ናፍቆት wrote:
እኔ ከሰውየው ይሄ ከላይ ደረብ የሚያደርገውን 'brown' ጎጃም-አዘነውን እወድለታለሁ::
ShyBoy - ውይ ስሞት .... እንዳታኮርፈኝ .... እስቲ አስበው ተራርቆ ኩርፊያ ምን ይመቻል በናትህ .... ከምር ..... አጠገቤ ብትሆን እንኳን መላ መላ አይጠፋም ነበር ለማባበል
ናፍቆት wrote:ዛሬ ጠዋት የገጠመኝ ..... እየነዳሁ የሆነ አካባቢ ላይ .... ጥቂት ሰዎች ሰብሰብ ብለው መጠነኝ ግርግር አይነት .... naturally ቀዝቀዝ አደረግሁና ሳልጠጋ ቆም አልኩ ..... አንድ በግምት ከ 22 እስከ 24 የሚደርስ ወንድ ወጣት ... ቀይ .... ጸጉሩ ሉጫ ግን ያልተበጠረ ... በቅርቡም አልተቆረጠም አይነት ..... ቀጠን ዘለግ ያለ ..... ፌድ ያረገ ጅንስ .... ነጣ ያለ ሸሚዝ .... ጃኬቱን በመንገዱ ዳር ጣል አድርጎታል ... በጁ ትልቅ ድንጋይ ይዟል .... እና ለመወርወርና ላለመወርወር ግራ የተጋባ አይነት ይመስላል .... ድንገት ስታየው የሚያሳዝን ነገር የሚሰማህ አይነት ..... ከሰፈሩ ወዳስፋልቱ ሲወጣ የተከተሉት ሰዎች ይመስሉኛል ሰብሰብ ያሉት .... ገና ጀማሪ እብድ ....
ድንገት ከኔ ጎን አካባቢ 'ይሄ የንትና ልጅ አይደል እንዴ? ' ... አሉ አንድ ሴት ወደ ቤ/ክ የሚሄዱ ወይም ከዛ የሚመለሱ የሚመስሉ .... ልጁን ማንም አልደፈረውም ነበር ... መኪናዎች ከሁአላዬ ቆም ቆም እያሉ መደርደር ጀምረዋል .... ሴትዮዋ በኮንፊደንስ ወደመሀል አስፋልቱ ገቡ .... መጀመሪያ ዞር ብሎ ሲያያቸው ድንብር ነገር አለ ወጣቱ ... በድንጋዩ እንደማስፈራራት አላቸው ... ሴትዮዋ ግን አልፈሩትም ... ቀጥ ብለው ሄደው ድንጋይ የያዘበትን እጁን ያዙ ...... ካስፋልቱ ወደዳር አወጡት ... ታዘዛቸው .... ወዲያው ቅዝዝ ነገር አለ ...... ዝምብሉ ተጎተተላቸው .... አይኖቹ ያሳዝናሉ ... .... ከዛ ሴትዮዋ ጃኬቱን አንስተው ሊያደርጉለት ሲታገሉ .. አንድ ሰውዬ ምንተፍረቱን ሊያግዛቸው ጠጋ አለ ......ይህ ሁሉ ሲሆን ዝም ብዬ ቆሜ ልብ ብዬ እያየሁት ነበር ... በሀሳቤ ብዙ ነገሮች ተመላለሱብኝ ... ስለ ውጣትነት ... ስለእብደት .... ስለመኖር .... በአለም ላይ ከሁሉም ነገር ቀላሉ ማበድ ይመስለኛል:: በዚህ 'ኑሮ' በሚባለው ውጥንቅጥ ጉድ ውስጥ ላለማበድ መታገሉ ይመስለኛል ከባዱ ....
.......... ብንን ያደረገኝ ከሁአላዬ ቆመው የነበሩ ያንድ ጥቁር መላጣ ሽማግሌ የመንግስት መኪና ሾፌር ክላክስ ነበር .... To my own surprise, እንባዬ ከመነጽሬ ስር ይፈስ ነበር ....
Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
Users browsing this forum: No registered users and 0 guests