ሰልማ1 wrote:shyboy እረ ለመሆኑ የናፍቆት ናፍቆት እንዴት አስችሎህ እንዲህ ጥፍት አልክ? ነው ወይስ በግል አገኘሀት.. አግኝተሀት ከሆነ i am happy you full filled your dream :lol: :lol: :lol:
ሀይ ሀሪክ: ሰላም ነህ ወይ? እኔ አለሁ: ምንም አልልም ብርዱ ሊገለኝ ነው እንጅ:: ሀሪክ ዋርካ የመጨረሻ እየሸከካት ስለሄደች ነው ባጠቃላይ መምጣት ያቆምሁት:: ድሮም ጀምሮ ክብራቸውን ጠብቀው የሚሄዱት ቤቶች አሁንም ከነሞገሳቸው ናቸው:: እነሱን እያነበብሁ ውልቅ እላለሁ:: በተለይ ግን እንደ ዋርካ ፖለቲካ የቀፈፈኝ የለም::
በተረፈ ያን ያህል መልስ መስጠት አስፈላጊ ሁኖ ያገኘሁበት ቦታ ስለሌለ ነው የማልጽፈው:: አሁንም በቀጥታ ስለጠየቅኸኝ ነው መልስ መስጠቴ:: የናፍቆትን ነገር ተወው...........ስትናፈቅ ጊዜ ኮራች :lol: :lol: :lol: ደሞ ነገር ማጦር ጀመርህና በግል አገኘሀት ወይ አልኸኝ? ባገኛት ደስታየ ነበር-አድናቆቴን ለመግለጽ! ነገሩን ወደሌላ አዙረኸው ከሆነ የኔን ነገር መቸም ታውቀዋለህ............እንኳን ባካል የማላውቃትን ሴት ይቅርና አንድ ክፍል ውስጥ አብራኝ የምትማረዋን ወይም አንድ ቢሮ አብራኝ የምትሰራዋን እንኳን ለሌላ ጉዳይ ማናገር አልችልም :lol: (ከምሬን ነው)::
በነገራችን ላይ: ዋርካ እንደዚህ ቢደብረኝም ፓልቶክ ውስጥ ዋናው የከፈተው "ዋርካ" ሩም ባለፈው ቅዳሜ ገብቸ ተዝናንቸ ወጥቻለሁ (ቤቱ ሊዘጋ ነው ሲባል ነው የወጣሁት):: መቸስ የዋርካ አዝናኞች እነማን እንደሆኑ ታውቃለህ አይደል? ናፍቆት (አሁን ብትጠፋም): ዉቃው: መንፌው (በአዲሱ ስሙ Sylar.......ካልተሳሳትሁ እንደዚህ መሰለኝ አጻጻፉ) እና ጨጉዳ ናቸው:: ከአራቱ አዝናኞች ሁለቱ ፓልቶክ ውስጥ ነበሩ:: ዉቃው ማይክ ይዞ አጫውቶናል:: መንፌው ደሞ ማይክ የለኝም ብሎ በጽሁፍ ብቻ ስናወራ ነበር::
እዚህ ዋርካ ፎረም ውስጥ ሲጽፉ ብቻ የማውቃቸውን ሰዎች ድምጻቸውን መስማት በጣም ነበር የምመኘው:: ብዙ ጊዜ ጽሁፋቸውን የምታነበው ሰዎች በጭንቅላትህ የሆነ ኢሜጅ መቀረጹ አይቀርም:: በኔ በኩል በጭንቅላቴ ተቀርጾ የነበረው ምስል የሰዎችን ድምጽ ስሰማ ምንም አልተገናኘልኝም:---------------
*ዋናው: ዋኖስ እና ሾተል ሽማግሌ ይመስሉኝ የነበረ ቢሆንም ድምጻቸው ግን በሀያዎቹ መጨረሻ አካባቢ የሚገኙ አስመስሏቸዋል:: (በነገራችን ላይ የዋናው እና ሾተል መነባንብ ችሎታ እጅግ ልዩ ነው!!!! ሾተል "አምሳ አለቃ ገብሩንም" አሪፍ አድርጎ ተጫውቶታል:: ዋርካ ፎረም ላይ "ሞገደኛ" አድርጌ የሳልሁት ሾተል ድምጹን ስሰማው የሰማይና ምድር ያህል ልዩነት አለው::)
*ብዙ ግጥም ማንበብ ስለማልወድ Yammi የምትጽፋቸውን ግጥሞች ባላነባቸው እና ስለሷ በጭንቅላቴ ውስጥ የቀረጽሁት ምስል ባይኖርም ድምጿ ለጉድ ነው:: በሚስረቀረቀው ድምጿ ግጥም ስታነብ ሰምቶ ልቡ ያልከዳው ወንድ የለም!!! :lol: (ከምሬን ነው)
*ዉቃው በሀያዎቹ እድሜ ያለ "ፍንዳታ" ይመስለኝ ነበር :lol: ከድምጹ እንደተረዳሁት ትንሽ በሰል ያለ ይመስላል............ያነጋገር ለዛው ግን ከሚጽፈውም በላይ ነው!!!
ስለሌሎች ደሞ ሌላ ጊዜ እጽፋለሁ:: (አንዴ ፖስት ማድረግ እንደጀመርሁ የተሰማኝን ሁሉ በመጻፌ ይቅርታ!!! ስለ ፓልቶኩ ዋርካ መጻፍ የነበረብኝ ለሱ በተከፈተው ቤት ውስጥ ነበር)::
በዚህ አጋጣሚ ሌሎቻችሁም ወደ ፓልቶኩ ዋርካ ብቅ እንድትሉ በተሳታፊዎች ስም እጋብዛለሁ:: ሩሙን ለከፈተው ለዋናው ከፍ ያለ ምስጋና እያቀረብሁ: ወደፊት ደሞ ዋርካዊያን በአካል የሚገናኙበት ሁኔታ እንደሚመቻች ተስፋ አለኝ::
የሩሙን መከፈቻ ጊዜ ለምትፈልጉ ቅዳሜ እና እሁድ ከ11:0am (Eastern Time) ጀምሮ ነው::
በሉ እንግዲህ ቅዳሜ 11:00am (8:00am Pacific Time; 16:00GMT) የፓልቶኩ ዋርካ ላይ እንገናኝ::
እስከዛው ሰላም ሁኑ!!!