ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ሰዎች....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ለማርስዬ ብቻ !!!!

Postby Eritrossse » Sun May 02, 2004 2:39 am

ማርስ
አንቺን መከታተል እወዳልሁ እዚህ ሰላለሽ ነው የገባሁት እንጂ የማቀው ምንም ነገር ኖሮ አይደልም ማለትም ያቅራቢዋ መልዕክት አይገባኝም :: Compalin or Complex የትኛው በሽታ እንደተጣናወታቸው በቅርበት ስለማላቅ ነው ይቅርታ :: ብቻ ግን አንድ ነገር አንቢቤ በሳቅ ልቤን ውልቅ ስላረግሽው ልጠይቅሽ ነው አገባቤ

የውልሽ ላቅረቢዋ ምን ነበር ያልሻት " ካንቺ ጋ የዋለ አይደብረውም ............" ነበር ያልሽው ስትፎግሪ ነው አይደል ግን ???
በናትሽ ወይም ስሞትልሽ ንግሪኝ ለኔ ብቻ ቅቅቅቅ?

እኔ ልንገርሽ አይደል ከሷ ጋ ብውል በኮምፕሌኗ ሆዴ ተወጥሮ የምመለሰ ነው የሚመሰለኝ:: ከዛ በቃ አለ አይደል ቀን ከሌሊት ኮምፕሌን ሰሸና መዋል ....እስኪ ይታይሽ ከዚች ሰው ጋ ወጥቼ ከዛም እራት ልጋብዝ ተግባብተን >>>>ባይነ ህሊናሽ ሳይው ....እንበለው ለራት እኔ ቤት ...አቤት ታይኝ :; ቀኑን ሙሉ የተላያየ ምግብ ...መጽሀፍ አገላብጬ ሰርቼ...ጭንቅ ብሎኝ ...ደንገዝገዝ ና ሰፋ ካለው የመመገቢያ ሳሎን አንድ ጠርቤዛና ሁለት ወንድበሮች ከማህልሉ ላይ በውበት አስግጬ ....... ቤቱን ደብዘዝ ባለ ብርሀን ...... ጠርቤዛው ማሀል ላይ ካንድል ...አብርቼ .... ላቤን ያፈሰስኩበት ክሽን ያሉት ምግቦቼ....ልቤ ውልቅ ያሉበትን የመመገቢያ ሳሎኑን ይሳጌጥኩበትን ጉልበቴ......አትርሽው......የማድቤት ሽርጤን እንዳገለደምኩ ...ቱር ቱር ቱር ብዬ አስተናግጄ ... ከዛም ....ልሰለስ ያለውን ሙዚቃ... አትርሽ አሁኑም ሰንት ጎደኞችን እንዲሁም እናቴን አማክሬ ነው ሙዚቃው የሚመረጠው ....... አብረን ተቀምጠን ሰንመገብ ...ድካሜን ትታ ጣራን ግድግዳውን ...የፍቅር ትረካዬን ማዳመጥ ትታ... አይ!! ምግብ ሰርተህ ሞተሀል ...እያለች ስታስብ ...ቀጥላም ..እኔ ውጭ በሞኖሬ አቃቂር ስታወጣ ..... አንተን ብሎ ፈረንጂ!! ስትለኝ ታየኝ :: እንደዚህ አይንቷ ድክም ነው ይምታደርገው ...አትመቸኝም...ልቧን ከኔ አርቃ አንገቷን 180 ዲግሪ እያዞረች ቤቱን አቃቂር ሰታወጣለት ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ ይታይሽ እኔ ልቤ ቅልጥ .....ጉልበቴ ፍስስስስ ሲል...አላሳዝንም ?? ያስራሁለት ሳአት ይጉልበት ስራዬ... የ 8 ሰዐት ያይምሮ ቅንብሬ ....እረ አታንሽው...ብቻ አላሳዝንም ከዚች አይነቷ ጋ ብውል?? ::...... አንቺም እኮ አብረሻት ብትሆኝም ሰውን ሰውን እያየች እኮ አታናግርሽም......እረ አንቺንም አቃቂር ወጦልሽ ቆየት ብለሽም .....በ ኮምፕሌን ወይም ኮፕሌክስ ይክብር ዲግሪ ይዘሽ ትወጫለሽ ቅቅቅቅ ከዛም ሰው ለፍቶ ባጌጠበት አንቺ ናላሽን አዙረሽ ..... የአእምሮ ካንሰር በናጻ ፈርመሽ ትቀበያለሽ ማለት ነው :; ሰው እንደፈለገው ይኑር!!! ማርሲ
ከምር ነው የምልሽ ማርሲ እኔ ራሴን አሞኝ ሲያጥወለውለኝ ታዬኝ ባንቺ ፈንታ ከሷ ጋ ሁኘ...... ለምን ትይ ይሆናል ሁሉን ጥሩ ነገር ለፈረንጂ ማን ሰጠው?? አበሻ ጥሩ አይፈልግም?? አበሻ ሴቶቻችን ጥሩ ነገር ዺዘርቭ አያረጉም?? ሮማንቲክ የሆነ ነገር??

"ኤዲያ ሰንት አይነት ሰው አለ አድሀሪ ሁላ አቦ!!" አሉ እማታገኝ ቅቅቅ

እማታገኝ "አቦ" ምን እንደሆነ አያቁትም....እንዴው ሲባል ሰምተው ነው ::

ኤሮ ነኝ
Eritrossse
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 14
Joined: Wed Sep 17, 2003 12:55 am

Postby Eritrossse » Sun May 02, 2004 2:52 am

-------
Last edited by Eritrossse on Thu Jan 14, 2010 4:24 pm, edited 2 times in total.
Eritrossse
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 14
Joined: Wed Sep 17, 2003 12:55 am

ኤሩ መንገድ ተሳስተሃል

Postby ትምህርት » Sun May 02, 2004 8:54 am

ኤሩ መለእክትህ ቦታ የሳተ ይመስለኛል:: የምንፅፍበትን መድረክ ልብ እንበል:: የዚህ ዓይነት ፅሁፍ ቦትው እዚህ መድረክ አይመስለኝም::

ልብ ይስጠን::
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

ለትምህረት ብቻ

Postby Eritrossse » Sun May 02, 2004 4:58 pm

ከላይ አንብበኽዋል ?? "ለማርሲ ብቻ" ነው የሚለው እሺ??

ኤሩ
Eritrossse
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 14
Joined: Wed Sep 17, 2003 12:55 am

ለኤሪው ብቻ

Postby Joe » Mon May 03, 2004 9:00 am

ኤሪው ምን ላርግህ!! እዚህ መድረክ ሁለተኛ አልመለስም ብየ ነበር:: ባንተ ንግግር ምን ያህል እንደተደሰትኩ ሳልገልጽልህ ብቀር አንተ ባታየኝ አምላክህ ያየኛል:: የኮምፕሌንና ኮምፕሌክስ ዲግሪ ነው ያልከው? ቅቅቅቅቅ:: እነዚህን ሁለት ቃሎች አንድ ላይ ጨምቀን አንድ ቃል ብንፈጥርስ... እኔ ሀሳብ ልስጥ:: ካልተስማማህ አንተ ትቀይረዋለህ:: እኔ ያሰብኩት የሁለቱንም ቃሎች የመጀመሪያዎቹን የተወሰኑ ፊደሎች ወስደን -ሎጂ መጨመር ነው: ኮምፕሌሎጂ ይሆናል:: በዚህ ፊልድ የመጀመሪያዋ ተመራቂ ማርስ ትሆናለች:: አስተማሪዎች ሞልተውናል, ሳይማሩ የሚያውቁ, ሲወለዱ ኮምፕሌሎጂስት ሆነው የተወለዱ ምርጥ የፊልዱ ሰዎች.... ቅቅቅቅ (ስቀልድ ነው)

ትምህርት አልገባኝም:: ያንተ እህት እንደዚህ አረገችና ሁሉም እንደሷ ያረጋል ማለትህ ነው? ከሆነ ተሳስተሀል:: ያንተ እህት ውጭ ከሚኖረው 1 ሚሊዮን አበሻ አንዷ ናት:: እናም ኮመን ሴንስ ይነግርሀል አንድ ሰው 1 ሚሊዮንን አይወክልም::

በሉ አደከምከን እንዳትሉኝ ይብቃኝ ቅቅቅቅቅ
ቸር ይግጠመን
Joe
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 12
Joined: Tue Sep 09, 2003 11:27 am
Location: united states

ለ eritrosse ስና ለ joe ብቻ

Postby ማርስ » Mon May 03, 2004 5:28 pm

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ቆይ ግን አንተ እኔን ከኌላ መከተል አትተወውም? እማ ታገኝ እንዲህ ሲገጥማቸውም ምንም ብለው አያውቁም? ማለቴ እሳቸው ለሁሉ መልስ አላቸው ብየ ነው::

ቆይ ግን በነገራችን ላይ እማ ታገኝ ምንህ ናቸው? ያልጠረጠረ ተመነጠረ ነው ታሪኩ እኔም ጠርጥሬአለው:: ቅቅቅቅቅቅቅ ይኼ ተዳብሎ ንሮ እንዳው!! መጨረሻው የት እንደሚጥል አይታወቅም::

አሁን ስለ እማ ታገኝ ሳወራ የአርእስቱን ፈር እንዳልስት ተሎ ወደ እዚያ እመለሳለው::

ኤሩየ አንድ ነገር አለ ያልተረዳኸው--እሱም ናፍቆት የጻፈችው ጽሁፍ እኔ ያደነኩበት የራሴ የሆነ መስፈርት አለው:: 1ኛ ነገር ናፍቆት ስትጽፍ የአጻጻፍዋ ዘይቤ ይመቸኛል:: ይኼን ስልህ አንዳንድ ቀን እየገባች ጣል የምታደርጋቸው መልሶች ያስቁኛል ከዛ አልፈው ተርፈውም ያዝናኑኛል:: ልጅቷን ሳስባት ቀልደኛ እና በተመሳሳይ ሰአትም አስተዋይ ትመስለኛለች::

2ኛ ነገር ወደዚ አሁን በጻፈቸው መድረክ ብንመለከት አንተ እንዳልከው ነገሩ ሀሜት ነው ብቻ ብየ በደፈናው አልኮንናትም:: ከዚ ጽሑፍ ባሻገር ያየሁት ነገር አለ:: እሱም የልጅቷን የስነጽሁፍ ችሎታዋ ማለት የሁኔታዎችን ድርጊት እንዴት አድርጋ በተዋበ መልክ አቀነባብራ በጽሁፍ መልክ ልታቀርበው በመቻልዋ እንዳደንቃት አድርጎኛል::

3ኛ ደግሞ እሷ በጽሁፏ ያለችው ነገር ሁሉ እውነት ሊኖረው ይችላል ላይኖረውም ይችላል ግን መገንዘብ ያለብህ ነገር አንድ ነገር ቀስቃሽ አነሳሽ ከሌለው እንደማይሆን ነው:: ናፍቆት ደግሞ ከ አንድ ጭብጥ ያለው ነገር ሳትነሳ እንደዛ ብላ ለመጻፍ የምትነሳሳ አይመስለኝም::

4ኛ ምንም እንዲህ እንደ ናፍቆት ያሰፈረችው የተጋነነ ነገር አይሁን እንጂ በዓይኔ ያየሁትም ብዙ ነገር አለ:: ሁሉ አይሁን እንጂ አንዳንድ ሀበሾች አገር ቤት ሄደው እንዴት እንደሚሆኑ አይቻለው:: ራሳቸውን ትተው የሌላውን ያልሆኑትን ባሕሪያት የሚላበሱ ጥቂቶች አይደሉም::

ለፈረንጅ ብቻ ማን ጥሩ ነገር ሰጠው ላልከውና ሀበሻ ጥሩ ነገር አያስፈልገውም ወይ ላልከው ነገር ካንተ ጋር እስማማለው:: እንኳን ለሰው ልጅ ይቅርና ለእንስሳም ጥሩ ነገር ያስፈልገዋል:: ግን አንድ ነገር ጥሩና መልካም የሚሆነው በቦታውና በግዜው እንዲሁም በወጉና በባህሉ ሲሆን ነው:: አንዳንዱ ሀበሻ እኔም እንደፈረንጅ ልሁን ብሎ ቢነሳ አያምርበትም ምክንያቱም ባህሉ አይደለምና:: እንዴት ነው በ አሳማ አፍንጫ ቀለበት እንደማንጠልጠል አይነት ነው የሚሆንበት:: በዚ አትስማማም??????

ደግሞ ያቺ የወይኗ ነገር ኤሩየ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ እኔ ንክች አላደርጋትም:: ላንተ አስቀምጣታለው:: እኔ የምወዳትን ታውቃታለህ::

እምጷ ሳምምምምምምምምምምምም


ለ ጆ

ቆይ አንተ ግን እኔ በዛ ምን ነበር ያልከው ስሙም ጠፋብኝ ቅቅቅቅቅቅ ከተመረኩ ዘመን አለፈኝ እኮ:: ምነው ያኔ ለምርቃቱ በተደረገው ድግስ ጠርቸህ መጥተህ ሆድህ እስኪገለበጥ በልተህ አልነበር?!:: አይ ያንተ ነገር መቸስ የሆድ ነገር አያስችልህ አሁንም ደግመህ ልታስመርቀኝ የከጀለህ ለሆድህ አይደለ:: ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

እምጷ ሳምምምምምምምምምም ጣትህ ላይ
I dreamed of some one like you
you see too marvelous for it to be true.
-
-
Image
ማርስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 44
Joined: Sat Jan 03, 2004 12:54 am

ለጆዬ ብቻ ::

Postby Eritrossse » Mon May 03, 2004 9:13 pm

ሀይ ጆ ወንድሜ ባክህ አንተ እኮ የገባህ ነህ ከምር አስተሳስሰቦችህ ጥርት ያሉ አድር ባይ አይነቶች ስላልሆኑ እወዳቸዋለሁ ከምሬ ነው :; ግን ላንተ ጠላት እንደሚያበዙብህ አልጠራጠርም::ቅቅቅቅ ሰው እንዳይሰማ::

ለማንኛውም " ካንፕሌሎጂ" አልከኝ በጣም ነው የተሰማምሁበት ተመችቶኛል ሰሙ ቅቅ :: አሁን የቀረህ ቢኖር ምን መሰለህ ቅቅቅ ቦታ ካምፓሱ የት ይሁን ነው የኔ ጥያቄ ??.....ከተሰማማህ መሀል አራዳ ፒያሳ አካባቢ ወይም በዛ "በደምብል" የገባይ አዳርሽ አካባቢ ብናደርገው አይመች የመስልሀል?? .....በሀሳብ ደረጃ ነው ከተሰማማህ ጥሩ ካልሆነ እስኪ ሌላ ቦታ አፈላልግ ቅቅቅቅ ለብሮፌሰሮቹ የተሰማማ ቦታ

መልካም ቀን ጆዬ!!! በደምብ ጥና እንዲሁ አይገባም ቢያንስ ጥሩ GPA ሳያስፈልግህ አይቀርም ቅቅቅ:: ዋ ማውደልደል ይቅርብህ ቅቅ

"ኤዲያ!! እንዲህም አይነቱም ጀግና ይወለዳል. እናቱ ትውለድ " አሉ እማታገኝ

12 ልጆች ነበር እማታገኝ የነበሯቸው ቅቅቅ አንዱ ልጃቸው በሬ ሰርቆ ሰላእመጣ ነበር ጆ እንዲ ያሉት :: አንተን ቢያዩ ምን ሊሉ ነበር??

ወንድምህ

ኤሩ ነኝ
Eritrossse
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 14
Joined: Wed Sep 17, 2003 12:55 am

ማርስዬ ብቻ ( የመጨረሽ )

Postby Eritrossse » Mon May 03, 2004 9:26 pm

-------
Last edited by Eritrossse on Thu Jan 14, 2010 4:27 pm, edited 1 time in total.
Eritrossse
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 14
Joined: Wed Sep 17, 2003 12:55 am

ናፍቆትዬ የከፈተችውን ቦታ ላይ አትሟዘዙብን

Postby ረች » Mon May 03, 2004 9:40 pm

እዚህ አርእስት ስር ለማየት የምንመጣው የናፍቆትዬን ውብ ጽሁፍ ለማንበብ ነው::

አሩ (Eritrossse) አዲስ አርእስት ከፍተህ ተወያይ:: ስምህም ለፍቅር አይመችም: ቀይረው!

ማርስ: ጥሩ ሰው አልነበረሽ? ለማርስ ብቻ እያለ የሚጽፈውን በprivate message እንዲያደርግ ምከሪው
'perpetual optimism is a force multiplier' - C. Powel
ረች
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 2
Joined: Fri Mar 12, 2004 12:08 pm

ረች

Postby Eritrossse » Tue May 04, 2004 12:39 am

ኤውውውውውውውውው ኢኺኺኺ !! ካካ ::
Last edited by Eritrossse on Thu Jan 14, 2010 4:28 pm, edited 1 time in total.
Eritrossse
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 14
Joined: Wed Sep 17, 2003 12:55 am

Postby አዲስ » Tue May 04, 2004 1:25 am

ኤርትሮስ.....እባክህ.........እባክህ የእርጎ....ምናምን አትሁን የፍቅር መድረክ ሌላ ቦታ ነው :!: :!:
አዲስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 15
Joined: Fri Aug 22, 2003 12:08 am

Postby ናፍቆት » Tue May 04, 2004 7:44 am

በውሻዋ barbeque ዜና ሞራላችሁ የተነካችባችሁ ሰዎች ያላችሁ ትመስላላችሁ:: ካላችሁ እኔ ልላችሁ የምችለው ነገር ቢኖር 'አዝናለሁ' ብቻ ነው::

እ........... በተረፈ............ አንዱ cheap ሆቴል kitchen ውስጥም ስሩ - የፈረስም ጥርስ እጠቡ - አንድዋን የፈረንጅ አሮጊትም አዝናኑ - ወይም ደሞ ውሻም አንፍሱ .... whatever! ምንም አርጉ - ብቻ as long as u somehow get the money and bring it here, እናንተም ያንን ወይም ደሞ ያንን መሰል barbeque ለማድረግ የምትችሉ ይመስለኛል:: እስከዚህ bother ካረጋችሁ ማለት ነው:: It seems it doesn't matter how you get the money, what matters is 'ይዞ መገኘት' እና እስከዚህ ከባረቀባችሁ ከባድ ነገር አይደለም ለማለት ያህል ነው:: እ....... የመሰለኝን ነው::
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby GIZO » Tue May 04, 2004 9:23 am

ናፍቆት

ጽሁፎችሽ ጥሩ ናቸው ነገር ግን ባጠቃላይ አቀራረብሽ ላይ ቅሬታ አለኝ

ንቀት.....................ማናለብኝነት ..............ሞልቃቃነት ትምክህት......ትእቢት .........ወዘተ ታበዥያለሽ............ኢትዮጵያዊ ስነምግባር ይጎድልሻል..............እና ያንችን ጽሁፎች ማንበቤን ከማቆሜ በፊት እርምት ብትወስጅ .............

ግዞ ከሰባት ቤት
GIZO
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 2
Joined: Fri Feb 27, 2004 12:59 pm

ሳይብስብህ ብትገባ ጥሩ ነው

Postby ባድ 666 » Tue May 04, 2004 11:33 am

ተጭበርብሮብሀል አይደል ስለዚህ ቦታክ እንዳይያዝ ብትገባ ጥሩ ነው
ባድ 666
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Mon Mar 15, 2004 4:01 pm
Location: landveter

Postby ናፍቆት » Thu May 06, 2004 11:33 am

ሰርግ ብዝት ብሏል እዚህ.... አንዱ ሰርግ ሄጄ ነበር ባለፈው ...... ቆንጆ ሰርግ ነበር ...... እኛ በተቀመጥንበት በስተግራ ጥግ ይዘው ከክፍለሀገር የመጡ ነገር የሚመስሉ ሰዎች አንድ ቴብል ይዘው ቁጭ ብለው ነበር:: ........... in between the ceremony....... ዘፋኙ መዝፈኑን አቁሞ 'አንድ ጊዜ ለሙሽሪት እና ለሙሽራው የደስታ መግለጫ መልክት አለ..... አንድ ጊዜ.....' ቀጥሎ ምን እንደሚል ገብቶኛል.. ምክንያቱም እንደሰርግ አይነት የተለመዱ ነገሮች ላይ የሚሰማው ወይም የሚታየው ያው የተለመደ ነገር ስለሆነ.... anyways.... ዘፋኙ ቀጠለ.... 'እንትና እንትና ከአሜሪካ.... እንትና ከለንደን.... እንትና እና እንትና ... ከግሪክ..... ከፊንላንድ......' ደሞ በየመሀሉ 'አጨብጭቡ እንጂ.....' ቻ ቻ ቻ..... እንትና ከለንደን ' እረ ሞቅ ያለ ጭብጨባ....' (ተበልቶ ገና አላለቀም) ሰውየው መች ሊበግረው እሱ .. 'የበላችሁ አጨብጭቡ እንጂ'.... ወይ ጣጣ..... እነዛ በስተግራ በኩል ያሉ ሰዎች እጃቸው ተቃጠለ... ደሞ እንዴት ነው የሚጮህላቸው? ከምር ... ያዲሳባ ሰው እጅ እንደዚህ ማጨብጨብ የሚችልበት አይመስለኝም እኔ..... ግን ከምር ሆዳችሁ የሆነ ነገር አልተሰማውም ያ ሁሉ ሲጨበጨብላችሁ? ከምር? እኔማ ይሄኔ የሚጨበጨብለት ሰውዬ በዚች ቅጽበት ምን እያረገ ይሆን? ብዬ ለራሴ አስቤው ለራሴ ፈገግ ሲያስብለኝ...... ስልክ እንኩዋን የግድ መደወል አያስፈልጋችሁም እኮ .. አንድ ውጪ አገር መሆናችሁን የሚያውቅ ሰው ብቻ ይኑር በብጫቂ ወረቀት ስማችሁን ጽፎ ለዘፋኙ መስጠት ብቻ ነው:: ...........

እና ታድያ በመሀል አሰብኩዋቸው እነሱን.... የቶቹን? የክፍለሀገሮቹን ነዋ.... መቼ ይሆን 'ሙሉጎጃም ከጎጃም.... ባህርወርቅ ከባህርዳር... ቱሉ ከቱሉቦሎ....' ወይ ደሞ 'ኤሪት ከኤርትራ..... ጆጆ ከጆጆባ (ጆጆባ የሚባል አገር ሊኖር ይችል ይሆናል በማለት). ባለፈው እዛ አውቶቡስ ተራ የሰማሁት ደሞ ምን ነበር ..... Oh, I should remember that ...... yeah, ጋሞ! ጋሜ ከጋሞ .... Oh God , I am laughing....... መቼም አይደለም ስልክ ደውለው ማርና ቅቤ ጭነው ቢመጡ እንኳን እንዲህ የሚባልላቸው አይመስለኝም:: ደስ አይልም?.... ለነገሩ የክፍለሀገር ሰው ለንዲህ አይነት ጉዳይ ሲመጣ ባዶ እጁን የሚመጣ ብዙ ያለ አይመስለኝም:: ያቅሙንም ቢሆን.... ግን even ላያውቁት ለሚችሉት ሰው ሁሉ እጃቸውን ያቃጥላሉ..... የዋህነታችን ደስ አይልም? እንዲህ ግራ የሆኑ ነገሮች ሲያዝናኑኝ....... ለነገሩ life ላይ ብዙ ነገር ግራ ነው ..... like....... እ............ like .......... what can i say now? .......... yeah yeah...... like ለንጀራ ብሎ እንጀራ የሌለበት አገር መሄድ ... አይጥምም?
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests