አለመሞት
እንደተለመደው ሁሉ ተፈጥሮ እንዳስለመደን ሁሉ ዛሬ ነግቶ እና እረፍዶ መመሻሸት ጀምሮዋል:: የጉለሌን ሠፈር ዳመና ተጭኗታል ድንገት በመሀል እያጮለቀች ብቅ የምትለው ፀሐይቱ እንኳን ጉለሌን ኪልኪላ ልታደርጋት ብትሞክር ጉለሌ ግን ዛሬን ለመሣቅ የፈለገች አትመስልም:: በአሕያ ኮቴዎች የሚቀበቀበው አዋራማ መሬቷ ዛሬ በድንነቱ ከብዷል ዛፎቹ ሀዘን እንዳጠለኡ ሁሉ ተከፍተው ይሁን ተኮፍሠው በለሆሣስ ይወዛወዛሉ::
ሳጋዬ ይሁን ነፍሴ አላወቅኩም ብቻ ሲጋራ እንዳሰኘኝ ሁሉ ዓይኖቼ እምባ አቁረው እስኪያፈሱ ደጋግሜ አዛጋለው... ሳዛጋ አፌ ተመልሶ የማይገጥም እየመሰለኝ በቅፅበታዊ ስጋቴ እገረማለው::ፊቴን በመስታወት ሳላየው ቀለም አልባ ድባብ አልባ ገፅታ እንደተነበበብኝ ታውቆናል አሁን ግን የተዛባ ስሜትና ገጼን በሲጋራ ጪሳ ላስተካክለው እየሄድኩኝ ነው: ጥቂት መንገድ የሸኙኝ ሠዎች ነበሩ... ለምን እንደሸኙኝ ትዝ አይለኝም::
ጥቂት የመንደሬን መንገድ ተራምጄ ከልጅነት እስከዕውቀት ድረስ አብሮኝ ያደገዉን ወይም እንደኔ ሠውነት እየጠበበ የመጣዉን የሠፈራችንን ቅርፅ አልባ ሜዳ ላይ ደረስኩኝ እዛ የደረስኩት ሡቆች ሁሉ በመዘጋታቸው ነው::
የማውቃቸው የሠፈር ሠውች ሁሉ በየአቅጣጫው በመቻኮል ይተማሉ...ከሜዳው ፈንጠር ብሎ ያለው ጉሊት ሳይቀር በችኮላ ግርግሩ ነግሶዋል ሻጮች ዕቃዎቻቸዉን እያሠሩ ነው:: ምናልባት ኃይለኛ ዝናብ መጥቶ ይሆን ብዬ ወደሠማይ አንጋጠጥኩኝ: በእርግጥ ዳመና ቢሆንም ሠማዩ ዝናብ ሊያፈስ የተዘጋጀ አይመስልም::
በዓይኖቼ ስማትር መጠየቅም መጠየቅም የሚፈልግ ሠው አጣው:: ከእንቅልፌ ያልባነንኩኝ ዓይነት ስሜት ሁሉ የሠፈራችን ኃይሌ በያጁ የወጠረዉን አልጋ አላልቶ ዕቃዎቹን ወደውስጥ ያገባባል ከመበየጃ ቤቱ ጎን ቁመትና ወርዷ የቀጭን ሠው የምታክል መጠነኛ ሸቀጦች የታጎሩባት ሡቅ ቢጤ ውስጥ ያለች ቀጫጫ ሚስቱ ዕቃዎቹን በከረጢት ነገር እየከታተተች ነው::
እንሠሳቱ ድመትና ውሾች ሳይቀሩ ጆሮዎቻቸውን አቁመው ጭራቻእዉን በውኃላ እግሮቻቸው መሀል አሾልከው ወደ ሆዳቸው ልጥፍ አድርገዉና እግሮቻቸውን የፍረሀት ሠብስበው እንደለላ ቀን ከመጣላት ይልቅ ወደ ሠማይ አፍጥጠው ይመለከታሉ:: የነርሱን ዓይኖች ተከትዬ ድጋሚ አንጋጠጥኩኝ... ምንም የተቀየረ ነገር የለም: ያው ቅድም ያየዉት ሠማይ ነው::
ወደ ጀማል ሡቅ ጠጋ አልኩኝና ተዘግቶ የማያውቀዉን በር አይሉት መስኮት ብቻ አንድ የሚዛገ አሁን የተዘጋ ነገር ቀበቀብኩኝ... ዛሬ ከሱቁ ጀርባ ሁሌም ምሠማው መንዙማ ወይም ሀዲስ የለም ፀጥታ ሆኗል:: አንኳኳው... ደገምኩኝ.... እጄን ሲደክመው በሣንቲም አንኳኳው አሁን ድምፅ ሠማው
''ዛሬ አልከፍትም!''
ነጭናጫና አጭር መልስ
''ምነው ዛሬ ያለወትሮህ ዘጋህ...?''
''ከዚህ ሕዝብ ሁሉ መሀል ጀማል ነው የታየህ...?
ብሎ ወደ ፀጥታው ተመለሠ.... ምን እያደረገ ይሆን... እርግጠኛ ነኝ ዛሬ የሻይቅጠል ወረቀት እየጠቀለለ ወይም በሻማ ፍም ለውዝ በላስቲክ እያሸገ አይደለም::
የእናት ምግብ ቤት አሳላፊዎች የጠራ ገዋናቸዉን እንደለበሡ ያልተብጠረ ጨብራራ ፀጕራቸዉን እንዳንጨባረሩ በአጠገቤ አለፉ ደረት ኪሶቻቸው ውስጥ ባለ 3ጥርስ ሹካ እንደእስክሪፕቶ ሠክተው በመቻኮል ይራመዳሉ ልጠይቃቸው አልኩና ፍጥነታቸው ከኔ ማመንታት ጋር አልመጣጠን አለ:: ከውኃላቸው አንድ ሕፃን ጠርዞቻቸው ተቆልምመው ክብ የመሠሉ አዳፋ ደብተሮቹን ይዞ ይከተላቸዋል
''ማሙሽ...''
ጠራዉት ጥርዬ ግን ይባሱኑ አስሮጠው እንጂ ዞርም አላለ:: የጉለሌን አድባር እየለመኑ የሠፈራችንን አስፓልት ጫፍ የሙጢኝ ብለው ያረጁት እማማ አስናቁን ቡቱቶዋቸዉን ከጀርባቸው እንደተሸከሙ በከዘራቸው ቆልማማ አቋማቸዉን ለማቅናት እየታገሉ ሲመጡ አየዋቸው... እሳቸው እንኳን አያመልጡኝም አልኩና ተዘጋጅቼ ጠበቅኳቸው::
''እማማ አስናቁ ዛሬ ምንድነው ሠዉ ሁሉ አልተረጋጋም እርሶም የደነገጡ ይመስላሉ ሠላም አይደለም...?''
አልኳቸው:
''የጉለሌ አድባር ይጠብቀን ልጄ እሱ ይታረቀን... ሌላ ምን ይባላል ምነው አትጠቅምም አሮጊት ናት ብለህ ነው... ሞኞ ማምሻም ዕድመ ነው:''
ብለው ለጥያቄዬ መልስ ሳይሠጡኝ ጥለዉኝ ሄዱ አሁን እኔም መፍራት ወይም መሸሽ ወይም መቸኮል ፈለግኩኝ ግን ከምን? ...ለምን? ውስጤ ገና መደንገጥ አልጀመረም ፍረሃት በንክኪ ወይም በትንፋሽ አይተላለፍ...???
ሁለት ሠዎች ዓይኖቻቸው አብጠው በሐዘን ያዜማሉ ዜማው ያሬዳዊም ሞዛርታዊም አይደለም የለቅሶ ይሁን የምስጋና የልመና ይሆን የፉከራ አያስታውቅም የዜማው አወራረድ ግን አንዳች የተለየ ስሜት ይሠጣል በጥቋቁር ሸሚዞቻቸው ኮሌታ ጫፍከአበጡ የዓይኖቻቸው ቁብ ስር የረጠበ እምባቸዉን እየጠረጉ ቅላሴያቸዉን ይቃኛሉ::
ወደ 8 የሚሆኑ ቅጠል ተሸካሚ አሕዮች ግማሾቹ አንድ አንድ ግማሾቹ ሁለት ሁለትና ከዛም በላይ ሠውች ጭነው ይሮጣሉ ሁሉም ሚያዘግመው ወደ ቤተክርስቲያን ነው የቤተክርስቲያኑ ደውል ከሩቅ ይሠማል አሕዮቹ ላይ የተጫኑት ሠዎች መግረፊያዎች አሊያዙም አሕዮቹ ግን ጆሮዋቸዉን አቁመው ይከንፋሉ የሠዎቹ ጆሮ ቆሞ ይሆን ብዬ ለማየት መሞከሬ ፈገግ አስብለኝ በርግጥ የሠው ጆሮ ሲቆም ያስታውቅ ይሆን?
አንድ ሽበት ወጋ ወጋ ያደረገው የሠፈራችን ሠው ከማዶ ሲመታ አየዉት በቅርቡ ነው ሠፈራችን ቤት ተከራይቶ መኖር የጀመረው እሱ ግን ሠዎች ወደሚሸሹበት ወይም ውደሚሮጡበት ሳይሆን እየመጣ ያለው ወደተቃራኒው ነው:: ስሙ ጠፍቶኛል
''ይቅርታ ጋሽ.....ምንድነው ችግሩ ሠዉ ሁሉ ለምንድነው የሚራወጠው?''
''ምነው ጎበዝ ሲያዩህ ትልቅ ሠው ትመስላለህ... ነው ወይስ ዓይነ ስውር ነህ...? ከቤተ መንግስት አንበሶች ተለቀቁ... ልበልህ ወይስ እሳተ-ጎመራ ሠፈራችን ፈነዳ እንድልህ ፈለግክ...?''
በድፍርስ ዓይኖቹ ገላምጦኝ መንገዱን ቀጠለ
''እሺህ ልከተልህ...?''
አሁን ፍረሃቱ በቀስታ ሊጋባብኝ እንደሆነ ታወቀኝ
''ይልቅ ቶሎ በልና ራስህን ተከተለው''
ብሎኝ የቅድሙን ግልምጫ ሳይዞር ደግሞት ፍጥነቱን ጨመረ::
በሠፈራችን ውስጥ ብረት በመግፋት በሶ በመጠጣት ተወዳዳሪ ያልተገኘላቸው ጡንቸኞች ፊታቸው ጠቁሮ ጡንቾቻቸው ብቻ ተወጥሮ በፍረሀት እየፈጠኑ ይሮጣሉ እነሱንስ ደፍሬም አልጠይቅ አልኩኝ ለራሴ ከውኃላቸው ሱክ ሱክ የሚለውን ተሸካሚ የተሸከመዉ እሕል እንደከበደው ፊቱን ቋጥሮ ሹክክ ብሎ ሲያየኝ
''ምነው ለምን ተጣደፍክ?''
አልኩት
''በሶ ነው የያዝኩት ''
አለን ያልጠየቅኩትን
''ምን?''
አልኩት ግራ እንደገባኝ
''በሶ ነው የነሱ ነው...''
እያለ ፍጠነቱን ከነሱ እኩል ለማድረግ ገሠገሠ:: ቅፅበታዊ ድንጋጤ ውስጤን ሲሰማኝ ደግሞ ይጋባብኝ ይሆን ብዬ አስቤ ወደነበረው ስሜቴ ራሴን ለመመለስ ስታገል አባ ወልደዮሐንስ በአንድ ዓይናቸው ውደደመናው እያዩ የብር መስቀላቸዉን በቀኝ እጃቸው እንደጨበጡ እርሳቸዉም እንደሁሉ ሲጣደፉ አየዋቸው::
''እንደምን ዋሉ አባ... እስቲ ይባርኩኝ''
አልኳቸው መንገዱን ዘግቼባቸው ወገቤን በመቀንጠስ: ከሠጠሙበት ፍረሀት ድንገት ነቁና አንድ ዓይናቸዉን ከዳመናው ነቅለው ወደኔ እየወረወሩ
''ድሕና እንድልህ ተፈልጋለህ... በዛሬ ቀን ባርኩኝ የምትል እኔን መፈታተንህ ነው? ለነፍሴ ባድርም ያንት ዓይነት በስባሳ ስጋ መሸከሜን አትርሳ...''
አሉኝ ጫን በሚል አማርናቸው: የማያየው ዓይናቸዉን ትኩር ብዬ ሳየው ከሚያዠው እንባቸው ጋር ታግሎ የዛሬዉን ጉድ ለማየት እሱም በድንነቱ ረስቶ የሚንቀዠቀዥ መሰለኝ
''አባ እርስዎ የእግዚያብሔር ሠው ኖት ዛሬ ከእርስዎ መልስ ካላገኘው ማንም ሊረዳኝ አይችልም የተፈጥረዉን ሊነግሩኝ ይችላሉ...?''
አልኳቸው ወደጎን እየሸሹኝ ጥቁር ረጅም ቀሚሳቸዉን እየሰበሰቡ ሲያዩኝ
''ነፍሱን ያለ ጌታ ፈቃድ እንዲወጣ የሚፈቅድ ሁሉ በሠማይ ቤት እንደሚጠየቅ አታውቅም?''
ብለዉኝ በመስቀላቸው እያስፈራሩኝ ሩጫቸዉን ቀጠሉ: አባ ከመጡበት መንገድ ሌሎች የሠፋርችን 8 ሴቶች ነጠላቸዉን አንጠላፍተው ይሁን አዘቅዝቀው በማያስታውቅ አለባበስለብሠው እየተቻኮሉ ይመጣሉ በሠፈሩ ውስጥ የታወቁ አሜቴኞች ናቸው:: ዛሬ ግን የነርሱም ፊቶች ደነጋግጠዋል ዓይኖቻቸው ለወሬ ቢስገበገቡም ድንጋጠው አሸንፏቸዋል የተወሰኑት ንብረትነቱ የሴቶች ዕድር የሆኑ የምግብ ማብሠያ ዕቃዎች ይዘዋሉ... ከእድር ይሆን ሚመጡት ብዬ አሰብኩኝ አሁን ትኩር ብዬ ሳያቸው ነጠላዎቻቸው ተዘቅዝቀዋሉ:: ወደ እኔ ሲቀርቡ ከመዐላቸው ለእኔ ሚቀርቡትን የጌይዶን እናትን ከመሀል ነጥዬ
''የጌዶን እናት... ምነው ተጣደፋችሁሳ?''
አልኳቸው
''ምነው እሷ ሞት ትፈራለች ብለው ነገሩህ እንዴ...?''
ብለውኝ በቸልተኝነት አለፉኝ: አሁን አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ ሀሰብኩኝ እንደሠዉ ለምፍራት የግዴታ ምክኒያት ያስፈልገኛል እንደሁሉም ለመሸሽ ያባረረኝን ነገር ማወቅ ይኖርብኛል... ስለዚህ ከአሁን በኌላ ጥያቄዬን መቀየር አለብኝ ብዬ ወሠንኩኝ::
አንዱ ከጉሊቱ ወደ እኔ ሲመጣ አየውት: አንገቱ ላይ የሞቱና በነፍስ የሚኳኩሉ ዶሮውች እንደ ተሸላሚ ሯጭ አንገቱ ዙሪያ አንገቷል::አጠገቤ ሲደርስ
''ምነው ዛሬ ደስ ደስ ያለህ ትመስላለህ?''
አልኩት:: ከሚያስካኩ ዶሮውች ሚረገበገብ ክንፍ ራሱን ዘምበል አድርጎ አየኝና ባቄላ የሚያካክሉ ጥርሶቹን አሳየኝ... ከብናኝ ተዶሮ ትንንሽ ላባዎች ከቃሙ የነዠረገገ ፂሙ መሀል ብቅ ያለዉን ባቄላዊ ፈገግታ ሳይ አሁን የቀየርኩት ዘዴ እንደሠራ ተሠማኝ: ወዲያው ፈገግታዉን ከሱ ወስጄ እኔም እንደጅል ገለፈጥኩለት ፈገግታ ጠኔ የሆነበት ጊዜ ብዬ ተገረምኩኝ...
''ጥያቄህን ወድጄዋለሁ ቢሆንም ግን የእነዚህ ዶሮውች ማንነት ቤት ገብቼ ማጣራት አለብኝ ገና ከሁሉም ጋር ረጅም ቃለመጠይቅ እናደርጋለን:: ስለዚህ ሠዓት አይበቃኝም በርግጥ በቂ ሠዓት እንኳን ባገኝ ሌላ በቂ ሠዓት ለመፈለግ መጀመሬ አይቀርም ስለ ጊዜ የያዝኳቸው ድርዎችም ከእኔ የተለየ ግምት የላቸዉም ሌሊት ሲጮኹ የነበሩት ሁሉ ዛሬ ቀን ሲጮኹ ነበር ገና ብዙ ጩኸቶች እንደሚጠበቅባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ...''
ላቋርጠው ፈለግኩና ምንኛ በስሜት ተመስጦ ማውራቱን አስተውዬ ፈዝዤ ማየቴን ቀጠልክኩኝ
''በነገራችን ላይ ዶሮውች የሚበሉትን እንደሚቆጥሩ ታውቃለህ? ሂሣብና ሠዓትም ያውቃሉ ሲዞሩና ሲራመዱም ልክ እንደ ኤሌክትሮኒክስ በዲጂታል እንቅስቃሴ ነው: አንስታይን ደብቆን ነው እንጂ ዶሮውች የቅርብ ጓደኞቹ ነበሩ ይሄንን የሚያውቅ የሠው ዘር የለም ለኔም የነገሩኝ እነኚህ ዶሮውች ናቸው ማንም ዶሮ የቅድመ ሀያቶቹን ምንነት የማወቅ ግዴታ አለበት ስለዚህ ስለነበረው ሁሉ ያውቃሉ... መተንበይ ግን ከፈጣሪያቸው የሚሠጣቸው ችሎታ ነው ... እድግሞ'ኮ እንዴት የዋህ መሠሉህ ወንዱ ዶሮ ሚስቱን ይጋብዝሀል አንተ ግን ሠው ስለሆንክ ምንም አታደርግም አይደል? ይሄን ተገንዝባ ሴቷ ከባሏ ያረገዘችዉን እንቁላል ታበረክትልሀለች ይሄ ምነገርህ Bእሕይወት እስካሉ ፍቅራቸዉን ሚገልፁበት መንገድ ነው በኌላ ግን ሕይወታቸዉን ሠጥተው ላንተ ሆድ ሙላት መሠዋት ሆነው ያልፋሉ:: ''
የመጨረሻዉን ዐረፍተነገር ሲናገር ዓይኖቹ በእምባ ተሞሉ::
''ከዶርዎችህ ጋር ክፉኛ የተቀራረብክ ትመስላለህ''
አልኩት ዝም ላለማለት ያህል ውስጤ በርሱ ንግግር ቢገረምም የዛሬዉን ውዥንብር ምንነት ለማወቅ እንደተስገበገበ ነበር::
''ሕይወት ነው ወንድሜ...''
አለኝ የሾሉ የድሮዎቹ ጥፍሮች ክንዱን ሲቧጥጡት እያሸሸ
''ከድሮ ጋር ፍቅር ይዞሀል...''
''ፍቅር የያዘኝ ከማወቅ ጋር ነው ይሄ ደግሞ ግዴታዬም ነው አይዞህ ሁሉንም ነገር ትደርስበታለህ...''
ብሎ እየሳቀብኝ ሄደ
''ቆይ እንጂ ምጠይቅህ ጥያቄ አለኝ'ኮ?''
አልኩት እንደመከትል ብዬ
''እዚህ መንገድ ላይ እንደ ዐቡነጴጥሮስ ሀውልት ደርቀህ ትቀራለህ እንጂ ስለዛሬው የሚነግርህ አታገኝም..
አለኝ ሳይዞር ድሮዎቹ ክንፋቸውን እያፍታቱ መኮከል ጀመሩ ሩቅ ከሄደ በኌላ ዞሮ በግንባሩ አየኝና ድምጹን ከፍ አድርጎ
''ላወቀባት እቺ ቀን ውብ ናት ሠዎች ስንባል ውበት የት እንዳለ አናውቅም...''
አለኝ:: ዕብድ ይሆን ብዬ አሰብኩን ማረጋገጫ ግን አልነበረኝም ለመሆኑ የሠው ዕብደት መመዘኛው ምን ይሆን ለየት ማለት? ይህ አይሆንም ከራሴ ጋር ስሟገት አንዱ አጠገቤ ደርሶ
''ወንድሜ ራዲዮን ይዘሀል?''
አለኝ:: አንድ ክንዱ ሠው ሠራሽ ነው
''ከመቼ ጀምሮ ነው ደግም ሠው ራዲዮን ይዞ የሚዞረው?''
አልኩት ንድድ ብሎኝ
''ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ''
አለኝ ለዛ በሌለው ሳቅ ታጅቦ
''ቀልድህን አልወደድኩትም''
አልኩት የተንከረፈፈ ላስቲ እጁን እያየው ነቅዬበት ግንባሩን ብቀውረው ተመኘው
''እኔ መች ግዛኝ አልኩህ?''
ወሬ ማብዛት አልፈለግኩም
''ስለ ፍረሀት የምትለኝ ነገር አለ?''
አልኩት ፈጠን ብዬ
''ራዲዮ የጠየቅኩህ ለሱ ነበር''
አለኝ የፊቱ ሞዛዛ ሳቅ ወደ ሀዘን እያጠላ እንደኔ ግራ የተጋባ መሆኑን አስተዋልኩኝ ትኩር ብዬ ሳየው አንደኛው እግሩ አጭር ነው ከለላኛው ጤነኛ እግሩ ጋር ለማመጣጠን ከፍታው የገነ ትልቅ ጫማ አጥልቋል
''ቀናተና ነህ... ፍረሀቴን ልታባብስ ነው አይደል እኔ እንደሆን አልፈራም ብፈራስ የትኛዉን ሙሉ አከላቴን ላድን..''
እያለ ላስቲክ ክንዱን እና ባለ ፎቅ ተረከዝ ጫማዉን አሳየኝ: እንባዎቹ ፊቱ ላይ ኩልል ብለው ወረዱ
''ተረጋጋ ወንድሜ''
አልኩት ታግዬ ያቆየዉትን የራሴን መረጋጋት እንዳያደፈርስብኝ በመታገል
''እኔ አልፈራም አልፈራም!''
እየፎከረ በአጭርና ረጅም ቅልጥሞቹ እንጣጥ እንጣጥ ብሎ ከፊቴ ተሠወረ::
ወደቤቴ ለመመለስ ፈልጌ ስጋት ያዘኝ ዛሬ አንድ ያማላውቀው ሠልፍ እንዳመለጠኝ ተሠማኝ ማንም ሊነግረኝ የቻለ የለም ባለዶሮው ሠውዬው ያልኝን ማመን አለብኝ ወደበቴ የሚወስደዉን አቅጣጫ እንደያዝኩኝ ድንገት ዓይኖቼ ከቀበሌያችን ብሎኬት ግንብ ላይ የተለጠፈው ማስታወቂያዎች ላይ አረፈ :
ዝግ የስራ ማስታወቂያ የሚለው ጎልቶ ይነበባል ማንበቤን ቀጠልኩኝ
...የሥራው መጠሪያ ኮከብ ቆጠራ
አስፈላጊ ማስረጃ - ከታወቀ ቤተ -ጠንቋይ ዲፕሎማ ያለው /ያላት ወይም ሲፈጠር ጀምሮ በሙያው መስክ ያገለገለ /ለች
ቦታው . ብረሐን በሌለበት
ዕድሜ ለአቅመ ማወቅ የደረሰ /ሰች
አመልካቾች ይህ የሥራ ማስታወቂያ ከመውጣቱ 13 ቀን ተኩል በፊት ቀድመው ማመልከት ነበረባቸው : አንብቤው እንደጨረስኩኝ ልክ እችለው ይመስል ወይም ማስረጃው በእጄ እንዳለ ሁሉ ተቆጨው ፈገግ አልኩና 'ይሄንን ማስታወቂያ ያ ባለ ዶሮ መሆን አለበት የለጠፈው ብዬ አሠብኩኝ ' ከጎኑ ሌላ ማስታወቂያ አየው
ገርበብ ያለ የሥራ ማስታወቂያ የሚል በትልቁ ሳይ ቢያንስ ይሄ ይሻላል አልተዘጋም አልኩኝ ::
የሥራው መጠሪያ ውሸታም
አስፈላጊ ማስረጃ ከታወቁ ድርጅቶችና ግለሠቦች ንብረት ወስዶ /ስዳ የካደ /ከደች
ቦታው አያስፈልግም
ዕድሜ በማንኛዉም የዕድሜ ክልል ሆኖ ጷጕሜ 8 የተወለደ
ደሞዝ . በሠራዉና በዋሸው ሐሠት መጠን የነበረበት ዐጢያት ይሠረዝለታል ::
ይልና ድርጅቱ ብሎ ከስር ዝርክርክ ባለ ፊርማ ማስታወቂያው ይዘጋል
3ኛ ሌላ ማስታወቂያ አየው
የስብሠባ ጥሪ ይላል ይሄ ደግሞ
ጉዳዩ በምድር ላይ እያሉ ኑሮዋቸው ያልተመቻቸዉን ሁሉ ይመለከታል :
ክቡራን እና ክቡራት የማሕበሩ አባላት በሙሉ ቀኑ ከላይ በተጠቀሠበት ዕለት ከቀትር 13 መቶ ሠዓት ላይ መሐበሩ የተመሠረተበትን የ 100ኛ ዓመት የወርቅ እዩቤልዩ በሀል ስለሚያከብር እንድትገኙ ያመለክታል
ይልና ወደታች ፈንጠር ብሎ ለማልቀስ ለማዘን ለማግጠጥ ለመበሣጨትና ለማኵረፍ ነውና የተፈጠርነው ኑና አብረን ሁሉን እንሁን በሚል ፅሑፍ ማስታወቂያው ይዘጋል ምናልባት የተመዘገቡና ሥብሠባው የሚያገባቸው ሠዎች ይሆን ተደናግጠው ሲሄዱ የማያቸው ? አንዲት መልኳ ብዙም ባይሆን ቆንጀት ያለች ሴት ማስታወቂያዉን አንብባ ስትጨርስ ተመለከተችኝ አላስተዋልኳትም እንጂ አጠገበ ነበረች
''እንተዋወቅ...''
አልኩና እጄን ዘረጋዉላት አልጨበጠችኝም
''ስለ ጊዜ የምታውቀው ምስጢር አለ?''
እጄን አንከርፍፌ ስላስቀረው አናዳናለች ስታወራ ሢጋራ ያወፈረው ድምጿ ይነዝራል
''ሲጋራ ይዘሻል...?''
አልኳት: ድንገት ስለሢጋራ ሳስብ ሡሴ ከስር እየቆነጠጠኝ
''ጊዜ ባንተ ውስጥ ምን ያህል ስልጣን ያለው ይመስልሀል?''
.
.
.
አላለቀም ቀሪዉን ለማነበ እቺን ይጫኑ