የሰንዘርከውን ሀሳብ በጥሞና አንብቤዋለሁ። ከጽሁፍ ውስጥ ምላሽ ልሰጥባቸው የፈለግሁዋቸውን አውጥቼ በጥቅስ ውስጥ ቀንፌአቸዋለሁ።
እነሆ
በተለይም የቡርቃ ዝምታ በተስፋዬ እንዳልተጻፈ ለማሳመን እየሞከርክ ነው ::
ለማሳመን ሳይሆን ለጥርጣሬዬ መሰረት የሆኑትን ነጥቦች ለማሳየት፣ አዎ ሞክሬአልሁ። አንባቢ የቀረቡትን መረጃዎች አይቶ የራሱን ግምት ይሰጣል ብዬ አምናልሁ። የማሳመን አልማሳመን ጉዳይ ሳይሆን እንደ አንድ የመወያያ ርእስ መነሳት የሚችል ይመስለኛል።
እንደምገምተው የቡርቃ ዝምታን ከማንበብህ በፊት የጋዜጠኛው ማስታወሻን ስላነበብክ የአጻጻፍ ዘይቤውን በጣም ስለወደድከው ይመስለኛል ::
የሰጠሁት አስተያይት በመውደድና በመጥላት ላይ እንዳልተመሰረተ ቁልጭ ብሎ የሚታይ ይመስለኛል። ከመጽሀፉ የጠቀስኩዋቸው አረፍተ ነገሮች ውስጥ ሰዋስዋዊ ቅርጻቸው፣ የቃላት አጥቃቀምና ማንም አማርኛ ተናጋሪ የማይስታቸውን ብሂሎች ተዛብተው ይገኛሉ። ከዚህ በመነሳት ነው፣ ድርሰቱ የሌላ ሰው ብእር ነክቶታል የምለው፣ እንጂ የጋዜጠኛው ማስታወሻን ስለወደድኩልት ብቻ አይደለም።
የብርሀኑ ዘርይሁንን ቀደምት ስራዎች ብታነብ እውን እሱ ነው እንዲህ ደርቶ ደርቶ የጻፈው ብለህ ትገረማለህ ::
ሁለቱን መድብሎች አንብቤአቸዋለሁ።
vበኔ ግምት ተስፋዬን ምልኡ በኩልሄ ያደረግከው ይመስለኛል ::
ግምትህ የተሳሳተ ነው። የጋዜጠኛው ማስታዋሻ እንደ ቡርቃ በፓስወርድ መነጽር ስር ቢውል ብዙ እንከን ይገኝበት ይሆናል ብዬ እገምታለሁ። የማስታወሻ ጽሁፍ ውስጥ ንግግሮች፣ በመቀርጸ ድምጽ ካልተቀዱ በቀር፣ እንዲህ ቃል በቃል የመጻፋቸው ጉዳይ የሚያሰነሳው ጥያቄ አለ ብዬ ከሚያምኑት ወገን ነኝ።
ተስፋዬ ያንን መጽሀፍ በመጻፉ ምን ያህል እንደሚኮራና ለስደት ካበቁትም ጉዳዮች አንዱ እንደሆነ በጋዜጠኛው ማስታወሻ ላይ በግልጽ አስቀምጦታል ገጽ 225
ተስፋዬ በቡርቃ ስራ ላይ የፈጽመውን ስህተት አሁንም የተረዳው አይመስልም፣ ስለዚህ መኩራራቱን ሊቀጥል ይችላል። ራስህን ማየት በጣም ከባድ ነው። ፊትህን የምታይበት አንድ ጥሩ መስታወትና መስታወት የሚይዝልህ ደህና ወዳጅ ያስፈልግሀል። በዚህ መጽሀፍ ማን ምን እንደሚጠቀም ሊያስረዳ የሚችል አይመስለኝም። የባድሜው ግጭት የተፈጠረ ሰሞን ወያኔ ብአጠቃላይ የኢትዮፕያን በተለይ ደግሞ የትግራይን ህዝብ ለማነሳሳት የተጠቀመበት የቅስቀሳ ስልት ሁላችንንም ያስደመመ ነበር። የአቶ ገብሩን ንግግር ያስታውሱዋል። ኤርትራዊያን 'ለአንድ ሺ ዝንብ አንድ ፍሊት ይበቃዋል።" ይላሉ....
በሚሊዮን የሚቆጠር ኤርትራዊያንና በትውልደ ኤርትራዊ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደርስባቸው የበቀል እርምጃ ግድ ያልነበርው ስድ ንግግር ነበር።
ይህን ሲስማ ተስፋዬ ምን ተሰምቶት ይሆን? በዚያን ስሞን በመንግስት መገናኛ ሚዲያ ይተላለፍ የነበርው ለጆሮ የሚቀፍ ቅስቃሳ አይዘነጋም።
ኤርትረዊያን የአማራ፣ የኦሮሞ ለተለይም የትግራይ ህዝብ ላይ ንቀት አላቸው የሚል ሀላፊነት በጎደለው መልኩ ይዘከዘክ ነበር። አላማው በወቅቱ የህዝብን የጥላቻና የበቀል ስሜት ለመቀስቀስ ነበር። ያንን ተስፋዬ እንዴት ያየው ይሆን? የሱስ ቡርቃ ከዚያ በምን ይለያል? ቡርቃ ሰዎችን ለበቀል የሚያነሳሳ ይዘት የለውም? አንዳንዴ እንኩዋን ህዝባችን ፊደል አልቆጠረ ያሰኛል። ፊደል ቆጥሮ የትኛውን የረባ ነገር ሊያነብ!
ክንፈ ሰበብ ፈጥሮ እኔን ከሀገር እንዲያባርር መታዘዙን ጠረጠርኩ :: የቡርቃ ዝምታም አልተመቻቸውም ::
አቶም ቦንብን የፈጠሩ ሳይንቲስቶች ቦንቡ የሚያስከትለውን ጥፋት ካስተዋሉ በሁዋላ መልሰው ሊያጠፉት መጣራቸውን ታውቃለህ ብዬ እገምታለሁ። አነ ክንፈ የብሄርስቦችን መቃቃር የሚፈልጉት በተወሰነ መጠን ይመስለኛል። ለአገዛዛቸው በሚመች መጠ። አንሱ በሚገዝዋት ኢትዮጵያ ሁዋላ ሊያቆሙት የማይቻላቸው የጎሳ ጦርነት እንዲቀጣጠል አይፈልጉም። የሚፈልጉት በልክ ነው። የተስፋዬ "ዶስ" የበዛባቸው ይመስለኛል እና አልወደዱትም።
አንተ ደሞ ሽንጥህን ገትረህ የምትከራከረው ይሄ ርካሽ ፕሮፓጋንዳ በሌሎች ሰዎች ተስፋዬ ላይ እንደተጫነ እንጂ የተስፋዬ አማርኛ እንዳልሆነ ነው ::
በእንድ አማርኛ ተናጋሪ ሊባል የማይችል ሀረግ ሳነብ ምን ልበል? እስኪ ይሄን እይ።
ጂብሪል፣ ምንም እንኩዋ የስራተኛው ፓርቲ አባል ቢሆንም ብዙውን ጊዜ የታዘዘውን እንደ ጥሩንባ ከማስተጋባት የተቆጠበ ....
እግዜር ያሳይህ አንተስ ብትሆን እንዲህ አይንት አረፍተ ነገር ስታነብ አማርኛ ተናጋሪ አልጻፈውም ብለህ አትጠራጠርም። አንድ ቦታ አንቱ ያለውን ገጸባህሪ ሌላ ቦታ አንተ የሚለው ከሆነ ምናልባት ደራሲያኑ ከሁለት በላይ ይሆናሉ አትልም? ለምሳሌ፣ አንቱ ሲባል የነበረውን ፕ/ መንግስቱ ገጽ 252 ላይ አንተ ብሎታል።
ይህ የተስፋዬን ማንነት በደንብ ካለመረዳት ወይም you are overwhelmingly charmed by his recent book.
ከማንነቱ ጉዳይ የለኝም። And I have enormous respect for his resent book both as a literary work and source of vital information.
አንተ ስታስበው እንዲህ አይነት ተራ ፕሮፓጋንዳ መጻፍ ባይችል ኖሮ , ከትምህርት ትምህርት ሳይኖረው , ከልምድ የታጋይነት ልምድ ሳይኖረው (ወያኔን የተቀላቀለው በሰማኒያዎቹ መጀመሪያ እንደሆነ ተናግሩዋል ) ባንዴ የኢትዮ ፕሬስ ዋና ስ /አስኪያጅ ሊሆን እንዴት ይችላል ብለህ ታስባለህ ?
የኢህአዴግ ሹመት አስጣጥ መስፈርት ቅድሚያ የሚሰጠው ታማኝነትን እንደሆነ አባላቱ አይደብቁም። የፕሬስ መምሪያን ለመቆጣጠር ተራ ፕሮፓጋንዳ መጻፍ የሚችል ሰው ሳይሆን አንድ እሺ ባይ ነው የሚያስፈልግህ። አቶ ታምራት ተስፋዬን ሲሾሙት እሺ ባይነቱን እንጂ ለትምህርቱ ግድ አልነበራቸውም። እሳቸውም ቢሆኑ እንኩዋን አገር አንድ አውራጃ ለማስተዳደር የሚያበቃ ትምህርት የነበራቸው አይመስለኝም።
so, I'm afraid you are misleading your readers when it comes to who was behind this 'crap'.
I was simply entertaining my right to share my opinion with warka mates. Readers are entitled to freely form theirs opinion as well. "Misleading" is not the right word here.
It was written by Tesfaye and only by Tesfaye with his consent to fulfill Afeworki's 100-years homework for Ethiopia.
This is a serious allegation. If you really meant you words, you will be required to come up with a convincing evidence. I 'm sure your allegation is not based on the simple fact that Tesfaye is born to Eritrean parents.
ብርሀነ ትንሳኤው ለሁላችንም ።