ቫንፐርሲ ማን.ዩናይትድ ገባ (የማን.ዩናይትድ የ2012 ሲዝን)

ስፖርት - Sport related topics

Postby ሙትቻ » Fri Jul 03, 2009 2:55 pm

Man Utd Replace Ronaldo With Toon Donkey!
ካሪም ቤንዜማን በሪያል ማድሪድ በመቀማት የመጀመሪያውን የሲዝኑን የዝውውር ሽንፈትን የቀመሰው ማን.ዩናይትድ የኢንግላንዱን አጥቂ ማይክል ኦውን ለማስፈረም ከጫፍ ደረሰ::
በዚህ ሳምንት ከኒውካስትል ጋር የነበረውን በሳምንት የ120 ሺህ ፓውንድ ደመወዝ ያጠቃለለው ኦውን ቡድኑ ውስጥ መቆየትን ባለመፈልጉ የተለያዩ ክለቦችን ሲያፈላልግ ነበር:: ኦውንን ለማዘዋወር አስቶንቪላ, ሁል ሲቲና ከሌሎችም ክለቦች ፍላጎቶች ቢኖሩም ኦውን ማን.ዩናይትድን መርጧል:: ኦውን ዛሬ ጠዋት በካሪንግተን ትሬኒንግ ግራውንድ ተገኝቶ ሜዲካል የወሰደ ሲሆን ጤናማ ከሆነ ወይም በቅርብ የማገገም ተስፋ ካለው ክለቡን በነጻ የዝውውር ዋጋና በሳምንት የ50 ሺህ ፓውንድ ደመወዝ ማን.ዩናይትድ ሊቀላቀል ይችላል:: ኦውን ወደ ማን.ዩናይትድ ለመቀላቀል ከጫፍ መድረስን በማስመለከት የኒውካስትል ጦማሮች {ብሎጎች} Man Utd Replace Ronaldo With Toon Donkey! የሚሉ ዘገባዎችን ጭምር እያስነበቡ ነው::
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ሙትቻ » Fri Jul 03, 2009 3:04 pm

የባየርሙኒኩ ስታር ፍራንክ ሪቤሪ 'ክለቤን ከለቀቁኝ የምፈርመው ለሪያል ማድሪድ ነው' ማለቱ ተስፋ ያስቆረጣቸው አሌክስ ፈርጉሰን በተጫዋቹ ላይ ያላቸውን አይን በማንሳት ሌላ አጥቂ በማፈላለግ ሲሆኑ የኢንተር ሚላኑን አጥቂ ዝላታን አብራሞቪችን ጠይቀዋል:: ፈርጉሰን ለረዥም ጊዜ የስዊድናዊው አጥቂ አድናቂ መሆናቸው ሲታወቅ ኢንተርሚላን ልጁን በክለቡ ለማቆየት; ባርሴሎና ለመውሰድ ከሚያደርጉት ትንቅንቅ ጋር ይፋጠጣሉ:: ፈርጉሰን ኢቭራሞቪች ካልተሳካላቸው የአትሌቲኮ ማድሪዱን ዴቪድ ቪያንም ጠይቀዋል::
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby ወሮበላው » Fri Jul 17, 2009 5:09 pm

ሰላም ሰላም ማንቺስተራዊያን ... እንዴት ናቺሁልኝ ? እኔ ከማንቼ እና ከ እናንተ ናፍቆት በስተቀር ሁሉ ነገር አማን አማን ነው ::
ፈርጉሰን ወደ የዘውት የተጉዋዙት ቀያይ ጦር ማሌዥያ ላይ ቦንብ ሲሰሙ ለአምስት ቀናት ሊያርፉበት የነበረው ሆቴል በቦንብ ሲናወጥ ጃካርታ እዛው በጸበልሽ ብለው ጉዞዋቸውን ሰርዘዋል :: ወንዳታ ፈርጂ
ከሁሉ ግን የገረመኝ ፈርጉሰን እንዲህ በታዳጊዎች ላይ መጨከናቸው ነው .. ክለቡ ኮትኩቶ ያፈራቸው ልጆች ካምቤል እና ኤርክስሬይ ነው ማነው የሙሉት ያ ሙሉ ቀይ ልጅ ( ቅንድቡም ቀይ ነው) ከሁሉም ወሽመጤን የቆረጠው ደሞ የ ሮድሬጎ ፖስቦንን ማዋሳቸው ነው ... ዛሬ ደሞ ማኑቾን ምንም ሳያምርበት ወደ ስፔን ሸንተውታል:: ሰውየው ምን አስበው ነው ወይስ አይዞት ያላቸው ሰው አለ :: በወጣቶቹ ዘመቱ ::
ከሊዮን የመጣው ኦበርታን ካሁኑ ወገቤን እያለ ነው 3 ወር ቀሪ መዝገብ ላይ ተመዝግቦዋል :: ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ ተናፋቂው አርግሬቭስ እያገገመ ነው አሉ :: ቱ ቱ ብለናል ::
ብቻ የዘንድሮው ማንቼ ግራ አጋብቶኛል እስኪ ሚሆነውን አብረን ለማየት ያብቃን ::
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby አፍሪክ » Mon Aug 24, 2009 6:41 pm

ሰላም ሰላም ማንቼዎች
በእውነቱ የጨዋታን ትኩስ አሰላለፍና ጌምካስት እስከማድረግ ደረጃ የተደረሰበትን ሩም አሁን ከአንድወር በላይ ሳይጻፍበት ማየት( ወሮበላው ጁላይ 17 የጻፈው የመጨረሻ ጽሁፍ) ጥሩ አይመስለኝምና እስከነልዩነታችን እንድንቆይ ተመለሱ እያልኩ ጥሪዬን አስተላለፋለሁ::
ይህ በንዲህ እንዳለ ዩናይትድ ሊጉ ከተጀመረ አንስቶ በሶስት ጨዋታዎች የተዘባረቁ ፐርፎርማንሶችን አሳይቶን አልፏል:: ከበርሚንግሀም ጋ ደህና ነበሩ:: ከበርንሊ ጋር ግን ፍጹም ይቅር የማይባል ፐርፎርማንስን አሳይተው ተገቢ መሸነፍን ተሸንፈው ወጥተዋል:: ወትሮ ጠንካራ ተፎካካሪ ሲገጥማቸው ደካማ ማንነታቸው ይወጣ የነበሩ አንዳንድ ተጭዋቾቻችን ከበርንሊ ጋር እንኳን ሲጋለጡ አስተውለናል:: ስም መጥቀስ ቢሰለቸኝም አሰልጣኑን ግን ከመውቀስ ወደሗላ አልልም:: ይበልጥ ደሞ የሚደንቀው ሰር አሌክስ ፈርግሰን ካለው ስብስብ የቱ ቡድን ጠንካራ ቤስት11 እነደሆነ ጠንቅቆ ማወቁና ያሰላለፍ ስህተቶችን የሚሰራው በማናለብኝነት ይመስላል:: ከዊጋን ጋር ይዞት የቀረበውን አሰላለፍ ስንመለከት ማንም ደጋፊ ሊረዳው የሚችለው ካሉን ተጭዋቾች አሁን ባላቸው አቋም Reasonable ቡድንን ይዞ ገብቶ አይተናል:: በተለይ ከበርንሊ ጋ የነበረው joke አማካዩ ሙሉ ለሙሉ ተቀርፎ (አራቱም ተቀይረዋል) ስኮልስና ፍሌቸር መሀል ናኒና ቫሌንሲያ ክንፉን ይዘው እጅግ የተሻለ እንቅስቃሴን እና አጥቂዎችን ያሳተፈ ጨዋታን አሳይተውናል:: ፍሌቸር ካሉን ሚድፊልደሮች ቦታው የሚገባው በጥረቱ እዚህ የደረሰ ልጅ ነው:: ይህንን ልጅ ማጣመር የሚቻለው ካንድ ኳስን መሰንጠቅ ከሚችል ጥሩ ዲስትሪቢውተር ጋር መሆኑን አውቆ ስኮልስን አጣምሮለታል:: አሰላለፉ ፍሬም አፍርቶ ፍሌቸር ጥሩ ከቨር እየሰጠው ስኮልስ መልካም እንቅስቃሴን ከማድረጉም ባሻገር ለቤርባቶቭ ጎል ያቀበላት ምጡቅን ኳስ አበርክቷል:: ሌላው ጥሩ መሻሻልን ያሳየው ናኒ ነው:: ናኒ አሁን አሁን ትክክለኛ ዊንገር እየሆነ የመጣ ይመስላል:: በተለይ መጪ ቅዳሜ ከእርሱ ብዙ እጠብቃለሁ:: ብራዚላዊው አንደርሰን ለአርሰናል ጨዋታ ጉልበትና ፍጥነቱን ከመፈለግ አንጻር ሊሰለፍ ይችላል::( ሴስክ ፋብሪጋስን ደጋግሞ ከጭዋታ ውጭ ሲያደርግ አይተናል) ግን ኳስን ለአጥቂ በማቅረብ ረገድ ልጁ ምን እንደነካው አይታወቅም እርባና ቢስ ነው:: ምናልባት እንደሚባለው ፋብሪጋስ ለጭዋታው ካልደረሰ አንደርሰንን ባያሰልፈው ይመረጣል:: አንቶዮ ቫሌንስያ ያለማችንን ኮከብ ሮናልዶን ቦታ ለመተካት የመጣ አዲስ ተጭዋች እንደመሆኑ እክሳሁን ያሳየው እንቅስቃሴ ይበል የሚያስኝ ጉልበተኛ ተጭዋች ነው:: ቤርባቶቭ በቀደም ከ ዊጋን ጋር ልክ ባይምሮዬ የሳልኩትን አጭዋወት ሲጫወት ነው ያረፈደው:: የልጁ ቴክኒካል brilliance ለአጋር ተጭዋቾች ( አስተሳሰቡን ቶሎ ቶሎ ከተረዱለት) መንገድን የሚያመቻችና ለጎል ብዙ መንስኤ የሚሆኑ እንቅስቃሴዎችን ይፈበርካል:: ሩኒም የጎል አካውንቱን 3 አድርሷል:: ይበል ይቀጥል የሚያሰኝ ነው::
በተረፈ አሁንም በተለይ ለቻምፒየንስ ሊግ ላሉ ውድድሮች አንድ ሁነኛ ጨዋታን ዲክቴት የሚያረግ አቀናባሪ ሚድፊልደር ያስፈልጋቸዋል:: ፕሪምየርሊጉም ዘንድሮ ከባድ ፍልሚያ አይለበት ይመስላል:: እንዴት እንደሚዘልቁት ለማየት ያጓጓል::
አፍሪክ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Fri Feb 18, 2005 9:05 pm
Location: united states

Postby ወሮበላው » Sat Aug 29, 2009 8:26 am

ሰላም ሰላም ማንቺስተራዊያን ... እንዴት ከረማቺሁ ?
ዛሬ ማንቼያቺን አርሴን እንደሚያስተናግድ የሚታወቅ ሲሆን እንቡር እንቡር ያሉት ፈላዎች ዛሬ የፈተናቸው ቀን እንደሚሆን አልጠራጠርም ... በማንቼ በኩል የ ፕሪ ሲዝኑ ጨዋታዎች ጀምሬ ሁሉንም ያየዋቸው ሲሆን ማንቼ ካለፉት ሲዝኖች ከነበረው የማጥቃት ሀይል ቀነስ ያለ ሆኖ አይቼዋለው ... ምናልባት ቡድኑ አዲስ ተጫዋቾች እና አዲስ መልክ ይዞ ስለመጣ ከለት ወደ እለት ይሻሻላል ብዮ አምናለው ... በ ዊጋን ላይ የዘነበው ዝናብ አርሴ ላይ አያባራም ... እንደውም በረዶ ቀላቀል ዶፍ ሁሉ ሚሆን ነው ሚመስለኝ ::
ለዛሬው ጨዋታ መሀል ላይ እና ተከላላክይ ላይ ፈርጉሰን እንደ ኔቭል ያሉ እና ብራውን ያሉ ከ ታዳጊዎች እኩል መሮጥ የማይቺሉትን ቤንች ላይ ቢያኖሩዋቸው አሪፍ ነው ... መሀል ሜዳውን ግዴታ አንደርሰን እና ካሪክ መያዝ አላባቸው .. በተለይ አንደርሰን ወሳኝ ነው ::
ፓርክ ለእንደ እነ አርሰናል አይነት ብድኖች ውጤታማ ተጫዋች ቢሆንም የናኒ እና የ ቫሌንሽያ ወቅታዊ አቁዋም እንዲሁም እርሱ ባለፉት ጨዋታዎች ያሳየው የወረደ ጨዋታ ቤንች ግድ ይለዋል :: ከፊት የታወቀ ነው ... ዘመኑ የሩኒ ነው እንደውም ዘንድሮ እንደ ሮናልዶ ከ አርባ በላይ ጎሎቺን አግብቶ ሚጨርስ ይመስለኛል ::


መልካም እደል ለቀያይ ሰይጣኖች !!! --->> ወዮልሽ ወዮልሽ አርሴ መጣንልሽ ....
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby ሙትቻ » Tue Sep 01, 2009 2:09 am

ሰላም ውድ የማን.ዩናይትድ ፍቅር የለከፋችሁ ደጋፊዎቻችን በዋርካ ስፖርት መድረክ ላይ ዳግም ስለተገናኘን ይመስገነው ጌታን:: አዲሱን ሲዝን ዘግየት ብዬ ብቀላቀልም ለሁላችሁም ስለማታዬ ይድረሳችሁ::
Image
ሙትቻ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2633
Joined: Fri Mar 31, 2006 7:38 am
Location: other

Postby አክየ » Tue Sep 01, 2009 4:31 am

ሰላም ሙትቻ .. ዛሬ ከየት ተገኘህ ቤትህን እኮ ጭራሽ ረስተህ እዚያ ፍቅር ቢታ እየሄድክ ስለሴቶች የወንድ ማጣት ችግር ታወራለህ .... ለማንኛውም እንኳን ደህና መጣህ ከ አሁን ብሗላ ይሄ ቤት ሞቅ ደመቅ ማለት አለበት .. ያች ሙጢ እናትየስ የት ጠፋች .. የ አርሰናሉ ሻኛ ደረመሳት እንዴ በሳቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ አለች እርሷ ራሷ...

እስኪ አንድ ነገር ልበል እና .. የ አርሰናሉ አሰልጣኝ አርሰን ቪንገር ለተወሰነ ጊዜ ቢያንስ እስከ ክሪስማስ ድረስ ቡድኑን በማንም ቡድን ሳይሸነፍ ለማዝለቅ ያደረገው ጥረት በ ቀያዮቹ ሰይጣን በፕሪየር ሊጉ ሶስተኛ ጨዋታ ላይ ሽንፈትን ስለቀመሰ የተናደደ ይመስላል ያውም ከመጠን በላይ ..ለዚህም ማንችስተር ዩናይትዶች ጸረ-ኳስ (LAnti-Football) ናቸው ብሎ እስከመናገር ደስርሷል በእርግጥ ከዚህም አልፎ የሆነ ተጨዋች ጥፋት ሲሰራ እና አጨዋወቱ ከኳስ ውጭ ሲጫወት አይቻለሁ ይህም እንደ ኢድዋርዶ ዳይቭ ከማድረግ የባሰ ነው ብሏል እንደዚህ የሚያስብል ጨዋታ ማንችስተሮች የተጫወቱ አይመስለኝም ይህንንም ሊል የቻለበት ምናልባት ዳረን ፍሌቸር አርሻቪንን ፔናሊቲ ቦክስ ላይ በኳስ ስለጠለፈው ይሆን ሲጠየቅ . ስም መጥቀስ አልፈልግም ብሏል ....

አዝናሉ ፕሮፌሰር ቪንገር . እንደኔ እንደኔ ይህንን ሊል የፈለገው ፍሌቸርን እንደሆነ ግልጽ ነው .. ፍሌቸር ደግሞ በ አርሰናሉ ጨዋታ ላይ በተለይ ከ እረፍት በሗላ ሞተር ሆኖ ነው ያመሸው ለዚህም ሰር አሌክስ ፈርጉሰን የጨዋታው ኮከብ ተጨችነት ለፍሬቸር ሰጥቻለሁ ሲል አድናቆትን አችሮታል ..ብዙ ጊዜ አይችሁ እንደሆነ ፍሌቸር ከትላልቅ ክለቦች ጋር ሲሰለፍ የሚያሳየው ፕርፎርማንስ ከተጠበቀው በላይ ነው ለዚህም ነው አርሰናልን መሀል ሰቅዞ ስለያዘ ፕሮፌሰሩ ቢጫ ካርድ ሳያይ ወጥቷል ብሎ ወቀሳውን ቀጥሎ የተናገረው.........

ማንቼ ፍቅር የኳስ ፍቅር እንጅ ጸረ ኳስ አይደሉም .. ጸረ ኳስ ሳይነኩት ዳይቭ የሚያደርግ ነው እንደነ ኢቡዌ አይነቱ
"Say what you have to say in the fewest possible words"
አክየ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2615
Joined: Thu Jul 28, 2005 7:43 am

Postby ወሮበላው » Sun Sep 27, 2009 7:05 pm

ሰላም ሰላም ማንቺዬዎች እንኩዋን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደርሳቺሁ ... አሜን ::
ወደ ብሪታኒያ ስታዲዬም ያመራው ማንቼያቺን ትላንት ስቶክን በሜዳው ስቶክ አርጎት ተመልሶዋል :: ጨዋታው ብዙም ለማንቼ የከበደ አልነበረም ... በጣም የበላይነት ወስዶ ነበር ያሸነፈው :: የትላንቱን ጨዋታ ሳይ የናኒ እንዲህ መሆን ገርሞኛል ... እርሱንም ትዝብት ላይ ጥሎታል ... የሚገርመው ሩኒ ምን ያህል ይበሳጭ እንደነበረ አይታቺውታል ... እኔ ደሞ ጨሼ ነበር :: ልጁ ቺሎታ ሳያንሰው የ ኮሰንትሬሽን ቺግር አለበት ... ጨዋታ እየተጫወተ ሁሉ ቺኩን ሚያስብ ነው ሚመስለኝ ... በጨዋታው ውስጥ አሪፍ ተሳትፎ ቢያደርግም ... የሚያበላሸው ኩዋስ ብዛቱ ...የኩዋስ ጡር ቢኖር ... :lol: :lol: ... ጊግስ አሁንም ጠቃሚነቱን አሳይቶዋል ... ::
ፍሌቸር እና ቪዳም አሪፍ ነበሩ :: ፎስተር እንደ ሲቲው እንዳይሸወድ ፈርቶ በረጂሙ ሚጠልዛቸው ኩዋሶች ምንም ሙድ የላቸውም ::
ማንቼ እሮብ የጀርመኑን የአምና ሻምፒዮና ዎልቭስቡርግን ኦልትራፎርድ ላይ እሮብ ይገጥማል :: ከወዲሁ መልካም እድል ለቡድናቺን እንመኛል ::
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby ቃላት » Fri Oct 16, 2009 11:11 pm

ሰላም ሰላም ብለናል ማንቼዎች እንዴት ናችሁ? ብዙም አሳማኝ ባይሆንም በማያሳማ ብቃት እየተጓዘ ያለው ማንቼ ነገ ያለ ሩኒ ቦልተንን ይገጥማል:: ለመሆኑ የዘንደሮውን ቡድን እንዴት አያች ሁት? እኔ በበኩሌ አንድ ጨራሽ አጥቂና አንድ ደግሞ ወሳኝ የመሀል ተከላካይ ያስፈልጋል ባይ ነኝ:: ፈርዲናንድ በጣም እየወረደብኝ ነው የመጣው:: ባለፈው ከሲቲ ጋር ባለቀ ሰአት ለቤላሚ እንካ ብሎ ያቀበለው ኳስ ኦልሞስት ዋጋ አስከፍሎን ነበር:: ባለፈው ቅዳሜም ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢንግላንድ በ ዩክሬይን ስትሸነፍ: እሱን ያለፈ ኳስ ሄዶ ነው ለግሪን በቅይ መውጣትም ሆነ ለ ሪጎሬው ብLኦም ለሽንፈቱ ምክንያት የሆነው::

እረ እስኪ መለስ በሉ እና የሄን ቤት አሙቁት:: ሙቴክስ መቼም ጠፍቷል ወሮ እስኪ ብቅ ብቅ በል:: እናትዬ የት ይሆን ያለሽው?

ምንግዜም ማንቼ

በነገራችን ላይ አርጀንቲና በማለፉ አልተደሰታቺሁም?ያለም ዋንጫን ያለ ሜሲ እና ሮናልዶ ማየት አልፈልግም
ቃላት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 84
Joined: Sun Apr 23, 2006 1:46 pm

Postby ቃላት » Sat Oct 17, 2009 9:29 am

ባለፍው አርብ የሴት ልጅ አባት የሆነው ቤርባቶቭም ልጁን እና ባለቤቱን ለማየት ወደ ቡልጋሪያ ሊሄድ ሰለሚችል ላይሰለፍ ይችላል የሚል ዜና አለ:: እንዳዛ ከሆነ የፊት ከፍሉ በጣም የሳሳ ነው የሚሆነው:: ምናልባት ግን ይሄ ለወጣቶቹ ዌልቤክ እና ማኬዳ ሙሉ ጨዋታ የመሰለፍ እድል ይሰጣቸው ይሆናል:: እኔ እንደሚመስለኝ ፈርጊ ደፈርው ለነዚህ ልጆች እድሉን ቢሰጥዋቸው የተሻለ ነው:: ገፋ ቢል የዚህን አመት ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ መስዋእት ቢያደርጉ ነው::

ድል ለማንቼ!
ቃላት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 84
Joined: Sun Apr 23, 2006 1:46 pm

Postby ወሮበላው » Sat Oct 17, 2009 10:23 pm

ሰላም ማንቼዎች እንኩዋን ደስ አላቺሁ :: ቃላት ሰላም የማንቼው ወንድማቺንን ... ብቅ ብቅ በልና እንዲህ እስኪ ሞራላቺንን አነሳሳው ::
የዛሬው ጨዋታ ማንቼ በጣም ቀጥቅጦ አሸነፈ ባንልም ግን በጣም ድስ የሚል ጨዋታ በለተይ በመጀመሪያው የጨዋታው ጊዜ የተራቀቀ ጨዋታ ነበር የተጫወተው ::
አቤት አቤት ቫሌንሽያ እንዴት ተመቸኝ መሰላቺሁ :: በተለይ ከረፍት በፊት ... ድልት ነው ያለኝ :: ልጁ ኩዋስ ሲይዝ የሆነ ሞገስ አለው ከምር .... ምችት ይበለው :: በተረፈ የቫንደርሳር መመለስ ማንቼን ግርማ ሞገሱን መልሶለታል ... ቤርባቶቭ ምርጥ ነበር ... ቅምምም ያለ ኩዋስ ሲጫወት ነበር ያመሸው :: ሮኒያቺንን ቤት አስቀምጠን ውጤት ይዘን መውጣታቺን ተመቺቶኛል ::
ሉዘርፑል እንኩዋን ሰው ፊኛም ጠልቶት ... ቤኔቴዝ ፊቱን ቲማቲም አስመስሎ ወቶዋል ... ድሮግባም እንዲሁ .... ::

በድጋሚ እንኩዋን ደስ አላቺሁ :: ታናሽትዋ አናሳዎች ላይ ማናፋትዋ አይገርማቺሁም ግን ??

የማንቹካው ወሮበላ
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby እኔውነኝኝ » Sun Oct 25, 2009 5:09 pm

ምን ልል ነበር? :lol: :lol: :lol: :lol: ኤጭ እረሳሁት::

ወሮበላው ዘመዴ: አንተም ብራዘርም ለምንድነው ስልክ የማታነሱት ዛሬ ደግሞ? በሰላም ነው? :lol: :lol:
እኔውነኝኝ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 623
Joined: Sat Jan 20, 2007 11:17 am

Postby እንደጉድ! » Mon Oct 26, 2009 11:00 pm

ወይ መቃጠል, አለ! :x
«አትናገር ብዬ ብነግረው፣ አትናገር ብሎ ነገረው።»
እንደጉድ!
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 380
Joined: Fri Sep 19, 2008 4:16 pm

Postby ወሮበላው » Tue Nov 03, 2009 6:04 pm

ሰላም ማንቼዎች ... ዛሬ አይኑን ባይኑ ያየውን የማንቼውን አለኝታ ሩኒያቺንን እንኩዋን ደስ አለህ እላላው :: ሚስቱንም ማሪያም በሽልም ታውጣሽ እላለው :: ለትንሹ ሩኒም ጣሰው የሚል ምርጥ ስም አውጥቼለታለው :: ልጅ ጣሰው አለህልኝ ::
Man United Forever
ወሮበላው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 841
Joined: Sun Oct 17, 2004 10:52 pm
Location: united states

Postby ወንዳታ25 » Sun Nov 08, 2009 7:50 pm

ወይ ነዶ አለ....5 ነጥብ....
The future belongs to those who believe in the beauty of their dreams......dream big & live big.
ወንዳታ25
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 145
Joined: Tue Oct 20, 2009 11:19 am
Location: zendirom ezaw

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 0 guests