የዋናው አጫጭር ልቦለዶች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ዘይገርም!

Postby ዋኖስ » Tue Aug 25, 2009 2:48 pm

ዘይገርም! አንቲ ዉዕቱ ይህ ክታቤ ዘየሌለ ዉስተ ዓለም ብየዋለሁ! ሊቁ! ቅቅቅ
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Re: ዘይገርም!

Postby ዋናው » Thu Aug 27, 2009 10:46 pm

ዋኖስ wrote:ዘይገርም! አንቲ ዉዕቱ ይህ ክታቤ ዘየሌለ ዉስተ ዓለም ብየዋለሁ! ሊቁ! ቅቅቅ


መሪ ጌታ ኸረ ይሄ ነገር ይተርጎምልኝ
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

የንታ ባቲ

Postby ዋኖስ » Thu Aug 27, 2009 10:52 pm

ቅቅቅቅ...ደህና ነዎት! በጓሮ ነበርኩ ቀሩብኝ::

የንታ ባቲ ይተረጉሙታል! ቅቅቅ
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ጣዝማዊት » Fri Sep 04, 2009 12:55 pm

ዋንሽ በመጅመሪያ እንክዋን በሰላም ተመለስክ
ይሄንን ድርሰት 3 ጊዜ አነበብኩት መቼም በ1ጊዜ እንደማይገባኝ አንተም ታውቀዋለህ :lol: በጣም ደስ ይላል አጭር ጽሁፍ ረጅም ታሪክ እስቲ ፕሊስ ይልመድብህ


አድናቂህ ጣዝሚት
ጣዝማዊት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 92
Joined: Sun Mar 07, 2004 6:51 pm

ሸጥኳት

Postby ዋናው » Sun Apr 18, 2010 3:19 am

ሸጥኳት!


በትንሽ ጊዜ ውስጥ 5ተኛ ሲጋራዬን ሳቀጣጥል
''ይታወቃሃል በጣም ታጨሳለህ...!''
አለችኝ አንደበቷ ሲጣፍጥ
''አ...አጨስኩ...?? 'ኔንጃ...''
በመጠኑ ካንገቷ ወደ ደረቷ የተበታተነ ፀጉሯ ጡቶቿ ላይ ለመድረስ የተንጠራራ ይመስላል:: ያደረገቸዉን የማታ ልብስ ትኩር ብዬ ሳየው
''ቢጃማዬን ነው ምታየው...?''
አለችኝ አጎንብሳ ራሷን እየቃኘች: በአዎንታ ራሴን ነቀነቅኩኝ
''ምነው አልወደከዉም?''
''አሃ...ይ ደስ ይላል''
''ያንተ ምርጫ አይደል....?''
ፊቷ ስር የሚነበውበው ሃዘን ልቤን ስፍስፍ አደረገው ውስጤ የነበረውን የበደለኝነት ስሜት አባባሰው... ምነው የኔ ባልሆንሽ አስባለኝ ራሴን አስረገመኝ ላጣት መሆኑን ሳውቅማ ብግን አደረገኝ እሷ ግን አታውቅም እሷ ምታውቀው የኔ እንደሆነች ብቻ ነው የዋህ ልብ አላት:: እንዳልኳት ትሆናለች ያልኳትን ታደርጋለች የመጨረሻ ምስኪን ናት::
ራሴን ስወቅስ ስሜቴ ሲቀያየር አይታኝ
''ምነው... ምን ሆንክ?''
ትለኛለች ቢራዬን ተጎነጨው
''እስቲ ወጣ በልና ተናፍሰህ ና... ስንት ቀን ሙሉ ከነ ጋር ቤቱስጥ ታጉረህ...''
አለችኝ 'ነኚያ ቀምበጥ ከናፍርቷን በምራቋ እያወዛች
''ዛሬ ትቼሽ አልወጣም...''
አልኳት
''መች ተለየህኝና እየው ካወቅኩህ ጀምሮ ከኔ ጋር ነህ...''
''ከኔ ጋር እስካለሽ ከኔ ጋር ነሽ ዝም ብዬ እንዳይሽ ፍቀጂልኝ...''
አልኳት ፈገታዋን እያየው... አቤት ውበት....
''አንተ ባትኖር'ኮ እኔ አልኖርም ነበር ስታየኝ ብትውል ይከፋኝ መስሎሃል...?''
ምናለ በዚህ ዓለም ያሉ ሠዎች ሁሉ እንዳንቺ የዋህ ቢሆኑ ብዬ በሆዴ ተመኘው::
ዝም ብለን ተፋጠጥን ታየኛለች አያታለሁ ዓይኖቿ የዋህ ናቸው ደግነት ሞልቶ የፈሰሰበት የዋህነት
''ግን ሁሉም ሠዓሊ እንዳንተ ሞኛ ሞኝ ነው?''
አለችኝ ትኩር ብላ አይታኝ ስታበቃ
''እኔ'ንጃ ይሆኑ ይሆናል ''
''አይመስለኝም''
''እኔ የዋህ ነኝ?''
አልኳት ልቤን እየከነከነኝ:: አሳልፌ ልሰጣት መሆኔን ስላላወቀች አዘንኩላት ጨካኝ'ኮ ነኝ ምንም ምሕረት የሌለኝ አሪዮስ ሆዳም.... እቺ ዓለም በግሳንግሷ ስትሸነግለኝ የታለልኩላት ሽንፍ! አንዴ አይደለም አስር ጊዜ የተሸነፍኩኝ ቀሽም እንዲህ የዋህ ሆና የኔ የመሆኗን ምስክርነት ደጋግማ እየነገረችኝ ልራራላት 'ንኳን ያልዳዳው ከይሲ... ራሴን ስለረገምኩት አይወጣልኝም
''ያንን የጀመርከዉን ስዕልህን ለምን አትቀጥለዉም?''
አለችኝ
''ምን ያረግልኛል?''
''ምን ሊያደርግልህ ጀመርከው?''
''እንጃ... ምናልባት የቀለም ዛር አዝለፍልፎኝ... ባክሽ ተዪው ይልቅ አንቺን ብቻ ልይሽ ... በጣም'ኮ ነው ምወደሽ ይታወቅሻል ግን ?''
''ምን'ነካህ ላንዲት ቀንም እንደማትወደኝ ጠርጥሬ አላውቅም''
አሁን ከሀዲነቴን ብነገራት ወደድኩኝ ከዛም ስድብ አድርጋ ቀጥቅጥ ብታደርገኝ...
''እኔ ግን ምን ዓይነት ሠው እመስልሻለሁ?''
''እ... የዋህ... ለሙያው ሲል የሚሞት ጥሩ አፍቃሪ''
አቤት መለያየት ውስጣችን እና ላያችን እንደቀጋ ፍሬ መሆኑን ታዘብኩት
''እሺ ሌላስ...?''
''ለራሱ ግድ የሌለው...''
''አቤ....ት ለራሴ ግድ ባይኖረኝ አንቺን ሆዳም ሆኜ ሳታውቂ ጉድ ባልሰራዉሽ
'' እኔ ምልህ ..?''
አለችኝ ድንገት ራሴን ከምረግምበት አቋርጣኝ
''እህ..?'
''አንተ ኃይማኖተኛ አይደለህ ...ለምን ይሄን መስቀል መረጥክልኝ ግን?''
አለችኝ ያንገቷን መስቀል እያሳየችኝ, ድንቄም ሃገራዊ ስሜት በኔ ቤት ሀበሻዊነት ተሰምቶኝ ነው የላሊበላ መስቀል አንገቷ ላይ ያጠለቅኩት ሠው እንዴት 'ሚወደዉን ለሆዱ ሽጦ ሃገሩን ይወዳል?

''እ... አንቺ ላይ የሚያምረው ያ ነው ብዬ ነዋ?''

''አመሠግናለሁ ግን ያዩት ሁሉ ወደውታል::''
''በምርጫዬማ አንድም ቀን ተከፍተሽ እንደማታውቂ አውቃለሁ...''
አልኳትና ሌላ ሲጋራ አቀጣጥዬ ቫይብሬት ላይ ሆና ምትንፈራፈር ስልኬን አነሳዋት አሁን ሠዓቱ ደርሷል:: እቺን ውብ ልሰናበት ነው::
የሆነ የገባት ነገር ያለ ይመስል በፀጥታ ተዋጠች
ተነስቼ በሬን ከፈትኩ ::

''የቀለምና የሲጋራ ሽታ የሠዓሊ ቤት አወጉ ነው መቼም''
አለች ሚስስ ዳንኤል ሽበት የወረራት የሴት ጎልማሳ ናት ገና ሸራዎቼን ሳሟሽ ቀብድ ከፍላ ትሄዳልች ከዛም ቆይታ ትመጣና ትንሽ ብር ወርውራልኝ ትሄዳለች ብሩም ሳይበረክት ስዕሉም ያልቅና ይዛው ትሄዳለች::

''የታለች ያቺ ውብ?''
ያቺ ውብ አሁን በድን ሆና ሸራዬ ላይ ስዕል ሆናለች በብሩሽ ኪልኪላ ስላት ስትስቀልኝ ሳኮሳትራት ስትቆጣኝ ሳሳዝና ስታለቅስብኝ ... የመኖሬ ትርጉም ሆና ኑራ በሆዴ ልቀይራት ዛሬ ላይ ደርሳለች ምናልባትም አንድ የሃብታም ቢሮ በር ስር አድፍጣ እስከወዲያኛውኑ ትኖራለች እኔ የምወዳትን ያህል ግን ማንም ሊወዳት አይችልም ምክኒያቱም ልጄ ናትና ፍቅሬም ናትና
እናም ሸጥኳት:: ብሩ ያልቃል እሷ ግን የኔ አትሆንም ከግርጌዋ ያለው ፊርማዬ ያባቷ ስም ነው ታምሪያለሽ እንጂ አባትሽ ማነው ብሎ ሚያስታውሳት ላይኖር ይችላል::
.
.
.
ዋናው

ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby Tጂ » Sun Apr 18, 2010 6:45 am

ዋንቾ ዋርካን ነብስ ዘራህባት ነው ሚባለው:: የተሸጠችዋ ልጅ ግን የ አባቷን ስም እንደምታስጠራ ጥርጥር የለውም::
እጅህ ይለምልም::

ከአክብሮት ጋር
“Love is like the wind, you can't see it but you can feel it."
Tጂ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 301
Joined: Sat Aug 11, 2007 3:59 am

Postby ifa » Mon Apr 19, 2010 6:12 pm

በጠዋት ተነስቼ ቤቴንም ሳልጠራርግ ዋርካ ጎራ ብል(ትኖራለህ ብዬ ገምቼ) እያስደሰተ የሚያስለቕስ አይነት ነግር ጠበቀኝ...እንባዬን አርከፈከፍኩት የእውነት መስሎኝ ...ይሁን ቤቴን ለማጽዳት አልተቸገርኩም...አብዋራው ሳይቦን ጠራረግ ሁት...
ዋንች በጣም ደስ ምትል ልብ ስውር የምታደርግ ጽሁፍ ናት...
ረጅም እድሜ ይስጥልን

አድናቂዎ አይፋ
Ethiopians are: " THE BLAMELESS RACE "

Homer (Greek poet of the 8th century B.C.)
ifa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 135
Joined: Mon Jul 09, 2007 6:24 am

Postby ስርርር » Mon Apr 19, 2010 10:59 pm

ድንቅ ድርሰት ነው! እኛም ከተፈቀደልን ለመፃፍ ቃል እንገባለን::
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

የቅፅበት

Postby ስርርር » Mon Apr 19, 2010 11:52 pm

የቅፅበት

በህሙማን መመርመርያ ክፍል ውስጥ ሆኘ የእለቱን የህክምና ስራዬን ለመጀመር እየተሰናዳሁ ነው:: ሲስተር ትርሲት የክፍሉን በር ከፍታ የተለመደውን ማኪያቶ አቅርባልኝ ወጣች:: ጃኬቴን ከመስቀያው ላይ አኖርኩና ገዋኔን ለብሸ ቁጭ አልኩ:: ከፊቴ ብዙ የህሙማን ፋይሎች ተደርድረዋል::

በሽተኛ ላስገባ? አለችኝ ሲስተር ትርሲት
አዎን አልኩ::
አንድ ወጣት አይነርግብ የለበሰች ውርዚት ብቅ አለችና
"ሀይ ዶክ" አለችኝ:: ሀይ ፕሊስ ሀቭ ኤ ሲት! አልኩ

እሺ ጀሚላ...ምንድነው ችግሩ? ምን ሆንሽ?
ዶ/ክ እኔ ከዚ በፊት ወንድ አላውቅም:: ግን ፔሬዴ ከቀረ ቆይትዋል:: አንተ ደግሞ ፕሮፌሽናል ጋይኒስት ነህ ሲባል ሰምቼ ቼክ እንድታደርገኝ ነው....አለች እንደማፈር እያለች::

የተወሰኑ ተጨማሪ ጥያቄዎችን ጠየቅህዋትና ቃሬዛውን አስተካክየ በይ ነይ እስኪ ...ፊዚካል ቴስት ያስፈልግሻል አልክዋት::
እያፈረች ቀሚስዋን ገልባ በጀርባዋ ጋደም አለች::

two bud and a leaf ይሉታል በሳይንስ:: ሁለቱን የፊት እና አውራ ጣቴን ደርቤ ለአመል ያህል ወደብልትዋ ከተትኩት:: ዋው!!!!! እውነትም ውርዚት! ድንግል ናት:: ወንድ አታውቅም:: በዚያ ላይ እስላም ናት:: ፔሬዷ ለምን ቀረ????
ደምና ሽንት እንድትሰጥ ነግሬያትና ወጣች:: ከዚያ በህዋላ...ቀኑን ሙሉ ያ ትኩስ ገላዋ በአይኔ ድቅን እያለብኝና ሙያዬን ሲፈታተነኝ ዋለ:: በምሳ ሰዓትም እንዲሁ ቁጭ ብየ ስለራሴ ሳስብ...እስከመቼስ እንደማላገባ? ልጅስ መቼ እንደምወልድ....ስተክዝና ስቆዝም የሚያፅናናኝ የነበረው ረጅም ባትዋ, ዝብርቅርቅ ብሎ እዚህም እዚያም የበቀለው ጭገሯ, ብስል ቀይ ገላዋ....ነበር:: እንደሳይንሱ ከሆነ የፔሬድ መቅረት ኖርማል ነው:: እስከ ሁለት ወር ድረስ ሊቀር ይችላል::

የምርመራዋ ውጤት ኖርማል ከሆነ እንደማገባትና ሌላው ቢቀር ice breaker እንደምሆን ለራሴ ወስኜ ወደቢሮየ ገባሁ::

የብዙ እንስቶችን የምርመራ ውጤት ሳስረዳ, መድሀኒቶችን ሳዝ, ኮንግራ ስል, አብሬ ሳዝን...ምናምን ቆይቼ ተራዋ ደርሶ የወደፊትዋ ሙሽራዬ....የዛሬዋ በሽተኛዬ ገባች:: ፈገግ ስትል ጉንጮችዋ ስርጉድ! እያሉ ልቤን አዘለሉት:: ጭገርዋ ላንድ አፍታ በአይኔ መጣብኝ:: እንደምንም ራሤን ተቆጣጥሬ ውጤቱን ማንበብ ጀመርኩ::

ሥሜቴ ሁሉ በአንድ ግዜ ኩምሽሽ አለ:: ላብ ላብ አለኝ ቀና ብየ ሳያት የጥዋቱ ትዝ ብሏት ይመስላል ፈገግ አለች:: ድንጋጤዬን እንዳታውቅብኝ በጣም ተጠንቅቄ ለአንዳንድ ተጨማሪ ምርመራዎች ስለምንፈልጋት ነገ ተመልሳ እንድትመጣ ነግሬያት ወጣች:: በሩ ላይ ስትደርስ ግን መለስ ብላ በሁለቱም አይኖችዋ ጥቅስ! አደረገችኝ:::

ኖ ኖ ኖ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል???? የ19 አመትዋ ወጣት ልጃገረድ የሁለት ወር እርጉዝ ናት:: የደም ምርመራ ውጤትዋን ሳዬው...ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭ....

የቅፅበት ሙሽራየ! ሳላስበው እንባየ በጉንጨ ክብልል አለ...
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Wed Apr 21, 2010 12:25 am

:P :P ይህን ሁሉ ፅፌ የሚያነብ ይጥፋ? አሁን ምናለ ሰው ብታበረታቱ..... :twisted:
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Thu Apr 22, 2010 10:39 pm

:P :P :P :P :P :evil:
:x :x :x :x :x :evil:
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ኤስመር » Fri Apr 23, 2010 1:48 pm

:lol: :lol: :D :roll:
ስርርር የማህጸን ስፔሽያሊስቱ :wink: :lol: የትረካህ መጨረሻው ባያስደስትም(ግራ ገብቶህ ግራ ብታስገባንም) ... አዝናኝ ነው (ቢያንስ እኔን አስቆኛል)! :!:
.........................................................................
Opinions are like assholes... everybody's got one, and they're often full of shit. :D (from some forum)
.......................................................................
ኤስመር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 95
Joined: Sat Jan 23, 2010 10:17 pm
Location: ኤድሪያን ሲቲ (somewhere in estern Europe!)

Postby ስርርር » Fri Apr 23, 2010 6:58 pm

አመሰግናለሁ አሴመር:: በጣም....በሌላ ድንቅ ድርሰት ፅሁፍ እስክመለስ ድረስ....ደህና ሁኑ ውድ አንባቢዎቼ:: በቅርቡ የሚታተመው መፅሀፌን አንብቡት:: ብዙ እውቀት ታገኙበታላችሁ:: ድርሰር ማለት በእውነቱ እሱ ነው:: ይህንን ችሎታዬን ለማየት ስለበቃችሁ እናንተ የታደላችሁ ናችሁ::

ደራሲ ስርርር
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ዋናው » Sat Apr 24, 2010 2:35 am

ስርርርርቲ አንቺ(ተ) አሰለሺ(ስ) እንጂ አንባቢው ይጎርፋል ግዴለም ብቻ ፃፊ(ፍ)
እኔምለው ግን ሳያስፈቅዱ ሠው ቤት ዘው ብሎ መከራየት ዋርካ ፈቀደች ማለት ነው ወይ 8ኛው ሺ አለ ውቃው ... ረፍዶበት 9ዋ ላይ መድረሱን ሳያውቅ

:D
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ኤስመር » Sat Apr 24, 2010 2:52 am

ዋናው wrote:ስርርርርቲ አንቺ(ተ) አሰለሺ(ስ) እንጂ አንባቢው ይጎርፋል ግዴለም ብቻ ፃፊ(ፍ)
እኔምለው ግን ሳያስፈቅዱ ሠው ቤት ዘው ብሎ መከራየት ዋርካ ፈቀደች ማለት ነው ወይ 8ኛው ሺ አለ ውቃው ... ረፍዶበት 9ዋ ላይ መድረሱን ሳያውቅ

:D

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
ዝም አትለውም ..የሆነ አይነ ደረቅ ነገር...ዝም ብሎ የሰው ቤት ዘው ይገባላል?.. (በኔ ቤት ማጋጋሌ ነው) :!:
ኤስመር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 95
Joined: Sat Jan 23, 2010 10:17 pm
Location: ኤድሪያን ሲቲ (somewhere in estern Europe!)

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests