Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)
by yammi » Sat Nov 29, 2008 8:30 pm
ርእስ ወደፊት ይፈለግላታል
ማለዳ ይሁንሽ ብሎ
......መርቆ ነበር የሰጣት
ከቀትር ሀሩር ብሶ
.....አሁን እንዲህ ሊያነዳት
የምርቃቱ መጣመም
.....ሳይሆን ልቧን የሰበረው
የቀትሩንም ሀሩር ቢሆን
.....ልቧ እየወደደው መምጣቱን ነው:: :( :(
29/11/08
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ጦምኔው » Sat Nov 29, 2008 8:36 pm
ሠላም ቆንጂት:: መልካም ነው ይበርቱ ብለናል::
አትጥፊማ 8)
-
ጦምኔው
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1529
- Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
- Location: Right here
by yammi » Sat Nov 29, 2008 8:45 pm
የቁራ ጩኸት
በሱባኤ ቅንጦት
በቸነፈር ፍትፍት
................ ምኞት
በሰኔ ሰኞን
..............ናፍቆት
እንግልት
እሱ ራሱን በቃ ሳይል
በ""ኸረ በቃ በለኝ"" ጩኸት
ስልችት::
29/11/08 ከሰሞኑ ትዝብቶቼ
(እንደዚህ አይነት ሰው ታዝባችሁ አታውቁም?)
ያሚ
Last edited by
yammi on Thu Mar 12, 2009 5:57 pm, edited 2 times in total.
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Sat Nov 29, 2008 9:00 pm
ጦምዬ ጦልጧላው.........ሳላይህ በየት ገባህ.........እኔ የምለው ዋርካዎች አገር ካረጋጉ በኋላ ዘበኝነት ቀጠሩህ እንዴ?
ምስጋናዬ ግን የትየለሌ ነው :D :D ደግሞ ናፍቀኽኛል :roll: :roll:
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ጦምኔው » Sat Nov 29, 2008 9:14 pm
ዘበኝነት ቀጠሩህ ወይ?.....እንደ ኮካ ኮላ ቆርኪ በዛሁብሽ አይደል?.... :lol: ....ምን አባቴን ላድርግ ያሚታ?......መሄጃ እኮ ጠፋ............እናንተም እንደ ድሮው በጓሮ ማዳበሩን ረሳችሁት :lol: በዚያ ላይ ያቺን እህምምን ላግዛት ብዬ ነው :lol:
አሁን ሌላውን ተይና አርፈሽ ግጠሚ: :lol:
-
ጦምኔው
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1529
- Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
- Location: Right here
by ናቲሜሽን » Sat Nov 29, 2008 9:51 pm
ጦም :lol:
የዋርካ ጦም አጦምም እንዴ? እንደኔና እንደሾተል ብትበዛ እኮ ነው ዘበኝነት ተቀጠርክ ወይ የተባልከው :lol:
-
ናቲሜሽን
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 541
- Joined: Wed Oct 22, 2008 8:47 pm
by yammi » Sun Dec 14, 2008 3:39 pm
.......................
ከሚቆነጥጡ አይኖች
ከሚቧጥጥ ፈገግታ ሽሽት
....................... እየተደበቁ
ትላንት የሸመትኳቸው
ወፋፍራም ቀናቶች
ተ-ሳ-ቀ-ው አለቁ!!
በ passage ላሳለፍኳቸው ቀናቶች
ያሚ
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ትርንጎ* » Sun Jan 11, 2009 1:38 pm
አህህህህህህ :cry: ቁስሌን ጫረችው:: የስንቶቻችን የህይወት ታሪክ በዚች ግጥም ውስጥ ተካቶ ይሆን :idea:
ያሚታዬ አሁንስ እንዳላሰለችሽ ፈራሁ...ባንቺና በትሩዝ ጽሁፎች ተለከፍኩ መሰል ፖስት እንዳደረጋችሁ ሳይ ያከታልበኛል...ከዛ ደግሞ ምጥምጥ አድርጎ በዝምታ ሹልክ ማለቱ ሀጢያት ይመስለኛል መሰል:: እጅሽ ልምልምልምልም ይበል እሙ!
እስቲ ደግሞ የፈረደበትን ትሩዝ ላሳድ :D በስቶከርነት እንዳትከሱኝ ብቻ::
-
ትርንጎ*
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 716
- Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am
-
by yammi » Sun Jan 11, 2009 3:45 pm
ትርንጎዬ.....አመሰግናለሁ የኔ ቆንጆ..........እኔም ሰሞኑን የመጫር አባዜዬ ተነስቷል:: ትሩዝማ ሰሞኑን የት እንደገባ እንጃ.....የግጥም ጎጆው ወደጓሮ መዛወሯን ልብ ብለሻል?
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by ትርንጎ* » Sun Jan 11, 2009 5:50 pm
yammi wrote:........እኔም ሰሞኑን የመጫር አባዜዬ ተነስቷል::
ወደሽ መሰለሽ....የኛ ስለት ነው:: :wink:
ትሩዝማ ሰሞኑን የት እንደገባ እንጃ .....
እንጃለት...ቢመጣ ይሻለዋል አይደል? ልብወለዱን አነበብሽልኝ? 'አልገኝቶ' ነው መሰል የሚለው...ዛሬ በጠዋቱ በሳቅ አፈረሰኝ::
የተባረከች ቀን ትሁንልሽ ያሚታዬ!
-
ትርንጎ*
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 716
- Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am
-
by ራያራዩማ » Mon Jan 12, 2009 2:49 am
[quote=ፍቅር ከ ሀ እስከ ፐ]
ሲያገኘኝ:
ፍቅሬን ለመግለጽ ሰማይን እንዳልቆርስልሽ
ቡራኬ ሰጪ ጠፋ አለኝ::
..............እኔም አመንኩ::
ሲያገባኝ:
ከጨረቃና ከከዋክብት መሀል ጎጆ እንዳልቀልስልሽ
መሰረት ማቆሚያ አጣሁ አለኝ::
.....................እኔም አመንኩ::
ሲፈታኝ:
ደስታየን ለመግለጽ ከነፋሱ ጋር እንድደንስ
ከላባ ያቀለኝ ዘንድ ጸልይልኝ አለኝ:
.................እናም
.................ጸለይኩ::
10/1/2009
ያሚ
[/b]
-
ራያራዩማ
- አዲስ

-
- Posts: 16
- Joined: Fri Jul 18, 2008 9:52 pm
by ራያራዩማ » Mon Jan 12, 2009 2:55 am
አሪፍ ነች! አድንቄአለሁ!
-
ራያራዩማ
- አዲስ

-
- Posts: 16
- Joined: Fri Jul 18, 2008 9:52 pm
by yammi » Mon Jan 12, 2009 10:21 pm
ራያራዩማ አመስግኛለሁ::
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Wed Jan 14, 2009 3:44 pm
የአገር ያለህ
በአይኑ ይቀበላቸዋል ብዬ አይኖቼን ብጥላቸው
አሳባሪ መንገደኛ ድንገት አፍሶ ወሰዳቸው::
14/01/2009
Last edited by
yammi on Fri Jan 16, 2009 9:46 pm, edited 1 time in total.
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
by yammi » Wed Jan 14, 2009 4:11 pm
ሱባኤ የመግባቴ ምክንያት
ጨረቃና ጸሀይ ሲቧደኑ
ወንዞች ሽቅብ ሲከንፉ
ንቢቱ በእንቡጥ ስትጨክን
ሰማያት ምድርን ሲያኮርፉ
ጾሜ ሰግጄ ነበር
እኔም ለአይኖችህ እንዳላንስ
እንዳታየኝ ከግርድፉ
ዳሩ
የእለቱን ትቼ የምጻቱን ስለምን
መገሰጽ መቅጣቱን የታደለ
ውበት በነቂስ አውጥቶ
ካስማ በዙሪያህ አስተከለ
አንተም ለአይኖቼ ከበድክ
ማቅለያውም ከኔ አይደለ::
14/1/09
ያሚ
Last edited by
yammi on Sat Jan 17, 2009 11:23 am, edited 1 time in total.
-
yammi
- ኮትኳች

-
- Posts: 441
- Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm
Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
Who is online
Users browsing this forum: Bing [Bot] and 2 guests