ጊዜ እና ሕይወት :
ሕይወት ገና በተሲዐት በቁም አንቀላፍታ
"'በጊዜ"" ተረታ ""ለጊዜ"' እጂ ሰጥታ
ዛቢያዋን- መሽከርከሪያ ምህዋሯን ስታ
ስታዘግም በሰው ምህዋር ""በጊዜ"" ባለፋንታ
እንበለ ሀገር; በሰው ቀየ-በሰው ቦታ;
""ጊዜ"" ግን ይሮጣል
የልቡን ይሰራል
ሕይወትን ገትሮ እንደጉድ ይበራል
ዘመን ይቆልላል::
እንዲያ እየከነፈ;
አንዳንዱን ያነሳል
አንዳንዱን ይጥላል
አንዳንዱን ይክባል
አንዳንዱን ይንዳል::
ሕይወት ብርቱ! እንደምንም ብላ ምህዋሯን ብታገኝ
""ጊዜ"" እንደሁ አይተዋት; መሽከርከሪያ ጊዜ እንደልብ አይገኝ::
ሚያዚያ 25, 2001 ዓ.ም
ቶሮንቶ
(ጊዜ ለባከነባቸው እና ለተፈናቀሉ)