የኮምፒውተር የሶፍትዌር እና ተዛማጅ ጥያቄዎች እና መረዳጃ..

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ocean12 » Sat Sep 05, 2009 11:37 pm

ndave እንኩዋን ብቅ አልክ ደግሞም አትጥፋብን
አዋሽ ጥያቄህን ለመመለስ ጊዜ ቆርጨ ነበር ቀልጣፋው
ndave ብትንትን አርጎ አስቀመጣት ምስጋናችን ይድረሰው::
በል በነካ እጅህ ከሲዲ ላይ ሪፕ የተደረገ ዘፈን ለመጫን
ምን ማድረግ እንደሚገባ ጣፍ ጣፍ አርግልን...ለነገሩ
አይፓዴን በሆነ ምክንያት ካጣሁት በሁዋላ እርም ብልም
አዋሽን ጨምሮ ብዙ ተጠቃሚ ይኖራል::
የቲፔይንን Application ትላንት cnet ላይ አይቼው ይሄ Iphone
የማያመጣብን ነገር የለም እያልኩ ነብር::ደስ ይላል::
የግንኙነቱን ነገር እኔ ጠርጥር ብያለሁ.... :)
ሰላም ሁኑልኝ
መልካም አዲስ አመት ለሁላችን::
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby አዋሽ98 » Mon Sep 07, 2009 5:55 pm

ኦሽኔ
አይገርምም የndave ፍጥነት. እንደውም ወደ ዊንዶውስ ሚዲያ rip በማድረግ ጊዜ ማጥፋት አያስፈልግህም ሲዲ pcህ ላይ ስትጭን itunes ራሱ import ላድርግ ብሎ ይጠይቅሀል ok በለው ከዛ ndave የዘረዘራቸውን steps መከተል ብቻ ነው:: እንዴ ሁለት ጊዜ ምን አስለፋን:: ሌላው youtube ላይ የሚገኙ ዘፈኖችን ወድ mp3 format የሚለውጥ ፎርማት አለ ብለውኝ ዛሬ ሞክሬው ነበር በምን ምክንያት እንደሆነ አላውቅም አልሰራም አለ:: ምናልባት ሶፍትዌሩ አፕዴት መደረግ ይኑርበት ወይም ደሞ ጭራሽ ይሄን ኮንቨርተር youtube ብሎክ አድርጎት እንደሆነ አላወቅኩም:: ndave በነካ እጅህ የምታውቀው ነገር ካለ እስኪ ሁለት በለን በተለመደው ፍጥነት :lol:
ከብዙ አክብሮት ጋር
አዋሽ98
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 172
Joined: Mon Sep 26, 2005 3:22 pm
Location: Lay Sefer

Postby ocean12 » Tue Sep 08, 2009 4:16 pm

ሰላም አዋሽ
የትኛው አይነት የyoutube downloader እንዳለህ አላወኩም
ምክንያቱም ጥቂት አይነቶች አሉና ነው::
በነገራችን ላይ እኔ ይህኛውን አይነት ነው የምጠቀመው:
በጣም ቀላል አይነት ነው እንዴት ዳውንሎድ እና መጠቀም እንደሚቻል የምታሳይ ቪዲዮ ጭምር ሰርቼላታለሁ::
ተመልከታት እና ከወደድካት ተጠቀምባት :)
መማማሪያ ቪዲዮዎች

ndave...እንዲህ አይነት መማሪያ ቪዲዮ ስለ አንዳንድ ነገሮች ብታዘጋጅ የሚል
ሃሳብ አቀርባለሁ:: :)
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

አርብ መስከረም 1, 2002

Postby ወልዲያ » Wed Sep 09, 2009 5:40 pm

ሠላም ለቤቱ!


ታደስ ዓለሙ (አውድ ዓመት)

Image

http://www.youtube.com/mertoabet#play/a ... 4DozMF7taI

መስከረም 11, 2009 (መስከረም 01, 2002) አርብ ዕለት የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ይከበራል:: እንኳን ለኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በሠላም እና በጤና አደረሳችሁ::

Image


ፍቅር ጀባ
ወልዲያ - የጁ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby ዘመዴ ገንዘቡ » Wed Sep 09, 2009 8:52 pm

ዛሬ ዋርካ ዘው ስል ለ5 አመት አሳር ሲያበላኝ የነበረው
ችግር እድሜ ለኦሽን ገላገለኝ እድሜ ይስጥሕ ወንድሜ
ዋርካ ለምገባት ያስቸገርኝን xxxx ምልከት ማለቴ ነው

እስኪ ሌላ ጥያቄ ላንሳ እንድሁ ያስቸገሩኝን

1- ወርድ ፓድ ላይ በአማረኛ ጸፌ ሴፍ ሳደርገው ///// ምልከት ይሆናል ችግሩ ምንድነው??

2-ለልጄ የልደት ካርድ ፎቶ አስድግፌ ላዘጋጅ ፈልጌ ነበርእንዴት ነው ሚሰራው??
ምስጋናዬ ወደር የለውም እንኮን አደረሳችሁ ለአዲስ አመት
ዘመዴ ገንዘቡ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 32
Joined: Wed Sep 09, 2009 8:36 pm

Postby እርም » Thu Sep 10, 2009 3:59 pm

በመጅመሪያ ለዚህ አምድ አዘጋጆች ምስጋና እያቀረብኩ እንካን ለአዲሱ አመት በሰላም አደርሳችሁ መጪው ዘመን ይሰላም የፍቅር የደስታ ዘምን ለመላው ኢትዮፕያ ይሁንልን
አዲስ አመት ምክንያት በማረግ አዲስ ላፕ ቶፕ ገዘቸ ነበር እነ የምጠቀመው ዊንዶው ኤክስ ፔ ስሂሆን አሁን ግን የገዛሁት ሌፕ ቶፕ ዊንዶው ቪስታ ነው ተንሽ ግራ ያጋባል በዙ ማወቅ የሚገባኝ ቢሆንም በ አዳቭተሩ የልኮስኩት ሌፕ ቶፕ በዙ አይቆይም ምናልባት ለግማሽ ቀን ነው የሚያግለግለው በዲስነቱ ምንም ጥርጣሬ ባይኖረኝም ረጅም እንዲያገለግል የሚነካካ እንዳለ ነገር እንዳለ ቢገባኝም የት ቦታ ማስተካከል እንዳለብኝ ጠቆም አረጉኝ አመስግናለሁ
Long Live Ethiopia !!!
እርም
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1254
Joined: Tue Oct 11, 2005 12:21 pm
Location: ethiopia

Postby ocean12 » Sat Sep 12, 2009 12:24 am

ሰላም ለዚች ቤት እና ለመላው ዋርካ ተሳታፊዎች::
እንኩዋን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ አዲሱ አመት ካለፈው የበለጠ የምንማማርበት የምንረዳዳበት እንዲሆን እመኛለሁ::
ዘመዴ ገንዘቡየዋርካ መግቢያ ችግርህ በመቃለሉ ደስ ብሎኛል::
የወርድ ፓዱ ችግር የፊደል ይመስላል:
እርግጠኛውን ለመናገር ባይቻልም:: ምናልባት ተጨማሪ የአማርኛ ፊደሎች ብትጨምርለት መፍትሄ ሊሆን ይችላል::
መሞከር ነው ደጉ :)
ፊደሎቹ በብዙ ድረገጾች ላይ ይገኛሉ::

የልደት ካርዱ ጉዳይ አንተን የሚመችህን የፎቶ ኤዲቲንግ ሶፍትዌር ጭነህ መለማመድ ነው: :)
ኮምፒውተርህ ላይ ካለው paint ጀምሮ
ጥቂት ጥሩ የሆኑ የፎቶ ኤዲቲንግ ሶፍትዌሮች በነጻ ማግኘት ትችላለህ ::
አድራሻውም ይሄው
http://download.cnet.com/2797-2192_4-255.html?tag=contentBody;photoPromoMain

GIMP ወይም Paint.net ጥሩ አማራጮች ናቸው
ፎቶሻፕ የሚባል ሶፍትዌር አለ እሱ ነጻ አይደለም ነገር
ግን በጣም ብዙ አይነት አገልግሎት ያለውአይነት ሲሆን
ለጀማሪ ግን ትንሽ ግር ይላል::
ለሁሉም ከተቻለ እሱን ሞክር ምክንያቱም ብዙ የመማሪያ
ቪዲዮዎችና ቱቶሪያሎችን ታገኛለህ በዚሁ ዋርካ ተሳታፊ በዋናው ጭምር ጠቃሚ የአማርኛ ቱቶሪያል አለ::
በነጻ የሚገኝበት (መቼም ሌብነቱ ተለምዱዋል :) ለመግዛት ቢሞከር ወገብ የሚያሲዝ ስለሆነ)
መንገድም አለ እሱን በሁዋላ መነጋገር እንችላለን :) :)
እርም የላፕቶፕህን ባትሪ እድሜ ለማራዘም
አዎ የሚነካኩ ነገሮች አሉ በቀላሉ ሊያስረዳ የሚችል
የምስል እና ቪዲዮ ማሳያ አዘጋጅቻለሁ ይህንን ተጫን እና ተመልከተው
http://ethio.freeforums.org/computer-related-q-a-and-help-t117.html#p244
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby ዘመዴ ገንዘቡ » Sat Sep 12, 2009 3:55 pm

ኦሽን ሰላም!!
እጅግ በጣም አመሰግናለሁ የልጄን ካርድ ቆንጆ አደርጌ ሰራሁ እድሜ ላንተ ፊደሉ ግን አስቸግሮኛል እስኪ ደጋግሜ
ልሞክረው ችገሩ ያለው አንተ በደረጃ እንዳስቀመጥከው
ወደታች 3ኛው ሳጥን በቀኝ በኩል የእኔ ባዶ ነው ያንተ ኢትዮፒያ ጅረት ስላንት ይላል
እሱ ይመስለኛል ችግሩ እስኪ አንድ ጥያቄ የኔ ችግር እያደር ይጎተታል :lol: :lol:ከ ዩ ቱፕ ዘፈን ዋርካ ላይ እንዴት ነው ፖስት ሚደረገው
አመሰግናለሁ
ዘመዴ ገንዘቡ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 32
Joined: Wed Sep 09, 2009 8:36 pm

Postby ocean12 » Mon Sep 14, 2009 7:33 pm

ዘመዴካርዱን ለመስራት በመቻልህ ደስ ብሎኛል::
የፊደሉ ነገር ethiopic የሚለው ላይ እስከሆነ ድረስ ያን
ያህል ለውጥ የሚያመጣ አይመስለኝም የኔው የተለየው
ያንን ጂረት ፊደል በራሴ ስለጨመርኩበት ብቻ ነው:
ተጨማሪ አማርኛ ፊደል አይነቶች ካስፈለገህ ልልክልህ እችላለሁ::
ሌላው ዋርካ ላይ እስከማውቀው ድረስ የዩቲዩብ ቪዲዮ
መለጠፍ አይቻልም::
አሁን የተለያዩ በቀላሉ ኮምፒውተርን እና
ፕሮግራሞችን የሚመለከቱ መፍትሄዎች ማስተማሪያ
ቪዲዮዎች በአማርኛ ስላሉ እነሱንም መመልከት ጥሩ ነው
http://ethio.freeforums.org/tutorial-videos-in-amharic-t107.html
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby ocean12 » Mon Sep 14, 2009 7:35 pm

ዘመዴካርዱን ለመስራት በመቻልህ ደስ ብሎኛል::
የፊደሉ ነገር ethiopic የሚለው ላይ እስከሆነ ድረስ ያን
ያህል ለውጥ የሚያመጣ አይመስለኝም የኔው የተለየው
ያንን ጂረት ፊደል በራሴ ስለጨመርኩበት ብቻ ነው:
ተጨማሪ አማርኛ ፊደል አይነቶች ካስፈለገህ ልልክልህ እችላለሁ::
ሌላው ዋርካ ላይ እስከማውቀው ድረስ የዩቲዩብ ቪዲዮ
መለጠፍ አይቻልም::
አሁን የተለያዩ በቀላሉ ኮምፒውተርን እና
ፕሮግራሞችን የሚመለከቱ መፍትሄዎች ማስተማሪያ
ቪዲዮዎች በአማርኛ ስላሉ እነሱንም መመልከት ጥሩ ነው
http://ethio.freeforums.org/tutorial-videos-in-amharic-t107.html
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby ndave » Mon Sep 14, 2009 8:26 pm

ሰላም እንደምን ሰነበታችሁልኝ ትንሽ ብትዘገይም እንኳን አደረሳቹ !! መጪው አመት የሰላም የፍቅር ና አላማችን እሚሳካበት ይሆንልን ዘንድ የልብ ምኞቴነው ::

ዛሬ ደግሞ ከጠቀመች ብዬ ከ Itunes ተግባሮች አንዷን ይዤ ቀረብኩኝ ::

እሱም Ipod ወይም Iphone ውስጥ ዘፈን ከጫን በሗላ የዛፋኙን ወይም ዘፋኙዋን ምስል ለመጫን እምታስችለን ትሆናለች ::


1ኛ-እምንፈልገው ዘፋኝ ምስል ካለን በስካነር ወደ ፒሲያችን እንጫን : ከሌለን ደግሞ ኢንተርኔት ላይ በመፈለግ አውርደን እምናውቀው ፎልደር ውስጥ እናስቀምጥ ::

2ኛ Itunes እናስነሳ በመቀጠልም ከላይብረሪ ታች ምዩዚክ እንጫን : በዚህ ወቅት Itunes ላይ ያሉንን ሙዚቃዎች እናገኛለን ::

3ኛ- ምስሉ ያለን ዘፈን ላይ ራይት ክሊክ እናድርግ : ከዛም Get info እንጫን ከዛም አዲስ መስኮት ይከፈትልናል ::

4ኛ-እዚህ ውስጥም Artwork እንጫን ከዛም Add ስንጫን ሌላ ትንሽ መስኮት ይከፈትልናል :;

5ኛ-እዚህ ውስጥ የዘፋኙን(ዋን) ምስል ያስቀመጥንበትን ፎልደር ክሊክ ስናደርግ ምስሎችን ያስቀመጥንበት ሲከፈት ምስሎቹ ይታዩናል ::

6ኛ-በመቀጠልም እምንፈልገው ምስል ላይ ምልክት በማድረግ open እንጫናለን : በመቀጠልም Ok በማድረግ እንጨርሳለን ማለት ነው ::


መልካም ግዜ !!!
ndave
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Mon Sep 22, 2003 10:29 am

Postby CUBBY » Mon Sep 14, 2009 10:31 pm

ocean12 wrote:ዘመዴ
ሌላው ዋርካ ላይ እስከማውቀው ድረስ የዩቲዩብ ቪዲዮ
መለጠፍ አይቻልም::


ሰላም ለዚህ ቤቶች በጣም ደስ የሚል መማማር ነው:: በዚህ አጋጣሚ ስለ ዋርካ ስዕልም ሆነ የዩቲዩብ ቪዲዮ መለጠፍ የተከለከለ አይመስለኝም:: ይመስለኛል ሌላ ክፍል እንደ ጉዋዳ ተበጅቶለታል:: ይሄን እያነበብክ እስቲ url አድራሻውን እየው 'warka4" ይላል 4 ትን ወደ አምስት(5) ስትቀይራት እንዳልኩት ፎቶ ማየትም ይቻላል መለጠፍም ሳይቻል አይቀርም (በጣም እርግጠኛ አይደለሁም ስለመለጠፉ ስላልሞከርኩኝ):: Image
CUBBY
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Wed Oct 15, 2003 3:53 pm

ይቻላል

Postby CUBBY » Mon Sep 14, 2009 10:37 pm

CUBBY
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Wed Oct 15, 2003 3:53 pm

Postby ሾተል » Tue Sep 15, 2009 10:24 pm

CUBBY wrote:
ocean12 wrote:ዘመዴ
ሌላው ዋርካ ላይ እስከማውቀው ድረስ የዩቲዩብ ቪዲዮ
መለጠፍ አይቻልም::


ሰላም ለዚህ ቤቶች በጣም ደስ የሚል መማማር ነው:: በዚህ አጋጣሚ ስለ ዋርካ ስዕልም ሆነ የዩቲዩብ ቪዲዮ መለጠፍ የተከለከለ አይመስለኝም:: ይመስለኛል ሌላ ክፍል እንደ ጉዋዳ ተበጅቶለታል:: ይሄን እያነበብክ እስቲ url አድራሻውን እየው 'warka4" ይላል 4 ትን ወደ አምስት(5) ስትቀይራት እንዳልኩት ፎቶ ማየትም ይቻላል መለጠፍም ሳይቻል አይቀርም (በጣም እርግጠኛ አይደለሁም ስለመለጠፉ ስላልሞከርኩኝ):: Image


ሰላም ለዚ ቤት ይሁን::እንኩዋን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ::

ሰላም ወንድሜ ኩቤ...እንደምን አለኽ?ካየውህ ረጅም ጊዜ ሆነኝ...በጤና ነው?
አንድ የገረመኝን ነገር ልንገርህ....የለጠፍከውን ፎቶ አትኩሬ የአለም ታውቂ ሰዎችን ስፈልግ የኔኑ ፎቶ ከብሩዝሊ አጠገብ አየሁትና ደነገጥኩኝ...እራሴን እንድጠራጠር አደረገኝ...እንዴት ሆኖ እዚህ ድንቅ አርት ውስጥ ገባ ወይም ማን አስገባው ብዬ ተገረምኩ ነው የምልህ....እባክህ ማን እዛ ውስጥ እንደዶለው ንገረኝ...ከነ ብሩዝሊ አልበርት አንሽታይን ዳርዊንና ወዘተ የአለማችን እውቅ ሰዎች ጋር የራስን ፎቶ ማግኘት ምን ያህል እንደሚያስደስት ተደስቼ አየሁት::ክብርነታችንን አክብራችሁ እዛ ክብር ስለሰጣችሁን ደስ ብሎናል::

ኩቤ ሚስጥሩን እንደማትነፍገኝ ነው

መልካም ጊዜ ይሁንልህ

ሾተል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby CUBBY » Wed Sep 16, 2009 2:13 pm

ሰላም ሾተል እንኩዋን አብሮ አደረሰን::
ስዕሉ እንዳለ እዚህ ቤት ውስጥ ነው ያገኘሁት: ያንተን ፎቶ ያሰገባሁት ግን እኔ ነኝ:: ግዜው ግን በጣም ሩቅ ነው ይሄን ያንተን ፎቶ ያስገባሁት አሁን አይደለም:: በዛን ወቅት(ግዜ) አንተ ብዙዎቻችንን አስገርመሃል:: በቀን ውስጥ የማትሰራው ነገር የለም:: በትንሹ ለመጥቀስ በቀን ውስጥ እዚህ የምትጽፈው ብዛት, ስፖርት ሰርተህ, ስራህን ሰርተህ እንደገና ለትያትርህ የሚነበበውን አንበህ ብቻ ስንቱን ነገር ስትሰራ;ከምር ግዜ ሳንሰራበት አጠረን የምንለውን ግዜ ብዙ እንደሆነና ስንፍና እንደሆነ በአንተ በምትሰራቸው አደንቅ ስለነበረ ፎቶህን ከለጠፍካቸው ላይ የካራቴው ስለተመቸኝ በአዶቢ ፎቶሾፕ ሳይሆን ፔይንት በሚለው ብቻ ያኔ አስገባሁት እና ያው የፎቶ ማጠራቀሚያዬ የነበረው ፍሊከር ውስጥ አስቀምጬው ነበር:; በአጋጣሚ አሁን ለቤቱ ይሄን መልስ ለመመለስ ስል ለሙከራ ወደ ፎቶ ያስቀመትኩትጋ ስሄድ ይሄን ሳይ (ያኔም ስላላሰፈርኩት) ዛሬን አሰፈርኩት::

በዚህ አጋጣሚ 4ትን በ5 ስትቀይሩ ኢንተርን እንዳትረሱ:: ስዕሉንም ፖስት ሲደረግ መለጠፉ ወዲያው ላይታይ ይችላል ያው በ4 ስለሆነ ከለጠፋችው በውሃላ አሁንም 5 ወይም 3 ትቀይሩና ኢንተር ስታደርጉ የለጠፋችሁት ይታያል:: ልወጣ ስለሆነ የጻፍኩትን ኤዲት ሳላደርግ ነው የምልከው::
CUBBY
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Wed Oct 15, 2003 3:53 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 2 guests