( :( (ላስታውሰውም ሆነ ልረሳው ለማልሻው ውስጤ ለተቀበረው ትዝታዬ)
ያሚ 07/2/2008
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Sun Feb 10, 2008 5:37 pm
ገድል
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
Who is online
Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 2 guests