ቶሮንቶ ዳግም በሳቅ ሊፈነዳ ነው!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሊስትሮው » Tue Aug 25, 2009 5:26 pm

brookk wrote:ሊስትሮው
ምናለ ቢደማህ ? ትቀልዳለህ
ሜዳና አዳራሽ አሁን ምን ልዩነት አላቸው ? አዳራሹም ሰፊ --- ሜዳውም ልቅ
እኛ የለመድነው --- ሰው ሳያየን -- ሳይታዘበን ወደውስጥ ገባ ብለን --- ጠበብ ያለውጋ ነው --- ስቅስቅ ብለን ምናፈሰው አባ! ዕንባችንን

በረሮማ ደከመች -- አረጀች እሷም --- ሄዶ ሄዶ መቼም ማርጀት አይቀር :lol: :lol: ተለወጠች እንደድሮም መዝለል ተወች
ቢሆንም በጣሙን ናፍቃሀለች --- እራስህን በራስህ በሷ ስም እንድትስምም ጋብዛሀለች
በል ኢንጆይ ዩርሰልፍ

በነገራችን ላይ ሰሞኑን በጣም ተከስተናል -- አትጥፋ
አርዕስቱን ግን አትርሳ --- ቶሮንቶ ዳግም በሳቅ ሊፈነዳ ነው - ነው የሚለው :: ከለቅሶው በኋላ ሳቅ በሳቅ ሆነን ነበር --- ጣዕሙንም በአካል አየሁት --- ማለፊያ ልጅ ነው ቅቅቅ ክርስትያኖ ድምጡ አልተሰማም :: እኔም ስልክ አልመታሁም --- ግን አዳራሹ ውስጥ ስጣራ ነበር -- ብቅ ብለው አስተያየት ቢሰጡ ብዬ ነበር --- እነሱ እንደኔ ስራ የፈቱ አይመስልም :lol:
ድራማው የተጀመረበት ሰዐት ግን በአበሻው አቆጣጠር ነበር :lol: :lol: ግን በዝግጅቱ ተካስን


አባው እነ በረሮ ባረጁበት ዘመን አንተ ጨዋታህ አልቀነሰም ባክህ ቅቅቅ ሰፊ ጠባብ እያልክ ተያይዘሀዋል ቅቅቅ ዋንው ሁለቱም ላይ መጨፈሩ ላይ ነው ቁምነገር ንባን ተቆጣጥሮ :) ..... የቀጠሮ ነገርንማ ተወው ግን በዝግጅቱ ተካስክ ዋና ሱም አይደል ስኪ ንግዲ ኛም ወንዙ ሞልቶ አላሻግር ብሎን ንጂ ከች ልንል ነበር ስቲ ማለፊያ ካለው ንሞክራለን ......... :arrow:
ሊስትሮው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 233
Joined: Tue Feb 03, 2004 11:30 pm

ቅቅቅ

Postby ዋኖስ » Fri Aug 28, 2009 4:19 pm

አይ! ቡሩኬ! መች አንተ ዙሪያ ገባህን ታይና! ዓይንህ ምን እንደሚያይ እኔ እንጃ ያን ዕለት እኮ! ሰክሬት ሻፐር ሆኜ በመዋሌ ደስተኛ ነበርኩ! ቅቅቅቅ ከነ አለባበስህ ነው ስመለስ የምስልህ! ቅቅቅ


ጣዕሙ ግን ሳያኮርፈኝ አይቀርም! "ቡፍ" ሳልል በመምጣቴ ቅቅቅቅ...

ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ጣዕም » Mon Aug 31, 2009 5:10 am

ሰላም ሰላም ብሩኬ
ደህና ነህ ወይ?
ለጊዜው ዋርካ ብቅ ባለማለቴ አስተያየትህን ለማንበብ ዕድል አላገኘሁም ነበር::

የግልነስ; እንዴት ነሽ የአገር ልጅ ደህና ነሽ. መልዕክትሺን ተሹለክሌም ቢሆን ካሉበት ገብቸ አድረሻለሁ:: ሰላምሽ ይብዛ::

አዎ እንዳልከው የትያትር ቤቱ የመግቢያ በር ቀደም ብሎ በመከፈቱ ተመልካቾችም በስአቱ ወደ አዳራሹ ገብተው ነበር:: ዝግጅቱ ግን ከተባለው ስዐት ዘግየት ብሎ በመጀመሩ ፕሮግራሙ ሲከፈት ለተመልካቾቹ ከፍተኛ ይቅርታ መቀረቡን አይቻለሁ:: መቸም የኪነጥበብ ባለሙያ በመድረክ ላይ ሲንጎባለል ዝግጅቱን ለማየት የመጣው ተመልካች በዛ ብሎ በአድራሽ ውስጥ መኖር ምን ያህል እንደሚያስደስተው ይታወቃል:: ታዲያ ያ እስከሚሆን ድረስ ቀድሞ የመጣው ሰው መንገላታቱ ያሳዝናል::

ብሩክ እንዳለው; በርግጥም የመጀመሪያው የመክፈቻ ትርኢት የሰውን ስሜት ለትካዜ የሚመራ ቢሆንም ከተወሰነ ስዐት በኍላ ግን በጣም ጥሩ የሆነ ትርኢት በማቅረባቸው የመጣው ሰው ተደስቷል::
የተለያየ ምክንያት ቢደረደርም የተመልካች ቁጥር አነስተኛ መሆኑ ያሳስባል:: ወደፊት በይበልጥ ዜናውን ለማሰራጭት መጣር ያስፈልጋልና አዘጋጆቹ ቢያስቡበት መልካም ነው::

ብሩኬ; ከአዳራሹ ውስጥ ጥግ ላይ ተቀምጠህ ደመቅ ባለ ጭብጨባ ደስታህን ስታስተጋባ የነበርከው ነህ? አንተማ ከፊት ለፊቴ ተቀምጠህ ነበር:: አወኩህ:: አቤት ቁመት! ቅቅቅ

ዋኖሴ; ምነው እንዲህ ቄጠማ አስጎዝጉዥ ስጠብቅህ ድምፅህ ጠፋ; እንደዉም ብሩኬ ምን እንደምትወድ ሹክ ብሎኝ ነበርና ከቤት ውስጥ በእጅ የተፈጭ በሶ; እኔ ክንዴ እስከሚዝል ወቅጨ ዘመዴ ጉልበቷ እስኪላጥ ፈጭታ አዘጋጅተን ስንጠብቅህ እንዲህ ጉድ ተሰራን? የውሀ ሽታ ሆነህ ቀረህ:: በል በሚቀጥለው ዘመን መለወጫ ጎራ በል:; ደግነቱ በሶ አይበሰብስም ካላረጠቡት:: ቅቅቅ

በሉ እስቱ ለዛሬው ይብቃኝ:; ሰላም ሁኑልኝ
If there is a book that you want to read, but it hasn't been written yet, you must be the one to write it.
--Toni Morrison
ጣዕም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 231
Joined: Sat May 01, 2004 2:02 am
Location: canada

Postby brookk » Tue Sep 01, 2009 8:30 pm

ጣዕም wrote:
አዎ እንዳልከው የትያትር ቤቱ የመግቢያ በር ቀደም ብሎ በመከፈቱ ተመልካቾችም በስአቱ ወደ አዳራሹ ገብተው ነበር:: ዝግጅቱ ግን ከተባለው ስዐት ዘግየት ብሎ በመጀመሩ ፕሮግራሙ ሲከፈት ለተመልካቾቹ ከፍተኛ ይቅርታ መቀረቡን አይቻለሁ:: መቸም የኪነጥበብ ባለሙያ በመድረክ ላይ ሲንጎባለል ዝግጅቱን ለማየት የመጣው ተመልካች በዛ ብሎ በአድራሽ ውስጥ መኖር ምን ያህል እንደሚያስደስተው ይታወቃል:: ታዲያ ያ እስከሚሆን ድረስ ቀድሞ የመጣው ሰው መንገላታቱ ያሳዝናል::ጣዕማቸው የኪነጥበብ ሰው አርግዞ የወለደውን ብርቅዬ ልጁን በብዛት ሰው ሲወደው ከማየት የበለጠ ደስታ ሊኖረው እንደማይችል አልዘነጋሁትም::

በአጋጣሚ በወቅቱ ዝግጅት የነበረውን የሰው ብዛት እኔም እንደአዘጋጆቹ መለስ ቀለስ እያልኩ ስቆጥርና ስገምት ነበር የዋልኩት :: በሰሞኑ ቶሮንቶ ይመጣሉ የተባሉት የኪነጥበብ ሰዎችና ፕሮግራሞች የመብዛታቸውን ያህል ሰዉም ፋይናንሻሊ ላለመጎዳት ብሎ እራሱን ለተወሰኑ ዝግጅቶች የመደበ ይመስላል ::
እኔም ከምር ለናንተ ያለኝን ድጋፍ ለማሳየት ስል ገባሁት እንጂ እንደብዛታቸው ሁሉንም ለመቀበል አስቸጋሪ ነበር ::
እናም እንዳሰባችሁት ባይሆንም --- ካለው ሁኔታ አንጻር የገባው ሰው ቀላል አልነበረም :: ትርፍ ባይኖረውም ብዙ የከሰራችሁ አልመሰለኝም::

አርፍደው ቢጀምሩም ግን -- ከምር በዝግጅቱ ካሱን :: እጅግ የተዋጣለትና ከጠበኩት በላይ የሆነ የኪነጥበብ ዝግጅት ነው :: በሀዘን መጀመሩምኮ መጥፎ አልነበረም :: የሰውን ህሊና ገዝቶና ተቆጣጥሮ ማስለቀስ መቻል እራሱ የዝግጅቱን መሳካት የሚያበስር ነው ::
"ጴጥሮስ በዚያን ዕለት" የሚለው አጭር ድራማም ላይ የ"ሰውየው" ድምጽ ከማነሱ በስተቀር ማለፊያ ነበር :: አርቲስቱም ያንን ሁሉ ህመም ተቍቁሞ ያን ያህል ተጉዞ ለሙያው ያሳየው ክብርና ፍቅር በእጅጉ የሚደነቅ ነው ::

"በመስከረም ኮሜዲ" ላይ ጓደኛዬ ጓደኛዬ -ኣ ---እያለች ስታላቅስ የነበረችው ልጅ --- በዚህም ዝግጅት ላይ ያሳየችው ብስለት ዋው የሚያሰኝ ነው ::
የእለቱ ዝግጅት ፍጹም የተዋጣለት ነበርና --- ይቅርታም ባይጠየቅ --- ረፍዶ መጀመሩ ተረስቷል አባ!

በጉልበት ባንረዳም የምታቀርቡትን ዝግጅት እየመጣን ከማየት አንቦዝንም አባ ! ተማመኑብን --- ቢያንስ አራት አምስት ሆነን :lol:
እኔና ብሩክ

ዋኖሴው አንተን እንደጣዕሙ የማይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ከነግጥምህ :lol:
brookk
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Tue Nov 11, 2003 3:46 pm
Location: ethiopia

Postby brookk » Wed Mar 06, 2013 7:52 pm

ለሙያቸው እስከመጨረሻዋ እስትንፋሳቸው ድረስ ክብር የሚሰጡ ሰዎች በስራቸው ምንጊዜም ሲታወሱ ይኖራሉ ---
ለበሀይሉ ቤተሰቦች መጽናናትን ለሱም ገነትን ፈጣሪ ያድላቸው
RIP

Code: Select all
አርቲስት በኃይሉ መንገሻ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አለምፀሐይ ወዳጆ
በኢትዮጵያ የትያትር ሙያ ተደናቂና ተወዳጅ የነበረው አርቲስት በኃይሉ መንገሻ በተወለደ በ 57 ዓመቱ ማርች 3/2013 (የካቲት 24/2005) ዓ .ም . ነዋሪ ሆኖ በቆየበት በሰሜን አሜሪካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።አርቲስት በኃይሉ መንገሻ ከአባቱ ከአቶ መንገሻ ከበደና ከእናቱ ከወ /ሮ አየለች ተክለወልድ የካቲት 1 ቀን 1948 ዓ .ም . በአዲስ አበባ ከተማ ነበር የተወለደው። የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአዲስ አበባ መድኃኒዓለም ሁለተኛ ደረጃ ት /ቤት አጠናቅቆ፤ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የ 2 ዓመት በቴአትር ሞያ ሠልጥኗል። በማከታተልም በታንዛንያ በሚሊተሪ ሣይንስ ትምህርት ሁለት ዓመት የተማረ ሲሆን፤ ወደ ሶቪየት ህብረት በመጓዝ በሞስኮ የቴአትር ኪነጥበብ አካዳሚ ለ 5 ዓመታት ትምህርቱን በመከታተል በቴአትር ዝግጅት (ማስተር ኦፍ አርትስ ) ዲግሪውን አግኝቷል።ወደ ሀገሩ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት በተለያዩ የኃላፊነት ሥፍራዎች ላይ ሠርቷል። ከእነዚህም በጥቂቱ የቴአትር ክፍል ኃላፊ፣ የፕሮግራምና ፕሮዳክሽን ኃላፊ፣ ከፍተኛ ቴአትር አዘጋጅ፣ አርቲስቲክ ዳይሬክተር ሆኖ አገልግሏል።ከ 1984 ጀምሮ በክልል 14 የባህልና የስፖርት ቢሮ የሚሰጠውን ከፍተኛ የሙያ እገዛ በመቀጠል በአርቲስቲክ ዳይሬክተርነት፣ በቴአትር፣ በሙዚቃ በሥዕልና ሥነጽሁፍ የሥነጥበባት ማስተባበሪያ ቡድን መሪ፣ በሥነጥበባት ዋና ክፍል ኃላፊነት፣ በፊልም ትምህርት መምህርነት፣ በትወና ሞያ በወጣቶች አሰልጣኝነት አገልግሏል።በሥራውና በሙያው የሚያሳየው ከፍተኛ መሻሻል ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የቴአትርና የባህል አዳራሽ ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ለ 6 ዓመታት ያህል አገልግሏል። በኃይሉ በተውኔት ሙያ ውስጥ በትወናና በአዘጋጅነት ከመሥራቱ ሌላ በፊልም ተዋናይነት ያለውን ችሎታና ሙያ አሣይቷል። The adventure of Tom Sweyer፣ The Big Battalions "የክትነሽ " ቪዲዮ ፊልም አባውቃውና ጋዜጠኛው ላይ ተሳትፏል።በመድረክ ቴአትር ደግሞ የአርባ ቀኑ መዘዝ፣ ሀሁ በስድስት ወር፣ አፅም በየገዱ፣ አቦጊዳ ቀይሶ፣ እና ሐምሌት ላይ በተዋናይነት ተሣትፏል። በቴአትር አዘጋጅነት ሞያው የእጮኛው ሚዜ፣ አንቺን አሉ፣ ቅኝት፣ ውጫሌ 17፣ ፍቅር በአሜሪካ፣ የደም ቀለበት፣ የከርቸሌው ዘፋኝ እና የምሽት ፍቅረኞችን አዘጋጅቶ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፏል።በኃይሉ ጥር 30/1979 ከወ /ሮ ዓለምእሸት ከዱ ጋር ህጋዊ ጋብቻ በማድረግ የአንድ ልጅ አባትና የሁለት የልጅ ልጆች ባለፀጋ ነው። ከሴፕቴምበር 10 ቀን 2005 ጀምሮ ወደ አሜሪካን በመሄድ ከቤተሰቡ ጋር እየኖረ በጤናው ላይ በደረሰበት ችግር በተለያዩ ሆስፒታሎች የተለያዩ ሕክምናዎችን ሲያደርግ ቆይቷል። ይሁንና በኃይሉ የጤና መታወኩ ከሚወደው ሙያው ሳይነጥለው ከጣይቱ የባህል ማዕከል ጋር በመሆን በተለያዩ የአሜሪካ ስቴቶች ካናዳን ጨምሮ እየተጓዘ በሙያው ተመልካቹን ሲያስደስት ከመቆየቱም ሌላ በየወሩ የግጥም ምሽት ላይ በሚያቀርባቸው ድንቅዬ የጥናትና የሙያ ፅሁፎች ተሣታፊዎችን እያሳቀ በማስተማር ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል።በኃይሉ ዕድሜውን ሙሉ ከገበረለት ሙያው ድንቅ ውጤት በተጨማሪ በግል ባህሪው እጅግ ተወዳጅና ተፈቃሪ ሰው ነበር። የታመመ ጠያቂ፣ የተጣላ አስታራቂ፣ የሞተ ቀባሪ፣ ያዘነና የተከፋ መካሪ፣ የሁሉ ቤተሰብ የሁሉ ወንድም የሁሉ ልጅ የሁሉ ጓደኛ ነበር። በደረሰበት ልዩ ልዩ የጤና እክል ላይ ሁሉ እንደ ቀለደና እንዳፌዘ ፈጣሪውን አንድም ቀን ሳያማርር ይህችን ምድር የተሰናበተ ለሁላችን አርኣያ የሚሆን የጥሩ ሰው ምሣሌ ነበር። የሱን ፅናትና ጥንካሬ የሱን ሰው አፍቃሪነት ለሁላችንም ያድለን። እግዚአብሔር ነፍሱን ከአብርሃምና ከይስሐቅ ጎን በገነት እንዲያኖራትና ቤተሰቡን ወዳጆቹን ዘመዶቹንና ጓደኞቹን መፅናናት እንዲሰጣቸው እንፀልያለን።


brookk
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Tue Nov 11, 2003 3:46 pm
Location: ethiopia

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest