ሀይ ሰልማ! እንዴት ነህ? አሁን አሁን ጠፍተሀል: ብዙ አላይህም:: ለነገሩ እኔም እዚህ የናፍቆት ቤት እና ዚዳን ቤት ነው እንጅ መጻፍ ትቻለሁ::
ሰልማ/ሀሪክ.......እንግዲህ ያልሆንሁትን መምሰል በጣም አልወድም:: እና አትደነቅ:: በቃ የገጠር ልጅ ነኝ! ምንም ላደርገው አልችልም:: እኔ ፈልጌው ሳይሆን እግዜር ያለው ነው:: የገጠር ልጅ በመሆኔ ምንም አላፍርም! በማንነቴ እኮራለሁ (በርግጥ የሚያኮራ ነገር የለም እኔ ፈልጌው አይደለምና.........ግን ጭራሽ አላፍርም):: የገጠር ልጅ ሁነው የአዲስ አበባ ነን በሚሉት ግን እጅግ አፍራለሁ!!!! አንተ ያልኸውን ልጅ ምን እንደምለው አላውቅም...........ግን ልክ ልኩን እነግረው ነበር! አንድ ቲያትር ነበረ "የእግዜር ጣት" የሚል::............."አሁን አንተ ፈልገህ ነው ደብረ ሲና የተወለድኸው?" የሚል አረፍተ ነገር ነበረው ቲያትሩ ውስጥ (እንግሊዘኛ ፊልም ባላይም አማርኛ ቲያትሮች አልፎ አልፎ አይ ነበር):: እና ሰው በማንነቱ ለምን ያፍራል? ሌሎችንስ ለምን በማንነታቸው ይንቃል? ፈልገው እኮ አላመጡትም!!!!!!!!!!!
በጣም የሚገርመኝ ደሞ.........እዛ ገጠር አሁንም ድረስ ሸማኔ: ፋቂ ምናምን እየተባለ ክፍፍል አለ:: ሁሌም እጨቃጨቅ ነበር:: በማህበራዊ ኑሮ ባይገለሉም ጋብቻ ግን ችግር አለ:: በ1997 (በኢትዮጵያ) የአጎቴ ልጅ ሲያገባ የሚያገባትን መፈለጉ መከራ ሁኖ ነበር:: የየከሌ ልጅ ጥሩ ናት ይባልና ከዛ አይ አያቷ ሸማኔ ነበር አሉ...........ምናም እየተባለ በቃ ስንት ሴቶች ተማረጡ መሰለህ:: እኔ ቅጥል ነው ያልሁት:: በጭራሽ ሊሰሙኝ አልቻሉም:: ይህ ነገር አሁንም ድረስ መኖሩ በጣም ያሳዝነኛል:: አልቻልሁም እንጅ ያጎቴ ልጅ ሲያገባ በጣም ጥሩ ናት የተባለችውን እንዲመርጥ ወትውቸ ነበር:: እሱ ለዛውም በጣም የተማረ እኮ ነው (ዶክተር):: ግን የሆነ ዩኒቨርሲቲ ሲያስተምር ያጫት (ቀለበት ያሰረላት) ልጅ ፒ.ኤች.ዲውን ሊሰራ ውጭ በሄደበት ስለከዳቺው ቤተሰብ የመረጣትን ነው እንጅ ካሁን በኋላ እኔ አልመርጥም አለ:: በነገርህ ላይ ያች እኔ ተወልጄ ያደግሁባት ትንሽየ የገጠር ከተማ ብዙ ልጆች አሳድጋ አስተምራ ለውጤት አብቅታለች::
እሰከዛሬ ካየኌቸው ፊልሞች ሁሉ ወደድኩት god must be crazy
shy boy ይህንን ፊልም ያላየ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም ነበር ...
እዚህ ላይ በጣም ተሳሳትህ! የየት ሀገር ንግስት ነበረች ከራባቸው ለምን ኬክ አይበሉም ያለችው? ገጠር ቲቪ ከየት ይመጣል ብለህ ነው? እናንተ የአዲስ አበባ ልጆች ከትምህርት ቤት ተመልሳችሁ ፊልም ላይ ስታፈጡ እኔ በግ እና ከብት እፈልግ ነበር:: :lol: :lol: ወይ ወፍጮ ቤት ሂድ ተብየ እላክ ነበር:: እና አንተ ፊልም እያየህ ስላደግህ ሌላው ኢትዮጵያዊ ፊልም ያያል ብለህ ካሰብህ በጣም ተሳስተሀል!
እኔ ለምሳሌ እንደዚህ የሚባል ፊልም መኖሩን ያወቅሁት ራሱ ባለፈው ሳምንት ፊልሙን ሳይ ነው:: እንኳን ፊልም ማየት ዘፈን እንኳን መስማት ከባድ እኮ ነው:: ለረጅም አመት እኛ ቤት እንኳን እንጠቀም የነበረው ኩራዝ ነው:: እኔ 7ኛ ክፍል ስደርስ ነው ማሾ እንኳን የተገዛው:: አሁን እንኳን ቤተሰቦቼ ጀነሬተር ገዝተው ቲቪ ማየት እንደጀመሩ ነግረውኛል:: ሰልማ: እስቲ ስንቱ ኢትዮጵያዊ ነው ስለዚህ ፊልም ቀርቶ ቲቪ የሚባል ነገር መኖሩን የሚያውቅ:: እውነት እልሀለሁ ሬዲዮ እንኳን የማያውቁ እጅግ ብዙ አሉ:: 85% የኢትዮጵያ ህዝብ እኮ ገጠር ነው ያለው:: እኔ የገጠር ከተማ ውስጥ አድጌ ካላወቅሁት ከኛ ሰፈር ወጣና: እጅግ ወጣ ያሉት እልም ያሉ ገጠሮች ውስጥ የሚኖሩት ሰዎች እንዴት ሊያዩት ይችላሉ? የኛዋ ትንሽዬ የገጠር ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ቲቪ ያየችው France 98 ያለም ዋንጫ ነው.......ለዛውም በጀነሬተር: ለንግድ:: ከዛ ሰውየው አከሰረኝ ብሎ ዘጋው:: አሁን ግን አንድ ሁለት ሰዎች እንዳስገቡ ሰምቻለሁ::
በል ሰላም ዋል!