ሴትዬዋን ከነ ቤተሰባቸው አገር ቤት አውቃቸዋለሁ :: ልጆቻቸው አድገው ለአቅመ አዳምና ሄዋን ደርሰው ተምረው እስከ ኮሌጅ የዘለቁም አሏቸው :: ዕድሜያቸው 40ዎቹ መጨረሻ ደርሷል :: ባለቤታቸው እውቅ ሰው ነበሩ ሰውዬው ከሞቱ አንድ አራት ዐመት አለፋቸው :: ባልና ሚስት አሜሪካን አገር ለሥራምሆነለቫኬሺን በመጡ ጊዜ ሁሉ እንደ ወዳጅነታችን መጠን እኔ ጋ እየመጡ አንዳንዴ ያርፉ ነበር ::
እናማ አሁን ምንድ ነው መሰላችሁ ጭንቀቴ ሴትዬዋ በቅርቡ ወደ እኔ ብቻቸውን መጥተው የተወሰኑ ጊዜያት እኔ ጋ አረፉ :: በዚህ ጊዜ ግን ትንሽ ልዩ ነገር ተፈጠረ ሁለታችንንም ሳናውቀው እስከ ወሲብ ተደራረስን :: ሴትዬዋ ከእኔ በእድሜ 17 ዐመት ያህል ይበልጣሉ :: እኔ ስንግል ነኝ :: ግን የራሴ የሆነ ቤት አለኝ :: የጎደለ ነገር ቢኖር ሚስትና ልጅ ማፍራት ነው :: አሁን ጭንቀቴ ሴትዬዋ አዝማሚያቸው ጨርቃቸውን ጠቅልለው ወደ አሜሪካን አገር አንደኛቸውን እኔ ጋ ለመምጣት ሲነግሩኝ በይሉኝታ እሺ ማለቴ የእግር እሳት ሆኖብኛል :: እሳቸውን ማግባት አልችልም እኔ ልጅ እፈልጋለሁ የምትመጥነኝን አግብቼ ላይፍ እፈልጋለሁ :: በዚህ ላይ የሚያዛምደን ነገር ብዙ ስላለ ለሰሚ አይመችም :: ከሁሉም መጥፎ ነገር ደግሞ አገር ቤት የሄድኩ ጊዜ ከአንደኛዋ ሴት ልጃቸው ጋር ስለ ትዳርና ስለ ሁሉም ነገር አውርተናል :: ለሌላ ነገር ባንደራረስም በጊዜው የእኔን መመዘኛ ስላማታሟላ ትቻታለሁ ::
አሁን በጣም ችግር የሆነብኝ ዋርካዎች እኚህ ሴትዬው ንብረት ሀብታቸውን ሽጠው መሥሪያ ቤታቸውን ተሰናብተው ቲኬት ቆርጠው ሊመጡ በረራ እየተጠባበቁ ነው :: መጀመሪያ ሳላገናዝብ በቀጭኗ ሽቦ በስልክ አንድ ቃል ብቻ እሺ ምን ችግር አለ ብቻ ነበር ያልኳቸው - ከዚያን በኋላ ምን እንደሚያደርጉ ዕቅዳቸውን እንኳ አላማከሩኝም :: ቀኑ ጨልሞብኛል :: ምናባቴ ላርግ ? እስቲ እባካችሁን ራሳችሁን በእኔቦታ ላፍታ አስቀምጡት ::
ከአክብሮት ጋር ::