ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ሰዎች....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሰልማ1 » Tue Dec 11, 2007 2:32 am

ሰላም ሻይ ቦይ እንደምን አለህ በነገራችን ላይ i like your orginality, ለተወሰነ ጊዜ ሳነብህ ነበር እናም አንዳንዶቹ ታሪኮችህ ይገርሙኛል ያስቁኛልም ከሁሉም ያደንቅኩልህ ነገር ቢኖር ያልፍክበትን እና የኖርከውን ሂወት ለመደበቅ አለመሞክርህ .....
ይህን ያልኩህ ዝም ብየ አይደለም እዚህ አንድ የማውቀው የክፍለ ሀገር ልጅ አለ አዲስ አበባ ከ1 አመትም በላይም አልኖረም ግን ሁልጊዜ ለሰወች የአዲስ አበባ ልጅ እንደሆነ ሲናገር እሰማዋለሁ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ይረሳውና ለእኔም ይነገረኛል የእኛ ሰፈር ልጆች እኛ ሰፈር ይለኛል.... እኔ ደግሞ ምን እንደምለው ግራ ግብቲንግ ይለኛል ማለቴ ላሳፍረው እልና መልሽ እተወዋለሁ ....... ሻይ ቦይ አንተ ብትሆን ምን ትለው ነበር?

እሰከዛሬ ካየኌቸው ፊልሞች ሁሉ ወደድኩት god must be crazy
shy boy ይህንን ፊልም ያላየ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም ነበር ...
senisebiyorom
ሰልማ1
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1304
Joined: Sun Aug 05, 2007 2:11 am

Postby ShyBoy » Tue Dec 11, 2007 5:39 pm

ሀይ ሰልማ! እንዴት ነህ? አሁን አሁን ጠፍተሀል: ብዙ አላይህም:: ለነገሩ እኔም እዚህ የናፍቆት ቤት እና ዚዳን ቤት ነው እንጅ መጻፍ ትቻለሁ::

ሰልማ/ሀሪክ.......እንግዲህ ያልሆንሁትን መምሰል በጣም አልወድም:: እና አትደነቅ:: በቃ የገጠር ልጅ ነኝ! ምንም ላደርገው አልችልም:: እኔ ፈልጌው ሳይሆን እግዜር ያለው ነው:: የገጠር ልጅ በመሆኔ ምንም አላፍርም! በማንነቴ እኮራለሁ (በርግጥ የሚያኮራ ነገር የለም እኔ ፈልጌው አይደለምና.........ግን ጭራሽ አላፍርም):: የገጠር ልጅ ሁነው የአዲስ አበባ ነን በሚሉት ግን እጅግ አፍራለሁ!!!! አንተ ያልኸውን ልጅ ምን እንደምለው አላውቅም...........ግን ልክ ልኩን እነግረው ነበር! አንድ ቲያትር ነበረ "የእግዜር ጣት" የሚል::............."አሁን አንተ ፈልገህ ነው ደብረ ሲና የተወለድኸው?" የሚል አረፍተ ነገር ነበረው ቲያትሩ ውስጥ (እንግሊዘኛ ፊልም ባላይም አማርኛ ቲያትሮች አልፎ አልፎ አይ ነበር):: እና ሰው በማንነቱ ለምን ያፍራል? ሌሎችንስ ለምን በማንነታቸው ይንቃል? ፈልገው እኮ አላመጡትም!!!!!!!!!!!

በጣም የሚገርመኝ ደሞ.........እዛ ገጠር አሁንም ድረስ ሸማኔ: ፋቂ ምናምን እየተባለ ክፍፍል አለ:: ሁሌም እጨቃጨቅ ነበር:: በማህበራዊ ኑሮ ባይገለሉም ጋብቻ ግን ችግር አለ:: በ1997 (በኢትዮጵያ) የአጎቴ ልጅ ሲያገባ የሚያገባትን መፈለጉ መከራ ሁኖ ነበር:: የየከሌ ልጅ ጥሩ ናት ይባልና ከዛ አይ አያቷ ሸማኔ ነበር አሉ...........ምናም እየተባለ በቃ ስንት ሴቶች ተማረጡ መሰለህ:: እኔ ቅጥል ነው ያልሁት:: በጭራሽ ሊሰሙኝ አልቻሉም:: ይህ ነገር አሁንም ድረስ መኖሩ በጣም ያሳዝነኛል:: አልቻልሁም እንጅ ያጎቴ ልጅ ሲያገባ በጣም ጥሩ ናት የተባለችውን እንዲመርጥ ወትውቸ ነበር:: እሱ ለዛውም በጣም የተማረ እኮ ነው (ዶክተር):: ግን የሆነ ዩኒቨርሲቲ ሲያስተምር ያጫት (ቀለበት ያሰረላት) ልጅ ፒ.ኤች.ዲውን ሊሰራ ውጭ በሄደበት ስለከዳቺው ቤተሰብ የመረጣትን ነው እንጅ ካሁን በኋላ እኔ አልመርጥም አለ:: በነገርህ ላይ ያች እኔ ተወልጄ ያደግሁባት ትንሽየ የገጠር ከተማ ብዙ ልጆች አሳድጋ አስተምራ ለውጤት አብቅታለች::

እሰከዛሬ ካየኌቸው ፊልሞች ሁሉ ወደድኩት god must be crazy

shy boy ይህንን ፊልም ያላየ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም ነበር ...


እዚህ ላይ በጣም ተሳሳትህ! የየት ሀገር ንግስት ነበረች ከራባቸው ለምን ኬክ አይበሉም ያለችው? ገጠር ቲቪ ከየት ይመጣል ብለህ ነው? እናንተ የአዲስ አበባ ልጆች ከትምህርት ቤት ተመልሳችሁ ፊልም ላይ ስታፈጡ እኔ በግ እና ከብት እፈልግ ነበር:: :lol: :lol: ወይ ወፍጮ ቤት ሂድ ተብየ እላክ ነበር:: እና አንተ ፊልም እያየህ ስላደግህ ሌላው ኢትዮጵያዊ ፊልም ያያል ብለህ ካሰብህ በጣም ተሳስተሀል!

እኔ ለምሳሌ እንደዚህ የሚባል ፊልም መኖሩን ያወቅሁት ራሱ ባለፈው ሳምንት ፊልሙን ሳይ ነው:: እንኳን ፊልም ማየት ዘፈን እንኳን መስማት ከባድ እኮ ነው:: ለረጅም አመት እኛ ቤት እንኳን እንጠቀም የነበረው ኩራዝ ነው:: እኔ 7ኛ ክፍል ስደርስ ነው ማሾ እንኳን የተገዛው:: አሁን እንኳን ቤተሰቦቼ ጀነሬተር ገዝተው ቲቪ ማየት እንደጀመሩ ነግረውኛል:: ሰልማ: እስቲ ስንቱ ኢትዮጵያዊ ነው ስለዚህ ፊልም ቀርቶ ቲቪ የሚባል ነገር መኖሩን የሚያውቅ:: እውነት እልሀለሁ ሬዲዮ እንኳን የማያውቁ እጅግ ብዙ አሉ:: 85% የኢትዮጵያ ህዝብ እኮ ገጠር ነው ያለው:: እኔ የገጠር ከተማ ውስጥ አድጌ ካላወቅሁት ከኛ ሰፈር ወጣና: እጅግ ወጣ ያሉት እልም ያሉ ገጠሮች ውስጥ የሚኖሩት ሰዎች እንዴት ሊያዩት ይችላሉ? የኛዋ ትንሽዬ የገጠር ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ቲቪ ያየችው France 98 ያለም ዋንጫ ነው.......ለዛውም በጀነሬተር: ለንግድ:: ከዛ ሰውየው አከሰረኝ ብሎ ዘጋው:: አሁን ግን አንድ ሁለት ሰዎች እንዳስገቡ ሰምቻለሁ::

በል ሰላም ዋል!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ዞብል2 » Wed Dec 12, 2007 2:51 am

ጤናይስጥልኝ shyaboy ከናፍቆትና ከሌሎችም ጋር የምታደርገውን ለዛና ስነስራት ያለውን ምልልሶችህን ሁልጊዜ አነባለሁ በጣም ጥሩ አዝናኝና ሀገርንና ወገንን እንዳንረሳ ትምህርት የሚሰጥ ነው!!!!
ሰልማ1 የአዲስ አበባ ሰው አይደለም ክላሽኑን በትክሻው ከበሮውን በጉያው አድርጎ የዛሬ 17 ዓመት አዱ_ገነት የገባ የደደቢት ስልጡን ነው :P :lol: :lol:

shyaboy መቼም በዚህ አትቀየመኝም ምክንያቱም እሱ ራሱ የጓደኛውን የአዱ_ልጅ አለመሆን እንደ ቢግ ዲል ቆጥሮት ሲፅፍ በማየቴ ነው......ለኔ አገሩንና ወገኑን አይካድ እንጂ
ገጠር ተወለደ ከተማ ወገኔ ነው :D
አንድ ነገር አዱ_ገነትም የተቆረቆረችው ከገጠር በመጡ ሰዎች ነው :o :o

በል ሰላም ሁን

ዞብል ከፒያሳ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2368
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Postby ማካሮቭ » Wed Dec 12, 2007 4:38 am

ዞብል2 wrote: >>>>> አንድ ነገር አዱ_ገነትም የተቆረቆረችው ከገጠር በመጡ ሰዎች ነው :o :o

በል ሰላም ሁን

ዞብል ከፒያሳ


አዱ ገነት በናንተ በገጠሬዎቹ ተቆረቆረች ልትል ነው ??? :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: ሲሉ ሰምታ ..... አሉ ቅቅቅቅ
Wisdom is better than weapons of war: but one sinner destroyeth much good.
ማካሮቭ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 337
Joined: Tue Dec 07, 2004 7:20 am
Location: united states

Postby ShyBoy » Wed Dec 12, 2007 4:42 am

ዋው! ዞብልም ከፖለቲካ ወጦ እዚህ መጻፍ ጀመረ? ዞብል: እንዴት ነህ ባያሌው? ለሰጠኸኝ አስተያየት ከልብ አመሰግናለሁ!!!! እኔ ግን ሰው እንደዚህ ይገረማል ብየ አስቤው አላውቅም ነበር:: ናፍቆት ስለ "አትንኩት" ስታወራ የልጅነቴ ትዝ ብሎኝ ነው ሳላስበው ገጠር ካሳለፍሁት በጣም ትቂቱን ጻፍ ጻፍ ያደረግሁት:: ብዙ ከተማ ተወልደው ያደጉ ሰዎች ወደ ገጠር ሂዶ የማየት አጋጣሚ ስላልነበራቸው መሰለኝ ስለገጠሩ ሲወራ ኢምፕረስድ የሚሆኑት:: እንግዲህ ምናልባት እኔ እድለኛ ነኝ ማለት ነው ሁሉንም አይነት አኗኗር ማወቄ :lol: .........የ'በጣም ገጠሩን': የ'ትንሽዬ ገጠር ከተማውን': የ'ተለቅ ያለ ገጠር ከተማውን': የ'አዲስ አበባውን' እንዲሁም አሁን ደሞ የ'ውጭውን' ኑሮ ምን እንደሚመስል ከሞላ ጎደል አይቻለሁ!!!

ስለሀገሬ እያወራሁ እኮ ናፍቆቱ ባሰብኝ.........ኧረ ባካችሁ ከዚህ ድብርታም ሀገር ገላግሉኝ!

በሉ ሰላም እደሩ!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby አንበርብር » Mon Dec 17, 2007 9:17 am

ይህ አምድ ወደ ሁለተኛው ገፅ እንዲሄድ አልፈልግም!!!! ሁሌም የማነበው ነውና አንዳንዴ የሻይ ቦይን እና የናፍቆትን ፅሁፎች እደግማቸዋለሁ....... ሻይ ቦይ ብቻ ስለ ግልፅነትህ ስለማንነትህ ይህ ነህ ለማለት ቃላት የለኝም......... በእውነት ነው የምልህ አንዳንዴ ስለ አንተ እያነሳሁ ከጓደኞቸ ጋር እወያያለሁ..... ሻይ ቦይ እንዲህ አለ......... ሻይ ቦይ እንዲህ አይነት ሰው ነው እያልኩ!!! ልክ በአካል እንደማውቅህ....... እና ከልብ የምመኝልህ ሀሳብህ ተሳክቶልህ ወደ ምትናፍቃት እና ወደ ምትወዳት ሀገር በሰላም እንድትመለስ ነው........ መልካም ቀን/አዳር
Image
አንበርብር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Apr 09, 2005 12:01 am
Location: everywhere

Postby ናፍቆት » Tue Dec 18, 2007 7:15 am

'Sex is a Gift' የተሰኘ መጽሀፍ በቅርቡ ተመርቋል እዚህ:: ጸሀፊው ጀንበሩ ይባላል (ጀንበሩ ሀይሌ ካልተሳሳትኩ) እና ምረቃው ላይ የተከበሩ ሎሬት አፈዎርቅ ተክሌ ነበሩ .... እና አስተያየታቸውን ሰጡና (መጽሀፉ አስተማሪነት አለው ... እና ባማርኛ ቢተረጎም የበለጠ ብዙ ኢትዮጵያዊ ሊያነበው ይችላል ... ምናምን ነገር ... ) ከዛ አንድ ትዝታቸውን ጣል አደረጉ .... ምናሉ ...... ድሮ ተማሪ እያሉ የዳቪንቺን የሆነ ስእል ይስላሉ ... እርቃን ነገር ነው መሰለኝ ... እና አስተማሪው አይቶ ይቀጣቸዋል ...... ከዛ ለንደን ሄደው ስእል ሲማሩ ሴት ከነነፍስዋ ፊት ለፊታቸው እርቃንዋን ቁጭ አርገው መሳል ነበረባቸው .... መጀመሪያ ፈራ ተባ እያሉ ይጀምሩና ከዛ .... በቃ ይለምዳሉ ምናምን .... እና ይህንንስ ላገሬ ልጅ ላሳየው ብለው በወቅቱ ለንደን ትምህርት ላይ የነበሩትን ደራሲ መንግስቱ ለማን ይጠሯቸዋል ..... እና መንግስቱ ይመጡና ሲያዩ .... ኢትዮጵያዊ አስተዳደጋቸው ... ባህል ወግ አክባሪነታቸው ...... እርቃኑን ያለ ሰው በሙሉ አይናቸው አላሳይ ብሏቸው እግሬ አውጪኝ ብለው እንደሸሹ ..... ታዳሚውን አጫወቱ:: አይጥሙም?
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Tue Dec 18, 2007 7:19 am

ዲናው መንግስቱ የተባለ ካናዳ ነዋሪ የሆነ ሀበሻ ደሞ 'The Beautiful Thing that Heaven Bears' የተሰኘ መጽሀፍ እንዳወጣስ ሰማህ? መጽሀፉ በያገሩ ተበትነው ስላሉት አፍሪካውያን ስደተኞች አስከፊ የኑሮ ገጽታ እና .... በተለይ ደሞ አሜሪካን አገር ስላሉ ኢትዮጵያዊ ስደተኞች ኑሬ በዝርዝር እንደጻፈ ሰምቻለሁ:: I'd love to read it.
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Tue Dec 18, 2007 7:31 am

ደንበል ሲቲ ሴንተር በሀራጅ ሊሸጥ እንደሆነ መቼም ሳትሰማ አትቀርም ..... እነዛ ሁሉ ቺኮች በደንብ ሱቆቹን በደንብ የነገዱበት አልመሰለኝም ...... I don't know .....

እና ከሱ ጋር በተያያዘ እነዚህ በከተማው ሀብታም ሽማግሌ ስለተያዙ ቺኮች ምናምን .... እንዲሁ chat ስናደርግ ... እዚህ አንድ አሁን በከተማው የበዛች መኪና አለች ..... Atoz የምትባል (Korean made , if I am not mistaken) ... እና ከተማው ውስጥ መኪናዋ ትታማለች በጣም ..... እነዛ ወንዶች ለወዳጆቻቸው ልጃገረዶች የሚሰጧቸው ናት በመባል ..... እንዲያውም Atoz መባልዋ ቀርቶ 'Atoms' ተብላልሀለች .... ዋጋዋን ማወቅ ከፈለክ .... ከ65 እስከ 70 ሺህ ብር ነች ..... እና በፊት ሴቶች ነበሩ በብዛት የሚይዟቸው ... አሁን አሁን ግን ወንዶች ጎረምሶች ይይዟቸው ጀምሯል .... ሴቶቹ ደሞ ወስደው ለሚወዷቸው ወንዶች እየሰጡ ምናምን ነገር .... እና ይቺን መኪና የሚይዙ ወንዶች ምን እንደተባሉ ለምን አልንገርህም? 'አስመላሽ' ..... ደስ አይልም? እኔ ሲነገረኝ እየው ፈረስኩኝ ነው የምልህ .....
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Tue Dec 18, 2007 7:50 am

ShyBoy - The gods must be crazyህን ሳነበው.... አልደብቅህም ... እየው በሳቅ ቆሰልኩኝ ነው የምልህ .... ለምን እንደሆነ አላውቅልህም:: ከምር ...... 'You yourself must be crazy' ነው ያልኩህ ...... ግን ልክ ነው .... It's a funny and very nice film.

ፊልም እወዳለሁ .... ጊዜ ግን ይፈልጋል ... እንዲያም ሆኖ በተቻለኝ መጠን ጊዜዬን አብቃቅቼ ለማየት እሞክራለሁ .... '40 ብር አልበዛም ወይ? ' No, No , No. አልበዛም:: ይሄ የበሰበሰ ፊልማቸውን በ 5 ብር እዛ አምባሳደር ከማየት ይሻለኛል ...... ለማንም ይሻላል .... ፊልም እኮ የሆነ 'dynamic' ነገር ነው በጊዜው ካላየህው ጣእሙ ሊቀንስ ይችላል .... ምክንያቱም ሁሌም የተሻሉ የፊልም ቴክኒኮች እና የአክተሮች better performance የሚታይበት ስለሆነ ..... ይመስለኛል እንግዲህ ....

ለዛሬው ምን ልጋብዝህ ..... እ...... በሀሳቤ የመጡልኝ ሁለት ፊልሞችን .... 'Schindler's List' ትንሽ ቆየት ያለ ግን በጣም የወደድኩት ፊልም ነው:: ሌላ ደሞ ቅብጠት አይነት ነገር ትወዳለህ? ...... እስቲ 'Unfaithful' የተሰኘውን ፊልም ተጋበዝልኝማ .... በጣም በጣም የወደድኩት ፊልም ነው:: ቅብጠት ነገር ደስ ይለኛል:: አንዳንዴ:: ሰዎች ወሰን ሲያጡ ደስ አይልህም ... በቃ ዝም ብለው ወደላይና ወደሩቅ ብቻ ሲያስቡ ..... ካለምንም ወሰን? እንደዛ አይነት ከሆንክ ደሞ 'Aviator' ን ጋብዤሀለሁ - ዲካፕሪዮ አሪፍ አድርጎ የሰራው ፊልም ነው:: ከሶስቱ አንዱን እንደምትወድ እገምታለሁ::


***
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ዩፎ » Tue Dec 18, 2007 7:00 pm

ናፍቆት...ለምንድ ነው ብዙ ጊዜ linear equations የምንጠቀመው (although most processes are really non-linear). ብዙዎቻችን የምንለው 'በጣም ቀላል ስለሆነ' ነው:: አንዱዋ ፌሚኒስት ፈረንሳዊት ግን የተለየ ምክንያት አላት (መጽሀፉዋ ውስጥ እንደገለጠችው):: እሱዋ የምትሰጠው ምክንያት የሚከተለው ነው "ብዙ ማቲማቲሺያንስ ወንዶች ናቸው:: ወንዶች ደግሞ ከ ብልታቸው ጋር obsessed ናቸው:: ብልታቸው linear ስለሆነ ነው linear equations ተወዳጅ ሊሆን የበቃው":: What do you think?
ዩፎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 132
Joined: Sat Dec 25, 2004 10:29 pm
Location: united states

Postby ShyBoy » Wed Dec 19, 2007 8:07 pm

አንበርብር wrote:ይህ አምድ ወደ ሁለተኛው ገፅ እንዲሄድ አልፈልግም!!!! ሁሌም የማነበው ነውና አንዳንዴ የሻይ ቦይን እና የናፍቆትን ፅሁፎች እደግማቸዋለሁ....... ሻይ ቦይ ብቻ ስለ ግልፅነትህ ስለማንነትህ ይህ ነህ ለማለት ቃላት የለኝም......... በእውነት ነው የምልህ አንዳንዴ ስለ አንተ እያነሳሁ ከጓደኞቸ ጋር እወያያለሁ..... ሻይ ቦይ እንዲህ አለ......... ሻይ ቦይ እንዲህ አይነት ሰው ነው እያልኩ!!! ልክ በአካል እንደማውቅህ....... እና ከልብ የምመኝልህ ሀሳብህ ተሳክቶልህ ወደ ምትናፍቃት እና ወደ ምትወዳት ሀገር በሰላም እንድትመለስ ነው........ መልካም ቀን/አዳር


አምቤው የገነርሱ: እንደት ነህ ባያሌው? ለአድናቆትህ ከልብ አመሰግናለሁ!!! ግን ለምን እንደተደነቅህ ገርሞኛል! ምንም የስነ-ጽሁፍ ችሎታ የለኝም:: ቁምነገርም ሆነ ቀልድ አልችልበትም:: ለዛ የለሽ ነገር ስለሆነ የምጽፈው ሰው ወዶት ያነበዋል ብየ አላስብም ነበር:: እንዲያው ናፍቆት የምትጽፈው ነገር በጣም እየሳበኝ አላስችል ብሎኝ ነው እንጅ ዝም ብየ የምቸከችከው::

አምቤክስ: መቸ ነው አንተ እና እኔ ኢምሬትስ እና ስታድ ደ ፍራንስ ሂደን ኳስ የምናየው? :lol: :lol: እስቲ አስብበት.........
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ShyBoy » Wed Dec 19, 2007 8:28 pm

ናፍቆት: እንደምን ሰነበትሽ? እኔ እግዚአብሄር ይመስገን ካንች ናፍቆት በስተቀር በጣም ደህና ነኝ!

የምር አሁንስ አበዛሽው! ለምን ሳምንት ቆየሽ ስትባይ ሁለት ሳምንት ጠጥተሽ ትመጫለሽ? ይሄንን አመልሽን ካላስተካከልሽ ዘብጥያ መውረድሽን እወቂ! :lol:

ከነገርሽኝ ያንቺ favorite ፊልሞች ውስጥ ባጋጣሚ Unfaithful የሚለውን አዲስ አበባ እያለሁ አምባሳደር ቲያትር ቤት አይቸዋለሁ (25 አካባቢ ፊልሞች አይቻለሁ አላልሁሽም? ከነዛ ውስጥ አንዱ እሱ ነው):: ሌሎች ሁለቱን ግን ያሁ ሙቪ ውስጥ ገብቸ ፖስተራቸውን ሳየው የሆኑ ጨለማ ፊቶች ናቸው (ይቅርታ አድርጊልኝና ጭልምልም ያለ ፖስተር አይመቸኝም):: ቢሆንም ግን ፈልጌ አያቸዋለሁ::

እዛ ያሁ ሞቪ ስገባ እግር መንገዴን ያሁ ሚውዚክም ጎራ ብየ ነበር:: ከዛ አምና American Idol ሳይ በጣም የወደድኋትን እና ስደግፋት የነበረችውን (በኋላም ያሸነፈችውን) Jordin Sparks ማፈላለግ ጀመርሁ (አዲስ አልበም እንዳወጣች ሰምቸ ነበር):: ዘፈኖችን መስማት ባልችልም ግን የአንደኛው ዘፈን ርዕስ በጣም ሳበኝና ጠቅ ሳደርገው ያች የምወዳት ጆርዲን እኔን በእግር በፈረስ እያፈላለገች እንደሆነ ተረዳሁ! :lol: :lol: :lol: ካላመንሽኝ እዚህ ግቢና አንብቢው......... (ኮፒ አድርጌ ላመጣው ስል እምቢ አለኝ)
http://music.yahoo.com/Jordin-Sparks/Sh ... s/51846392

የእንግሊዝኛ ዘፈን ገዝቸ አላውቅም ነበር እንግዲህ የጆርዲንን ሲዲ ግን መግዛት ግድ ሳይለኝ ላይቀር ነው (የምትለውን ባልሰማውም ዝም ብየ አዳምጣታለሁ):: እስቲ ተመልከቻት ልጅቷ እንዴት እንደምታምር!

Image

እንግዲህ አንችን ሽማግሌ አድርጌ ልልክሽ ስለምችል ተዘጋጅተሽ ጠብቂ.... :lol:

በይ ሰላም ሁኚ!!!!!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ዩፎ » Mon Dec 24, 2007 2:23 am

ብዙ ጊዜ Linear Equationsን የምንጠቀመው ለምንድ ነው (though most processes are non-linear)? ብዙዎቻችን simplicity ነው መልሳችን አይደል?! አንዱዋ ፈረንሳዊት ፌሚኒስት (በመጽሀፉዋ) ግን የተለየ ምክንያት ትሰጣለች:: እሱዋ የምትለው ይህን ነው 'most mathematicians are males. Males are obsessed with their genitals, and hence with linearity'. ድጋፍ/ተቃውሞ?
ዩፎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 132
Joined: Sat Dec 25, 2004 10:29 pm
Location: united states

Postby ናፍቆት » Wed Dec 26, 2007 8:02 am

ShyBoy - ውይ ልጅትዋስ ታምራለች:: ከምር:: እያስፈለገችኝ ነው ያልከኝ? እንድታገኝህ እመኛለሁ::

የንግሊዝኛ ሙዚቃ ሲዲ መግዛት መጀመርህ ጥሩ ነገር ነው:: እስካሁንም ተጎድተሀል ባይ ነኝ:: ይሄ ጥቁሮቹ የሚቀባጥሩትን እንኳን (በጣም እጠላዋለሁ ያልከውን) እኔ ሁሉንም ባይሆን እንኳን አንዳንድ የምወዳቸው አሉ::

ልንገርህማ - እዚህ አገር ያሉ የወንድ ግብረሰዶማውያን የሆነ ነገር አርቅቀው ለፓርላማ አቀረቡ ነው ምናምን ሰማህ? አይገርምህም? የሀይማኖት ሰዎች ይህንን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርጉ ታስቦ ነበር ... ነገር ግን መንግስት በቂ የፖሊስ ሀይል አሁን የለንም ለሰልፉ የሚሆን ነው ምናምን ብሎ ከለከለ ምናምን ነገር ...... 'Globalization' ሲባል በኢኮኖሚ ብቻ እንዳልሆነ ነው መቼም ...... ብዙ ነገር ነው አብረህ የምታግበሰብሰው .... It consists of everything like fashion, culture, values, ...... ምናምን ..... እርግጠኛ ነኝ እዚህ ውስጥ የዲያስፖራው involvement ሊኖር እንደሚችል ...... People with good financial status can bring big influence on such things, I believe

እኔ አሁን ልጠይቅህ የፈለኩት - የዚህ አገሩን እንኳን ወደፊት እኔው እሰማዋለሁ ... ግን አሁን አንተ ባለህበት አገር the gays ለመሰሎቻቸው ማቆላመጫ የሚያወጡት ዘፈን አለ? ገጥሞህ ያውቃል? እ.... like ለሴት ዳሌዋ - ሽንጥዋ - ጡትዋ - ባትዋ - ቅብርጥስ እንደሚባለው ወንድ ለወንድ የዘፈነውን አንድ phrase ጣል ብታደርግልኝ ደስ ይለኛል - ካለ ማለቴ ነው ....... I'm just wondering.

ስለፊልሞቹ ... ጨለምለም አሉብህ? I don't know .... እንደዛ አይነት 'personalities' ስለምወድ ነው .... ይሄ ለ 'purpose' የሚኖር ሰው ደስ ይለኛል .... ይሄ ዝም ብሎ እጅ እግር ኖሮት ሰው ሆነ ተፈጥሮ ዝም ብሎ ኑሮን የሚኖረው 'ordinary people' ብዙም እንትን አይለኝምና ነው :: አንዳንዱ ተምሮ ስራ ይዞ ቤተሰብ እየረዳ ወይም መስርቶ መኖር በቃ ኑሮ ነው ለሱ:: ... ከዛ በቃ መኖር - መኖር ... መኖር .... በቃ ዝም ብሎ መኖር:: ድክ...ም አይልም?

***
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest