''አዲስ ጉድ'' ሚጢጢ ልብ-ወለድ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

''አዲስ ጉድ'' ሚጢጢ ልብ-ወለድ

Postby sonaf » Tue Jan 27, 2009 10:04 pm

አዲስ ጉድ
ሚጢጢ ልብወለድ

የኔን ዐይንት ደስተኛ ህይወት የሚኖሩ ሰዎች ስለመኖራቸው የማውቀው ነገር የለም። ለማወቅም ፈልጌ አላውቅም፣ ጉዳዬም አይደለም። ሰለራሴው ህይወት ደሰተኛነት ማስተዋል የጀመርኩት እንኩዋን በቅርብ፣ በእንድ አጋጣሚ ነው። ከዚያ በፊት ስለደስተኛ ወይም አልደስተኛ ህይወት ምንም ግንዛቤ አልነበረኝም፣ አልደስተኛነት እስኪሰማኝ ድረስ አልደስተኛነት መኖሩንም አላውቅም ነበር።

ህይወቴን በደስታ የምትሞላው አንዲት ሴት ነች። ሁለመናዋ ደስ የሚለኝ ሴት። ስትጠራኝ እንኩዋ ድምጽዋ ልቤን ሲያሻሸው ይሰማኛል። ስትዳብሰኝማ ከደስታ ብዛት የምበርርና በአየር ላይ የምንሳፈፍ ይመስለኛል። ስታጎርስኝ ጣቶችዋን ካላስኩ ምግቡ አይጠምኝም። ደስታዬ ሞልቶ የሚያፍነኝ አብሪያት ስተኛ ነው። እቅፍዋ ውስጥ ስሆን፣ በአለም እኔና እስዋ ብቻ ያለን እስኪመስለኝ ድረስ፣ አለምን እረሳለሁ። ቤት ውስጥ ከኔና ከእስዋ በቀር ሰው ስለሌለ ሰውነትዋ ላይ ስንከባልል የሚሰማኝ የባለቤትነት ስሜት ወደር የለውም። ላይዋ ላይ ወጥቼ ስገላበጥ በስውነትዋ ቅርጽ ልክ አስተካክላ ታቅፈኛልች እንጂ አብረን መኖር ከጀመርንበትን ቀን ጀምሮ አንድ ቀን ለአመል እንኩዋ ገፋ አድርጋኝ አታውቅም።

አብረን መኖር የጀመርንበትን ቀን አላስታውስም። ስለማላስታውሰው አብረን ሳንፈጠር አንቀርም በዬ ነበር የማምነው። እኔ ለእስዋ፣ እስዋ ለእኔ የተፈጣጠርን ይመስለኝ ነበር። ብዙ ጊዜ ያን፣ እኔና እስዋ ብቻ ሆነንጅ ያሰልፍነውን ጊዜ በሃሰቤ እኖረዋልሁ። ያ እንደ ንጉስ የፈልኩትን እዝዤ የማገኝበትን ጊዜ። አረ ማዘዝም አየስፈልገኝም ነበር፣ የምፈልገውን ሳልጠይቅ፣ ቃል ሳልተነፍስ፣ ራስዋ አውቃ ነበር የምታደርግልኝ። የዛሬን አያድርገውና ።

ዛሬ ነገር ሁሉ ተገለባብጦኣል። ከየት መጣ የማልለው ሰው ሁሉንም ነገር ቀይሮታል ። እንድ ጎሪላ የሚያክል ጢማም ሰው። ያን የምሳሳለትን ጉንጩዋን ሲስም፣ እንደጣኦት የማመልካቸውን፣ እነዚያ ካይኖቼ የመማይጠፉትን ጡትዎችዋን ያለ ርህረሄ ሲጨመድድ ሳይ እውስጤ የሚቀጣጠለው እሳት አንዴት እስካሁን ለብልቦ እንዳልገደለኝ ይገርመኛል። ይሄ ሁሉ ሲሆን ዝም ብለህ ታያለህ፣ የሞትክ፣ የሚለኝ አይጠፋም። አዎ ያላየ ይላል። ሰውየው የኔን ስንት ይሆናል እ? አስራ አስር የሚባል ቁጥር ካለ ያን ነው የሚያክል። ግን እኔ ያን ፈርቼ ዝም አላልኩም። ትግሌን የጀመርኩት ገና ከመጀመሪያው ቀን ነበር።

የመጀመሪያውን ቀን አልረሳውም። ማልዳ ነው፣ እኔና እስዋ አልጋ ላይ ነበርን። እኔ እንደ ልማዴ ላይዋ ላይ፣ እስዋ ከስር። አልጋ ላይ ስንጫወት ሁሌ እኔ ከላይ፣ እስዋ ከሰር ነው የምንሆነው። ዝም ብለን ስንተኛ ነው፣ ጎን ለጎን። ከላይ እንድትሆን ጠይቂያት አላውቅም። እስዋም ከላይ መሆን እትወድም መሰል አድርጋው አታውቅም። ለኔ ከላይ ሆነች ከስር አጠገቤ እስካልች ድረስ ለውጥ የለውም። እና አልጋ ላይ እየተላፋን በር ይንኩዋካል።

"ማን ልበል " ትላልች እኔን ወደ ጎን ገፋ አድርጋ። ስትገፋኝ የመጀመሪያ ጊዜዋ ነበር። በጭራሽ ገፍታኝ አታውቅም።

"እኔ ነኝ። " ብቻ ነበር ያለው ሰውየው። እንዲያ አይነት ሙሉና ጎርነን ያል ድምጽ ትዝ ይለኛል ግን የእገሌ ነው ብዬ ማለት አልችልም።

" ከቤዬ " ብላ እንዴት እንደዘለለች እልረሳውም።

ከቤዬ ? ይህን ስም ስትጠራ ደሞ አስራ አስር ጊዜ ሰምቻታለሁ። እቃ ሲወድቅባት፣ ስትደነግጥ ከቢዬ ትላለች። ምንድነው ? ማን ነው ? ብዬ ለመጠየቅ አስቤ አላውቅም።

በቢጃማ ሄዳ በር ከፈተች።

ይቀጥለል።...
Last edited by sonaf on Tue Jan 27, 2009 10:23 pm, edited 1 time in total.
i c u.
sonaf
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Fri Oct 19, 2007 3:07 pm
Location: uk

Postby sonaf » Wed Jan 28, 2009 8:37 am

2.
ሰውየው፣ ጉዋዝ ሲያራግፍ ነው መሰልኝ በረንዳ ላይ ትንሽ ከተንጎዳጎድ በሁዋላ ይገባል። ረጅም ነው። ፊቱ ግማሽ በግማሽ በጸጉር ተሽፍኖአል። ግራ ቀኝ ሳይመለከት በቀኝ እጁ ባርኔጣውን እያወጣ በግራው ሳባትና እቅፍ አድርጎ ክንፈርዋን በረጅሙ ሳመው። ይህን ሳይ በውነት ልነሳ ነበር፣ ላዩ ላይ ወጥቼ ልዘነጣጥለው። የስዋን ሁኔታ ስመለከት ግን የማደርገው ጠፍቶኝ ዝም አልኩ። እስዋም እየተንጠራራች የምታደርገው መቼም እንዲህ እንዲያ ብሎ ለማለት የሚያስቸግር ጉድ ነበር። አንዴ አፉን ትስመዋለች፣ ሌላ ጊዜ ጆሮውን ትነካክሰዋለች፣ እንደግና አንገቱ ስር ትወርድና ትለካክፈዋለች። እኔንም እንደዚያ ትስመኛልች ግን እንዲህ ልትበላኝ ተቅበዝብዛ አታውቅም።

ሰውየው እየሳማትና እየተሳመ ካፖርቱን አውልቁ እንደ ቅጠል ከመሬት ሲያነሳት ከአልጋ ወረድኩና ቤቱ መሀል ሄጄ እንደ ተዋጊ ወይፈን እግሬን ተክዬ ቆምኩ። ወለሉን በእግሬ ጫር ካደረኩ በኍላ ከቆምኩበትጋ ጎሪላውን በድንብ አጠናሁት። ከዚህ በፊት በጭራሽ አይቼው አላውቅም። መልኩ ግን ጨርሶ እንግዳ አይደለም... የት እንደማውቀው ብቻ ነው መለየት ያቃታኝ,,, አወቅኩት አላወቅኩት ጉዳዬ አልነበረም... ተዘርፌአልሁ... ተንቄአለሁ... ስለሆነም በግኛለሁ.

አፍንጫውን ልደረምስ.. እኮብኩቤ ወደሱ ስንደረደር ሰውዬው እስዋን አወረደና እኔን በእንድ እጁ አፈፍ አያደርገኝም! እንዳንጠለጠለኝ በእግር በእጄ ተወራጨሁበት ግን አጅሬ ጎሪላ አላፈናፈነኝም። በቀላሉ እንደ እቃ ወደ ላይ አነሳኝ። ጣራውን ያን ያህል ቀርቤው አላውቅም። ኮርኒሱን በጭንቅላቴ ሲያስነካኝ ግዝፈቱንና ጉልበቱን ሳልወድ አደነቅሁ።

"ሊማታ ይከጅለዋል። ጎርምስሶ የለ እንዴ!" አለ ባየር ላይ እንደ አሻንጉሊት እያወዛወዘኝ። መወራቸቴን ማቆም አሳፍሮኝ ቀጥያለሁ።

"ማሙሽ ማን እንደሆን አወቅህ?" አለችኝ አንጋጥጣ እያየችኝ። "ቆይ አስተዋውቅሀለው።"

"ሳይወድ ያውቀኛል።" ጎሪላው ግንባረን ሳም አድርጎ እኔን እወረደና ወደ እስዋ ዞረ...

እንደገና ሲጣበቁ መጀመሪያ ውስጤ ተገላበጠ፣ በኍላ እንባዬ መጣ። ግን እሱ ፊት አላለቅስም ብዬ ወደ ጉዋዳ አመራሁ። ውስጥ ከመግባቴ በፊት በሩን ተከልዬ ታዘብኩዋቸው።

ሰው ልቡሱን ለማውጣት እንደዚያ ሲቻኮል እይቼ ኣላውቅም። እሱ ሲያወላልቅ እስዋ ቢጃማዋን መሬት ጥላ የሱን ሸሚዝ ቁልፍ ትፈታታለች። የውስጥ ሱሪው ብቻ ሲቀር፣ እስዋ አልጋ ላይ ቀድማ ወጣችና ራቁትዋን ተንጋለለች። ወዲያው ዘሎ ጉብ ሲልባት እኔ ላይ እንደ ሰፈረብኝ ነገር ከበደኝና ተመልሽ እንደገና ጥቃት ለመሰንዘር አሰብኩ ግን የሆነ ነገር ይዞኝ መመለስ አቃተኝ...

መላ ሰውነቴ ዘፍ አለ... ሄጄ አልጋ ላይ ተንጋለልኩ።

ብዙም አልቆዩ ትንፋሻቸው ይሰማኝ ጀመር። ከዛ እስዋ መጮህ ጀመርች። አላስቻለኝም። ጭንቅላቱን በምናምን ፈርክሰው መጣብኝ። ተነስቼ የመስኮት መቀርቀሪውን አመጣሁ... በዚያ ሁለቴ ማጅራቱን ብከካው አይነሳም፣ በማለት ራሴን አደፋፈርኩና ሄጄ፣ የጉዋዳውን በር ጠርዝ ተከልዬ አጮልቄ ተመለከትኩ።

ቤት ቤት ይጫወታሉ መስል አልጋው ላይ ድንኩዋን ሰርተው ይላፋሉ...

አልጋው ተነቅሎ ሊሄድ ምንም እልቀረውም። እንደ ጉድ ይወዛወዛል። ይንሳጠጣል። ማን ማን እንደሆን መለየት ባለመቻሉ። ልጥል ላሰብኩት ድንገተኛ ጥቃት አይመችም። እሱ ከላይ ቢሆን ሳያየኝ ጠጋ ብዬ አደባየው ነበር። ትንሽ ጠብቄ ተመለሼ ጉዋዳ ገብቼ ተኛሁ።

አመት አይሞላም አንድ ከኔ የባስ ደቃቃ ጉድ መጣና ያን አንድ አገር የሚያክል ጎሪላ ከዚያ አልጋ አባረረው። ደስ አልኝ። እሱን ካባረርክልኝ፣ አንተ አታቅተኝም ብዬ አድብቼ መጠበቅ ጀመርኩ። እሱ ምኑ ሞኝ፣ ሊለቃት ነው። እኔንም እስዋጋ ጭራሽ አላስደርስ አለኝ። ብዙም አልቆየሁ እጄን ሰጠሁ.

አሁን ጎሪላውና እኔ አንድ አልጋ ላይ እንተኛለን።

"ማሙሽ " ጎሪላው ጠራኝ ከጎኔ ተኝቶ።

"እ" ብቻ አልኩት እንቅልፍ ስለተጫጫነኝ።

"ምንም አይደል፣ እዚህ ካንተ ጋር የሚተኛበት ጊዜ ሩቅ አይደለም።"

የሆነ ቃል ተንተባተብኩ። ቁዋንቁዋ ብዙ አንግባበም እንጂ፣ 'እኔንም እንዲያ ነበር ያደረከኝ' የማለት አይነት ነው ያልኩት። ግን ገባው መሰል ሳቀና ሳመኝ። አቀፈኝ። ለካስ የሱም እቅፍ እንደስዋ ደስስስስስስስስ ይላል። ጠረኑን ለማስታወስ አልቻልኩም ግን ለኔ አዲስ አልነበረም።

አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እሱ ማሙሽ ሲለኝ፣ እኔ አባዬ እለው ጀምር። ምስጋን ለዚህ ለአዲሱ ጉድ። አሱ ባይመጣ አባዬን ቶሎ አላውቀውም ነበር። ለካስ የአንድ አመት እድሜ ሳልሞላ በስራ ምክንያት ውጭ ሄዶ ስለነበር እንጂ ድሮም የሚኖረው እዚሁ ነበር...

ኦሜጋ!
Last edited by sonaf on Mon Aug 18, 2014 12:17 pm, edited 5 times in total.
sonaf
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Fri Oct 19, 2007 3:07 pm
Location: uk

Postby Debzi » Wed Jan 28, 2009 4:26 pm

አሪፍ ነው..sonaf! ሁለተኛውን ክፍል እስከማነብ ድረስ ስለፍቅረኛህ የጻፍክ ነበር የመሰለኝ:: ወይ ችሎታ! እሚደነቅ ነው::
Ke akbrot selamta gar!!
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

Postby ላምባዲናየ » Fri Jan 30, 2009 9:42 pm

ሶናፍ የሀገር ልጅ.........ልብ-ወለዷ እጥር ምጥን ጥፍጥ ያለች ናት!........አድናቆቴ ካለሁበት ይድረስህ!!!!
lamba
ላምባዲናየ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 46
Joined: Tue Dec 26, 2006 3:17 pm
Location: Gorgora

Postby ሚቲቱ » Sat Jan 31, 2009 12:14 am

ብጣም አሪፍ ነው ቀጥልበት::
ሚቲቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Sat Nov 15, 2008 5:04 am

Postby sleepless girl » Mon Feb 02, 2009 3:13 am

በጣም የሚመች ጽሁፍ ነው............ግን ልጅቷ??? እንዴት ነው???? ስንት ስኮርት ጎማ ነው ያላት?? :roll: :roll:
Nothing is impossible!!
sleepless girl
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1510
Joined: Sun Feb 19, 2006 3:56 am
Location: near u!

Postby sonaf » Fri Aug 15, 2014 4:52 am

"ስኮርት ጎማ?" .... ምኑንን እንደህ ሳይገባኝ እስክ ዛሬ አለሁ...

የገባችሁ ብታስረዱኝ በማለት,

ዋርካን ማሞቂያ ይሆን ዘንድ...በማለት...

አውጥቼዋለሁ....

ሶናፍ
sonaf
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Fri Oct 19, 2007 3:07 pm
Location: uk

Postby ፕላዞግ » Sat Aug 16, 2014 4:11 am

አሪፍ ልብ-ወለድ!
ፕላዞግ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 38
Joined: Sat Dec 06, 2008 7:21 pm

Postby ፕላዞግ » Thu Oct 02, 2014 6:26 am

በርታ ማለት ጥፋ ማለት ሆነ እንዴ?
ፕላዞግ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 38
Joined: Sat Dec 06, 2008 7:21 pm


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests