ኢትዮጵያውያን የጥበብ ሰዎች-ከሐርቫርድ እስከ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ኢትዮጵያውያን የጥበብ ሰዎች-ከሐርቫርድ እስከ

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Apr 20, 2010 6:36 pm

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

ይህ ዓምድ ስለኢትዮጵያውያን የኪነት ሰዎች የሚዘገብበት ነው ::

ጁሊ ምህረቱ ትባላለች : አዲስ አበባ ከተማ በ1962 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1970) ተወልዳ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ተዘዋውራለች :: ያደገችው ኢስት ላንሲንግ : ሚችጋን (አሜሪካ) ሲሆን የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በዚያው በላንሲንግ አጠናቃ : በአርት የመጀመሪያ ዲግሪዋን ከካልማዞ ኮሌጅ (ሚቺጋን) : ፕሮቪደንስ (ሮዴ ደሴት) ከሚገኘው የሮዴ ደሴት የንድፍ ትምህርት ቤት በሥነ-ጥበብ የማስተርስ ዲግሪዋን በ1987 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1997) አግኝታለች :: የሁለተኛ ዓመት የኮሌጅ ተማሪ በነበረችበት ወቅት ዳካር (ሴኔጋል) በሚገኘው ዩኒቨርሲቴ ቼክ አንታ ዲዩፕ ትምህርቷን ለመቀጠል አጋጣሚው ነበራት :: በዘመናዊ ሥነ-ስዕል ሥራዋ በዓለም የታወቅች ሥትሆን በኒው ዮርክ ከተማ ወል-ስትሪት በሚገኘው የጎልድማን ሣክስ ዋና መሥሪያ ቤት ግድግዳ ላይ ተሠቅሎ የሚገኘው ግዙፍ የሥዕል ሥራ የእርሷ የሥራ ውጤት ነው :: ጁሊ በአሁኑ ጊዜ ነዋሪነቷ ኒው ዮርክ ሲሆን በተላያዩ የዓለማችን ክፍሎች የሥዕል ሥራዎቿን ታሣያለች ::

ጁሊ በዚህ የመካከለኛ ዕድሜዋ በዛ ያሉ የዓለም አቀፍ ሽልማቶች አሸናፊ ናት : ከብዙ በጥቂቱ :-
1 ........... 1992 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 2000) ከዘመናዊ ሥነ-ሥዕል ደጋፊ ድርጅት ሽልማት
2 ............ 1993 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 2001) የፔኒ ማካል ሽልማት
3 ............ መስከረም 10 ቀን 1998 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. September 20, 2005) የማካርተር ፌሎውሺፕ አሸናፊ ...

ምንጮች:-

Wikipedia, Julie Mehretu

Julie Mehretu Project

Interview with Julie Mehretu

የዚችን አስደናቂ የጥበብ ሰው ታሪክ በዚች አንድ ትንሽዬ ዓምድ ለመወሰን የማይቻል መሆኑ የታወቀ ነው :: ስለዚህ ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች የምታገኙትን እናንተው ጨማምሩበት ::

ተድላ
Last edited by ተድላ ሀይሉ on Mon Jun 10, 2013 12:19 pm, edited 12 times in total.
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ዘንጉ1 » Tue Apr 20, 2010 7:15 pm

ጌቶች ክምር ምስጋና አቅርቢያለሁ:: እጅግ በጣም ተሰጣኦ ያላት ልጅ ናት.............. እግዜሩ ብሩሿን ይባርከው:: ጁሊ እኛ ዋርካዎች ባንቺ በእምዬ ልጅ ኮርተንብሻል.................
እንትፍ እንትፍ እደጊ ተመንደጊ ስሪ ዲ የሆኑትም ጥበቦችሽ ወደ ፎር ዲ ይመንደጉ...................
ዘንጉ1
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 79
Joined: Sun Feb 22, 2009 11:51 pm
Location: Here

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Apr 21, 2010 1:03 am

ሰላም ወገኖቼ :-

በዚ ዓምድ ሥር የጎላ የጥበብ ሥራዎች ባለቤት የሆኑ ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያንን አስተዋውቃለሁ ::

ከዚህ በፊት ስለ ኃይሌ ገሪማ የከፈትኩትን ዓምድ በሚከተለው ጠቋሚ ያገኙታል ::

ኃይሌ ገሪማ : ትውልድ ተሻጋሪ የጥበብ ሰው

ዘንጉ 1:-

እስኪ አንተም ስለምታውቃቸው የጥበብ ሰዎች አካፍለን ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ዘንጉ1 » Wed Apr 21, 2010 1:49 am

ወንድሜ ተድላ ስለግብዣህ አመሰግናለሁ:: እስቲ ከወደ እየሩሳሌም ገዳም ከሚኖሩት እማሆይ ጽጌማርያም ገብሩ ትንሽ ልበል:: እማሆይ ኦርጋንን ቫዮሊንን እና ፒያኖን አሰቃይታ ነው የምትጫወትባቸው....... ኑሯቸውን ገዳም ያደረጉት እማሆይ የሙዚቃ ኖታ አቀላጥፋ የምትጽፍ ሲሆን ከአንድ መቶ በላይ የዘፈን ግጥሞችን ደርሳለቸ:: የተለያዩ የውጭ ሀገር ቋንቋን ተናጋሪ ስትሆን:: ከነዚህም መሀከል እብራይስጥ ፈረንሳይኛ እና ጀርመንኛ ተጠቃሽ ናቸው:: እማሆይ የሙዚቃ ትምህርትን በአውሮጳ እና በግብጥ አገር ተከታትላለች:: እንግዲህ ተድላ ያው እንደምታውቀው የጥበብ ሰው እርሶ ስለማይባል ብዬ ነው እማሆይን የሚያህል ታላቅ ሰው አንቺ በማለት የተዳፈርኩት....

እስቲ ይህንን የፈጠራ ፍሬዋን እናዳምጥላት

http://www.youtube.com/watch?v=UvkNBEft ... elatednull
ዘንጉ1
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 79
Joined: Sun Feb 22, 2009 11:51 pm
Location: Here

Postby ዘንጉ1 » Wed Apr 21, 2010 2:22 am

ባለቅኔ እና ሰአሊ ወይስ ሰአሊ እና ባለቅኔ አንዳንዴ ምን ብለን እንደምንጠራው እንቸገራለን:: ገብረ ክርስቶስ በኢትይጵያ የዘመናዊ ጥበብ አባትነት ዋነኛው ተጠቃሽ ነው:: በተለይ አብስትራክት ተብሎ የሚፈረጀው የስአል ዘርፍ ወደ ከኢትዮጵያውያን ጋር በማስተዋወቅ ግንባር ቀደሙ ነው::
ገብረ ክርስቶስ ብዙዎቹ ያለ እድሜው የተቀጨ አርቲስት እንደሆነ ያምናሉ::
እስቲ የምወደውን የገበረ ክርስቶስ ግጥም እነሆ ብያለሁ:

ፍቅር ጥላ ሲጥል
በገና
ቢቃኙ:
ሸክላ
ቢያዘፍኑ:
ክራር
ቢጫወቱ:
ለሚወዱት
ምነው
ሙዚቃ
ቢመቱ:
ቢቀኙ
ቢያዜሙ
ቃል ቢደረድሩ:
ጌጥ
ውበት
ቢፈጥሩ:
ቤት
ንብረት
ቢሰሩ:
አበባ
ቢልኩ:
ምነው
ቢናፍቁ:
አገር
ቢያቋርጡ
ቢሄዱ
ቢርቁ:
አመት
ቢጠብቁ:
ዘመን
ቢጠብቁ:
ለሚወዱት ምነው......
ዘንጉ1
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 79
Joined: Sun Feb 22, 2009 11:51 pm
Location: Here

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Apr 21, 2010 6:06 am

ሰላም ዘንጉ 1 :-

እኔ እማይሆይ ጽጌማርያም ገብሩን 'አንቱ' ብዬ መጥራቱን እመርጣለሁ : ለሃይማኖታዊ ክብሩ ሥል :: ያለበለዚያ በጥበብ ሰው ደረጃ ካየናቸው ምንትዋብ ገብሩ ብሎ መጥራቱ ይሻላል ::

ሥለ ገብረክርስቶስ ደስታ ብዙ ሣላውቅ እንዲሁ በወሬ ጠገብ ብቻ እየሠማሁ አገሬን ለቅቄ ወጣሁ :: እንደምታውቀው የዘመኑ ኢትዮጵያውያን የራሣችንን የጥበብ ሰዎች ሣይሆን የሌሎቹን እያደነቅን እናወራለን :: እኔም በከፊል ከዚያ ምድብ ነኝ ::

በተጨማሪም በደርግ የአገዛዝ ዘመን 'አብዮት : አብዮት' ያልሸተተ የጥበብ ሥራ እንደ ጥበብ ሥራ የማይቆጠርበት ዘመን ሥለነበረ እኔም በኩርፊያ ሁሉንም ትቼ ኖርኩ :: የአሁኖቹ ደግሞ ይበልጥ ወደ ንዋይ ማጋበሱ አደሉ :: ስለዚህ እኔና የኢትዮጵያ የጥበብ ሥራ ትልቅ ድልድይ ካልተሠራ በስተቀር በሩቁ ብቻ ማዶ ለማዶ እየተያይየን ልንዘልቅ ሆነ :: ከዚህ ዓይነቱ አዚም በከፊል ያላቀቁኝ በነፃው ዓለም ራሣቸውን ሆነው ኢትዮጵያን በማስተዋወቅ ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ናቸው :: ማን ያውቃል ቀስ በቀስ ከኢትዮጵያ የጥበብ ሥራ የሚያርቅ የያዘኝ አባዜ ይለቀኝ ይሆናል ::

በተሣትፎህ ቀጥልበት ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ዉቃው » Sun Apr 25, 2010 11:35 pm

ጓድ ተድላ

ጤና ይስጥልኝ :: እኔ ዉቃው እባላለሁ :: እዚሁ ነው ተወልጄ ያደኩት :: እርግጥ ነው..... አልፎ አልፎ ...ስታሊን (ጓድ ደጉሰው) ቤት ing ching ang wing ውስጥ ስትፅፍ አስተውያለሁ :: ጥሩ እና ቀና እንዲሁም አስተዋይ የሆንክ ለመሆኑ በምትሰጣቸው አስተያየቶች መረዳት ችያለሁ ::

በማለት የማክበር ሰላምታዬን ካቀረበኩ በኋላ ..ወደ ጉዳዬ ስመለስ ...በተለይ ..በጁሊ ...ላይ ያቀረበከውን መጣጥፍ አስመልክቶ ...ባይገናኝም የራሴን አስተያየት ይህንን ዕድል በመጠቀም ለማለት ወደድኩ ::

አየህ ጓድ ተድላ ...እኔ የወንድና የሴት ብልቶች ...እንዲፋቀሩ ...እንዲዋደዱ ...በመከባበር ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ ግንኙነት እንዲያዳብሩ ...እንዲሳሳቡና ትውልድ በእዝጋቤር አፈጣጠር ወይም በተፈጠሮ መልኩ እንዲቀጥል ...ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል እንቅልፌን አጥቼ ስባክን እውላለሁ :: ይህንን አንተም የምትደግፈው ይመስለኛል :: ሆኖም ግን እንደ ጁሊ ዓይነቶቹ ጥረቴን እና ልፋቴን መና ያስቀሩታል ...በታዋቂነት ሰበብ :: ስለዚህ እሷ የመደብ ጠላቴ ነች :: እናም ባገኘሁት አጋጣሚ እዋጋታለሁ :: ጌይ መሆኗ ወይም የሴክሹዋል ኦሪየንቴሽኗ ጉዳይ የግል ነው ...በስራዎቿ ብቻ ላይ እንወያይ ቢባልም ..ከመደብ ጠላቴ ጋር ላለመወያየት እና ላለመስማማት ፈቃደኝነቴን በፊትህ አረጋግጣለሁ :: በነገራችን ላይ ሰለአይዳ አሸናፊም ከተነሳ ..ተመሳሳይ አቋሜን ከማንጸባረቅ ወደኋላ እንደማልል ቃል እገባለሁ ::

ስላዳመጥከኝ አመሰግናለሁ ::
በአጭር የተቀጨው ረጅሙ ጉዟችን !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1038
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Apr 26, 2010 7:25 pm

ዉቃው wrote:ጓድ ተድላ

ጤና ይስጥልኝ :: እኔ ዉቃው እባላለሁ :: እዚሁ ነው ተወልጄ ያደኩት :: እርግጥ ነው..... አልፎ አልፎ ...ስታሊን (ጓድ ደጉሰው) ቤት ing ching ang wing ውስጥ ስትፅፍ አስተውያለሁ :: ጥሩ እና ቀና እንዲሁም አስተዋይ የሆንክ ለመሆኑ በምትሰጣቸው አስተያየቶች መረዳት ችያለሁ ::

በማለት የማክበር ሰላምታዬን ካቀረበኩ በኋላ ..ወደ ጉዳዬ ስመለስ ...በተለይ ..በጁሊ ...ላይ ያቀረበከውን መጣጥፍ አስመልክቶ ...ባይገናኝም የራሴን አስተያየት ይህንን ዕድል በመጠቀም ለማለት ወደድኩ ::

አየህ ጓድ ተድላ ...እኔ የወንድና የሴት ብልቶች ...እንዲፋቀሩ ...እንዲዋደዱ ...በመከባበር ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ ግንኙነት እንዲያዳብሩ ...እንዲሳሳቡና ትውልድ በእዝጋቤር አፈጣጠር ወይም በተፈጠሮ መልኩ እንዲቀጥል ...ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል እንቅልፌን አጥቼ ስባክን እውላለሁ :: ይህንን አንተም የምትደግፈው ይመስለኛል :: ሆኖም ግን እንደ ጁሊ ዓይነቶቹ ጥረቴን እና ልፋቴን መና ያስቀሩታል ...በታዋቂነት ሰበብ :: ስለዚህ እሷ የመደብ ጠላቴ ነች :: እናም ባገኘሁት አጋጣሚ እዋጋታለሁ :: ጌይ መሆኗ ወይም የሴክሹዋል ኦሪየንቴሽኗ ጉዳይ የግል ነው ...በስራዎቿ ብቻ ላይ እንወያይ ቢባልም ..ከመደብ ጠላቴ ጋር ላለመወያየት እና ላለመስማማት ፈቃደኝነቴን በፊትህ አረጋግጣለሁ :: በነገራችን ላይ ሰለአይዳ አሸናፊም ከተነሳ ..ተመሳሳይ አቋሜን ከማንጸባረቅ ወደኋላ እንደማልል ቃል እገባለሁ ::

ስላዳመጥከኝ አመሰግናለሁ ::

ውቃው :-

አንተ ያቀረብከውን መረጃ አላውቅም ነበር :: ስለጥቆማህ አመሠግናለሁ ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Jun 14, 2011 8:27 pm

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

ሙላቱ አስታጥቄ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ከከፍተኛ ደረጃ ካሠደጉት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስተወወቁም ረገድ ቀዳሚው ነው ::
ሙላቱ አስታጥቄን የኢትዮጵያ ድምፃውያን ሊጠቀሙበት ያልቻሉት ታላቅ የጥበብ ሰው ነው ::

ሠሞኑን ዊል ሮስ የተባለ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ስለእርሱ ሥራ ያቀረበውን ዘገባ ተመልከቱት ::

ምንጭ:- Will Ross BBC News, Addis Ababa, 14 June 2011 Last updated at 08:44 ET. Meeting the godfather of Ethiopian jazz.

Mulatu Astatke, the godfather of Ethiopian jazz music, is often flying around the world performing sell-out shows so I was lucky to find him at his home in Addis Ababa surrounded by art, conjuring up magic on his vibraphone - which looks like a giant xylophone.

He described the recipe for Ethio-jazz which he first cooked up 42 years ago while studying music in the United States.

"Most of our Ethiopian music is based on five notes [pentatonic]. What I did was fuse the five tones with 12 tones. For many years I've been experimenting and the more I do that the more complex it gets," Mr Mulatu told the BBC.

"I remember one teacher at Berklee College in Boston telling us to always be ourselves and that was always on my mind. I used to do a lot of analyzing of the music of Duke Ellington, Count Basie, Miles Davis and John Coltrane and I saw how great they were and what they had contributed to the world of music.

"So my aim was always to be like them and create something to give to my country and give to the world."
Heading to Glastonbury

Instead of simply copying the jazz greats, Mr Mulatu set about researching the music of Ethiopia and constantly added a generous pinch of this to his musical cooking pot.
Continue reading the main story

"There are tribes in the south called the Derashe. They are surrounded by people who play five tone music but they have created a diminished 12-tone scale," Mr Mulatu said.

"Diminished scales are very important in jazz music especially for improvising. We learn how Charlie Parker came up with diminished scales as well as [the French classical composer] Claude Debussy and Bach. But always on my mind is the question of who were first with the scale, these people or the Derashe tribe?"

Ethio-jazz is on a roll in Addis Ababa.

A new jazz club opened last week, new Ethio-jazz bands are forming and now there are several music colleges. It is also on the rise on the world stage.

Mr Mulatu is due to play at the UK's famous Glastonbury festival next week.

'Scientific music'

At Mekane Yesus Jazz Music School in Addis Ababa, students study Mr Mulatu's music and are even examined on it as part of the curriculum.

In a corridor of tiny practice rooms there were saxophonists, pianists, guitar players and some students with Ethiopian traditional instruments getting ready for the exams.

Two floors up the fire escape and the Blue Note band was cooking up a storm.

The seven-piece band was playing original Ethio-jazz songs - the unmistakable five tone scales, keeping a heavy hint of Ethiopia in the music.

"As a musician, I love all types of music but I love Ethio-jazz music most because it describes me very well - better than other jazz music," said the band's 20-year-old bassist, Robera Mekonnen.

"I'm influenced by the legendary musicians of Ethiopia who have brought about a change by mixing jazz with Ethiopian music. One of them is Mulatu Astatke, a man who is special because he loves his native music and has developed it scientifically."

Over the years, Mr Mulatu has brought musicians from across Ethiopia into the studio.

For one session, Derashe musicians turned up with their six-inch long bamboo flutes, others carried giant vuvuzela-style pipes up to four metres long. When mixed with his own band, the result was an extraordinary hypnotic sound.

Fishing for instruments

Among the stalls of the bustling Addis Merkato market, I found other Ethiopian instruments which Mr Mulatu has fused into his Ethio-jazz music.

Hanging from the ceiling of one shop were dozens of the one-stringed violin-like instruments known as masinko which are played with a bow.

It was like fishing for instruments in the roof of the house as the shopkeeper used a pole to bring down a krar - a five- or six-stringed Ethiopian harp.

To hear them played well, I visited Yod Abyssinia, a cultural centre where the mostly Ethiopian audience is treated to traditional music, dance and food.

Here the music is played in its pure form but Mr Mulatu is on a mission to develop the instruments so the players are not restricted.

"I have a very high respect for our cultural instruments. I have tried to develop the krar. I changed it from six to eight strings and managed to play for the first time songs like Guantanamera, Mercy Mercy and Summertime.

"For 3,000 years we couldn't play anything except five-tone music on the krar. My aim is to develop one with 12 strings," Mr Mulatu said.

I wondered if there was not also an argument for leaving the instruments in their purest form.

"Some believe that but I don't. Look, why do you think most young people go to the guitar?" asked Mr Mulatu.

"It is because the traditional instruments limit them - they cannot do what they want to do. On the guitar, they can experiment. If I can develop the krar so it can do what the guitar does, they will be playing their own instruments and they can also contribute to the world different sounds.

"When you have been kept to five-tone music all your life and you start playing 12-tone music you can do miracles. So it develops the instrument and the mind."

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Jul 18, 2011 2:05 am

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ:-

የኢትዮ-ጃዝ ሙዚቃን በዓለም በሥፋት እንዲተዋወቅ በማድረግ ረገድ ቀዳሚ ሥራ በመሥራት ላይ ያለው ሙላቱ አስታጥቄ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መቀመጫውን ቦስተን (ማሣቹሴትስ - አሜሪካ) በማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው :: የዛሬ አራት ዓመት አካባቢ በቶሮንቶ (ካናዳ) ተገኝቶ ያቀረበውን በጥናታዊ ፊልም የታጀበ ትምህርታዊ ዝግጅት ተከታተሉለት :: ዝግጅቱ 2 ሰዓት ከ17 ደቂቃዎች ያህል ይፈጃል ::

ምንጭ:- Mulatu Astatke, Red Bull Music Academy, Toronto 2007.

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Aug 11, 2011 2:11 am

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

ዛሬ 'Ethiopia Habtemariam' ብላችሁ ጉግል ብታደርጉ የሚወጣው የዜና መዓት የሚያወሣው ስለአንድ ወጣት የዩኒቨርሣል የሙዚቃ ኩባንያ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆና መሾም ነው :: ለመሆኑ ኢትዮጵያ ኃብተማርያም ማን ናት? እስኪ ስለእርሷ ዝርዝር ጉዳዮችን የምታውቁ ዜና አካፍሉን ::

ምንጭ:- Georg Szalai, The Hollywood Reporter, Wed August 10, 2011, 1:27. Universal Music Promotes Ethiopia Habtemariam to Head of Urban Music, Motown Senior VP

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ፋኖፋኖ » Fri Aug 12, 2011 3:07 pm

ተድላ ሀይሉ wrote:
ዉቃው wrote:ጓድ ተድላ

ጤና ይስጥልኝ :: እኔ ዉቃው እባላለሁ :: እዚሁ ነው ተወልጄ ያደኩት :: እርግጥ ነው..... አልፎ አልፎ ...ስታሊን (ጓድ ደጉሰው) ቤት ing ching ang wing ውስጥ ስትፅፍ አስተውያለሁ :: ጥሩ እና ቀና እንዲሁም አስተዋይ የሆንክ ለመሆኑ በምትሰጣቸው አስተያየቶች መረዳት ችያለሁ ::

በማለት የማክበር ሰላምታዬን ካቀረበኩ በኋላ ..ወደ ጉዳዬ ስመለስ ...በተለይ ..በጁሊ ...ላይ ያቀረበከውን መጣጥፍ አስመልክቶ ...ባይገናኝም የራሴን አስተያየት ይህንን ዕድል በመጠቀም ለማለት ወደድኩ ::

አየህ ጓድ ተድላ ...እኔ የወንድና የሴት ብልቶች ...እንዲፋቀሩ ...እንዲዋደዱ ...በመከባበር ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ ግንኙነት እንዲያዳብሩ ...እንዲሳሳቡና ትውልድ በእዝጋቤር አፈጣጠር ወይም በተፈጠሮ መልኩ እንዲቀጥል ...ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል እንቅልፌን አጥቼ ስባክን እውላለሁ :: ይህንን አንተም የምትደግፈው ይመስለኛል :: ሆኖም ግን እንደ ጁሊ ዓይነቶቹ ጥረቴን እና ልፋቴን መና ያስቀሩታል ...በታዋቂነት ሰበብ :: ስለዚህ እሷ የመደብ ጠላቴ ነች :: እናም ባገኘሁት አጋጣሚ እዋጋታለሁ :: ጌይ መሆኗ ወይም የሴክሹዋል ኦሪየንቴሽኗ ጉዳይ የግል ነው ...በስራዎቿ ብቻ ላይ እንወያይ ቢባልም ..ከመደብ ጠላቴ ጋር ላለመወያየት እና ላለመስማማት ፈቃደኝነቴን በፊትህ አረጋግጣለሁ :: በነገራችን ላይ ሰለአይዳ አሸናፊም ከተነሳ ..ተመሳሳይ አቋሜን ከማንጸባረቅ ወደኋላ እንደማልል ቃል እገባለሁ ::

ስላዳመጥከኝ አመሰግናለሁ ::

ውቃው :-

አንተ ያቀረብከውን መረጃ አላውቅም ነበር :: ስለጥቆማህ አመሠግናለሁ ::

ተድላ

ይኸው መረጃው...ሚስት አግብታ ወልዳለች

http://bandofthebes.typepad.com/bandoft ... mural.html

.
ፋኖፋኖ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 936
Joined: Wed Nov 08, 2006 10:39 am

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Aug 12, 2011 6:21 pm

ፋኖፋኖ wrote:
ተድላ ሀይሉ wrote:
ዉቃው wrote:ጓድ ተድላ

ጤና ይስጥልኝ :: እኔ ዉቃው እባላለሁ :: እዚሁ ነው ተወልጄ ያደኩት :: እርግጥ ነው..... አልፎ አልፎ ...ስታሊን (ጓድ ደጉሰው) ቤት ing ching ang wing ውስጥ ስትፅፍ አስተውያለሁ :: ጥሩ እና ቀና እንዲሁም አስተዋይ የሆንክ ለመሆኑ በምትሰጣቸው አስተያየቶች መረዳት ችያለሁ ::

በማለት የማክበር ሰላምታዬን ካቀረበኩ በኋላ ..ወደ ጉዳዬ ስመለስ ...በተለይ ..በጁሊ ...ላይ ያቀረበከውን መጣጥፍ አስመልክቶ ...ባይገናኝም የራሴን አስተያየት ይህንን ዕድል በመጠቀም ለማለት ወደድኩ ::

አየህ ጓድ ተድላ ...እኔ የወንድና የሴት ብልቶች ...እንዲፋቀሩ ...እንዲዋደዱ ...በመከባበር ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ ግንኙነት እንዲያዳብሩ ...እንዲሳሳቡና ትውልድ በእዝጋቤር አፈጣጠር ወይም በተፈጠሮ መልኩ እንዲቀጥል ...ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል እንቅልፌን አጥቼ ስባክን እውላለሁ :: ይህንን አንተም የምትደግፈው ይመስለኛል :: ሆኖም ግን እንደ ጁሊ ዓይነቶቹ ጥረቴን እና ልፋቴን መና ያስቀሩታል ...በታዋቂነት ሰበብ :: ስለዚህ እሷ የመደብ ጠላቴ ነች :: እናም ባገኘሁት አጋጣሚ እዋጋታለሁ :: ጌይ መሆኗ ወይም የሴክሹዋል ኦሪየንቴሽኗ ጉዳይ የግል ነው ...በስራዎቿ ብቻ ላይ እንወያይ ቢባልም ..ከመደብ ጠላቴ ጋር ላለመወያየት እና ላለመስማማት ፈቃደኝነቴን በፊትህ አረጋግጣለሁ :: በነገራችን ላይ ሰለአይዳ አሸናፊም ከተነሳ ..ተመሳሳይ አቋሜን ከማንጸባረቅ ወደኋላ እንደማልል ቃል እገባለሁ ::

ስላዳመጥከኝ አመሰግናለሁ ::

ውቃው :-

አንተ ያቀረብከውን መረጃ አላውቅም ነበር :: ስለጥቆማህ አመሠግናለሁ ::

ተድላ

ይኸው መረጃው...ሚስት አግብታ ወልዳለች

http://bandofthebes.typepad.com/bandoft ... mural.html

.

ሰላም ፋኖፋኖ :-

ወንድማችን ጋሼ ውቃው በሠጠኝ ጥቆማ መሠረት ያኔውኑ ጉግል አድርጌ የጁሊ ምህረቱን የግል ሕይወት አጣርቻለሁ :: መልስህ ቢዘገይም አመሠግናለሁ :) :) :) ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Dec 06, 2011 7:00 am

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውይን ወገኖቼ :-

ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሣ ባለ ዘርፈ-ብዙ የዕውቀትና የሙያ ባለቤት ናቸው :- የሥነ ጽሑፍ : የትያትር : የፍልስስፍና : የታሪክ ሊቅ : ሌላም ሌላም ሙያዎች ያሏቸው ከዘመኑ ምርጥ ኢትዮጵያውያን መካከል የሚመደቡ ናቸው :: በአንድ ወቅት ያዘጋጁትና ለአፍሪቃውያን-አሜሪካውያን የማነቃቂያ ደወል የሚሆን 'Multicolored Flowers' በተሠኘ ርዕስ የሚጠራ ፊልም ቅንጫቢ ከ'You Tube' አግኝቼ እዚህ ለጥፌላችኋለሁ ::

የራፕ ሙዚቃ ከሌላ የመጣ ሣይሆን የኢትዮጵያውያን የፉከራ ባህል ነው : ሹሩባ መሠራት : ሌላም ሌላም ከአፍሪቃ የተወሠዱ ባህሎች የምዕራቡ ዓለም ባህል ሆነው ተቆጥረዋል ...

ምንጭ:- Uploaded by gzayalu on Nov 29, 2010. multicoloredflowers.

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Dec 30, 2011 3:36 am

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ታላቁን የሥዕል ጥበበኛ ይገዙ ብሥራትን ምን ያህል ታውቋቸዋላችሁ ?

ይህ ድረ-ገፅ በዛ ያሉ መረጃዎች የያዘ ስለሆነ ውስጡን በርብራችሁ ስለ እኒህ የጥበብ ሰው ታሪክና ሥራዎች የበለጠ መገንዘብ ትችላላችሁ ::

የአቶ ይገዙ ብሥራት ድረ-ገፅ: አጭር የሕይወት ታሪክ ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests